#Ethiopia | በአለም በድህነት ከሚታወቁ ሃገራት ሶስተኛዋ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ስትሆን ፡ በጣም የሚገርመው በአለም በከፍተኛ ደረጃ አልማዝ ከሚያመርቱ ሃገራትም ሶስተኛዋ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ናት 🤔
ዛሬ ፡ በዱባይ የጌጣጌጥ መደብሮች. . በኒውዮርክ ፡ ፓሪስ ፡ ለንደን እና ቶኪዮ በሚገኙ ትላልቅ የዳይመንድ መሸጫ ሱቆች ላይ ሚሊየን ዶላሮች የሚጠራባቸው የአልማዝ ጌጣጌጦችና ወርቆች .. ተዝቀው የሚወሰዱት. . ከዚች ካልታደለች ደሃ ሃገር ነው ። እንደውም በአለም ላይ በአልማዝ ክምችታቸው ዲሞክራቲክ ኮንጎን የሚበልጡት ሩሲያና ቦትስዋና ብቻ ናቸው ።
ይሄ ብቻ አይደለም ፡ ከነዳጅ ሀብቷ በተጨማሪ ፡ በአለም ደረጃ ለሚመረቱ ለአውሮፕላን ፡ ለመኪና ለሴራሚክስና ለኤሌትሪክ እቃዎች መስሪያ የሚያገለግለው 60% የኮባልት ምርት የሚሄደው ከዚችው ሃገር ነው ።
ከላይ ያወራነው በመመረት ላይ ያለ ማእድኗን ነው ፡ ግን ይህ ብቻ አይደለም. .
ዲሞክራቲክ ኮንጎ. . ገና ያልተነካ ከ 23 ትሪሊዮን ዶላር በላይ የሚሆን ማእድን ያላትም ሃገር ነች ። በሌላ በኩል ደግሞ በዚህ አመት ብቻ 26 ሚሊዮን ህዝቦቿ ለምግብ ዋስትና ችግር ተጋልጠዋል ። 3.4 ሚሊዮን ህጻናት ደግሞ ለከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት በመዳረጋቸው የምእራባውያንን እርዳታ ይሻሉ ።
ፈጣሪ በአልማዝና በወርቅ ቀላቅሎ በሰራው በዚች ሃገር ፡ ከሚኖሩ ዜጎቿ መሃል ንፁህ የመጠጥ ውሃ የሚያገኙት ግማሽ ያህሉ ብቻ ናቸው ።
ጆይን👉 @mesaymekonnen1