Etho University Channel @mistea Channel on Telegram

Etho University Channel

@mistea


የተማሪዎችን የመረጃ ውስንነት ለማስፋት የተመሠረተ Channal

Etho University Channel (English)

Welcome to the Etho University Channel! This channel, managed by the username 'mistea', is a hub for all things related to ethology, the study of animal behavior. Whether you are a student, researcher, or simply fascinated by the intricate world of animal behavior, this channel is the perfect place for you. Get ready to dive deep into the fascinating world of ethology, where you will find a wealth of knowledge, latest research, and engaging discussions. Learn about different animal species, their behavior patterns, and the various factors that influence their actions. Join a community of ethology enthusiasts, where you can share your thoughts, ask questions, and connect with like-minded individuals. Stay updated with the latest news and trends in the field of ethology, and discover new insights that will expand your understanding of the natural world. Whether you are a beginner or an experienced ethologist, the Etho University Channel is your go-to resource for all things related to animal behavior. Join us today and embark on a journey of discovery and fascination!

Etho University Channel

07 Sep, 14:56


የቴሌብር ሱፐር አፕን በማውረድ በመመዝገብ እና በመገበያየት ተሸላሚ እዲሆኑ ጋብዤዎታለሁ. https://superapp.ethiomobilemoney.et:38443/customer/mgm/index0902.html#/?notoolbar=true&CampaignId=MGM1636545295560576&inviterId=1204845514905600&language=am&campaignType=collectPetal&time=Sept-04-2024-Sept-12-2024

Etho University Channel

07 Sep, 14:56


የቴሌብር ሱፐር አፕን በማውረድ በመመዝገብ እና በመገበያየት ተሸላሚ እዲሆኑ ጋብዤዎታለሁ. https://superapp.ethiomobilemoney.et:38443/customer/mgm/index0902.html#/?notoolbar=true&CampaignId=MGM1636545295560576&inviterId=1204845514905600&language=am&campaignType=collectPetal&time=Sept-04-2024-Sept-12-2024

Etho University Channel

18 Jul, 19:28


የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ካስፈተኗቸው ተማሪዎች ምን ያህል ፐርሰት ተማሪዎቸው አለፉ ?

እስካሁን ድረስ ይፋ ያደረጉት 👇👇👇

- ጎንደር ዩኒቨርሲቲ 89.35 በመቶ
- አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ 87.04 በመቶ
- ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ 84.7 በመቶ
- ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ 81 በመቶ
- ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ 81 በመቶ
- ቀብሪድሃር ዩኒቨርሲቲ 80.69 በመቶ
- ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ 80.6 በመቶ
- ወልድያ ዩኒቨርሲቲ 80.3 በመቶ
- አርሲ ዩኒቨርሲቲ 79.66 በመቶ
- ጅማ ዩኒቨርሲቲ 79.2 በመቶ
- ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ 77.6 በመቶ
- ወሎ ዩኒቨርሲቲ 72.2 በመቶ
- ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ 71 በመቶ
- ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ 70.62 በመቶ
- ሰመራ ዩኒቨርሲቲ 65.7 በመቶ
- መቱ ዩኒቨርሲቲ 53.00 በመቶ
- ወለጋ ዩኒቨርሲቲ 41 በመቶ ተማሪዎቻቸው ዘንድሮ የተሰጠውን የመውጫ ፈተና ማለፍ እንደቻሉ አሳውቀዋል።
#Mistea
t.me/Mistea

Etho University Channel

15 Jul, 18:15


#Exit
ውጤት እንዴት ማየት ይቻላል?

የመውጫ ፈተና የወሰዱ የ2015 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች ውጤታቸውን ከነገ እሁድ ሐምሌ 09/2015 ዓ.ም ማታ ጀምሮ ውጤታቸውን ኦንላይን ማየት ይችላሉ፡፡
#Mistea
t.me/Mistea

ፈተና የወሰዳችሁ ዕጩ ተመራቂዎች ለፈተናው የተሰጣችሁን User Name በመጠቀም በ https://result.ethemnet.edu.et/ በመግባት ውጤታችሁን ማየት ትችላችሁ።

Etho University Channel

15 Jul, 18:11


#MoE

ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከወሰዱ ዕጩ ተመራቂዎች መካከል 40.6% የሚሆኑት ፈተናውን አልፈዋል።

ከሰኔ 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለስድስት ቀናት የተሰጠውን ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና 150,184 ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች መውሰዳቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

