来自 የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia (@ministryofindustry) 的最新 Telegram 贴文

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia Telegram 帖子

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia ቴሌግራም ቻናል ነው፡፡
የኢፊዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርን የተመለከቱ መረጃዎችን
• ዜናዎች
• ሁነቶች
• የተለየያዩ ለአምራች ኢንዱስትሪ ማህበረሰብና ስለ ተቋሙ መረጃ የሚያገኝበት ቻናል ነው፡፡
https://t.me/+P0HOYJNw-wgyMmNk ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉ፡፡
10,024 订阅者
5,606 张照片
143 个视频
最后更新于 11.03.2025 07:50

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia 在 Telegram 上分享的最新内容

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia

08 Mar, 05:39

909

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውና የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለዘርፉ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነዉ/አቶ መላኩ አለበል /
=================
የካቲት 29/2017 ዓ.ም ( ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ክሮታጅ ጣህኒ የሰሊጥ ማቀነባበሪያ ፋብሪካን ጎብኝተዎል።

በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በትኩረትና በቅንጅት እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዎል፡፡

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውና የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለዘርፉ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል፡፡

ወደ ውጪ ከሚላኩ የግብርና ምርቶች መካከል ሰሊጥ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ጠቁመው ፋብሪካው ሰሊጥ ምርት ላይ እሴት በመጨመር ለገበያ የማቅረቡን ሥራ እንዲያጠናክር አሳስበዋል፡፡


#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት
http://linktr.ee/fdremoi
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia

06 Mar, 11:16

1,371

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ፂዮን ኢዱስትሪያል ኢጂነሪግ እና ብረታ ብረት ኢንተርፕራይዝ የመስክ ምልከታ አደረጉ ።
====================================
የካቲት 26/2017ዓ.ም (ኢሚ)ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል የፋብሪካ ምልከታ ሲያካሂዱ ለሚኒስትሩ ገለፃ ያደረጉት የፂዮን ኢዱስትሪያል ኢጂነሪግ እና ብረታ ብረት ኢንተር ፕራይዝ መስራች እና ባለቤት የሆኑት አቶ ዮሐንስ ግርማ ናቸው ።

በገለፃው ወቅት አቶ ዮሐንስ እዳሉት ፋብሪካው በ1999 ዓ.ም በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅቶ በ5000 ብር ካፒታል ስራ የጀመረ መሆኑን ገልፀዋል ።

ባለፉት 18 ዓመታት የተለዩ ደረጃዎችን አልፎ ሰልሣ ሚሊየን ብር የሚያንቀሳቅስ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ዞን አንድ ሺህ ካሬ መሬት ላይ ያረፈ ግዙፍ ፈብሪካ ያለው ለመሆን በቅቷል ብለዋል ።

በፋብሪካው የሚመረቱ ምርቶች የምግብ ማቀነባበሪያ ማሽኖች ፣ የዳቦ መጋገሪያና ማቡኪያ ፣ የቡና መቁያ እና መፍጫ፣ የእህል መከኪያ እና ማበጠሪያ ፣ የመኖ መፍጫና ማቀነባበሪያ ፣ የዕቃ ማሽን ክሬን እና የአመነበረድ ማሽኖች እንደሚያመርት ገለፃ አድርገዋል።

ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ስለፋብሪካው ለተደረገላቸው ገለፃ አመስግነው መንግስት ከዚህ በተሻለ እንዲያመርቱና ውጤታማ እንዲሆኑ የበኩሉን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል ።

ፋብሪካው ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሃገር ውስጥ በመተካት እየሰራ ያለው ስራ ተስፋ ሰጪ መሆኑን ለማየት ተችሏል ።

#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት
http://linktr.ee/fdremoi
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia

05 Mar, 16:48

1,208

በኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡልልታ የተመራ ሰባተኛው የቆዳ ተነሳሽነት ለዘላቂ የሰው ሀይል  ልማት/leather industry for sustainable employment Cerastion  / ውይይት ተካሄደ፡፡
=================
የካቲት 26/2017 ዓ.ም (ኢሚ) በውይይቱ  በቆዳው ዘርፍ ያሉ ዋናዋና ጉዳዮች የተነሱ ሲሆን  በተለይም ጥሬ ቆዳ ጥራትና አሰባሰብ፣የቆዳ ኢንዱሰትሪዎች የማምረት እቅም ፣አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎችን ማስፋፋት እና የገበያ ተጠቃሚነትን ማሳደግ እንዲሁም በመንግስት ትኩረት ተሰቶት  እየተሰራ የሚገኘው የሞጆ ሌዘር ሲቲ ፕሮጀክት አፈጻጸም በውይይቱ ተነስቷል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤት አቶ ታረቀኝ  ቡሉልታ በሞጆ ከተማ የተሟላ የሳተላይት ላብራቶሪ   መሰራቱን ጠቁመዉ መጋቢት ወር ላይ ስለሚመረቅ ቀሪ ስራዎች እንዲጠናቀቁ አሳስበዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም የሞጆ ሌዘር ሲት ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ  አሁን ያለውን የቆዳ ኢንዱስትሪ ለማዘመን እና ምቹ ለማድረግ ሚናዉ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው ፕሮጀክቱ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ በስራ ላይ ያለው የፕሮጀክቱ ኮሚቴ የአዋጭነት ጥናቱ በፍጥነት እንዲጠናቅ መመሪያ ሰተዋል፡፡

በውይይቱ  የሞጆ ከተማ አስተዳዳር ከንቲባ ፣ከግብና ሚኒስቴር፣ከገንዘብ ሚኒስቴር ከአውሮፓ ህብረት  እና ሌሎችም አካላት ተሳትፈውበታል፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia

05 Mar, 07:14

1,293

ዘላቂነት ያለው እና ሁሉን አቀፍ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ለመገንባት እንሰራለን ( ሚልኬሳ ጃገማ(ዶ/ር )
====================================================
የካቲት 26/2017 ዓ.ም (ኢሚ) አለማቀፉ የቆዳ ህብረት ስራ ( leather working group) በኢትዮጵያ ለሚገኙ የቆዳ ውጤቶች አምራች ፋብሪካዎች ለኤልኮ አቢሲኒያ የቆዳ ፋብሪካ እና ለኤልኮ አዋሻ የቆዳ ፋብሪካ የወረቅ ደረጀ የእውቅና ሰርተፍኬት እንዲሁም ለባቱ የቆዳ ፋብሪካ የብር ደረጃ ያለው የእውቅና ሰርተፍኬት ሰጥቷቸዋል ፡፡

በታዋቂው አለማቀፉ የቆዳ ህብረት ስራ የሽልማት ሥነ ሥርዓት እንግዳ ሆነው የእውቅና ሰርተፍኬቱን የሰጡት የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲዩት ዋና ዳይሬክተር ሚልኬሳ ጃገማ (ዶ/ር ) ናቸው፡፡

ለአምራች ኢንዱስትሪዎቻችን የተሰጠው የእውቅና ሽልማት በቆዳ ኢንዱስትሪ ውስጥ ዘላቂ እና ለአካባቢ ጥበቃ ኃላፊነት የሚሰማቸው ተግባራን በመስራት እና በማከናወን ለሥነ-ምህዳር ተስማሚ ምርትን ከማስተዋወቅ ባሻገር ኢንዱስትሪዎቻችን በአለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ሆነው እንዲቀጥሉ ያደርጋል ብለዋል ፡፡
አለማቀፉ የቆዳ ህብረት ስራ ተልእኮ ከሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ ሁኔታዎች እንዲሁም ከኢትዮጵያ መንግስት ዘላቂ የኢንዱስትሪ እድገት እና ራዕይ ጋር በትክክል የሚጣጣም መሆኑን ገልፀዋል ፡፡

ዶ/ር ሚልኬሳ አክለውም የተባበሩት መንግስታት የዘላቂ ልማት ግቦች የኢንዱስትሪ፣ ፈጠራ እና መሠረተ ልማት ስራዎችን ኃላፊነት ባለው መንገድ የምርት እና አጠቃቀም ስርዓት ዘርግተን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል ፡፡

ኦሬሊያ ካላብሮ የተባበሩት መንግስታት የኢዱስትሪል የልማት ድርጅት (UNIDO) ፕሮጀክት ሌዚክ ማናጀር በበኩላቸው የኢትዮጵያ የቆዳ ፋብሪካዎች ይህን አለም አቀፍ እውቅና ያለው አዋርድ ማሸነፋቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያደርጋል ብለዋል ፡፡

አምራች ኢንዱስትሪዎቻችን ያገኙት የእውቅና ሽልማት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እያደገና ለውጥ መምጣቱን የሚያሳይ ነውያሉት ዋና ዳሬክተሩ ሌሎች የሃገርውስጥ ፋብሪካዎች ከእነዚህ አምራቾች ተሞክሮና ልምድ በመውሰድ ውጤታማ እንዲሆኑ መንገድ የሚከፍት ነው ብለዋል ፡፡

