Merion School @merionsch Channel on Telegram

Merion School

@merionsch


Kg and primary

Merion School (English)

Welcome to Merion School, a Telegram channel dedicated to providing resources, tips, and support for kindergarten and primary school educators. Our channel, @merionsch, is the perfect place for teachers looking to enhance their teaching practices and engage with a community of like-minded professionals. Whether you're a seasoned educator or just starting out, Merion School offers a wealth of information to help you succeed in the classroom. From lesson plan ideas to classroom management strategies, our channel covers a wide range of topics to support you in your teaching journey. Join us at Merion School and connect with other educators who share your passion for creating a positive learning environment for students. Let's collaborate, inspire, and learn together at Merion School!

Merion School

06 Jan, 09:21


ሜሪኦን ት/ቤት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ የት/ቤታችን ማህበረሰብ በሙሉ መልካም የገና በዓል እንዲሆንላችሁ ከልብ ይመኛል!!

Merion School

03 Jan, 10:25


ውድ ወላጆች፡- ቅዳሜ ታህሳስ 26፣ 2017 ዓ.ም በት/ቤታችን ውስጥ አመታዊው የተማሪዎች ፌስቲቫል እንደሚካሄድ ይታወቃል፡፡

📍ተማሪዎች ወደ ሰርቪስ ውስጥ እና ወደ ት/ቤት ቅጥር ግቢ ሲገቡ ለፌስቲቫሉ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የመግቢያ ካርዱን ማሳየት ይጠበቅባቸዋል፡፡ (የመግቢያ ካርዶች ዛሬ አርብ ታህሳስ 25፣ 2017 ዓ.ም በኮሚኒኬሽን መፅሃፍ ውስጥ ተልከዋል፡፡)

📍ያልተመዘገቡ ተማሪዎች በፌስቲቫሉ እለት በመግቢያ በሮች ላይ መመዝገብ ይችላሉ፡፡

📍ሰርቪስ ተጠቃሚ ሁሉም ተማሪዎች በ2ኛው ዙር የሰርቪስ ሰዓት (ማለትም ከ1፡15 ሰዓት ጀምሮ) ወደ ት/ቤት የሚመጡ ይሆናል፡፡

📍ተማሪዎች የምሳ እቃ ወይም ቁርስ ይዘው አይመጡም፡፡ በት/ቤቱ የሚቀርብላቸው ስናክ /snack/ እና ውሃ ይኖራል፡፡ እንዲሁም በስጦታ መልክ የሚወሰዱ ቸኮሌቶች ይኖራሉ፡፡

📍ተማሪዎች በተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች እና ጨዋታዎች ላይ ስለሚሳተፉ የስፖርት ቱታ ዩኒፎርም ለብሰው የሚመጡ ይሆናል፡፡

📍ከአፀደ ሕፃናት እስከ 4ኛ ክፍል ድረስ የሚገኙ ተማሪዎች ስልክ ይዘው ወደ ት/ቤት እንዲመጡ አይፈቀድላቸውም፡፡ ከ5ኛ - 8ኛ ክፍል የሚገኙ ተማሪዎች ስልኮቻቸውን በራሳቸው ሃላፊነት በጥንቃቄ ስለመያዛቸው በወላጆቻቸው ከታመነበት ስልክ ይዘው መምጣት ይችላሉ፡፡

📍የፌስቲቫሉ መጠናቀቂያ ሰዓት ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ሲሆን ከ6፡10 ሰዓት ጀምሮ የሰርቪስ መውጫ ሰዓት ይሆናል፡፡
እናመሰግናለን!
የት/ቤቱ አስተዳደር።

Merion School

01 Jan, 03:03


ውድ ወላጆች:- ለአርብ፣ ታህሳስ 25፣ 2017 ዓ.ም ተይዞ የነበረው የተማሪዎች ፌስቲቫል በበርካታ ወላጆች ጥያቄ ምክንያት ወደ ቀጣዩ ቀን ቅዳሜ፣ ታህሳስ 26፣ 2017 ዓ.ም የተሸጋገረ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን።
                                                እናመሰግናለን!
                                       የት/ቤቱ አስተዳደር።