በኦንላይን የተሰጠውን የመውጫ ፈተና ከወሰዱ መካከል 61,054 ዕጩ ተመራቂዎች (40 ነጥብ 6 በመቶ) ፈተናውን ማለፋቸውን የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

የመውጫ ፈተናውን ካለፋ ዕጩ ተመራቂዎች ውስጥ 48,632 ከመንግሥት ተቋማት እንዲሁም 12,422 ከግል ተቋማት መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

ፈተናው በ215 የትምህርት ፕሮግራም መሰጠቱን የገለጹት ሚኒስትር ዲኤታው፤ ውጤት ለተቋማት መላክ መጀመሩን ጠቁመዋል።

የማለፊያ ነጥብ ያላመጡ ተማሪዎች በጥር 2016 ዓ.ም ፈተና እንዲወስዱ ይደረጋል ተብሏል።
#Mistea
t.me/Mistea

Etho University Channel

14 Jul, 19:54


#WeldiaUniversity

የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ውጤት ማምሻውን ይፋ መሆኑን ገልጿል።

እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት ዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ  ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ መሆኑን እንዳረጋገጠ አሳውቋል።

በዩኒቨርሲቲ ደረጃ 80.3% የሚሆኑት እጩ ተመራቂ ተማሪዎቹ የመውጫ ፈተናውን እንዳለፉ ተቋሙ ገልጿል።

መረጃው እንደሚያሳየው ከሆነ በርካታ የትምህርት ክፍሎች 100% ማሳለፍ ችለዋል።

Via ፦ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ
#Mistea
t.me/Mistea

Etho University Channel

14 Jul, 19:51


#Mizantepi

ሚዛም ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት ዛሬ ይፋ መሆኑን ገልጿል።

ተቋሙ በ41 ፕሮግሬሞች ካስፈተናቸው 1604 ተፈታኞች  ፡-
👉በ13 ፕሮግራሞች 100%
👉 በ7 ፕሮግራሞች ከ90-99%
👉 በ11 ፕሮግራሞች ከ80-89% በአጠቃላይ በ31 ፕሮግራሞች 80% እንዲሁም እንደ ዩኒቨርሲቲ 81% ተማሪዎች ያለፉ መሆኑን ይፋ አድርጓል

ዩኒቨርሲቲው ካስፈተናቸው 1604 ተማሪዎች 1289 ተማሪዎች ከ50% በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን ገልጿል።

Via ፦ ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ
#Mistea
t.me/Mistea

Etho University Channel

14 Jul, 19:46


#WelkiteUniversity

ወልቁጤ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን  የመውጫ ፈተና (EXIT EXAM) ካስፈተናቸው  1450 ተማሪዎች መካከል 78.5% ተማሪዎችን በብቃት ማሳለፈ መቻሉን አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ካስፈተነባቸው 43 ፕሮግራሞች መካከል፡-

👉 100%  ያሳለፉት 11 የትምህርት ክፍሎች/ፕሮግራሞች
👉 ከ90% በላይ ያሳለፉ 21 የትምህርት ክፍሎች/ፕሮግራሞች
👉 ከ80% በላይ ያሳለፉ 27የትምህርት ክፍሎች/ፕሮግራሞች
👉 ከ70%በላይ ያሳለፉ 32  የትምህርት ክፍሎች/ፕሮግራሞች መሆናቸውን ጠቁሟል።

" እንደአጠቃላይ ሲታይ የተመዘገበው ውጤት በእጅጉ አስደሳች ነው፡፡ " ሲል ተቋሙ ገልጿል።
#Mistea
t.me/Mistea

Etho University Channel

12 Jul, 16:27


#ExitExam

ከመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ የተለያዩ ጥያቄዎች ከተፈታኝ ተማሪዎች ለEtho University Channel እየደረሱ ይገኛሉ።

ሐምሌ 03/2015 ዓ.ም ከተሰጠው የMechanical Engineering
የHydrauluc and Water Resources Engineering ትምህርት የመውጫ ፈተና ጋር የተያያዙ ቅሬታዎች ለEtho University Channel ደርሰዋል።

