Construction Contractors Association of Ethiopia @ccaeethiocon Channel on Telegram

Construction Contractors Association of Ethiopia

@ccaeethiocon


Construction Contractors Association of Ethiopia (English)

Are you a construction contractor in Ethiopia looking to connect with like-minded professionals and stay updated on the latest industry news? Look no further than the Construction Contractors Association of Ethiopia Telegram channel! With the username @ccaeethiocon, this channel is the go-to source for all things related to construction in Ethiopia. The Construction Contractors Association of Ethiopia is a community of construction professionals dedicated to promoting excellence in the industry. Whether you are a seasoned contractor or just starting out, this channel provides valuable resources, networking opportunities, and support to help you succeed in your career. By joining this channel, you will have access to a wealth of information, including updates on new projects, construction regulations, training workshops, and job opportunities. You can also connect with other contractors, share your experiences, and learn from industry experts. The Construction Contractors Association of Ethiopia is more than just a channel – it is a community where members can come together to support each other and advance the construction industry in Ethiopia. Join us today and take your career to the next level! #EthiopiaConstruction #ContractorsAssociation #IndustryNetworking

Construction Contractors Association of Ethiopia

17 Nov, 17:40


የከተማ ግንባታን በተመለከተ

Construction Contractors Association of Ethiopia

13 Nov, 06:53


🫵የ 9ኛ ዙር Health and Safety in Construction እንዲሁም Ethics in Construction ስልጠና ጥሪ

🚧ለ9ኛ ዙር የHealth and Safety in Construction ስልጠና ለመሰልጠን የተመዘገባችሁ ድርጅቶች ሙሉ ስም ዝርዝር የሚከተሉት ስትሆኑ የስልጠናውን ቀናት በቅርቡ ቀድመን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ (በ8ኛው ዙር መርሐግብር ላይ በተለያየ ምክንያት ያልተሳተፋችሁ በተለየም የመስቀል በዓልን ለማክበር በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ሂዳችሁ የነበራችሁ ሰልጣኞች በዚህኛው ዙር ስማችሁ የተካተተ መሆኑን በማክበር እናሳውቃለን፡፡)

🚧ተጨማሪ 50 የማኅበራችን አባላት ለዘጠነኛው ዙር ስልጠና መመዝገብ ስለምትችሉ እስከ እሑድ ህዳር 08 ቀን ቀን 2017ዓ/ም ድረስ በዚሁ ቻናል ላይ ወይንም በስልክ ቁጥር 0941-80-87-88 መልዕክት በመላክ እንድትመዘገቡ እናስታውቃለን።

Construction Contractors Association of Ethiopia

12 Nov, 13:26


🚧 07 የአውሮፓ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፌዴሬሽን /European Construction Industry Federation/

የአውሮፓ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፌዴሬሽን (FIEC)52,000 አባላትን አቅፏል፡፡ በአውሮፓ ህብረት ውስጥ የኮንስትራክሽን ኩባንያዎችን ይወክላል፡፡የኮንስትራክሽን ህግ ላይ ይሰራል፡፡ የኮንስትራክሸን ስታቲስቲክስ ሪፖርትን ያሳትማል፡፡ዓመታዊ ኮንግረስን ያዘጋጃል፡፡

🚧 06 National Association of Home Builders / የቤት ገንቢዎች ብሔራዊ ማኅበር/

ከ 140,000 በላይ አባላት ያሉት ብሔራዊ የቤት ግንባታ ሰሪዎች ማህበር (NAHB) በሰሜን አሜሪካ በመኖሪያ ግንባታ እና በመልሶ ግንባታ ላይ ይሰራል። የቤት ፖሊሲ ጥናትን፣የትምህርት ፕሮግራሞችን፣በምርምር ማዕከሉ በኩል ደግሞ የግንባታ ደረጃዎችን ይቀርጻል፡፡

🚧 05 የግንባታ ኢንዱስትሪ ምክር ቤት / Construction Industry Council/

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ካውንስል (CIC)በዩናይትድ ኪንግደም 160,000 አባላት አሉት፡፡ ካውንስሉ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ያስተባብራል፣ ደረጃዎችን ያወጣል፡፡