በዘርፉ የተካሄደውን ዓለማቀፋዊ ውድድርቨ ውድድር እንዲካሄድ የፋይናስ ድጋፍ ያደረገው የአውሮፓ ህብረት ስለመሆኑ በመርሃግብሩ ላይ ተገልጿል ፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት
http://linktr.ee/fdremoi
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia

28 Feb, 16:29

1,460

ማንበብ ተቋሙን በመረጃ እና በእውቀት በማደራጀት እንደ ሃገር የተጣለብንን ሃላፊነት ለመወጣት ትልቅ አቅም ይሆነናል ( አቶ ሀዱሽ ሀለፎም)
============================
የካቲት 21/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሚኒስትር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀዱሽ ሀለፎም እንደገለፁት ዛሬ በተቋሙ እና በተጠሪ ተቋም ለምትገኙ አመራሮችና ሰራተኞች ያዘጋጀነው የቤተ መፀሐፍት አሰፈላጊነት አጠቃቀም ምን እና እዴት መሆን አለበት የሚለውን የዘርፉ ሰራተኞች በቂ እውቀት እንዲኖራችሁና የተቋሙን ራዕይና ተልዕኮ በአግባቡ እንድታስፍፅሙ በማሰብ ነው ብለዋል።

እንደ ኢዱስትሪ ሚኒስቴር ብዙ ሃለፊነት እና ተልዕኮ አለብን ያሉት አቶ ሀዱሽ ኃላፊነታችንን በብቃት እና በእውቀት ለመወጣት ተከታታይ የአቅም ልማት ስልጠናዎች አስፈላጊ ናቸው ብለን እናምናለን ብለዋል ።

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መፃህፍት አገልግሎት የቤተ መፃሕፍት ባለሙያ ወ/ሮ አሰቴር ፍሰሃ በበኩላቸው ቤተ መፃሕፍት ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መደራጀት እና በሰለጠነ ባለሙያ መመራት አለበት ብለዋል።

ቤተ መፃሕፍት በዓለማችን ላይ ባሉ የዕውቀት ዘርፎች ላይ የተሰሩ ሰራዎች ተደራጅቶና ተሰንዶ ትርጉም ባለው መንገድ የሚቀመጥበት ስፍራ ከመሆኑም ባሻገር ታሪካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ፋይዳ ያላቸው መፃሕፍት የምናገኝበት ቦታ ነው ሲሉ ገልፀዋል ።

በመሆኑም አሉ ባለሙያዋ ቤተ መፃሕፍት ሰናደራጅ የቤተ መፃሐፍት ዓላማ፣ የተጠቃሚ ዓይነቶች፣ የቤተ መፀሐፉ ህንፃ እና የቤተ መፀሐፍት ባሙያዎች ታስቦበት እና ተጠንቶ መቋቋም አለበት ብለዋል ።

በተጨማሪም ቤተ መፃሕፍት ሲቋቋም የተመቻቸና የተፈጥሮ ብረሃን ሊያገኝ የሚችል፣ ለማንበብ ብቻ ሳይሆን በማሰላሰል እና በተመሰጦ ውስጥ ሆኖ ዘና በማለት እውቀት የሚገኝበት ቦታ ነው ብለዋል ።

በአጠቃላይ ቤተመፃሕፍት እንደ የተቋሙ ዓላማ፣ እንደተጠቃሚዎቹ አይነትና እንደሚይዙት የመረጃ ዓይነት ይለያያሉ ሲሉ ገልፀዋል ።

በመጨረሻም ሰልጣኞቹ ሰልጠናው በቂ ግንዛቤና ዕውቀት ያገኙበት እና የማንበብ ክህሎታቸውን ያለበትን ደረጃ በመፈተሽ የንባብ ባህላቸውን የሚያሳድጉበትን መንገድ ለመቀየስ የማንቂያ ደወል ነው ብለዋል ።

#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት
http://linktr.ee/fdremoi
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia

28 Feb, 07:32

882

በይርጋለም የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፖርክ የህፃናት ማቆያ ተመርቆ ተከፈተ።
==========================
የካቲት 21/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢንዱስትሪ መሰረተ ልማትና ግብአት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን እና የሲዳማ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድርና ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ በየነ በራሳ የህፃናት ማቆያ መርቀው ስራ አስጀምረዋል ።