ተማሪዎቹ ከወሰዱት የመውጫ ፈተና ጋር የተያያዘ ጥያቂያቸውን ለሚመለከታቸው የዩኒቨርሲቲ አመራሮች በጽሁፍ ማቅረባቸውን ገልጸዋል።

"ፈተናው ዝቅተኛውን Competency አያሟላም"፣ "ፈተናው እጅግ በጣም ከባድ ነው"፣ ጥያቄዎቹ  በጣም እረጃጅም ስለሆኑ ከተሰጠው ስዓት አንፃር ለመረዳት አስቸጋሪ ናቸው "የፈተናው ጥያቄ እና የBlueprint ይዘት አይይገናኝም"፣ "የፈተናው ጥያቄ እና የተሰጠን ሰዓት ፍፁም አይመጣጠንም" እና ሌሎች ጥያቄዎችንም ተማሪዎቹ አንስተዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ ዩኒቨርሲቲዎችም ሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር የሚሉት ካለ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
#Mistea
t.me/Mistea

Etho University Channel

12 Jul, 16:26


#ExitExam

ከመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ የተለያዩ ጥያቄዎች ከተፈታኝ ተማሪዎች ለEtho University Channel እየደረሱ ይገኛሉ።

ሐምሌ 03/2015 ዓ.ም ከተሰጠው የMechanical Engineering
የHydrauluc and Water Resources Engineering ትምህርት የመውጫ ፈተና ጋር የተያያዙ ቅሬታዎች ለEtho University Channel ደርሰዋል።

ተማሪዎቹ ከወሰዱት የመውጫ ፈተና ጋር የተያያዘ ጥያቂያቸውን ለሚመለከታቸው የዩኒቨርሲቲ አመራሮች በጽሁፍ ማቅረባቸውን ገልጸዋል።

"ፈተናው ዝቅተኛውን Competency አያሟላም"፣ "ፈተናው እጅግ በጣም ከባድ ነው"፣ ጥያቄዎቹ  በጣም እረጃጅም ስለሆኑ ከተሰጠው ስዓት አንፃር ለመረዳት አስቸጋሪ ናቸው "የፈተናው ጥያቄ እና የBlueprint ይዘት አይይገናኝም"፣ "የፈተናው ጥያቄ እና የተሰጠን ሰዓት ፍፁም አይመጣጠንም" እና ሌሎች ጥያቄዎችንም ተማሪዎቹ አንስተዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ ዩኒቨርሲቲዎችም ሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር የሚሉት ካለ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
#Mistea
t.me/Mistea

Etho University Channel

12 Jul, 16:10


#ExitExam #የተማሪዎች ህብረት

ከ2015 ዓ.ም የተማሪዎች ምርቃት እና የምረቃ መርሃ ግብር ተሳትፎ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት በቅርቡ መግለጫ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡

በመግለጫው ከተማሪዎች ምርቃት ፕሮግራም ጋር በተያያዘ የተነሳው ሀሳብ ላይ ማስተካከያ ማድረጉን ህብረቱ አሳውቋል።

"ሁሉም ተማሪ ጊዜያዊ የትምህርት ማስረጃውን ከማግኘቱ አስቀድሞ የመውጫ ፈተናን ማለፍ እንደሚጠበቅበት" ህብረቱ ገልጿል።

"የምርቃት መርሃ ግብር ተሳትፎን በተመለከተ በተቋማት ሴኔት ብቻ የሚወሰን መሆኑንም" አመልክቷል።

#Mistea
t.me/Mistea
Etho University Channel

Etho University Channel

27 Jun, 09:52


#ExitExam

ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ምን አሉ ?

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተናን በተመለከተ ለፋና ቴሌቪዥን ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸው ምን አሉ ?

- የፈተናው አይነት " የምርጫ ጥያቄ " መሆኑን ገልፀዋል።

- የፈተናው ጥያቄ ብዛት በተመለከተ ጊዜው ሲደርስ እንደሚገለፅ፤ የጥየቄው ብዛት ግን ከ50 በላይ እንደሆነ ፤ በአብዛኛው ፕሮግራም 100 ጥያቄ እንደሚኖር አሳውቀዋል።

- በአብዛኛው ፕሮግራም 100 ጥያቄ ነው ፈተናው ፤ በተወሰኑ መስኮች ምርጫውን ለመሙላት ብዙ ሂሳብ ስለሚሰሩ የጥያቄ ቁጥሩ ከ100 ሊያንስ ይችላል።

