Ibn Awol @ibnawolllll Channel on Telegram

Ibn Awol

@ibnawolllll


الحق يقال ولو كان مرا

Ibn Awol (Arabic)

🌟 قناة Ibn Awol 🌟nn📚 تعتبر قناة Ibn Awol واحدة من أفضل القنوات على تطبيق تيليجرام التي تقدم محتوى ثقافي ومعرفي عالي الجودة. يُعتبر Ibn Awol وجهة مثالية لكل من يبحث عن المعرفة والإثراء الفكري لذا يمكنكم الاشتراك الآن للتمتع بمحتوى مميز.

🌍 من هو Ibn Awol؟nIbn Awol هو مشروع فريد تم إطلاقه بهدف نشر الثقافة والمعرفة بشكل مبتكر وشيق. يقوم فريق Ibn Awol بتقديم مقالات، كتب، فيديوهات، ونصوص ملهمة من جميع المجالات للارتقاء بالذهن والروح.

📖 ما هي محتويات القناة؟nقناة Ibn Awol تقدم محتوى متنوع يشمل مقالات عن الثقافة العامة، الفلسفة، التاريخ، الأدب والروايات، والعديد من المواضيع الشيقة التي تثري الذهن. بالإضافة إلى ذلك، يتم نشر كتب مختارة بعناية وفيديوهات تعليمية تضيف قيمة حقيقية للمشتركين.

💡 لماذا يجب الاشتراك في Ibn Awol؟nتعتبر Ibn Awol واجهة رائعة للاستفادة من محتوى ذو جودة عالية يعزز المعرفة ويثري الثقافة الشخصية. بفضل تنوع المواضيع والأساليب المقدمة، يمكن للمشتركين الاستمتاع بتجربة تعليمية ممتعة ومثيرة.

انضموا الآن إلى قناة Ibn Awol لتعزيز ثقافتكم وتحقيق الارتقاء الفكري والروحي. لا تفوتوا فرصة الاستمتاع بمحتوى مميز ومثير يناسب جميع الأذواق. الحق يقال ولو كان مرا! 📚✨

Ibn Awol

02 Jan, 04:25


ፂም መላጨት ሀራም ነው

ተኝቶም ቆሞም ተቀምጦም
ወንጀለኛ ነው ።

በሸይኻችን በሸይኽ አቡ ዘር ሓሰን (አቡ ጦልሓ) አላህ ይጠብቃቸው

https://t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha

https://t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha

Ibn Awol

25 Dec, 18:44


የሙነወር ልጅ ማምታቻ እስከ የት?!
—————
የሙነወር ልጅና የቡድኑ ዋና ዋና አባላት ከነበሩበት ጠንካራ የሱንና አቋምና በቢድዐህ ባለ ቤቶች የሰልላ ሰይፍ ሆነው ከማስጠንቀቅ ፈፅሞ ባልተጠበቀ መንገድ ቁልቁል ሲወርዱ (የተምይዕ ዋሻ ሲሆኑ) ከታላላቅ የሱንና መሻይኾችና ኡስታዞች ለሚደርስባቸው በማስረጃ የታገዘ ጠንካራ ምላሽ ተደናግረው ከትክክለኛ ማስረጃ የተራቆቱ በመሆናቸው መቋቋም ሲያቅታቸው ቲፎዞዎች እንዳይበተኑባቸው፣ የትቢትና በባጢል ላይ የጭፍን እልህ (ደራ) ባለ ቤት የሆነው የሙነወር ልጅ የሚደርስባቸውን ጠንካራ ምላሽ ይመክትልኛል ብሎ የያዘው መንገድ (ስልት) "በማስረጃ ማሳመን ካልቻልክ አደናግር" የሚለውን አባባል ነው።
ይህ የትም አያደርሳቹም!! ቲፎዞ እንዳይበተን ተጨንቆ ባለ በሌለ ሀይል ስራዬ ብሎ ለማደናገር መሯሯጡና አድፍጦ መጠበቁ የባጢልና የፖለቲካ ባለ ቤቶች መገለጫ ነው!!። ከእልህና ከትቢት ውጥረት ውጡና ትላንት የነበራችሁበት የሐቅ አቋም ላይ ሁኑ!! ለዱኒያቹም ለአኼራቹም የሚጠቅማቹ እሱ ነው።

🔸የሙነወር ልጅ ትላንት ከሶስት/ከአራት አመታት በፊት፣ የመርከዝ ኢብኑ መስዑድ (የነሲሃ) አመራሮች በድብቅ እየተሸማቀቁ ከአል ኢኽዋኑል ሙስሊሚን ጋር በኢፍጣር ሰኣት የተነሱትን ፎቶ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ለቆ "ነጭ ነጯን እንናገራለን" በማለት የጀመረውን ምላሽ የት አደረሰው? ወይስ የመርከዙ ሰዎች ከዛ በኋላ ደንግጠው ተውበት አድርገው ትተውት ወደ ሱናው ተመልሰው ነው?! በጭራሽ!!
የመርከዙ ሰዎችማ ከትላንቱ መደባበቅ ወጥተው ስለ ዲናቸው ጠንከር ያለ እውቀት ለሌላቸው ነጋዴዎች እንኳን ግልፅ በሚሆን መልኩ በአደባባይ ከአል ኢኽዋኑል ሙስሊሚን ጋር መደባለቃቸውን አውጀዋል። በኮንፈረንሶቻቸውና በተለያዩ ዝግጅቶቻቸው ከአል ኢኽኑል ሙስሊሚን ጋር መደመራቸውን ከቱባ ቱባ መሪዎች ከነ ጀይላን፣ ኢብራሂም ቱፋና ሙሀመድ ሃሚዲን… መሰሎች ጋር ሆነው አንድ ላይ መሆናቸውን በተለያዩ መድረኮች ሆነው ፎቶና ቪዲዮ በመልቀቅ ለህዝቡ በግልፅ አሳይተዋል። ከዚህም ባሻገር በየ ቦታው (በከተማ በገጠሩ) ከኢኽዋኖች ጋር ሆነው መጅሊስ ውስጥ ተሰግስገው የመንግስት የፀጥታ አካላትን በማሳሳት የሰለፊያ ደዕዋን ለማደናቀፍ እየታገሉ ነው። በነዚህ ሰዎች ላይ ብዕርህ ለምን ደለዶመ?!

