=======================================
የካቲት 13/2017 ዓ.ም (ኢሚ) በኢትዮጵያ ታምርት 2017 ዓ.ም ኤክስፖ የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ዓለማችን ከአራተኛው የኢንዱስትሪ አብዮት ወደ አምስተኛው እየተንደረደረች በመሆኑ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ሰዎችና ማሽን ተሰናስለውና ተቀናጅተው የሚያመርቱበት የምርት ስልት እየተገነባ ነው ብዋል።
በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ምክንያት ኢንዱስትሪ የላቀ ለውጥ እያሳየ ያለበት ዓለም ላይ ነን ያሉት አቶ መላኩ የሮቦቲክስ፣ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ዓለማቀፍ የኢንተርኔት ትስስር ኢንዱስትሪን ወደ አዲስ ምዕራፍ እያሽጋገረ በመሆኑ ይህ ለውጥ የምርት ሂደትን የበለጠ ውጤታማ፣ ፈጣንና በተመጣጣኝ ወጭ ለማምረት በማስቻል ዓለም ወደ አዲስ የኢኮኖሚ ዘመን እያመራች እንደሆነም ማረጋገጥ መቻሉን በመጠቆም በመጪው ዘመንም ይበልጥ እየረቀቀና እየዘመነ እንደሚሄድ ይጠበቃል።
የሀገራት የቀደምት ስልጣኔ መለያ የሆኑት በግብርና እና በምግብ ማምረት፣ በጽህፈት፣ በስነ ህንፃና የምህንድስና፣ በሂሳብና የሳይንስ፣ በፖለቲካና የማኀበራዊ ስርዓቶች፣ በንግድና የኢኮኖሚ፣ በሃይማኖት እና የፍልስፍና፣ የውጭ ጠላትን በመከላከልና ድንበርን በማስከበር፣ በባህልና በኪነጥበብ ኢትዮጵያን ከቀዳሚ የዓለም ሃገራት ተርታ የሚያሰልፍ የሰው ልጅን ታሪክ፣ ባህልና ዕድገት የሆኑት የስልጣኔ ማሳያዎች ቀደምት ባለቤቶች ብንሆንም እንደ አጀማመራችን የአመራረት ስርዓታችንን ማዘመን ባለመቻላችን ግብርናችን ከበሬ፣ ኪነ ህንፃችን ከላሊበላ፣ ሂሳብና ሳይንሳችን ከቀንና ከኮከብ ቆጠራ እና ፖለቲካችን ልዩነት ማስፊያነት ያለፈ ለውጥ የሚያመጣ ማድረግ አለመቻላችንን ገልፀዋል ::
ዘላቂና አካታች ኢኮኖሚ ለመገንባት ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ትኩረት መስጠት ግዴታ በመሆኑ መንግስት የቅድሚያ ትኩረት ከሰጣቸው አምስት ዘርፎች መካከል የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ቀዳሚ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ዘመናዊነትን ያልተከተለውን የአሰራር ስርዓታችንን በመቀየር ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት እናደርጋለን ስንል የትናንት ታሪካችንን በመልካም መነሻነት ተጠቅመን ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ አካተን ምርትና ምርታማነትን አሳድገን በሰለጠነ የፖለቲካ ባህል ልዩነቶቻችን በውይይት ፈተን እንደምናሳካው በማሰብ ነው ብለዋል፡፡
በ2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን ስንጀምር ሰፊ ገበያ፣ አማራጭ ግብዓት፣ አስተማማኝ የሃይል ምንጭ፣ ፈጥኖ ሰልጣኝ ጉልበት ከዲጂታል ዘመን ጋር ተደምሮ ኢንዱስትሪን በማስፋፋት የዘመናት ስብራታችን እንደሚጠገን በመተማመን ነው፡፡
እንደ ሀገር የጀመርነው የኢኮኖሚ ሪፎርም ማሻሻያ ፣ አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍን ለመደገፍ የተቋቋመው ካውንስል፣ የመንግሥትን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የተጀመሩ ሪፎርሞች፣ በክልል ደረጃ የተጀመሩ የኢትዮጵያ ታምርት ስቲሪንግ ኮሚቴ ስራዎች፣ ውድድርን የሚገቱ ህጎችንና አሰራሮችን ለማሻሻል በየተቋሙ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች የኢትዮጵያ ታምርት ስራን ውጤታማ እንዲሆን ያደረጉ ተስፋ ሰጭና ሁኔታ ቀያሪ ተግባራት ናቸው፡፡
የ2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ከሚያዚያ 29/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 7 ቀናት የሚከናወን መሆኑን የጠቀሱት አቶ መላኩ ለኤክስፖው ስኬታማነት ሁሉም ባለድርሻ አካል የበኩሉን አዎንታዊ አስተዋፅኦ እንዲያበረክት አሳስበዋል ።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት
http://linktr.ee/fdremoi