===========================
ጥር 19/2017 ዓ.ም (ኢሚ) በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተኪ ምርቶች ተወዳዳሪነት ስራ አስፈፃሚ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ፣ ተጠሪ ተቀማትና ለአምራች ኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ከጥር15/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ማሻሻልን በተመለከተና በዕሴት ሰንሰለት ዙሪያ የሰጠውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና አጠናቋል፡፡
በማጠናቀቂያ መርሀ ግብሩ ተገኝተው ንግግር ያደረገጉት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተኪ ምርቶች ተወዳዳሪነት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ መሳይነህ ውብሸት የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ውስጣዊ ችግር በመፍታት የመንግስትን ጥረት ልናግዝ ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
አቶ መሳይ አምራች ኢንዱስትሪዎች ትርፋማ ሆነው ከሌሎች ሀገራት ጋር ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በመካከላቸው የዕሴት ሰንሰለት እንዲኖር በትኩረት መሰራት እንዳለበትና በቀጣይም የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም የሚያጎለብቱ ተመሳሳይ ስልጠናዎች እንደሚሰጡ አክለዋል፡፡
የስልጠናው ዋና ዓላማ ሰልጣኞች ጥሩ የኢንዱስትሪ አመራር ክህሎት ኑሯቸው አምራች ኢንዱስትሪዎች ደረጃውን የጠበቀና ጥራት ያለው ምርት እንዲያመርቱ የራሳቸውን ሚና እንዲጫወቱ ማስቻል እንደሆነ ከስልጠናው ይዘት ማወቅ ተችሏል፡፡
በስልጠናው መሰረታዊ የአምራች ኢንዱስትሪ አመራር ክህሎት፣ የኢንዱስትሪዎች ማምረት አቅም የሚሻሻልበት ዘዴ፣ በኢንዱስትሪዎች መካከል የዕሴት ሰንሰለት መፍጠርን በተመለከተና የዕሴት ሰንሰለትን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ተብራርቷል፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት
http://linktr.ee/fdremoi