🔸 የሙነወር ልጅ ሆይ! እስቲ ልጠይቅህ ለማደናገር መፍጨርጨርህን ትተህ በግልፅ ተናገር፣ ዛሬ ላይም እነዚህ የመርከዙ አመራሮች አንተ ዘንድ ሰለፊይ ናቸው?!
የጀርህና ተዕዲልን ነጥብ ጉዳይ አቆየውና ይህን ጥያቄ መልስ፣ ምክንያቱም አንተ ስለ ጀርህና ተዕዲል ነጥብ የእውቀቱም ሽታ የለህም!! ለዚያም ነው "ውሃ ሲወስድ ውሃ ይጨበጣል" እንደሚባለው፣ ጭልጥ ወዳለው የተምይዕ ዋሻ ውስጥ ስትገባ በዚህ ርእስ ላይ ይረዳኛል ያልከውን አሰስ'ገሰሱን ኮተቱን ሁሉ ምኑንም ከምኑም ሳትለይ ከተለያዩ ዌብሳይቶች እየለቃቀምክ የነበረው። ይህ አላዋጣ ሲልህ ነው
ሰለፊዮችን አድፍጠህ ጠብቀህ የተቆራረጡ የሰለፊዮችን ቃላቶች እየመረጥክ በቃላት ስንጣ የተጠመድከው።
- ያ ሁሉ በቢድዐህ ባለ ቤቶች ላይ የነበረህ ሀይል የት ገባ?! ተውበት አድርገው ሁላቸውም ሰለፊዮች ሆነው ነው ወይስ አንተ ወደ ባጢል ሰዎች ተውበት አድርገህ ነው በሱንና ሰዎች ላይ አንበሳ በቢድዐህ ሰዎች ላይ ሬሳ የሆንከው?!
ለቀድሞዎቹ ኢኽዋኖችና ለቅርብ ጊዜዎቹ የነሲሃ ቲቢ ባለቤት ኢኽዋኖች ሽንጥህን ገትረህ ትከላከላለህ፣ በቀድሞው አቋማቸው የፀኑ መፅሃፍህን መቅደም በማድረግ ሲያበረታቱህ የነበሩ ጠንካራ የሱንና መሻይኾችን ደግሞ የተለያየ ጥላሸት በመቀባትና ውሃ በማይቋጥሩ ነገሮች በመተቸት ሰዎች እንዲርቋቸው ለማድረግና ጭፍን ተከታይ ቲፎዞዎችህ እንዲቆዩልህ ትፍጨረጨራለህ!!። በዚህ ስልትህ ጭፍን ተከታዮችህን ከጥመት ቡድኖች ጋር እንዲግበሰበሱ አድርገሃል።
ይህ ነው አይን ያወጣ ያፈጠጠ ጥመትና የተምይዕ ዋሻ መሆን። ሑዘይፋ ኢብኑል የማን (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ:- “ጥመት ብሎ ማለት፣ ትክክለኛው ጥመት የምታወግዘው የነበረውን ነገር እውቅና መስጠትህ ነው። የምታውቀው የነበረን ሀቅ ደግሞ ማውገዝህ ነው። ወዮልህ በዲን ላይ መቀያየርን ተጠንቀቅ!፣ የአላህ ዲን አንድ ነው።” [አል-ኢባነቱል ኩብራ 571]
አላህ ከጭፍን ተከታይነትና በባጢል እልህ ውስጥ ከመግባት ጠብቆ እሱን እስክንገናኘው ድረስ በሐቅ ላይ ያፅናን!!
✍🏻ኢብን ሽፋ t.me/IbnShifa
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

Ibn Awol

25 Dec, 18:44


አክቲቪስቱ የሙነወር ልጅ ሰሞኑን ለምን ተንፈራገጠ?

ቡዙ ግዜ ካያቹህ የስሜት ተከታዮች መንጫጫት ሚጀምሩት ሰለፊዮች የሆነ አመርቂ የሆነ ስራ ሲሰሩ ነዉ።

የሰሞኑን መፍጨርጨር ምክኒያትም ለመፈለግ ስሞክር ከሰለፊዮች በኩል ምንም አዲስ መገር አላየሁም።አዲስ ነገር ከሌለ አክቲቪስታችን ለምን መፍጨርጨር አስፈለገዉ ብዬ አሰብኩ።በመጨረሻም ምክኒያት ብዬ ያገኘሁት ኣንድ ነገር ትዝ ኣለኝ።

አይታቹህ ከሆነ ሰሞኑን ኣንዲት አጠር ያለች ፁሁፍ በሚዲያዉ ስትሰራጭ ነበር።ያቺ ፁሁፍ ቆየት ያለች የኢብን ሙነወር ፁሁፍ ስትሆን በዉስጧም ኣንድ ሰዉ ኢብን ሙነወርን ስለ ኢልያስ አህመድ ሰላሳ ሁለት ምክሮች ችግር ኣለባቸዉ ይባላል ብሎ ማብራሪያ እንዲሰጠዉ ይጠይቀዋል፣አቶ ኢብን ሙነወርም ሰዉዬዉን መልስ ከፈለክ ሼኽ ሁሴን በኢልያስ ሰላሳ ሁለት ምክሮች ላይ የሰጡትን ረድ እንዲያነብ ያመላክተዋል።
እናም ያኔ ኢሄ ቀን ይመጣል ብሎ ያላሰበዉ የሙነወር ልጅ ያንን ፁሁፉን ዛሬ ሲያየዉ ሚይዘዉ ሚጨብጠዉን ነገር ሲያጣ ቀጥታ ወደ ነዉሩ ገባ።

ነገር ግን መንፈራገጥ አይገባዉም ነበር።መልሱ ከሁለቱ ኣንዱ ነዉ።ወይ ሼኽ ሁሴን የድሮ አቋማቸዉን ቀይረዋሉ ወይም ኢብን ሙነወር በኢልያስ ያለዉን አቋም ቀይሮዋል።

ሼኽ ሁሴን አቋማቸዉን እንዳልቀየሩ ጋሀድ የወጣ ሀቅ ነዉ፣ስለዚህ በኢልያስ ጉዳይ አቋምህን የቀየርከዉ ኣንተ ነህ።
ስለዚህ ኢሄ አቋምህ ሀቅ ነዉ ብለህ ካመንክ ባደባባይ ወጥተህ ትላንትና በኢልያስ ሰላሳ ሁለት ምክሮች የነበረኝ አቋም ኢሄ ነበር ዛሬ ግን ከዚህ አቋሜ ተመልሻለሁ ብለህ ባደባባይ ለተከታዮችህ ግልፅ አድርግ።
እንደ ፖለቲከኛ ኢሄኛዉን ነዉርህን ለመሸፈን ሰዎች ላይ አትቅጠፍ።