- ተማሪዎች ፈተናውን እንደተፈተኑ ውጤታቸውን ወዲያው መላክ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ቢሮርም የመጀመሪያ ቀን የተፈተኑ ተማሪዎች ውጤት ቢገለፅ ሌሎች ላይ ከሚያሳድረው ጫና አንፃር ወይም ፈተናው ቀለል / ከባድ ነው ብሎ እንዳይዘናጋ / እንዳይጨነቅ ወዲያው አይገለፅም። የፈተናው ውጤት የሚገለፀው የመጨረሻው ፈተና ከተሰጠ ከአንድ ቀን በኃላ ነው።

- ውጤት አልፏል ወድቋል ብቻ ሳይሆን ተማሪው ያመጣው ውጤት ይገለፃል።

- የጤና ተማሪዎች ፈተና ሰኔ 30 ይጀምራል እስከ ሐምሌ 8 ድረስ ይዘልቃል። የጤና ተማሪዎች ቀድመው የሚፈተኑበት ምክንያት ቀኑን ሙሉ ፈተናውን ስለሚወስዱ ነው። ጥዋት ላይ ከሙያቸው ጋር የተያያዘውን ይፈታናሉ ፤ ከሰዓት ላይ የመውጫውን ፈተና ይወስዳሉ / በተቃራኒው / ።

- ፈተናው በከፍተኛ ጥንቃቄ ነው የተዘጋጀው ፤ በውስን ኃላፊዎች ብቻ እንዲታወቅ ተደርጓል፤ ስለማይታተም፣ እጅም ስለሌለበት ደህንነቱ አያሰጋንም።

- ፈተናውን ከመስጫው ሰከንድ በፊት ማየት የሚችል ሰው አይኖርም። ፈተናው ካለቀበት ሰከንድ በኃላ መስራት የሚችል ሰው አይኖርም። ይህ በማዕከል ነው ቁጥጥር የሚደረገው።

- የማለፊያው ነጥብ 50 % እና በላይ ሲሆን ይህን ያላለፉ (ኮርስ ያልጨረሱ) ከ5 / ከ6 ወር በኃላ ጥር እና የካቲት ላይ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና መውሰድ ይችለሉ። በዚህም ከለተሳካ ከቀጣይ አመት ተፈታኞች ጋር መውሰድ ይቻላል። በዓመት ሁለት ጊዜ ለመስጠት ታቅዷል።

- አብዛኛው ተማሪ በመጀመሪያው ዙር ያልፋል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል፤ ካልሆነ ግን በሁለተኛው ዙር ተፈትኖ ያልፋል። ሁለቴ ተፈትኖ ማለፍ ያልቻለ እስከሚያልፍ / 50 % እና ከዚያ በላይ ማምጣቱ እስኪረጋገጥ ፈተናውን መውሰድ ይችላል።

- ፈተናው ተማሪዎች አልተሳካላቸውም ብሎ የማሸማቀቅ ዓለማ ስለሌለው እስኪያልፉ ድረስ መፈተን ይችላሉ።

- ምናልባት ያላለፉ ተማሪዎች ዳግም ፈተና ለመውሰድ መጀመሪያ ሲማሩበት ወደነበረበት ተቋም መሄድ አይጠበቅባቸውም ፤ ባሉበት አካባቢ ባሉ ተቋማት ፈተናውን እንደሚወስዱ የሚደረግበት ሁኔታ ይኖራል።

- ከ50 በመቶ በታች  ያመጡ ተማሪዎች በምረቃ ፕሮግራም ላይ ይሳተፋሉ ? ትምህርት ሚኒስቴር የምረቃ ፕሮግራም በተመለከተ በፖሊሲው ላይ እንደማይፅፍ ገልፀዋል። ጉዳዩ የተቋማት ነው ብለዋል። ሚኒስቴሩ በፖሊሲ የሚያስገድደው ግን የመውጫ ፈተናው የስርዓተ ትምህርቱ አካል ስለሆነ ይህን ያላለፈ ዲግሪ/ጊዜያዊ ጭምር፣  ትራንስክሪብት አይሰጠውም። የምረቃ ፕሮግራም ከማዕከል አይመራም ይህ የተቋማቱ ጉዳይ ነው። እኛ የምንከታተለው ፈተናውን ሳያልፉ ዲግሪ እንዳይሰጣቸው ነው።

- የምረቃ ጉዳይ እና በዕለቱ በምረቃ ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎች ጉዳይ የሴኔት ነው ትምህርት ሚኒስቴር አይመለከተውም። ነገር ግን የመውጫ ፈተናው እየተሰጠ/ ሳይሰጥ በፊት ምረቃ ማድረግ በፍፁም አይቻልም።