🚧 04 የአሜሪካ የብረት ግንባታ ተቋም /American Institute of Steel Construction/

ከ170,000 በላይ አባላት ያሉት የሰሜን አሜሪካው ማኅበር /AISC/ በብረት ግንባታ/ Steel Construction/ ላይ ያተኩራል፡፡ ደረጃዎች ያወጣል እንዲሁም የብቃት የምስክር ወረቀት ይሰጣል። እ.ኤ.አ. በ 1921 የተመሰረተው ይህ ማኅበር የብረታ ብረት ኮንስትራክሽን መመሪያዎችን ያሳትማል፡፡የሰሜን አሜሪካ የብረታ ብረት ኮንስትራክሽን ኮንፈረንስን ያስተናግዳል::

🚧 03 የአሜሪካ አጠቃላይ ሥራ ተቋራጮች ማኅበር /Associated General Contractors of America/
በ1918 የተመሰረተው ማኅበሩ ከ200,000 በላይ አባላት ያሉት ሲሆን የሰሜን አሜሪካ የንግድ ዘርፍ ማህበር ነው፡፡በዋናነት በኮንስተራክሽን ላይ ያተኮረ የራሱ የመረጃ ማዕከል ያለው ሲሆን የሥራ ተቀራጩን እንቅስቃሴ የሚገልጽ መጽሔት ያዘጋጃል፡፡ሁሉም ሊጠቀምበት የሚችል የኮንትራት ሰነድም ያዘጋጃል፡፡

🚧 02 የአሜሪካ አርክቴክቶች ተቋም /American Institute of Architects /

ተቋሙ ወደ 250,000 የሚጠጉ አባላት ያሉት ሲሆን በሥነ ሕንፃ፣ ዲዛይን እና ግንባታ ላይ ያተኩራል፡፡ የአርኪቴክቸር መረጃን የያዘ መጽሔት ያሳትማል፡፡

🚧 01 የማሌዥያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት ቦርድ /Construction Industry Development Board/

የማሌዥያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት ቦርድ (CIDB) 300,000 አባላት ያሉት ሲሆን የማሌዢያን ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪን ለመቆጣጠር እና ለማዳበር በ1994 ተመስርቷል። የራሱ የሆነ የሥልጠና ማዕከላት አሉት፡፡SCORE የተባለ ሥራ ተቋራጮች የሥራ አፈጻጸማቸው የሚመዘንበት ሥርዓት አለው፡፡

Construction Contractors Association of Ethiopia

12 Nov, 13:24


➡️የአለማችን 10 ትላልቅ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ሙያዊ እና የንግድ ዘርፍ ማኅበራት

🚧በአለማችን ላይ ከትናንሽ ድርጅቶች ጀምሮ ግዙፍ ድርጅቶችን ያቀፉ በርካታ ስመጥር የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ሙያዊ እና የንግድ ዘርፍ ማኅበራት ይገኛሉ፡፡በዋናነት ዓላማቸውም ለኢንደስትሪው ተዋንያን የአቅም ግንባታ መስጠት እና የአባላቱን መብት ማስጠበቅ ነው፡፡

🚧ማኅበራችንም ባለፉት 33 ዓመታት ከላይ ከተጠቀሱት ዓለማዎች አንጻር በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ የራሱን አሻራ አሳርፏል፡፡

🚧ባሳለፍነው ቅዳሜ ጥቅምት 30 ቀን 2017ዓ/ም የተካሄደው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ ላይም የረዥም ጊዜ ስልታዊ ዕቅድ በመንደፍ አሁን የማኅበራችን አባላት እየገጠማቸው የሚገኘውን ፈተናዎች ለማለፍ አባላቱም ሆነ አዲስ የተመረጡት የዳይሬክተሮች ቦርድ የበኩላቸውን እንዲወጡ መግባባት ተደርሶበት ጉባዔው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡

🚧ለዛሬ ለዓመታዊው ጉባዔ ማስታወሻነት እንዲሆን እ.ኤ.አ በOctober 09 ቀን 2024 Construction Digital መጽሔት የዘገበውን የአለማችን 10 ትላልቅ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ሙያዊ እና የንግድ ዘርፍ ማኅበራትን እናስተዋውቃችኋለን፡፡

🚧10 የጃፓን የሲቪል መሐንዲሶች ማህበር /Japan Society of Civil Engineers/

በ1914 የተቋቋመው ማህበሩ (JSCE) ወደ 39,000 አካባቢ አባላት ያሉት ሲሆን በሲቪል ምህንድስና፣ በግንባታ ልምዶች እና በምርምር ላይ ያተኮረ ማኅበር ነው።

🚧09 የብሪቲሽ አርክቴክቶች ሮያል ተቋም /Royal Institute of British Architects/

በ1834 የተመሰረተው የብሪቲሽ አርክቴክቶች ሮያል ኢንስቲትዩት (RIBA) በሥነ ሕንፃ፣ ዲዛይን እና የግንባታ ደረጃዎች ግንባር ቀደም ድርጅት ነው፣ 44,000 አባላት ያሉት እና በተሻሻሉ ሕንፃዎች፣ ማህበረሰቦች እና አካባቢ ላይ ያተኮረ ነው።

🚧08 የአውስትራሊያ ሲሚንቶ እና ኮንክሪት ተቋም /Cement and Concrete Institute of Australia/

ወደ 50,000 የሚጠጉ አባላት ያሉት የአውስትራሊያ ሲሚንቶ እና ኮንክሪት ኢንስቲትዩት በኮንክሪት ማምረት፣ ደረጃዎች እና ምርምር ላይ ያተኩራል።

Construction Contractors Association of Ethiopia

12 Nov, 07:41


ቋሚ ኮሚቴው በህንጻ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያየ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሰረተ ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የህንጻ ረቂቅ አዋጅ ማሻሻያ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል።

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ  ዶ/ር እሸቱ ተመስገን ህንፃዎች ሲሰሩ ለዲዛይኖች ጊዜ ሰጥቶ በአግባቡ በመስራት የግንባታ ጊዜን የተቀላጠፈ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። የአዋጭነት ጥናትና የአካባቢና ማህበራዊ ተጽኖዎችም  በአግባቡ   መታየት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

ምክትል ሰብሳቢው ከመድረኩ ጥሩ ግብአት መገኘቱን ገልጸው፤ አዋጁ ረጅም ጊዜ የሚያገለግል እንዲሆን ተጨማሪ አስተያየቶችን በጽሁፍ ማድረስ እንደሚቻል ጠቁመዋል ። ዘርፉን ለማሳደግ የሙያ ማህበራት ተጠናክረው በጋራ መስራት እንዳለባቸውም ጠቁመዋል።

በውይይቱም የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ የአዋጁ ማሻሻያ ጥናት ላይ የተመሰረተ እና ዘርፉ የደረሰበትን ደረጃ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። 

የከተሞች ስታንዳርድ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መገባቱን ገልጸው፤ የሙያ ማህበራት በጋራ ሆነው ጠንካራ አቅም መፍጠር ቢችሉ የተሻለ መሆኑን ጠቁመዋል ።

በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የኮንስትራክሽንና መሰረተ ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ  መዲና አህመድ  አዋጁን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ አዋጁ የህዝብን ደህንነት ለመጠበቅ እና ለአካል ጉዳተኞችና ለሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች የህንጻ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ዝቅተኛውን ደረጃ ለመወሰን አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል
በነባሩ ህግ በአፈጻጸም የተለዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ፣ የአካል ጉዳተኞች ተደራሽነትን፣የግንባታ ጥራትና የሀብት ብክነት ችግሮች ለመቅረፍ የሚያስችል  ግልጽና ለአተገባበር ምቹ የሆነ የአሰራር ስርአት መዘርጋት ተገቢ ሆኖ መገኘቱን  ተናግረዋል ። 