t.me/ibnawolllll
t.me/ibnawolllll

Ibn Awol

24 Dec, 17:53


👆👆👆አክቲቪስቱ ኢብን ሙነወር በሰሞኑ ፁሁፉ ኢቺን ፁሁፍ አስታወሰኝ👇👇👇

ድንበር አላፊዉና ነዉረኛዉ ኢብን ሙነወርና ተከታዮቹ

ኢሄን ያልኩት እኔ አይደለሁም እራሱ ኢብን ሙነወር የተናገረዉ ነዉ።
ስለ ሀጁሪ በፃፈዉ ፁሁፍ ላይ"ኣንድ ሰዉ ተዉበት ያረገበትን ነገር አንስቶ መዉቀስ በሱ ላይ ድንበር ማለፍና ነዉረኝነት ነዉ"ብሏል።
በእንደዚህ አይነት አስነዋሪ ስራዉ ሚታወቀዉ ደሞ እሱና ተከታዮቹ ናቸዉ።
ዬቱጋና በማን ላይ እንደዚህ አይነት ስራ ሰራ ካላቹሁኝ መልሱ በሼኽ አብድል ሃሚድ ላይ ነዉ።
ሼኽ አብድል ሃሚድ ዱሮ ራያ አባ ሜጫና ጥቂት ኢኽዋኖችን አወድሰዉ ነበር ነገር ግን ከቆይታ ቦሃላ ከዚህ አቋማቸዉ ተመልሰዉ ባደባባይ ተመልሻለሁ ማለታቸዉ የታወቀ ነዉ።
ኢሄንን እያወቁና እሳቸዉም ተመልሻለሁ ያሉበት ድምፅ እያለ ኢብን ሙነወርና ተከታዮቹ በዚህ ጉዳይ ሲወቅሷቸዉ ነበር፣አሁንም ተከታዮቹ በየ ቦታዉ እያራገቡት ነዉ።
ስለዚህ የተከበሩ አክቲቪት ኢብን ሙነወር እባካቹሁን ከዚህ ነውራቹሁ መመለሳቹሁን ብታሳወቁን?።
እንዲሁም በዚህ ስራ ላይ የተሰማሩ አስነዋሪ ተካታዮቻቹሁንም ከዚህ ድርጊታቸዉ እንዲታቀቡ ብትነግሩልን?።
እንዲሁም ግራ የተጋባዉ ጓደኛቹህ እያራገበ ያለዉን የሼኹን ቪዲዮ እነዲያቆም ብትነግሩልን?።ምክኒያቱም በፁሁፋቹህ ወረድ ብላቹህ በፊቂህ ጉዳይ ላይ ያለ አግባብ መጮህ እንደሌለብን ለመጦቀም ሞክራቹሃል።ስለዚህ የጮሀበትን ሪከርድ እንዲያጠፋ ብትነገሩልን?።

በተረፈ ስለ ሀጁሪይ የፃፈዉ ፁሁፍ ሙሉ በሙሉ ኢጅማል ነዉ።ኢሄ ደሞ አደገኛ የሆነ የሙብተዲዖች አካሄድ ነዉ።ኢብን ሙነወር ባአሁን ጊዜ በተፍሲል ሚናገረዉ ሰለፊዮችን በተመለከተ ብቻ ነዉ።ሌላዉ ፁሁፉ ባጠቃላይ ኢጅማል ነዉ።ኢሄንን ሚያረገዉ ባአንድ በኩል ሲቲይዙት በሌላ በኩል ለማምለጥ ነዉ



t.me/ibnawolllll
t.me/ibnawolllll

Ibn Awol

20 Dec, 04:09


ነሲሃ ቲቢ በገንዘብ እጥረት ተዘግቶ አይዘጋም! የሙስሊሙ ህብረተሰብ ኪስ ይበዘበዝበታል እንጂ!!
—————ክፍል አንድ
በ ኢብኑ መስዑድ መርከዝ ስር የሚተዳደረው የሙመይዓ - ኢኽዋኑ ነሲሃ ቲቢ ተዘጋ በሚል ሙሾ አውራጅና አስለቃሽ ጭፍን ተከታዮች በየ ማህበራዊ ሚዲያው በዝተው እየተመለከትኩ ነው። የኢኽዋንና የሙመይዓ የጥምር የጥመት ቡድኖች የሆነው ነሲሃ ቲቢ መስኮት አንዳንድ ምስጢሩ ያልገባቸው ሰዎች በገንዘብ እጥረት ተዘጋ ሲባሉ እውነት መስሏቸዋል። አብዘሃኞቹ ደግሞ አፈቀላጤ የሆኑ ጭፍን አራጋቢ ሙሪዶችን አዘጋጅተው እያስጮሁ ስለሆነ ተጨባጩ ቢነገራቸውም እውነት ብለው ለመቀበል ሊከብዳቸው ይችላል።

በቅድሚያ ነሲሃ ቲቢ እውነት በገንዘብ እጥረት ነው የተዘጋው ወይ? በሚለው ነጥብ ላይ የተወሰነ ልበል።
ነሲሃ ቲቢ በየትኛውም ስሌት በገንዘብ እጥረት ሊዘጋ አይችልም!!።

ምክንያት አንድ:- በተለያየ መንገድ ገንዘብ ለመሰብሰብ እንቅልፍ የማይተኙ በመርከዟ አመራርነት ደረጃ የተቀመጡ ሰዎች በርካታ ቁጥር ያላቸው ከፍተኛ ባለ ሀብቶችን እና በየ ደረጃው የሚገኙ ነጋዴዎችንና በደሞዝ የሚተዳደሩ ደሞዝተኞችን ሳይቀር በተለያየ መንገድ በማጥመድ ለቲቢዋ ድጋፍ እንዲያደርጉ ከስራቸው አድርገዋል። ከነዚያ ባለ ሀብቶች ከፊላቸው በየ ወሩ መዋጮ በማድረግ ከፊላቸው ደግሞ በየ አመቱ ከፍተኛ የሆነ (ተራ ብር እንዳይመስላችሁ እያንዳንዱ ባለ ሀብት በሚሊየን ቤት) መዋጮ እንዲያደርግ አድርገዋል። ልብ በሉ! ገንዘቡ ሳይሰበሰብ እንዳይቀር ሰዎቹ ፖለቲካዊ ጫወታው ላይም የተዋጣልን አካሄድና የብር መሰብስብ ብቃት ያለን ብልጦች ነን ብለው ስለ ሚያስቡ ለባለ ሀብቶች ባለ ሀብት አስተባባሪዎችን ነው ያሰማሩት። ለሌሎች ደግሞ በየ ደረጃቸው በዘመድ፣ በአከባቢ ልጅነት፣ በየ ደርስ ቦታው… ወዘተ በየ ደረጃቸው ተመድቦላቸዋል። የተሰማሩ ባለ ሀብቶች ደግሞ በመሪያቸው ፍቅር ያበዱ የእነሱ ቀንደኛ ተላላኪና እራሳቸው ከፍተኛ የሆነን ገንዘብ ነይተው ሌሎችን በፉክክር የሚያስነይቱ ናቸው። ከባለ ሀብቶቹ ስለ ሚንሃጅ ብዙም ግንዛቤ የሌላቸው ኢኽዋኑም ሙመይዓውም… ሌላውም ለመልካም ነገር (ለዲን) ነው በሚል ስም እንዳሻው የሚያልባቸው አሉ፣ ከጅህልናቸውም ጋር በተለያየ ፊክራ የተዘፈቁ አሉ፣ ከነዚህም ውስጥ በኢኽዋን ፊክራ የተዘፈቁ ሆነው የመርከዙ ሰዎች ከእኛው ጀመዓ (ከኢኽዋኑ) ጋር አንድ ሆነዋል መደገፍ አለብን በሚል ስሜት የሚደግፉ አሉ፣ ቀደም ሲልም መርከዟን ባለ በሌለ ሀይላቸው ለዚህ ደረጃ እንድትበቃ ያደረጉ ለደዕወቱ ሰለፊያ ጉጉት የነበራቸው አሁን የመርከዙ አመራሮች ሲቀልጡ ይዘዋቸው የቀለጡና የሟሙ ከፍተኛ አቅም ያላቸው ባለ ሀብቶች አሉ። አይደለም እንዲህ ተረባርበው ይቅርና ብቻቸውን የቲቢውን ወጪ መሸፈን የሚችሉ ጠንካራ አቅም ያላቸው ባለ ሀብቶች ባሉበት "በገንዘብ እጥረት ተዘጋ" ብለው አስለቃሾችን ቀጥረው ሙሪዶችን አደራጅተው ማስጮሃቸው አሁንም ምስጢራቸውን ያላወቀውን ሙስሊሙን ማህበረሰብ "ና! አይንህን ጨፍንና እናሙኝህ" እያሉት ነው። ልብ ያለው ልብ ይበል!!

