እንኳን አመንኩህ አንተን ኢየሱሴ
እንኳን አወኩህ አንተን ኢየሱሴ
እንኳን አገኘው አንተን ኢየሱሴ
እንኳን አመለኩህ አንተን ኢየሱሴ
አረ እኔ ክብር አገኘው በአንተ
አረ እኔ ሞገስ አገኘው በአንተ
አረ እኔ እረፍት አገኘው በአንተ
አረ እኔ ክብር አገኘው በአንተ
አረ እኔ ሰላም አገኘው በአንተ
1)ግንበኞች የናቁትን ድንጋይ
ለእኔ ክብር ሆንክልኝ ሚታይ
አላፈርኩም አንተን አምኜ
ኢየሱስ ኢየሱስ ብዬ
ከአስተዋዮች እና ጥበበኞች
የሰወርከውን ምስጢር ገለፅክልኝ
ነፍሴን በከበረው ሰረገላ
አስቀምጥካት ከአንተ ጋራ
እንኳን አመንኩህ ....
2)እናት እና አባት እረሱኝ
በአንተ ግን ኢየሱስ ታሰብኩኝ
ከበግ ጥበቃ አምጥተኸኝ
በዘይት ስቀባ እኔ ማን ነኝ
ሳትንቀኝ ኢየሱስ አከበርከኝ
የንግስናን ማዕረግ ሰጠኸኝ
ከፍ አደረከኝ ከፍ በል
ሌላ ምላሽ የለኝ ምን ልበልህ
እንኳን አመንኩህ...
3)ለእኔም ቀን ወጥቶ ክብር እንደማይ
መች አወቀ ሀማ ሲንቀኝ
በንጉስ ደጅ ምቀር መስሎት
ሲያቃልለኝ ውርደቴን ለማየት
በዚህም ሳያበቃ ከሰሰኝ
ፍቃድን አግኝቶ ሊገድለኝ
አምላኬ አዋጁን ሽረህልኝ
ጠላቴን አዋርደህ አከበርከኝ