=============================
የካቲት 01/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኤች ኬ ቢዝነስ ግሩፕ ኃላፊነቱ የግል ማህበር ፕላስቲክ ፎርምዎርክ ፋብሪካ ምርቃት ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል መንግስት ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እና ክትትል በማድረግ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የተረጋጋ ኢኮኖሚ ለመፍጥር እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በጥናት ላይ የተመሰረተ የአምራች ኢንዱስትሪውን ችግሮች በመለየት ደረጃ በደረጃ መፍታት መቻሉን አስረድተዋል ፡፡
የአምራች ኢንዱስትሪ መሰረትን ለማስፋት፣ የሀገር ውስጥ ፍላጎትን በጥራትና ተወዳዳሪነት ለማሟላት ብሎም በዘላቂነት ምርቱን ለውጭ ገበያ የሚያቀርብ ጠንካራና ተወዳዳሪ ኢንዱስትሪ መገንባት የሚቻለው ገቢ ምርት የሚተኩ ኢንዱስትሪዎችን በመደገፍ እና በማበረታታት ነው ብለዋል።
ፕላስቲክ ፎርምዎርክ ፋብሪካው ለማንኛውም በኮንክሪት የሚሰሩ መሰረተ ልማቶችን ለመገንባት የሚያገለግል ነው ያሉት ሚኒስትሩ ከእንጨት የሚሰራ የግንባታ ግብዓትን በመተካት የደን መጨፍጨፍን እና የአከባቢ ብክለት በመቀነስ የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የሚደግፍ ነው።
ምርቱ ከአዲስ የፕላስቲክ ጥሬ እቃ በተጨማሪ ከወዳደቁ የፕላስቲክ ማቴሪያሎች የሚሰራ እና አገልግሎቱን ሲጨርስም እንደገና በመሰብሰብ ተመልሶ ጥቅም ላይ በመዋሉ የአካባቢ ብክለትን ከመቀነስ አንጻር ከፍተኛ አስተዋጾ መኖሩን ገልፀዋል ፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት
http://linktr.ee/fdremoi