Merion School

27 Dec, 06:45


ውድ ወላጆች፡- ዕሁድ፣ ታህሳስ 20፣ 2017 ዓ.ም የመጀመሪያው ሲሶ አመት የወላጆች ጠቅላላ ስብሰባ CMC ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አቅራቢያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢኰኖሚስቶች ማህበር አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል። በመሆኑም በዕለቱ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ላይ በአዳራሹ እንድትገኙ ከወዲሁ በአክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ማስታወሻ:- ሰርቪስ መጠቀም የምትፈልጉ ወላጆች 1፡30 ሰዓት ላይ ከጂሰቨን አደባባይ፣ ከ13 መጨረሻ፣ ከአያት ጣፎ ኮንደሚኒየም መናፈሻ፣ ከአያት ጣፎ ኮንደሚኒየም ከመንገድ በላይ መስኪድ ፊት ለፊት፣ ከጣፎ ሚሽን ፖሊስ ጣቢያ እንዲሁም ከክብር ደመና ቤተክርስቲያን፣ ከ49 ኮንደሚኒየም እና ከአያት አደባባይ የሚነሱ የትምህርት ቤቱ ሰርቪስ መኪኖች የተመደቡ በመሆኑ መኪኖቹን ተጠቅማችሁ መምጣት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
እናመሰግናለን!
የት/ቤቱ አስተዳደር።

Merion School

26 Dec, 04:03


ውድ ወላጆች፡- ዕሁድ፣ ታህሳስ 20፣ 2017 ዓ.ም የመጀመሪያው ሲሶ አመት የወላጆች ጠቅላላ ስብሰባ CMC ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አቅራቢያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢኰኖሚስቶች ማህበር አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል። በመሆኑም በዕለቱ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ላይ በአዳራሹ እንድትገኙ ከወዲሁ በአክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ማስታወሻ:- ሰርቪስ መጠቀም የምትፈልጉ ወላጆች 1፡30 ሰዓት ላይ ከጂሰቨን አደባባይ፣ ከ13 መጨረሻ፣ ከአያት ጣፎ ኮንደሚኒየም መናፈሻ፣ ከአያት ጣፎ ኮንደሚኒየም ከመንገድ በላይ መስኪድ ፊት ለፊት፣ ከጣፎ ሚሽን ፖሊስ ጣቢያ እንዲሁም ከክብር ደመና ቤተክርስቲያን፣ ከ49 ኮንደሚኒየም እና ከአያት አደባባይ የሚነሱ የትምህርት ቤቱ ሰርቪስ መኪኖች የተመደቡ በመሆኑ መኪኖቹን ተጠቅማችሁ መምጣት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
እናመሰግናለን!
የት/ቤቱ አስተዳደር።

Merion School

24 Dec, 10:26


ውድ ወላጆች፡- ዕሁድ፣ ታህሳስ 20፣ 2017 ዓ.ም የመጀመሪያው ሲሶ አመት የወላጆች ጠቅላላ ስብሰባ CMC ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አቅራቢያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢኰኖሚስቶች ማህበር አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል። በመሆኑም በዕለቱ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ላይ በአዳራሹ እንድትገኙ ከወዲሁ በአክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ማስታወሻ:- ሰርቪስ መጠቀም የምትፈልጉ ወላጆች በትምህርት ቤቱ ሰርቪስ መኪኖች መምጣት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
እናመሰግናለን!
                                       የት/ቤቱ አስተዳደር።

Merion School

20 Dec, 04:07


ውድ ወላጆች ቅዳሜ፣ ታህሳስ 12፣ 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት ድረስ የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ1ኛው ሲሶ አመት የተማሪዎች የውጤት ካርድ ለወላጆች ይሰጣል። በዕለቱ በተማሪዎች ውጤት እና ስነ-ምግባር ዙሪያ  የወላጅ - መምህራን የተናጠል ግልፅ ውይይት (Open House Conference) ይካሄዳል። በዚሁ መሰረት የሁሉም የአፀደ ህፃናት ግቢዎች ወላጆች በጋራ ዘንድሮ በአዲስ መልክ በተከፈተው በቁጥር 2 አፀደ ህፃናት ግቢ የሚገኙ ሲሆን የ1ኛ ደረጃ ተማሪ ወላጆች በ1ኛ ደረጃ ግቢ በመገኘት የልጆቻችሁን የውጤት ካርድ እንድትወስዱ ከወዲሁ በአክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።   
ማስታወሻ፡-     
በ ''Open House'' ዝግጅት ምክንያት አርብ፣ ታህሳስ 11፣ 2017 ዓ.ም ትምህርት የሚሰጠው በግማሽ ቀን መርሃ - ግብር ይሆናል፡፡     
                                                እናመሰግናለን!
                                         የት/ቤቱ አስተዳደር