ምክንያት ሁለት:- ይህ መርከዝ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ከላይ እንደጠቀስኩላችሁ ገንዘብ ለማግበስበስ ሌት ከቀን እንቅልፍ በሌላቸው አመራሮቹ አማካኝነት ከፍተኛ የሆነ የእራሱ የገቢ አቅም አለው። ይህ የገቢ አቅምም አዲስ አበባ ላይ ብዙዎች የሚያውቁት አል-ዓፊያ አክሲዮን ማህበር ነው። ማህበሩ በተለያዩ ቦታዎች ጠንከር ያለ ክፍያ እያስከፈ ከሌሎች የግል ትምህርት ቤቶች ጋር የሚወዳደር ከፍተኛ ገቢ ያላቸው ት/ቤቶች አሉት። የእራሱን ቦታ ገዝቶ የገነባውን ሆስፒታል ጨምሮ ሌሎችም አቅሞች ያሉት አክሲዮን ነው። ብዙ ሰዎች ይህን አክሲዮን ከመርከዙ ለይተው ሲመለከቱት ይስተዋላል። አይፈረድባቸውም 1ኛ, እነዚህ በመሪነት ደረጃ ያሉ አካላት ወሳኝ በሆኑ ቦታዎች ካልሆነ በስተቀር ስሙን ከመርከዟ ጋር አያይዘው ማንሳት አይፈልጉም። 2ኛ, ብዙ ሰዎች አመሰራረቱንና አሁን ከሚያስተዳድሩት ሰዎች ጋር ምን ያህል ትስስር እንዳለው በቅርበት የሚያውቁት ነገር ስለ ሌለ እራሱን የቻለ የንግድ ተቋም አድርገው ይመለከቱታል።
መጋቢት 29/2010 ላይ 18 አካባቢ በሚገኘው በመርከዙ ዋና ህንፃ "ከመጅሊሱ ተቀላቅለን ልንሰራ ስላሰብን እንዲሁም ቲቪ ለመክፈት ፕሮሰስ ጨርሰን እቃዎቹን እያስገባን ስለሆነ ልናወያያችሁ አስበን ነው" የሰበሰብናችሁ በማለት ከተለያዩ ቦታዎች በኡስታዝነት ደረጃ ተቀምጠው በስራቸው የሚገኙ ሰዎችንና የሱሩሪያ ፊክራ የነበራቸውን ሰዎች በሰበሰቡበት ወቅት ከመርከዙ በዋና አመራርነት ከሚጠቀሱ ሰዎች አዩብ ደርባቸው የሚባለው አል-ዓፊያ አክሲዮንን አስመልክቶ የመርከዙ ዋና ሀብትና የገቢ ምንጭ መሆኑን ተናግሯል። ይህን መናገሩን ያስታውስ አያስታውስ አላውቅም እንጂ በወቅቱ ወንድሜ ኡስታዝ ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ) ከሀዋሳ መጥቶ ተሳትፎ ነበር። ይህን እውነታ በተጨማሪ አክሲዮኑ ሲመሰረት የነበሩ አንዳንድ በገንዘባቸውም ጭምር ያገዙ ባለ ሀብቶች አጫውተውኛል። ታዲያ ይህ ሁሉ አቅምና የገቢ ምንጭ እያለ ቲቢዋን ዘግቶ የሙስሊሙን ማህበረሰብ ገንዘብ መበዝበዙ ለምን አስፈለገ? ህዝበ ሙስሊሙን መንሀጁንና ገንዘቡን አጭበርብረውት የት ሊያደርሳቸው ይሆን?!

በነገራችን ላይ በመጋቢት 29/2010 ስብሰባ ላይ የነበሩት አብዘሃኞቹ ተሰብሳቢዎች በቅርበት የማውቃቸው ሲያኮርፉና ሲያሻቸው ወደ ሱሩሪዮች ሲላቸው ወደ መርከዟ ልጥፍ የሚሉ የነበሩ የዛኔም ሚናቸውን ያልለዩ በሁለት ማሊያ እየተጫወቱ የነበሩ ሰዎች ነበር የሞሉት። እኔና ወንደሜን አቡ ሀመዊያን ጨምሮ አንድ ከሀረር የመጡ አሁን በትክክል ስማቸውን የማላስታውሳቸው ከመጅሊስ ስለ መስራት ሲነሳ በቁጣና በጩሀት አውግዘው ከተናገሩ በኋላ ጥለው የወጡ ሸይኽና ከባህር ዳር የመጡ በወቅቱ በእጅጉ አውግዘው በመናገር "ለምን እራሳችንን ችለን አንጓዝም?፣ ለሰለፊያ ደዕዋ እንዲህ ያለ መሰረት ካገኘን በኋላ (ህንፃውን ማለታቸው ነው) ለምን ትላንት ስናወግዛቸው ከነበሩት ከኢኽዋንና ከሱፊይ እንጨመራለን?!" በማለት ቁጣ አዘል ጥያቄ ያቀረቡ ሸይኽና በሰለፊያው ጀመዓ የሚታወቁ ጥቂት ሰዎች ብቻ ነው የነበሩት። ከስብሰባው በኋላ በተለምዶ (አባ ዱላ) በሚባለው በመርከዙ መኪና ወደ አየርጤና ስንሄድ ከመርከዟ አመራሮች አንዱ የሆነውን ኤልያስ አወልን በጠንካራ አቋማቸው የማውቃቸውን ሰዎች ስም ጠቅሼ ለምን አልመጡም?፣ ለምን አልተሳተፉም ወይስ አልጠራችኋቸውም ነው አልኩት? ምንም እንኳን ጥያቄ ምቾት ባይሰጠውም ሳይመልስልኝ ማለፍ አልቻለምና "እነ ባህሩ ተካን ማለትህ ነው አለኝ?" አዎ፣ ሌሎችም ብዬ የአሁኖቹን የአዲሶቹን ሙመይዓዎችንም ስም ጠቃቀስኩለት። "እነሱ ቢመጡም አንግባባም፣ ይልቁንም ሌላውንም ያስበረግጉብናል" አለኝ። እኔም:- ታዲያ በዚህ መልኩ መጓዝ ይሻላል? አልኩት። "አዎ በተለያየ ጊዜ እንወያይ ብለን ስንገናኝ ትርፉ ጭቅጭቅ ነው፣ ዝም ብለን ስራ ብንሰራ ይሻላል" አለኝ። እኔም ትዝብቴን ይዤ በጭንቅላቴ የሚመላለሱ ጥያቄዎችን ከዚህ በላይ መቀጠል ስላልፈለግኩ ዝምታዬን መርጬ አየርጤና ስንደርስ አውርዱኝ ብዬ ወደ ፉሪ ጉዟቸውን ቀጠሉ።
የተያያዘ ቀጣይ⤵️ፅሁፍ⤵️
https://t.me/IbnShifa/4467