የህጻናት ማቆያ ማዕከሉ መቋቋም የምርትና ምርታማነት መጨመር ፣ የማህበረሰብ ልማት ማጎልበት ያለው ሚና የጎላነው ያሉት የኢንዱስትሪ መሰረተ ልማትና ግብአት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ ለፓርኩ ሰራተኞችና በፓርኩ አካባቢ ለሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ምቹ እና ተስማሚ የስራ አካባቢ በመፍጠር ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ማደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልፀዋል ።

የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን በበኩላቸው የህፃናት መዋያ ስፍራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ በስነ-ምግባር የታነፀ በስነልቦና የዳበር ጤናማና አምራች ዜጋን መፍጠር ይገባልም ብለዋል።

በተለይም በፓርክ ውስጥ ያሉ ሴት ሠራተኞች በወሊድ ምክንያት ከስራ ገበታቸው ውጪ እንዳይሆኑና ውጤታማ ስራ እንዲሰሩ እንደሚያግዛቸው ተናግረዋል ።

በምርቃቱ ላይ ሌሎች የሚመለከታቸው የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት
http://linktr.ee/fdremoi
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia

28 Feb, 07:02

742

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር በመሆን 129ኛዉ የዓድዋ ድል በዓልን በተለያዩ ፕሮግራሞች አከበረ
==============================
የካቲት 21/6/2017ዓ.ም (ኢ.ሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር በመሆን 129ኛዉ የዓድዋ ድል በዓልን "ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል" በሚል መሪ ቃል አከበረ፡፡

የቀደሙ አባቶች ለሀገርና ለትውልድ ግንባታ ትልቅ ትርጉም ያለውና ዘመን የማይሽረው ታሪክ በመስራት ባህላችን፣ ቋንቋችን፣ ራሳችን የማስተዳደር ስልጣን እና ታሪክ ያለን ጥንታዊና ድል አድራጊ ሃገር ሆነን እንድንታይ አድረገዋል፡፡

በአንድነት ፣በጋራ እና በሀገር ፍቅር ስሜት በጋራ በመስራት እንደ ሀገር የተያዙ ዕቅዶችን በመተግበር እንደተቋም የተቀመጡ ተግባርና ሀላፊነትን በመወጣት ለሀገር እድገት መስራት ያስፈልጋል በሚል 129ኛዉ የዓድዋ ድል በዓል የተከበረ ሲሆን በእለቱም የጥያቄ እና መልስ ውድድር በማድረግ ተከብራል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት
http://linktr.ee/fdremoi
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia

22 Feb, 10:41

746

በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን በወንዶ ገነት ወረዳ ወንዶ የተጣራ የምንጭ ዉሃ ፋብሪካ በሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ ተመረቀ፡፡
=============================
የካቲት 15/2017 ዓ.ም (ኢሚ) በሲዳማ ክልል ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን በወንዶ ገነት ወረዳ ወንዶ የተጣራ የምንጭ ዉሃ ፋብሪካ በሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ ተመርቆ በይፋ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል ።

ፋብሪካዉ በቢ.ቢ.ኬ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/ የግል ማህበር በ268 ሚሊዮን ብር በ1.6 ኸክታር መሬት ላይ የተገነባ ስሆን በቀን 100 ሺህ ሊትር ዉሃ እያጣራ የሚያሽግ መሆኑና ለ100 ወጣቶች የስራ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ተገልጿል።

ፋብሪካዉን መርቆ ሥራ ያስጀመሩት የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ እንዳሉት ይህ ፋብሪካ በመገንባቱ ለአከባቢው ህብረተሰብና ለወጣቶች የስራ ዕድል የሚፈጥርና ዘርፈ ብዙ ጥቅም የሚሰጥ በመሆኑ ሁሉም የአከባቢው ማህበረሰብ መጠበቅና መጠቀም እንዳለበት አሳስበዋል ።

በተጨማሪም የሲዳማ ክልል ሰላማዊ ክልል በመሆኑ በክልሉ ዉስጥ እንቨስት ማድረግ የሚፈልጉ ባለሀብቶች በሚፈልጉት ዘርፍ እንዲሳተፉ ጠይቀዋል ።

የሲዳማ ክልል የኢዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጎሳዬ ጎዳና በበኩላቸዉ የክልሉ መንግስት ለእንደዚህ አይነት ልማታዊ ባለሀብቶች ክፍት መሆኑንና አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ አስገንዘበዋል ።