Merion School

19 Dec, 05:04


ውድ ወላጆች ቅዳሜ፣ ታህሳስ 12፣ 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት ድረስ የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ1ኛው ሲሶ አመት የተማሪዎች የውጤት ካርድ ለወላጆች ይሰጣል። በዕለቱ በተማሪዎች ውጤት እና ስነ-ምግባር ዙሪያ  የወላጅ - መምህራን የተናጠል ግልፅ ውይይት (Open House Conference) ይካሄዳል። በዚሁ መሰረት የሁሉም የአፀደ ህፃናት ግቢዎች ወላጆች በጋራ ዘንድሮ በአዲስ መልክ በተከፈተው በቁጥር 2 አፀደ ህፃናት ግቢ የሚገኙ ሲሆን የ1ኛ ደረጃ ተማሪ ወላጆች በ1ኛ ደረጃ ግቢ በመገኘት የልጆቻችሁን የውጤት ካርድ እንድትወስዱ ከወዲሁ በአክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።   
ማስታወሻ፡-     
በ ''Open House'' ዝግጅት ምክንያት አርብ፣ ታህሳስ 11፣ 2017 ዓ.ም ትምህርት የሚሰጠው በግማሽ ቀን መርሃ - ግብር ይሆናል፡፡     
                                                እናመሰግናለን!
                                         የት/ቤቱ አስተዳደር

Merion School

17 Dec, 08:29


ውድ ወላጆች፡- ሜሪኦን ት/ቤት በአመታዊው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት አመታዊ የተማሪዎች ፌስቲቫልን በደመቀ እና ባማረ ሁኔታ አርብ ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ለማካሄድ ዝግጅቱን አጠናቆ ይገኛል፡፡
በመርሃ - ግብሩ ከሚካተቱ ትምህርታዊ ፕሮግራሞች መካከል ጥቂቶቹ:-
1/ለሌሎች ሰዎች ጠቃሚ የሆነ የህይወት ተሞክሮአቸውን ለተማሪዎች የሚያካፍሉ እና በትምህርቱ አለም ውጤታማ የሆኑ ሰዎች ይጋበዛሉ፡፡
2/ የተለያዩ የሚዲያ ድርጅቶች ከአዝናኝ እና ትምህርት ከሚያስጨብጡ ገፀ-ባህሪያቶች /Characters/ ጋር ይቀርባሉ፡፡
3/ ባለልዩ ተሰጥኦ /Talented/ ተማሪዎች አስተማሪ ዝግጅቶቻቸውን ያቀርባሉ፡፡ ተማሪዎች እርስ በእርሳቸው የተለያዩ አዝናኝ እና ትምህርታዊ ውድድሮችን ያካሂዳሉ። አሸናፊዎች ይሸለማሉ።
4/ በመምህራን መካከል የተለያዩ አዝናኝ እና ትምህርታዊ ውድድሮች እና ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።
በዕለቱ ለተማሪዎች ቁርስ (Snack)፣ ውሃ እንዲሁም ወደ ቤት በስጦታ መልክ የሚወሰዱ ቼኮሌቶች በት/ቤቱ የሚዘጋጁ ይሆናል፡፡
ልጆቻችሁ በፌስቲቫሉ ላይ እንዲሳተፉ የምትፈልጉ ወላጆች ከረቡዕ ታህሳስ 9፣ 2017 ዓ.ም እስከ ሰኞ ታህሳስ 21፣ 2017 ዓ.ም ድረስ ባለፈው አመት በነበረው ክፍያ መሰረት 550 ብር በተማሪዎች በኩል በመላክ ወይም በአካል ቀርቦ በመክፈል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡ ተማሪዎች ፌስቲቫሉ ላይ የሚሳተፉት በፍላጎት ብቻ ይሆናል፡፡
ቦታ፡- በት/ቤቱ ቅጥር ግቢ ሲሆን ለሰርቪስ ተጠቃሚዎች የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጥ ሆኖ መርሃ ግብሩ በግማሽ ቀን ጊዜ ሰሌዳ እስከ 6:30 ሰዓት የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡
                                                እናመሰግናለን!
                                       የት/ቤቱ አስተዳደር።