ማንኛውም ሰው አዲስ ግንባታ ለማከናወን፣ ነባር ህንፃ ለማሻሻል ፣ለማስፋፋት ወይም ለማፍረስ እንዲሁም የአገልግሎት ለውጥ ለማድረግ በቅድሚያ ተገቢውን የግንባታ ፈቃድ ማግኘት እንዳለበት እና ማንኛውም ሰው የህዝብ መገልገያ የሆኑ የተጠናቀቁ ህንፃዎች አገልግሎት ላይ ከመዋላቸው በፊት የህንጻ መጠቀሚያ ፈቃድ ማግኘት እንዳለበት ገልጸዋል።

በውይይቱ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላት አዋጁን በሚመለከት አስተያየትና ጥያቄዎችን አንስተዋል። የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ምላሽ ሰጥተዋል ።

በውይይቱ ከክልል እና ከከተማ አስተዳደር የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ የመጡ የስራ ሃላፊዎች ፣ ከኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፣ ቲንክታ
አካላት ተገኝተዋል።

(ከመልሚ)

Construction Contractors Association of Ethiopia

12 Nov, 06:21


ኢትዮ ኮን ህዳር 2፤ 2017

Construction Contractors Association of Ethiopia

11 Nov, 12:38


👉 የዛሬ ምሽት ህዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም ኢትዮ ኮን ሳምንታዊ ፕሮግራሞቻችን

🗣ወቅታዊ ፕሮግራም

🔷 የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም  በኢንተር ላግዠሪ ተካሂዷል።

ይህን በተመለከተ ወደ እናንተ የምናደርሰው ፕሮግራም ይኖረናል።

🏗 የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የሚያቀርበው ልዩ ዝግጅት የፕሮግራማችን አንድ  አካል ነው።

✍️📞☎️የምታነሱት ሀሳብ አስተያየትና ጥያቄ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ በዚሁ በቴሌግራም ገፃችን ላይ አድርሱን፡፡

🥍📻🕰 ምርጫችሁ አድርጋችሁ ምሽት
ከ2፡30 — 3፡30 ሰዓት በአሀዱ ሬድዮ 94.3 ላይ ከቀጥታ ስርጭት ፕሮግራማችን ጋር ይሁን!
                                          

Construction Contractors Association of Ethiopia

11 Nov, 06:02


Slump Test ....very important

Construction Contractors Association of Ethiopia

09 Nov, 07:19


🔵 የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የመሠረተ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ አቶ የትምጌታ አስራት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር ባካሄደው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ካደረጉት የመክፈቻ ንግግር መካከል እነዚህን ነጥቦች አንሰተዋል፣

🔷የኮንስትራክሽን ዘርፋ ከአጠቃላይ የስራ ዕድል ፈጠራ ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። በአሁኑ ወቅት በየዓመቱ ከ150,000 በላይ ባለሙያዎች ወደ ዘርፋ እንደሚንቀሳቀስ የተለያዩ መረጃዎች ያሳያሉ።

🔷ባለፋት 26 ዓመታት በተሰሩ ስራዎች የአገር በቀል ተቋራጮች (የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ጨምሮ ) ከፌደራል የመንገድ ፕሮጀክቶች በገንዘብ 54 በመቶ በፕሮጀክት ብዛት ደግሞ 79 በመቶ አካባቢ የሚሆነውን ኮንትራት በመፈረም እየተሳተፈ ነው። ይህ እውነታ ከብዙዎቹ የአፋሪካ ሀገራት ጋር ሲነፃፀር የተሻለ ነው።

Construction Contractors Association of Ethiopia

09 Nov, 06:50


🔷 የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን ዛሬ በአሁኑ ሰዓት ጥቅምት  30 ቀን 2017 ዓ.ም
  በኢንተር ላግዠሪ (የቀድሞው ኢንተር ኮንቲነታል) ሆቴል በመካሄድ ላይ ይገኛል

🔵 የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የመሠረተ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ አቶ የትምጌታ አስራት ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።