መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ 998 ተማሪዎችን አስመርቋል።
ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት ፕሮግራሞች ስልጠናቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ የ5ኛ ዙር ተመራቂዎች የምረቃ ስነ-ስርዓት ዛሬ አካሒዷል።
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ 223 በድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም ፤ 389 በመደበኛ፣ በተከታታይ እና በክረምት መርሐግብሮች በመጀመሪያ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎችን ዛሬ አስመርቋል።
ከተመራቂዎቹ ውስጥ 127 ተማሪዎች በህክምና ትምህርት የተመረቁ መሆናቸው ተገልጿል።
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 1,513 ተማሪዎችን ዛሬ አስመረቋል።
የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እንዲሁም በተከታታይ መርሐግብር የቅድመ-ምረቃ እና የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ባከናወነው 14ኛ ዙር የተማሪዎች የምረቃ ስነ-ስርዓት መመረቃቸው ተገልጿል።
ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የመጀመሪያ ባች ተማሪዎቹን ዛሬ አስመርቋል።
ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ያስመረቃቸው የጤና ተማሪዎች ባለፈው ሳምንት የተሰጠውን የመውጫ ፈተና ወስደው ሙሉ በሙሉ ያለፉ መሆናቸው ተገልጿል።
ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ 232 በሁለተኛ ዲግሪ እና 107 በመጀመሪያ ዲግሪ በጤና ሳይንስ መስክ ያሰለጠናቸውን 339 ተማሪዎች አስመርቋል።
ዩኒቨርሲቲው በተጨማሪም በ Higher Diploma Program ስልጠናቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ 28 መምህራን በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ መርሐ ግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 366 የሕክምና ተማሪዎችን አስመርቋል።
ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ 🥳
@medicinedaily