Merion School

15 Dec, 17:28


ውድ ወላጆች በት/ቤታችን አመታዊ ካላንደር መሰረት የመጪው ጊዜ ዋና ዋና ክንውኖች ከዚህ በታች የተጠቀሱት ሲሆኑ በትኩረት በማንበብ እንዲገነዘቧቸው በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

📍ሐሙስ፣ ታህሳስ 3፣ 2017 ዓ.ም ሁሉም የማጠቃለያ ፈተና ወረቀቶች በግማሽ ቀን መርሃ-ግብር ለተማሪዎች ይመለሳሉ፡፡ (ወላጆች በተማሪዎች የፈተና ወረቀት ላይ የእርማት ስህተት (corrections) ካገኛችሁ እስከ አርብ፣ ታህሳስ 4፣ 2017 ዓ.ም 5:00 ሰዓት ድረስ ብቻ ፈተና ወረቀቱን ወደ ት/ቤት ይዞ በመምጣት ለመ/ራን ማሳየት የምትችሉ ይሆናል።)

📍አርብ፣ ታህሳስ 4፣ 2017 ዓ.ም እና ሰኞ፣ ታህሳስ 7፣ 2017 ዓ.ም  የመጀመሪያው ሲሶ አመት የተማሪዎች ውጤት ካርድ (Report Card) በመምህራን ይሰራል፡፡ (በእነዚህ ቀናት ተማሪዎች ወደ ት/ቤት አይመጡም፡፡)

📍ማክሰኞ፣ ታህሳስ 8፣ 2017 ዓ.ም የሁለተኛው ሲሶ አመት ትምህርት ይጀመራል፡፡

📍ቅዳሜ፣ ታህሳስ 12፣ 2017 ዓ.ም የመጀመሪያው ሲሶ አመት የተማሪዎች የውጤት ካርድ ለወላጆች የማሳወቅ ፕሮግራም (Open House Conference) በግማሽ ቀን መርሃ ግብር ይካሄዳል፡፡

📍እሁድ፣ ታህሳስ 20፣ 2017 ዓ.ም የመጀመሪያው ሲሶ አመት የወላጆች ጠቅላላ ስብሰባ CMC ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አቅራቢያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢኰኖሚስቶች ማህበር አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

📍ቅዳሜ፣ ጥር 3፣ 2017 ዓ.ም የት/ቤታችን አመታዊው የእንግሊዝኛ ቃላት ፊደላት ድርደራ ውድድር (Spelling Bee Competition) CMC ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አቅራቢያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢኰኖሚስቶች ማህበር አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።
                                                እናመሰግናለን!
                                       የት/ቤቱ አስተዳደር፡፡

Merion School

14 Dec, 09:16


Lineup Story Telling @ campus 2

Merion School

14 Dec, 09:15


Creativity Work @ campus 4

Merion School

14 Dec, 09:14


Video Class @ campus 3

Merion School

13 Dec, 13:48


Lineup Story Telling @ campus 4

Merion School

13 Dec, 13:44


Lineup Story Telling @ campus 3

Merion School

13 Dec, 13:41


Lineup Story Telling @ campus 2

Merion School

13 Dec, 06:11


ውድ ወላጆች የታህሳስ ወር የተጨማሪ ትምህርት (ጥናት) ክፍያ እና የሰርቪስ ክፍያ የሚከፈለው እስከ ታህሳስ 5፣ 2017 ዓ.ም ድረስ ብቻ መሆኑን በአክብሮት ለማስታወስ እንወዳለን፡፡
                                                እናመሰግናለን!
                                       የት/ቤቱ አስተዳደር፡፡

Merion School

11 Dec, 14:14


ውድ ወላጆች የታህሳስ ወር የተጨማሪ ትምህርት (ጥናት) ክፍያ እና የሰርቪስ ክፍያ የሚከፈለው ከህዳር 25 እስከ ታህሳስ 5፣ 2017 ዓ.ም ድረስ ብቻ መሆኑን በአክብሮት ለማስታወስ እንወዳለን፡፡
                                                እናመሰግናለን!
                                       የት/ቤቱ አስተዳደር፡፡