- የመውጫ ፈተና ያላለፈ ተማሪ በፍፁም ዲግሪ፣ ቴምፖራሪ ዲግሪ፣ ሰርተፊኬት እንደማይሰጠው አስገንዝበዋል።

#Mistea
t.me/Mistea

Etho University Channel

26 Jun, 21:58


#ETA

" ማንኛውም የግል ትምህርት ወይም ስልጠና ተቋም #የመምህርነት እና #የህግ ትምህርት ዘርፎችን ማስተማር አይችልም "

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ፤ ባዘጋጀው የከፍተኛ ትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ፈቃድ አሰጣጥ ረቂቅ መመሪያ ላይ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወይም የስልጠና ተቋማት በሁሉም መርሃ ግብሮች #የሕግ እና #የመምህርነት ትምህርት ዘርፎችን #አሁንም ማስተማር እንደማይችሉ ተገልጿል።

ከዚህ በፊትም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሁሉም መርሃግብሮች የሕግ እንዲሁም የመምህርነት ትምህርት እንዳይሰጡ የተደረገ ሲሆን አሁንም በአዲሱ መመሪያ የሕግ እና የመምህርነት ትምህርት መስጠት አይችሉም ተብሏል።

ሌሎች በአዲሱ የከፍተኛ ትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ፈቃድ አሰጣጥ #ረቂቅ መመሪያ ላይ ምን ተካቷል ?

- ማንኛውም ተቋም አዲስ ፕሮግራም ለመከፈት ወይም ነባሩን ፕሮግራም ለማስቀጠል የፍላጎት ዳሰሳ፣ የገበያ ጥናት እና ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ እውደ ጥናት ማካሄድ ይኖርበታል፡፡

- ለማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የፕሮግራም ፈቃድ የሚሰጠው ባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) የሚያወጣቸውን መስፈርቶች አሟልተው ሲገኙ ብቻ ይሆናል፡፡

- የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚከፍቷቸው ፕሮግራሞች ባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) የሚያወጣቸውን የመመዘኛ መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

- ለማንኛውም ተቋም የሚሰጥ ፈቃድ የሚያገለግለው በባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) ተገምግሞ ለተፈቀደለት ካምፓስና የትምህርት መስክ ብቻ ይሆናል።

- ማንኛውም ተቋም የጤና የትምህርት መስኮችን መስጠት የሚችለው በመደበኛ መርሃ ግብር ብቻ ይሆናል፡፡

- ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በርቀት ትምህርት መርሃ ግብር ማስተማር የሚችለው ከድንበር ተሻጋሪ ወጪ በመጀመሪያ ዲግሪ ብቻ ይሆናል።

- ማንኛውም የግል ትምህርት ወይም ስልጠና ተቋም #የመምህርነት እና #የህግ ትምህርት ዘርፎችን ማስተማር አይችልም፡፡

- ማንኛውም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋም የትኛውንም ስልጠና በርቀት መርሃ ግብር ለማሰልጠን የሚቀርብ የፈቃድ ጥያቄ የማይስተናግድ ይሆናል።

- ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም #በህክምና_ዶክትሬት እና #በስፔሻሊቲ ትምህርት ፈቃድ ለማግኘት ተቋሙ #የህክምና_ሆስፒታል ሊኖረው ይገባል።

- በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ በተቋም ደረጃ የጸደቀ ስርዓተ ትምህርት የፈቃድ ጊዜው ሳያበቃ የስርዓተ ትምህርት ወይም የዲግሪ ስያሜ ለውጥ ካለባለስልጣኑ ፈቃድ ወጪ ማድረግ አይችልም።

- በሀገር ደረጃ በትምህርት ፖሊሲ ስርዓተ ትምህርቱ እስካልተቀየረ ድረስ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ በተቋም ወይም በካምፓስ ደረጃ የጸደቀ ስርዓተ ትምህርት የፈቃድ/ፈቃድ እድሳት ጊዜው እስካላበቃ ድረስ በሌሎች ካምፓሶች መተግበር ወይም መጠቀም ይችላል።

- የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በበየነ መረብ ወይም በርቀት ትምህርት መርሃ-ግብር ፈቃድ ሲጠይቁ በባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) ስርዓተ-ትምህርቱ ቀድሞ መገምገም እና ተገቢ ማስተካከያ ተደርጎ መፅደቅ ይኖርበታል።

- ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በብሎክ ኮርስ ትምህርት ለመስጠት ያለው አመቺነትና ተገቢነት እንዲሁም የትምህርት ጥራት ላይ የሚኖረውን ተፅህኖ ከግምት በማስገባት ስርዓተ ትምህርቱ ከጸደቀ በኃላ ሊተገብር ይችላል፡፡

መረጃው የተገኘው
ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን መሪ አስፈፃሚ ሕይወት አሰፋ ነው።
#Mistea
t.me/Mistea

Etho University Channel

26 Jun, 21:51


#Exitexam
የተማሪዎች ምረቃ እና የመውጫ ፈተና ማለፍ / አለማለፍ ለምን አይነጣጠልም
የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እንዲሁም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማህበር ፕሬዜዳንት ዶክተር አረጋ ይርዳው ፦

" የ Graduation Ceremony ጉዳይ ፤ በጣም ብዙ ስብሰባ እያደረግን ነው የምንሰራው ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ።

አንዳንድ ጊዜ መመሪያዎችም ሲወጡ ተሳትፈንበት ፣ ተወያይተን ጠይቀን አንዳንድ ጊዜ compromise አድርገው win win situation እየተደረገ ነው የወጣው።

Graduation (ምረቃ) እስከ ዛሬ የነበረው ምን ነበር ? ይሄ የመውጫ ፈተና (exit exam) ታሪክ ከመምጣቱ በፊት፤ በአዋጅ መሰረት አንድ ተማሪ የተወሰነ ፕሬግራሙን አሟልቶ የትምህርት ቤቱ ሴኔት approve አድርጎት ልጁ Graduate ማድረግ ይችላል ሲባል Graduate ያደርጋል ፤ ዲግሪውን ያገኝ ነበር።

አንዳንዶቹ ደግሞ ለመርዳት ብሎ walk የሚያደርጉ ይባላሉ ፤ walk የሚያደርጉ ማለት በዛ ዓመት አንድ class ስለቀረችው ልጁ next year ድረስ ከሚቆይ ለበዓሉ አብሮ ይሳተፍ ምክንያቱም አንድ ዓመት ለመሳተፍ ለምን ይቆያል ቤተሰብ አሉት፣ ለቤተሰቡ almost ጨርሻለሁ ብሎ ሊሆን ይችላል አንድ class ነች ያገኛታል ተብሎ ሲታሰብ አብሮ walk እንዲያደርግ ይድረጋል ፤ ይሄም አብሮ ይሳተፋል ፤ የፎቶ ዕድል ያገኛል።

ይሄ ማለት ፎቶግራፍ እና ጋዎን ስለለበሰ ልጁ Graduate አድርጓል ማለት አይደለም። የceremonyውን part አብሮ ይሳተፍ ምንም ለውጥ የለውም የሚል ነገር ነበር እኛ ለምሳሌ (ዩኒቲ) walk ማድረግ አቁመናል ቆይቷል እኛ ጋር ለምረቃ የሚገባው ልጅ የሴኔትን approval አግኝቶ የት/ቤቱን ፖሊሲ አክብሮ ከጨረሰ Graduate ያደርጋል፤ ceremony ላይ ይሳተፋል።

አሁን exit exam መጥቷል ፤ ይህ ሲመጣ መጀመሪያ ላይ ሲነገር የነበረው ኃላም ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣው ' ምረቃ የምትባለዋ ነገር exit exam ላለፈ ልጅ ብቻ ነው ' አሉ ምን ማለት ነው ምረቃ የምትሰጠው ከሆነ ዲግሪውን እየሰጠኸው ስለሆነ ያ የሚሆነው exit exam ሲያልፍ ነው።

ስለዚህ exit exam ያለፈ ተማሪ ከሆነ ብዥታ የለም።

አሁን Situation የመጣው የexit exam ውጤት ሳይሳካለት ቢቀር / ቢሳካለት የሚለውን ትተን እኛ ceremony ላይ የኛን የሴኔት ጉዳይ የጨረሰ ሴኔት approve ያደረገው ግን exit exam ላይ ያልተሳካለት አብሮ በዓሉ ላይ ቢያከብር ምን አለበት ? የሚል ነው።

