Neueste Beiträge von የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia (@ministryofindustry) auf Telegram

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia Telegram-Beiträge

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia ቴሌግራም ቻናል ነው፡፡
የኢፊዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርን የተመለከቱ መረጃዎችን
• ዜናዎች
• ሁነቶች
• የተለየያዩ ለአምራች ኢንዱስትሪ ማህበረሰብና ስለ ተቋሙ መረጃ የሚያገኝበት ቻናል ነው፡፡
https://t.me/+P0HOYJNw-wgyMmNk ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉ፡፡
10,024 Abonnenten
5,606 Fotos
143 Videos
Zuletzt aktualisiert 11.03.2025 07:50

Der neueste Inhalt, der von የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia auf Telegram geteilt wurde.

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia

08 Feb, 10:55

497

ፕላስቲክ ፎርምዎርክ ፋብሪካ ተመረቀ።
=============================
የካቲት 01/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኤች ኬ ቢዝነስ ግሩፕ ኃላፊነቱ የግል ማህበር ፕላስቲክ ፎርምዎርክ ፋብሪካ ምርቃት ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል መንግስት ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እና ክትትል በማድረግ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የተረጋጋ ኢኮኖሚ ለመፍጥር እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በጥናት ላይ የተመሰረተ የአምራች ኢንዱስትሪውን ችግሮች በመለየት ደረጃ በደረጃ መፍታት መቻሉን አስረድተዋል ፡፡

የአምራች ኢንዱስትሪ መሰረትን ለማስፋት፣ የሀገር ውስጥ ፍላጎትን በጥራትና ተወዳዳሪነት ለማሟላት ብሎም በዘላቂነት ምርቱን ለውጭ ገበያ የሚያቀርብ ጠንካራና ተወዳዳሪ ኢንዱስትሪ መገንባት የሚቻለው ገቢ ምርት የሚተኩ ኢንዱስትሪዎችን በመደገፍ እና በማበረታታት ነው ብለዋል።

ፕላስቲክ ፎርምዎርክ ፋብሪካው ለማንኛውም በኮንክሪት የሚሰሩ መሰረተ ልማቶችን ለመገንባት የሚያገለግል ነው ያሉት ሚኒስትሩ ከእንጨት የሚሰራ የግንባታ ግብዓትን በመተካት የደን መጨፍጨፍን እና የአከባቢ ብክለት በመቀነስ የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የሚደግፍ ነው።

ምርቱ ከአዲስ የፕላስቲክ ጥሬ እቃ በተጨማሪ ከወዳደቁ የፕላስቲክ ማቴሪያሎች የሚሰራ እና አገልግሎቱን ሲጨርስም እንደገና በመሰብሰብ ተመልሶ ጥቅም ላይ በመዋሉ የአካባቢ ብክለትን ከመቀነስ አንጻር ከፍተኛ አስተዋጾ መኖሩን ገልፀዋል ፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት
http://linktr.ee/fdremoi
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia

07 Feb, 13:04

906

አካታችና ዘላቂ የማኑፋክቸሪንግ ስርዓት መዘርጋት የፖሊሲው ቁልፍ የውጤት መስክ ነው (አቶ ጥላሁን አባይ)
================================
ጥር 30/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በአካባቢና በአየር ንብረት ለውጥ ስራ ላይ ለተወከሉ የክልልና ከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲውን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የሰጡት የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚው አቶ ጥላሁን አባይ አካታችና ዘላቂ የማኑፋክቸሪንግ ስርዓት መዘርጋት የአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲው ቁልፍ የውጤት መስክ ነው።

በፖሊሲው ውስጥ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ዘላቂነትና አካታችነት እውን ለማድረግ አንድ ፕሮግራም እና ሁለት ንዑስ ፕሮግራሞች መለየታቸውንና ፖሊሲውን በመተግበር የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ስኬታማነት ለማረጋገጥ አራት ስትራቴጅዎችና ሁለት ፍኖተ ካርታዎች ተጠናቀው ወደ ትግበራ መግባታቸውን ገልፀዋል ።

የአየር ንብረት ለውጥ ቡድን መሪው አቶ እስማኤል መሀመድ በበኩላቸው አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ለከባቢ አየር ተስማሚ እንዲሁም ለመጭው ትውልድ ደህንነትና ጤንነት የቅድሚያ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ ዘላቂና አካታች ዘርፍ እንዲሆን የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ይጠይቃል ብለዋል።

በአምራች ኢንዱስትሪ ኢንስቲትዩት የኢንዱስትሪ ኢነርጅ ተመራማሪ የሆኑት አቶ መንገሻ አብርሃ እንደገለፁት የኢነርጅ ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የስራ ሞተር ከመሆኑም በላይ የማምረት ሂደቱ እጅግ ውድ በመሆኑ የአጠቃቀም ስርዓታችንን በየጊዜው በመፈተሽና ሙያዊ ኦዲት በማድረግ የማሻሻያ ስራ መስራትና የዘርፉን ውጤታማነት ማረጋገጥ ይጠበቅብናል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት
http://linktr.ee/fdremoi
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia

07 Feb, 08:24

900

ዘላቂ አካታች እና ተወዳዳሪ አምራች ኢንዱስትሪ ለመገንባት የክልል መንግስት የሚያደርገው ክትትል እና ድጋፍ ወሳኝ ነው (አቶ ዳዊት አለሙ)
=============================
ጥር 30/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአየር ንብረት ለውጥ ሴክተር ሪፎርም ፐርፎርማንስ ፕሮጀክት በአካባቢና በአየር ንብረት ለውጥ ስራ ላይ ለተወከሉ የክልልና ከተማ አስተዳደር የኢንዱስትሪ ቢሮ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በኢንዱስትሪ ፖሊሲ፣ በአከባቢ ጥበቃ ፓሊሲዎች፣ የአምራች ኢንዱስትሪዎች ውጤታማ የሃይል አጠቃቀም እንዲሁም ከአካባቢ እና ከአየር ብክለት የፀዳ የአመራረት ሂደት ተግባራዊ ለማድረግ የክልል መዋቅር ሚና ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ ነው።

የፕርጀክቱ ኃላፊ አቶ ዳዊት አለሙ እንደገለፁት ያለንን የተፈጥሮ ፀጋ በአግባቡ መጠቀም ዘላቂና አካታች አምራች ኢንዱስትሪ ለመገንባት ከተቀረጹ የኢንዱስትሪ ፖሊሲው ምሰሶዎች መካከል አንዱ ነው ብለዋል።

በቅርቡ መንግስት ያወጀው የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ የአምራች ኢንዱስትሪው ሃይልን በብቃት እንዲጠቀም እና ያላስፈላጊ የሃይል ብክነትን ለመቀነስ የሚያነቃቃ በመሆኑ ከዘርፉ ለመቀነስ የታሰበውን 40 በመቶ የሃይል ብክነትን ለማሳካት ክልሎች ድርሻቸውን መወጣት አለባቸው ብለዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት
http://linktr.ee/fdremoi
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia

31 Jan, 12:04

925

የአምራች ኢንዱስትሪው ለውጥ ሂደት
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት
http://linktr.ee/fdremoi
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia

31 Jan, 06:14

1,165

በኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ በርካታ ችግሮች ተፈተዋል (አቶ መላኩ አለበል)
============================
ጥር 23/2017 ዓ.ም (ኢሚ) በኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ ወደ ስራ ከተገባበት ጊዜ ጀምሮ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ላይ ተንሰራፍተውና ስር ሰደው የቆዩ በርካታ ችግሮች መፈታታቸውን የገለፁት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ዘርፉን ተወዳዳሪ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት እጅግ አበረታች ውጤት እያመጣ ይገኛል ብለዋል፡፡

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር ተያይዞ የአምራች ዘርፉ ተኪ ምርትን እና የኤክስፖርት ምርቶችን በተፈላጊው መጠን እና ጥራት እንዲያመርት በማስቻል በኢኮኖሚው ውስጥ ሊፈጠር የሚችለውን ጫና ከመቀነስ አልፎ ሀገራዊ ምርትን ከማሳደግ አኳያ ጉልህ ድርሻ እንዲኖረው በንቅናቄው በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቁመዋል፡፡

መንግስት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት ማሳያ ከሆኑት ጉዳዮች መካከል በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከተዘረጋው መዋቅራዊ አደረጃጀት ጎን ለጎን የተቋቋመው የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ብሄራዊ ካውንስል ሁኔታ ቀያሪ (game changer) ፋብሪካዎችን በመለየትና በጥናት ላይ ተመስርቶ ችግሮችን በቅርበት በመመልከትና አፋጣኝ መፍትሄ በሚያገኙበት አግባብ ላይ አቅጣጫ በመስጠት አበረታች ስራ ተከናውኗል ሲሉም ገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩል ያለንን የግብርናና የማዕድን እምቅ ሀብት በመጠቀም ኢንዱስትሪላይዜሽንን በገጠር አካባቢ በማስፋፋት ሰፊ የሆነ የስራ እድል ከመፍጠር ባሻገር ለትልልቅ ኢንዱስትሪዎች መነሻ የሚሆኑ ኢንዱስትሪዎችን ለመፍጠር ኢኮኖሚ መዋቅራዊ ስራዎች ተግባራዊ ማድረግ ተጀምሯል ያሉት ሚኒስትሩ ይህንንም ስራ በቀጣይ በተለዩ በሁሉም ወረዳዎች ተግባራዊ እንዲደረግ የተጠናከረ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ዕድገታችን የኢትዮጵያን ማህበራዊ፣ ፓለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ በአስገዳጅነት የማስቀየር አቅሙን ታሳቢ በማድረግ እንደ ተግዳሮት የሚታዩትን የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የፋይናንስ አቅርቦት፣ የየሴክተሮች ምርትና ምርታማነት ክፍተት፣ የመሰረተ ልማት አቅርቦት ክፍተቶች በተለይም ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስተሪዎች የመስሪያና መሸጫ ቦታ አቅርቦት ችግሮችን በመፍታት የኢትጵንያን የኢዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለመገባት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት
http://linktr.ee/fdremoi
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia

31 Jan, 05:59

874

በኮንትሮባንድ እና በህግ ሽፋን አማካኝነት ወደ ሃገር ውስጥ በሚገቡ የብረታ ብረት ምርቶችን ለመቆጣጠር እየተሰራ ነው (አቶ ሀሰን መሃመድ )
============================
ጥር 23/2017 ዓ.ም (ኢሚ) በኮንትሮባንድ እና ህግን ሽፋን ባደረገ መልኩ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች፤ የሃገራችን ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅማቸውን የሚቀንሱ እና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎችን የሚፈጥሩ በመሆናቸው በንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር የሚመራ ግብረ ሃይል በማቋቋም በክልል እና በከተማ ያለውን የኮንትሮባንድ ንግድ የመቆጣጠር ስራ እየተሰራ መሆኑን በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የመሠረተ ልማትና ግብዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሀሰን መሃመድ ገልፀዋል።

የብረታ ብረት ኢንዱስትሪውን ጨምሮ አጠቃላይ የሃገሪቷን ኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ የሆኑ ኢንዱስትሪዎችን ከኮንትሮባንድ እና ከህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ለመከላከል በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል ።

ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም ጉዳዩ የመንግስት ብቻ ባለመሆኑ ህብረተሰቡ ማንኛውንም ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ በማጋለጥ የዜግነት ሃላፊነት ያለበት በመሆኑ ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ጠንቅ የሆነውን የኮንትሮባንድና ህገ-ወጥ ንግድ ለመከላከል በሚሰራው ስራ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ማበርከት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት
http://linktr.ee/fdremoi
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia

30 Jan, 08:21

1,151

ከውጭ የሚገቡና በሀገር ውስጥ ተመርተው የሚወጡ ኬሚካሎችን በመመዝገብ ለ1,192 ፈቃድ መስጠት መቻሉን ተገለፀ፡፡
===============================
ጥር 22/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በሀገር ደረጃ የኬሚካል ክምችት አያያዝና አጠቃቀም ውጤታማ ለማድረግ ከውጭ የሚገቡና በሀገር ውስጥ ተመርተው የሚወጡ ኬሚካሎችን መመዝገብና ፈቃድ በመስጠት ላይ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ገልፀዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ለ1000 ምዝገባና ፈቃድ ለመስጠት ታቅዶ1,192 ምዝገባ በማከናወን የዕቅዱን 100% መፈፀም መቻሉን ተናግረዋል፡፡

እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ በድርጅቶች ወይም ፋብሪካዎች ውስጥ የሚገኙ ኬሚካሎችን ዓይነትና መጠን በመለየት ኬሚካል ለሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

በመሆኑም በስደስት ወራት የኬሚካል ፣ አያያዝና አጠቃቀምና አወጋገድ ስርአት ላይ አቅም ለማሳደግ 50 ታቅዶ 58 ድርጅቶች ላይ የኢንስፔክሽንና የማማከር ስራ በማከናወን የዕቅዱን 100% መፈፀም መቻሉን ገልፀዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት
http://linktr.ee/fdremoi
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia

30 Jan, 08:03

848

የፌዴራል መንግድ ስራዎች አፈጻጸም
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት
http://linktr.ee/fdremoi
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia

30 Jan, 07:47

850

የድንጋይ ከሰል ማምረቻ ፋብሪካ በተርጫ

#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት
http://linktr.ee/fdremoi
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር Ministry of Industry, Ethiopia

30 Jan, 06:45

1,011

65 አምራች ኢንዱስትሪዎች የኢነርጂ አጠቃቀማቸውን እንዲያሻሽሉ ተደርጓል፡፡
===============================
ጥር 22/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የኢነርጂ አጠቃቀማቸውን እንዲያሻሽሉ እና ስርዓት እንዲዘረጉ መደረጉን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ገልፀዋል፡፡

በ2017 በጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት 60 ታቅዶ 65 አምራች ኢንዱስትሪዎች ስርዓቱን በመዘርጋት ወደ ትግበራ እንዲገቡ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

አማራጭ እና ንፁህ አመራረት ሂደት በመከተል ስርኩላር ኢኮኖሚን ለማረጋገጥ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ረገድ 50 አምራች ኢንዱስትሪዎች ተግባራዊ ለማድረግ ታቅዶ 55 አምራች ኢንዱስትሪዎች ተፈፃሚ ለማድረግ የተቻለ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ታዳሽ ሀይል የተኩ ኢንዱስትሪዎች 2 ታቅዶ 7 የተከናወነ መሆኑን የገለፁት ሚኒስትሩ ደረጃውን የጠበቀ የፍሳሽ፣ የአየርና የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ ስርዓት እንዲዘረጉ አምራች ኢንዱስትሪዎች ድጋፍ ማድረግ ተችሏል፡፡

ይህም 150 ታቅዶ ከክልል ኢንዱስትሪ ቢሮ፣ ከተጠሪ ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን 175 አምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ ተፈፃሚ በማድረግ የዕቅዱን 100% ለመፈፀም መቻሉን አቶ መላኩ አለበል ገልፀዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት
http://linktr.ee/fdremoi