Ibn Awol

20 Dec, 04:09


ወደ ርእሴ ልመልሳችሁ…
ምክንያት ሶስት:- ሌላኛው የገንዘብ መበዝበዢያ መንገድ ብዙዎቻችን ከሁለት አመት በፊት በአደባባይ ሲሰበስቡ የተመለከትነው "ዳሩ ተውሒድ ፕሮጀክት" በሚል ስም ግዙፍ ህንፃ ገንብቶ ለማከራየት ሲሰበሰብ የነበረው ከፍተኛ ገንዘብ ነው። ይህ ህንፃ ተገንብቶ ከተከራየ ገቢው በቁጥር 1 ለነሲሃ ቲቢ… ወዘተ ወጪ መሸፈኛ ብለው ነው ሲያስተዋውቁት የነበረው። ገንዘቡ 100 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልጋቸው አስተዋውቀው ስለነበር ብዙ ሰዎች ለዲን ነው በሚል ስም መኪናቸውንና መሬታቸውን ሁሉ ሳይቀር አስረክበዋቸው ካሰቡት በላይ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሰበሰቡና የህንፃው ማሳረፊያ ቦታ እንደገዙ በተጨባጭ አውቃለሁ፣ ይህ ብዙዎች የሚያውቁትም የቅርብ ጊዜ እውነታ ነው። ታዲያ በየትኛው ስሌት ገንዘብ አጥቶ ተዘጋ?!

ምክንያት አራት:- ይሀው ልክ በዚህ መልኩ "ነሲሃ ቲቢ ተዘጋ፣ ሊዘጋ ነው…" እያሉ ስንት ጊዜ ነው ብር ያግበሰበሱት? ስንት ጊዜ ነው በዲን ስም ለዲኑ ሲባል በየዋህነት ምስጢሩን ባላወቀው ነገር ያለውን ጠራርጎ የሚሰጠው ህዝበ ሙስሊም ከፍተኛ ገንዘብ ያዋጣው? በቲቢዋ ስም ብቻ ህዝቡን ኪሱን የበዘበዙት ያ ሁሉ ገንዘብ የት ገብቶ ነው አሁንም ተዘጋ ብለው ህዝቡን ሊበዘብዙት የተነሱት?? ልብ ያለው ልብ ይበል!
ክፍል 2 ⤵️
https://t.me/IbnShifa/2628
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

Ibn Awol

20 Dec, 04:09


🔹 ወንድሜ ኢብኑ ሽፋ ባነሳው ሐሳብ ላይ ትንሽ ለማከል የመርከዙ ሰዎች በኢብኑ መስዑድ ስም የሰበሰቡት ገንዘብ የመስራቾቹ የግል ሀብት እንጂ የሰለፍዩ ማህበረሰብ ንብረት አይደለም። ለዚህ ማረጋገጫው ለህብረተሰቡ ለመርከዙ ነው ተብለው የተገዙ ቦታዎችም እንዲሁም መኪኖችና የባንክ አካውንቶችንም ጨምሮ በመስራቾቹ ስም ነው የሚገኙት ። አል ዓፊያ አክሲዮን የያዘው ድርሻ የኢብኑ መስዑድ መርከዝ እንደሆነ ቅርበት ያላቸው ሁሉ ያውቃሉ። ዛሬ ግን ከእነዚህ መስራቾች የግል ሀብትነት ማውጣት የሚቻልበት የህግ አግባብ ያለ አይመስለኝም። ምክንያቱም መሪዎቹ በዚህ ጉዳይ የተካኑ ስለሆኑ። የዛሬ 10 አመት አካባቢ ሸይኽ ዐ/ ባሲጥ (ረሂመሁላህ) በነበሩ ጊዜ ዛሬ በጉያቸው ከከተቱዋቸው ዳዒዎቻቸው ውስጥ ሁለቱ ኢብኑ መስዑድ ላይ ባነሱት ቅሬታ ፉሪ ሐጂ ሪል እስቴት አካባቢ የተወሰኑ ወንድሞች በወንድም ዙበይር ቤት ተሰብስበው የእስትራክቸር ለውጥ መደረግ አለበት ብለው ኢልያስ አሕመድን መልእክት እንዲያደርስ ልከው ቀጠሮ ተይዞ ተገናኝተን ኢልያስ አወል ለተሰብሳቢው ኢብኑ መስዑድ ማለት እኮ ንብረት ነው ለማን እንድናስረክብ ነው የምትጠይቁት ነበር ያለው።
    ይህ ማለት የዛኔ ራሱ ኢብኑ መስዑድ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እንጂ የሰለፍዩ ማህበረሰብ አልነበረም። ዛሬማ በዐቂዳ እንጂ በገንዘብ ከማይገናኙዋቸው ሌሎች ድርጅቶች ጋር ተደምረዋል። ሁሉም የሰበሰበውን ይወስዳል ባይሆን አንዱ ሌላውን እንዳያሸንፍና እንዳይበልጥ ፍልሜያ ነው ያለው።
    የመርከዙ ሰዎች በተጠና መልኩ ከኢትዮዽያ 20 ባለሀብቶች ተርታ ለመመዝገብ በሚያደርጉት ሩጫ የተለያዩ ገንዘብ መሰብሰቢያዎችን በመሀል ከተማ በክ/ሀገርና በውጭ ሀገር ይነድፋሉ። ከእነዚህ ውስጥ ነሲሓ ቲቢ ፣ ነሲሓ በጎ አድራጎት ፣ አልሂዳያ እና የመሳሰሉት ይገኙበታል። የዛሬ አመት አካባቢ በጉመር ወረዳ አረቅጥ አካባቢ ባስገነቡት መርከዝ አማካይነት ገንዘብ ለማሰባሰብ ከላይ ወንድሜ ኢብኑ ሺፋ የጠራቸው አይነት የተለያዩ ባለብትና ነጋዴዎችን እንዲሁም ያብሬት ሸይኽና የቃጥባሬ ሸይኽን የሚያመልኩ ገበሬዎችና ሙሪዶች በተሰበሰቡበት አቶ አዩብ ደርባቸው ፣ ሰላሁዲን መለስና ዐ/ካፊ መሐመድ መድረክ መሪ የነበሩ ሲሆን አዩብ ደርባቸው በአብሬት ሸይኾች ስም መቶ ሺህ ብር በቃጥባሬ ሸይኾች ስም መቶ ሺህ ብር በማለት ቀብር አምላኪው ሱፍዩና አሕባሹም ጭምር እያስጮኸ ነበር ያስነየተው።
     እነዚህ አካላት አጋጣሚዎችን በመፍጠር ወላእና በራእን በማጥፋት ሁሉም የእነርሱን ኪስ እንዲያደልብ መስራታቸውን ከጊዜ ወደ ጊዜ ስልቱን እየቀያየረ የመጣ ጉዳይ ነውና የነሲሓ መዘጋት አጀንዳም የዚህ እስትራቴጂ አንዱ ክፍል ነው ለማለት እወዳለሁ።
https://t.me/bahruteka

