ፍቅረ ነዋይ
በአበው መካከል ሊኖር የሚገባውን ፍቅረ ቢጽ (የባልንጀራ መዋደድ) ኖሮ ከሆነ ያጠፋዋል !
ከሌለ ደግሞ እንዳይኖር ያደርገዋል፡፡
መቀናናትንና አንዱ ለአንዱ ክፉ መመኘትንም ያመጣል።
የሁለት አኃው (ወንድሞች) ታሪክ እንዴት ያሳዝናል 😢
እነዚህ አባቶች በበረሃ ተፋቅረው ተሳስበው ይኖሩ ነበር፡፡
አንዱ ወጥቶ እስከሚመለስ ድረስ «ወንድሜ ወዴት ሄደ?» እያለ ይጨነቃል፡፡ ያም እንደዚያው ነው፡፡
✅ ከዕለታት በአንዳቸው ቀን
ድስት ሙሉ ወርቅ ያገኛሉ::
አንዱ ታመመና «ወንድሜ መድኃኒት አጠጣኝ» አለው።
✅ በሆዱ ግን
«ወንድሜ ሞቶልኝ፤ ኮሶዬን ጠጥቼ፧ ጠላቴን (በሽታዬን) አውጥቼ ፧ ይህን ወርቅ ይዤ ፧ ከተማ ገብቼ ከብሬበት ኖሬ .... .!» እያለ ይመኝ ነበር፡፡
ያም እንዲሁ አስቦ መድኃኒቱን ደቁሶ መርዝ ጨምሮ በጠበጠው::
በሽተኛ ውም በበኩሉ ሰይፍ ሲስል ዋለ፡፡ «ደርሶልሃልና ና ጠጣ› አለው፡፡ «ከመሬት አኑርልኝ» አለው::
ጎንበስ ሲል አንገቱን በሰይፍ ቀላው::
ያም መድኃኒቱን ጠጥቶ ለብቻው ወደቀ ወርቁ ከመካከል ቀረ።
✅ ከዚህ ታሪክ
ለሚያልፍ ብዕለ ዓለም (የዚህ ዓለም ሀብት) የማያልፍ መንግሥተ ሰማያትን የምታሰጥ ፍቅርን መተው ምን ያህል እንደሚጎዳ መረዳት ይቻላል፡፡
በፍቅረ ነዋይ የተያዘ ሰው ፍቅረ ቢጽ (የባልንጀራ ፍቅር) የለውም::
✅ ቅዱስ ዮሐንስ በመልእክቱ
«ኢታፍቅርዎ ለዓለም ወኢዘሀሎ ውስተ ዓለም ወዘሰአፍቀሮ ለዓለም ኢሀሎ ፍቅረ እግዚአብሔር ላዕሌሁ / ዓለምን ወይም በዓለም ውስጥ ያሉትን አትውደዱ ማንም ዓለምን ቢወድ የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም»
✅ በማለት በፍቅረ ነዋይ የተያዘ ሰው
እግዚአብሔር ያዘዛት የባልንጀራ ፍቅር በእርሱ ውስጥ እንደማትኖር ገልጦአል፡፡ (፩ዮሐ **፲፮ ትር.)
በፍቅረ ነዋይ ሳይሆን
በፍቅረ እግዚአብሔር እንኖር ዘንድ ፈጣሪ አምላክ ይርዳን🙏