እኛ ያደረግነው አዎ እነዚህን ሰዎች እናሳትፋቸዋለን፤ የኛን የሴኔት ጉዳይ የጨረሱ ከሆኑ exit exam ብቻ ያለፉትን አናደርግም ለበዓሉ፤ ለበዓሉ አብረው ይሳተፉ። ይሄ ቅርብ ጊዜ ያደረግነው ነው።

ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ተገናኝነት ለምንድነው exit exam ያለፉትን ብቻ የምታደርጉት እነዚህም ቢሳተፉ ምን አለበት ? ብለን ይሄ የናተ ጉዳይ ነው አለን ትምህርት ሚኒስቴር እኔ አቋሜ exit exam ተፈትኖ ምረቃ የሚለው ዲግሪ ስትሰጠው ነው አሉ።

እኛ የምናደርገው ግን ceremony ይሳተፋል፣ walk ያደርጋል ፤ ዲግሪውን ግን አያገኝም። እንኳን ዲግሪ temporary የሚባለውን አንሰጠውም። በዚህ ተስማምተናል።

ምረቃት ላይ ከባችለር ውጭ የexit exam የማይመለከታቸው የማስተርስ ተመራቂዎችም ይሳተፋሉ ፤ በዚህ ዓመት የመጀመሪያ ሴሚስተር ላይ የጨረሱ exit exam አይመለከታቸውም እነሱም በሴኔቱ ውሳኔ መሰረት ይሳተፋሉ። ሶስተኛው exit exam ይወስዳል የተባለው ሴኔቱን ካሟላ በምረቃ በዓሉ ላይ እንዲሳተፍ እናደርገዋለን።"
#Mistea
t.me/Mistea

Etho University Channel

20 Mar, 11:30


Channel photo updated

Etho University Channel

20 Mar, 11:26


#ቀብሪደሃር

በመኪና አደጋ የአራት ተማሪዎች ህይወት አለፈ

በቀብሪደሃር ዩኒቨርስቲ አራት ተማሪዎች በድንገተኛ የመኪና አደጋ ሕይወታቸው ማለፉ ተገለፀ።
#Mistea
t.me/Mistea
Etho University Channel

Etho University Channel

16 Mar, 11:18


Channel name was changed to «Etho University Channel»

Etho University Channel

15 Mar, 16:44


#MoE

በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ የላቀ ውጤት ያመጣችሁና የውጪ ሀገር የትምህርት ዕድል /Scholarship/ የተሰጣችሁ 273 ተማሪዎች ቀደም ሲል በትምህርት ሚኒስቴር ወደተመደባችሁባቸዉ ዩኒቨርሲቲዎች እንድትገቡ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

የውጪ ሀገር ትምህርቱ የሚጀመረዉ ከመስከረም/2016 ዓ.ም ጀምሮ በመሆኑ ቀደም ሲል ወደተመደባችሁባቸዉ ዩኒቨርሲቲዎች እንድትገቡ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

ለውጪ ሀገር ትምህርታችሁ የሚያግዝ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርትና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ቀደም ሲል ከተመደባችሁባቸዉ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመነጋገር የሚፈጸም መሆኑም ተገልጿል፡፡

በዚህ ጉዳይ በተናጠል ወደ ትምህርት ሚኒስቴር የሚመጣ ተማሪ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ ግልጿል፡፡

#Mistea
t.me/Mistea
Etho University Channal

Etho University Channel

15 Mar, 10:33


ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ከ3 ሺህ በላይ የሪሚዲያል ተማሪዎች ይቀበላል።

ዩኒቨርሲቲው ሚዛን አማን ከተማ እና ቴፒ ከተማ በሚገኙት ሁለት ካምፓሶች ተማሪዎቹን መጋቢት 08 እና 09/2015 ዓ.ም እንደሚቀበል ተገልጿል።

የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ሚዛን-አማን ከተማ በሚገኘው ዋናው ግቢ እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ቴፒ ከተማ በሚገኘው ቴፒ ግቢ በመገኘት ሪፖርት አድርጉ ተብሏል።
#Mistea
t.me/Mistea
Etho University Channal

Etho University Channel

15 Mar, 10:31


#DambiDolloUniversity

በ2015 ዓ.ም በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ተማሪዎች የመግኒያ ጊዜ መጋቢት 19 እና 20/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣
➧ ከ8-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና 2 ኮፒ፣
➧ ስምንት 3×4 ፎቶግራፍ፣
➧ የሌሊት አልባሳት፣
➧ ማጣቀሻ መጻሕፍት፡፡
#Mistea
t.me/Mistea
Etho University Channal