Ibn Awol

19 Dec, 18:05


الصدقة من جنس القتال فالجبان يرجف والشجاع يثبت.

ابن تيمية | مجموع الفتاوى

Ibn Awol

17 Dec, 04:56


🚥 ጉድኮ ነው!
ዘንጋ ቸነም አሉ!!!
————————

🎙 ኸድር ተመዩዕ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ስለ ኤሊያስ አህመድ የተናገረው

🏝 አልሃምዱሊላህ ትናንት በሚመሰክሩት ሀቅ ላይ ዛሬ ላፀናን ሀያል ጌታ አልሃምዱሊላህ

https://t.me/AbuImranAselefy/9510

Ibn Awol

12 Dec, 15:46


🔹 ታላቅ የሙሃዶራ ዝግጅት
በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል


በአላህ ፈቃድ የፊታችን እሁድ ታህሳስ 6/2017 በአይነቱ ልዩ የሆነ የሙሃዶራ ዝግጅት ተሰናድቷል

🕰 ሰዓት:- ከጠዋቱ 3:00 እስከ 6:30 (በጊዜ ይገኙ)

ተጋባዥ እንግዶች:-
ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ)
ኡስታዝ ዐብዱልቃዲር ሐሰን (ሀፊዘሁላህ)
ኡስታዝ ሻኪር ሱልጧን (ሀፊዘሁላህ)
በተለያየ ርእስ ይቀርባል

ዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል

አድራሻ:- አዲስ አበባ ኮ/ቀ ክ/ከተማ አለምባንክ ከኦርዶፎ ህንፃ ፊት ለፊት ባለው ቂያስ ወደ ቤተል በሚወስደው ኮብልስቶን መንገድ ከድልዲዩ በስተ ቀኝ ባለው ቂያስ እንገኛለን።
ለተጨማሪ መረጃ:- +251920908031

የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://t.me/DarASSunnah1444
https://t.me/DarASSunnah1444

Ibn Awol

09 Dec, 05:34


🚫 ጥምር የመጅሊስ አመራሮች ምን እየሰሩ ነው ?