የፋብካዉ ባለቤትና ሥ/አስኪያጅ አቶ ባላንቴ ባንኮ እንዳሉት ይህ ፋብሪካ በጥረታቸዉ የተገነባ መሆኑን ጠቁመው የሲዳማ ክልል በንጹህ የዉሃ ምንጭ የተከበበ ክልል መሆኑን ጠቅሰዉ እንቨስት በማድረጋቸዉ መደሰታቸዉንና የክልሉ መንግስት ድጋፍ የላቀ መሆኑን ገልጸዉ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።

በምረቃ ፕሮግራም ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ የክልል፣ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ አካላት ተገኝተዋል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት
http://linktr.ee/fdremoi
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia

21 Feb, 10:56

1,086

የሃገር ውስጥ ባለሃብቶችን ተሳትፎ የሚያሳድግ የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው ።
================================
የካቲት 14/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የንቅናቄ መድረኩን ያሰጀመሩት በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የመሰረተ ልማትና ግብዓት ዘርፍ አማካሪ አቶ ዳንኤል ኦላኒ እንደገለፁት ለአንድ ሃገር ዕድገት የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የሚያበረክተው ሚና ወሳኝ ነው።

በዘርፋ ላይ ያሉትን ዕድሎች በማመላከት ባለሃብቱ ወደ ዘርፉ በመቀላቀል ለሀገሩ ዕድገት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ለማስቻል ታስቦ የውይይት መድረኩ መዘጋጀቱን ገልፅዋል።

የአምራች ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት በንግድ በኮንስትራክሽን፣ በሪል ስቴት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሃብቶችን በውይይቱ ታድመዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት
http://linktr.ee/fdremoi
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia

21 Feb, 09:09

867

የኢትዮጵያ ታምርት ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ዕድገት የሚያበረክተው የላቀ ነው (አቶ መላኩ አለበል)
=================================
የካቲት 14/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የመንግስት ተቋማት የስራ ትስስር ችግርን በመፍታት ለሀገር እድገት በቅንጅት መስራት አማራጭ የሌለው ተግባር ስለመሆኑ በተግባር ያስመሰከረ ነው ብለዋል።

ባለፉት ሶስት ዓመታት ትልልቅ ግቦችን አቅደን አሳክተናል ሲሉ የገለፁት አቶ መላኩ ያሉን ኢንዱስትሪዎች በቁጥር ትንሽ ቢሆኑም የማምረት አቅም አጠቃቀማቸው ዝቅተኛ እንደነበር ጠቅሰው በተሰሩ በርካታ ስኬታማ የቅንጅት ስራዎች የኢንዱስትሪዎቻችን የማምረት አቅም አጠቃቀም ከ46 በመቶ ወደ 61.2 በመቶ ከፍ እንዲል ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

በ10 ዓመቱ 85 በመቶ የማምረት አጠቃቀም ለማድረስ ዕቅድ መያዙን የጠቀሱት ሚኒስተሩ የገቢ ምርት ምጣኔውን በመቀነስ በሀገር ውስጥ መተካትና የወጭ ምርት መጠናችንን በማሳደግ የዘርፉን ኢኮኖሚያዊ አበርክቶት ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር ዘላቂ ዕድገት ያለው ተወዳዳሪ ዘርፍ መፍጠር የሁላችንም የዕለት ከእለት ተግባር መሆን ይጠበቅበታል ።

የኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ የፈጠራቸው አደረጃጀቶች ቅንጅታዊ አሰራርን በማሳለጥ ዘርፉ ከላይ እስከታች ባለው የመንግስት መዋቅር አመራር ዘንድ ልዩና የቅድሚያ ትኩረት እንዲያገኝ ያስቻለው መሆኑን ገልፀዋል ።

የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ የገበያ ትስስር በመፍጠር፣ አዳዲስ ኢንቨስትመንትን በመሳብ፣ የወጪ ምርቶችን መጠን በመጨመር የውጭ ምንዛሬ ገቢን በማሳደግ፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት፣ ለዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር ዘርፉ ተስፋ የሚጣልበት የኢኮኖሚያችን መሠረት የመሆኑን አይቀሬነት ከወዲሁ እያረጋገጠ ነው ያሉት ሚኒስትሩ የ2017 ኤክስፖ ከ5 እስከ 6 ቢሊዮን ብር ግብይት ይፈጠርበታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል ።

#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት
http://linktr.ee/fdremoi