ከአሕባሽና ሱፍይ ጋር የተደመሩት ኢኽዋንና ሙመዪዓዎች የመጅሊስ ወንበር ላይ ሲፈናጠጡ ለእስልምናና ሙስሊሞች እንደሚሰሩ ሲደሰኩሩ ሰፊሁ ህብረተሰብ በሐሴት ተሞልቶ ነበር ። ደስታቸውን በተለያየ መንገድ ሲገልፁ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው ። በተለይ የኢኽዋን የእንጀራ ልጆች የሆኑት ነሲሐዎች ደስታቸውን የገለፁበት መንገድ የሚገርም ነበር ።
የተውሒድና ሱና የበላይነት የሚረጋገጥበት እድል እንተገኘ በማስመሰል በዚህ ያልተደሰተ ሙናፊቅ ነው እስከማለት የተደረሰበት ንቅናቄ እያደረጉም ነበር ። እንዳይፈረድባቸው የእንጀራ አባቶቻቸው በስሜት ስካር ውስጥ ሆነው " እንግዲህ እድሉ መጥቶልናል አሁን ያገኘነው እድል ሙሳም ቢመጡ ፣ ዒሳም ቢመጡ ፣ ነብዩና ሙሐመድም ቢመጡ ይህን እድል …… " አናገኘውም ነበር በሚል መሀላ ሲደረድሩ ከዛሬ ጀምሮ ከናንተ ከኮሚቴዬች አንስቶ ሱፍይ ፣ ሰለፍይ ፣ ኢኽዋንይ የሚለውን መስማት አንፈልግም እኛ የኢትዮዽያ ሙስሊሞች ነን ሲሉ መስማታቸው እነርሱንም አስክሯቸው ሊሆን ይችላል የሚለው ዑዝር ይከለክላል ።
የኢኽዋን መሪዮች የመጅሊሱን ወንበር ገና ከመፈናጠጣቸው የፈለገ መውሊድ ያውጣ የፈለገ ጫት ይቃም ብለው በአደባባይ በማወጅ አላማቸውና ፍላጎታቸው ምን እንደሆነ ሲገልፁ የስልጣን ፍርፋሬ የደረሳቸው ነሲሐዎች ምን እንደተሰማቸው ራሳቸው ይወቁ ። በአብዛኛው ምስኪን ተስፋ ላይ ግን ውሃ ቸለሱበት ። ራሱን እንዲጠይቅም አደረጉት ። ነገር ግን ማን ምን ሊያመጣ ዋናውን ስልጣን የተቆጣጠረው የኢኽዋን አንጃ ስልጣኑን ለማቆየት ኡማውን ቀብር አምላኪና ስሜቱን ተከታይ ማድረግ እንዳለበት ስለሚያውቅ ይህን ወደ መተግበር ገባ ።
አመራሮቹ የተውሒድ ዳዒ የሚባል ነገር መስማት አንፈልግም አሉ ። መጀመሪያውኑ እንደገለፁት አሕባሽ ፣ ሱፍይ ፣ ኢኽዋንይ የሚል ድምፅ ማጥፋት ዋና ተግባራቸው ሆነ ። የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው በሚል ስሜት ይህን እድል ተጠቅመው የነሲሓ ርዝራዦች ከመጅሊስ ባገኙት የስልጣን ፍርፋሬ ሰለፍዮችን ማፈናቀልና ማባረር ዋነኛው ስራቸው አድርገውታል ። በተለይ በስልጤ ዞን በስብጥር ከላይ እስከታች የተቀመጡ የመጅሊስ አመራሮች በጣም አሳፋሪ በሆነ መልኩ ኢኽዋኖችና ነሲሓዎች ከአሕባሽና ሱፍዮች ጋር በመሆን በተለያየ የመንግስት ተቋማት ላይ ያሉ አመራሮችን መጠቀሚያ በማድረግ የሕብረተሰቡን ህገ መንግስታዊ መብት በመርገጥና በመጣስ በሀይል መስጂዶችን መንጠቅና ኢማሞችንና ኡስታዞችን ማፈናቀልና ማባረር የሚቋወም ኮሚቴም ሆነ የሕብረተሰብ አካል ካለ ማሰር ግንባር ቀደም ተግባር እንዲሆን አድርገዋል ።
ስልጤ ዞን ላይ ያሉ የመንግስት ተቋም አመራሮች የተጣለባቸውን ህገመንግስታዊ አደራ ወደ ጎን በማለት ስልጣንን ለግል ስሜትና አመለካከት ማስፈፀሚያ እያደረጉ ይገኛሉ ። የሚገርመው የዚህ አይነት አፈናና የመብት ጥሰት በብልፅግና ዘመን ላይ መሆኑ ነው ።
በኢሀዲግ ዘመን የፀደቀው ህገ መንግስት አይደለም የህዝብ የግለሰብም የእምነት ነፃነት ይረጋገጣል የሚል ነው ። እንደሚታወቀው በኢሀዲግ ዘመነ መንግስት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ የማይፈልገውን አመለካከትና እምነት በመጅሊስ አማካይነት በመጫን ትላልቅ የመንግስት ተቋማቶች ያስፈፅሙ ነበር ። የህገ መንግስቱ የዜጎች መብት የሚያትቱ ህይወት አጥተው ወረቀት ላይ የነበሩ ቃላቶችን እንባ የሚጠርግም ሆነ የህዝቡን ጩኸት የሚሰማ አልነበረም ።
የዶ/ር አብር የብልፅግና ዘመን ሲቀየር ግን ሁሉም እነዚህ ህይወት አልባ ሆነው ወረቀት ላይ የቀሩ መብቶች ህይወት ዘርተው እውን እንደሚሆኑ ባለ ሙሉ ተስፋ ነበር ። ነገር ግን በየደረጃው ያሉ የኢሀዲግን ጃኬት አውልቀው የብልፅግና ጃኬት ያጠለቁ የህዝብን መብት ማክበር የሚለውን መርሕ ያልተቀበሉ አመራሮች አሁንም ተመሳሳይ ድራማ እየሰሩ ይገኛሉ ።
አብዛኛዎች ከላይ እስከታች በመንግሰት መዋቅር ያሉት አመራሮች ሀገሪቷንና ሕዝቦቿን እያስተዳደሩ ያሉት በህገ መንግስቱ ሳይሆን ከመጅሊስ አመራሮች በሚመጡ መመሪያዎችና ደብዳቤዎች ይመስላል ።
የትኛውም የመንግስት አመራር በየትኛውም ቢሮ ወንበር ላይ ሲቀመጥ የግል እምነቱን አመለካከቱንና ስሜቱን ከቢሮ በራፍ ውጪ አስቀምጦ ሁሉንም ህዝብ ህገ መንግስቱ ባስቀመጠው መመሪያ መሰረት መብቱን እንዲያገኝና ግዴታውን እንዲወጣ በማድረግ ማገልገል ይኖርበት ነበር ። ነገር ግን ይህ የሚታሰብ አይመስልም ። አብዛኛው በሀላፊነት ቦታ የተቀመጡ አመራሮች ማን ይጠይቀኛል የፈለኩትን መስራት መብቴ ነው የሚሉ ይመስላሉ ።
በተለይ የፀጥታ አካላት ከማንም በላይ የሀገርና ህዝብ አደራ የተሸከሙ ከመሆናቸው አንፃር የሀገርና የህዝብን ሰላም በማስጠበቅ ፍትህን ማስፈን አላማቸው አድርገው ሊንቀሳቀሱ ይገባል ። የሚያሳዝነው ግን በስልጤ ዞን ላይ በሚደርሰው የዜጎች መብት ረገጣ ድራማና ተውኔት ላይ አብዛኛዎች የድራማና ተውኔቱ ገፀ ባህሪ ጥቂቶች ደግሞ የድራማው ደራሲ ሆነው እያየን ነው ።
በስልጢ ዞን ቅበት አካባቢ እየሆነ ያለው ይህ ነው ። ሰላማዊ የሆኑ መስጂዶችና ጀማዓዎች ላይ ችግር አለ የሚል ድራማ እየሰሩ ለምን የሚልን ሰብስበው ማሰር ምን ይሉታል ። የህግ አካል ችግር አለ ከተባለ የመጀመሪያው እርምጃ በሰከነ ሁኔታ ነገሮቹን ማጣራትና መለየት ነበር የሚያስፈልገው ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አጣርተን ነው የምናስረው አስረን አናጣራም ሲሉ ያልተደመመ አልነበረም ። ይህ ማለት እሳቸው ስልጤ ዞን የሆነ ቀበሌ ላይ ወርደው ይፈፅሙታል ሳይሆን እሳቸው የሚመሩት ፓርቲ መርህ ነው ተብሎ ነው ስለሚታመን ነው ። በመሆኑም በየደረጃው ያሉ የፀጥታ ሀይሎች ይህን መርህ ተከትለው ይሰራሉ የሚል አንድምታ ስለተወሰደ ነው ቃሉን ሁሉም በአግራሞት የተቀበለው ።
ለመሆኑ የመጅሊስ አመራሮች እንዳሉትም የሀገር መሪዮች ናቸው ወይስ የአንድ የሌሎችን መብት መከልከል የማይችል ተቋም መሪዮች ? የአሁኑ ተግባራቸው ንግግራቸውን እውነት ነው እንዴ እንዲባል የሚያደርግ ነው ። ከክልል ጀምሮ እስከ ፌዴራል ድረስ አንዳንድ ተቋማትን ህገ መንግስቱን በተቃረነ መልኩ በደብዳቤ ሲያዙና ተፈፃሚ እንዲሆን ሲያስደርጉ እየታየ ስለሆነ አንድ ሊባሉ ይገባል ። በልካቸው እንዲቆሙ ካልተደረገ ሀገሪቷን እየመራ ያለውን ፓርቲ ገፅታ የሚያበላሽ ተግባር መፈፀማቸውን መቀጠላቸው አይቀርም ።
ለማንኛውም የሀገራችን ሙስሊሞች ባጠቃላይ ሰለፍዮች በተለይ የመጅሊስ አመራሮች ተውሒድና ሱናን የበላይ ያደርጋሉ ብላችሁ እንዳትጠብቁ ። ይልቁንም ትልቁ ጠላታቸው አድርገው የያዙት የተውሒድ ዳዕዋና የተውሒድ ዱዓቶችን ነው ።
➴➴ ቀጥሏል ↙️↙️↙️
https://t.me/bahruteka/5580

Ibn Awol

09 Dec, 05:34


🚫 ጥምር የመጅሊስ አመራሮች ምን እየሰሩ ነው?

➴➴➴ ከዚህ የቀጠለ ↙️
https://t.me/bahruteka/5579

በእነርሱ መዝሀብ ሁሉም የፈለገውን ማራመድ ይችላል ከተውሒድ ተጣሪዮች በስተቀር ። ማንም የፈለገውን መርዳት ይችላል የተውሒድ ተጣሪዮችን መርዳት ካልሆነ በስተቀር ። በስልጤ ዞን የዞኑ መጅሊስ ያወጣው መግለጫ ይህን እውነታ የሚያረጋግጥ ነው ። በየትኛውም መስጂድ ሰለፍዮች ዳዕዋ ማድረግ አይችሉም እገሌ እንዲህ ነው ብሎ መናገር አይፈቀድም ። የአሕባሽንም ስም ማንሳት አይቻልም ሁላችንም ሙስሊሞች ነን ። ማንም ሰው ደረሶችን እንዳይቀልብ ደረሳ ሲመጣ የማን ተማሪ ነህ መባል አለበት ብለው ይህንኑ በየመስጂዱ በኽጥባ እንዲነገር ተደርጓል ።

የአሕባሽ የመጅሊስ አመራሮች ይህን አላደረጉም ። የስልጤ ህዝብና የወሎ ህዝብ ከሚታወቅበት ትልቁ መለያው ደረሳ መቀለብ ነው ። ይህ ተግባር እነዚህን ህዝቦች ብቻ ሳይሆን ሀገርና ሁሉም ህዝብ ከአላህ በላእ እንዲጠበቅ ከሚያደርጉ ተግባሮች አንዱ ነው ። የጥምር መጅሊስ አመራሮች ግን ይህን ታላቅ ኢስላማዊ እሴት ለማጥፋት ተስማምተው ለህዝብ መመሪያ እንዲተላለፍ አድረገዋል ። ይህን ያደረጉት የተውሒድን አስተምሮ ለመግታት እንደመፍትሄ በማየት ነው ። ይህ የአላህን ብርሃን ለማጥፋት መፈለግ ነውና ተውበት አድርጋችሁ ተመለሱ ነው የምንለው ።
ለማንኛውም የመጅሊስ አመራሮች ዛሬ እገሌ አሕባሽ ነው እገሌ ሱፍይ ነው እገሌ ኢኽዋንይ ነው ማለትን ወንጀል አድርገዋል ። ነገ እገሌ ነስራንይ ነው እገሌ የሁድይ ነው ማለት ወንጀል ነው እንዳይሉ ነው የምንሰጋው ።
አላህ ሆይ ከመራኸን በኋላ ልባችንን አትቀይርብን ብለን መለመን ይኖርብናል ።

https://t.me/bahruteka

Ibn Awol

04 Dec, 17:59


ታላቅ የሙሀደራ ግብዣ በጀብዱ ቀበሌ
በጣም አጓጊ እና ልዩ የሆነ የዳዕዋ ዝግጅት

ተጋባዥ  ኡስታዞቻችን

1ኛ ውዱ ና ተናፋቂው  ኡስታዛችን አቡ አብዱረህማን አብዱልቃድር ሐሰን ከአዳማ

2ኛ ኡስታዝ አብዱልቃድር ከድድላ

3ኛ ኡስታዝ ከድር ከአዳማ

ሌሎችም ኡስታዞች ይኖራሉ ኢንሻአላህ

የፊታችን ጁምዐ በቀን 27/03/2017

ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ

ቦታ በቀቤና ወረዳ ጀብዱ ቀበሌ ስለዚህ በ4ቱም አቅጣጫ የምትገኙ ቀበሌዎች ተጋብዛቹሀል

ስለዚህ አይደለም መቅረት ማርፈድ ያስቆጫል
ከተማ ያላቹህ ወንድም እና እህቶች ቤተሰቦቻችንን በስልክ በመቀስቀስ እንረባረብ
ኢንሻአላህ ተውሂድ የበላይ የሚሆንበትና ሽርክና የሽርክ ባልተቤቶች የሚደመሰሱበት ቀን ይሆናል ኢንሻአሏህ በአሏህ ፍቃድ

ጁምዓ ለጀብዱ ልዩ ቀን ናት አቦ

Ibn Awol

03 Dec, 17:43


📌ስልጣንን መፈለግ
ኣንተ ሰለፊይ ሆይ እስቲ ትንሽ አዳምጠኝ(በልብህ)፤ለመሆኑ በሸሪያችን ስልጣን የመፈለግን ሁክም ታውቃታልህ?፤ሰለፊዮች እንዲበታተኑ ከሚያደርጉ ምክኒያቶች ትልቁ ስልጣን መፈለግ እንደሆነስ ታውቃልህ?።
ሼኽ ረቢእ ስልጣን መፈለግን አስመልክቶ መንሃጁል አንቢያ በሚለው ኪታባቸው ገፅ 97 ላይ ያሉትን እንመልከት እስቲ።
وينهى عن طلبها والحرص عليها،
ስልጣን መፈለግና በሷ ላይ መጓጓት ይከለከላል።
عن عبد الرحمان بن سمرة رضي الله عنه قال : قال لي رسول الله صلى الله عليه وسلم" يا عبد الرحمان! لا تسأل الإمارة،فإنك إن أعطيتها عن مسألة وكلت إليها، وإن أعطيتها عن غير مسألة أعنت عليها" أخرجه البخاري (٩٣)
አብድረህማን ኢብን ሰሙራ እንዲህ ኣለ፡የአላህ መልእክተኛ ለኔ እንዲህ ኣሉኝ፡ "አብድረህማን ሆይ! ስልጣንን ስጡኝ ብለህ አትጠይቅ፤ኣንተ ስልጣንን ስጡኝ ብለህ ከተሰጠህ አላህ ኣንተን አያግዝህም፤ኣንተ ሳትጠይቅ ስልጣን ከተሰጠህ አላህ ያግዝሃል።
📚ቡኻሪ 93
بل فوق كل هذه الأساليب يرسي قاعدة الإسلامية تحرم المناصب على من يتعشقها ويحرص عليها، عن أبي موسى الأشعري رضي الله عنه قال: دخلت على النبي صلى الله عليه وسلم أنا ورجلان من بني عمي، فقال أحد الرجلين: يا رسول الله! أمرنا على بعض ما ولاك الله تعالى، وقال الآخر مثل ذلك، فقال: "إنا لا نولي على هذا العمل أحدا سأله، ولا أحدا حرص عليه"
እንደሁም ከነዚህ ሁሉ ዘዴዎች በበለጠ ስልጣንን በሚወድና በሚጓጓላት ላይ ኢስላማዊ የሆነች መርሆን የቋቁሙ ነበር።
አቢ ሙሳ አል_አሽአሪይ እንዲህ ይላሉ፡እኔና ሁለት ካጎቴ ልጆች ሆነን በነቢዩ ላይ ገባን፤ከሁለቱ ኣንዱ እንዲህ ኣለ፡ኣንቱ ያአላህ መልእክተኛ ሆይ! አላህ በሾማቹህ ከፊል ስልጣን ላይ እኛንም ሹሙን፤ሌላኛውም ልክ እንደዚኛው ኣለ።ከዛ ነቢዩ እንዲህ ኣሉ፡እኛ በዚህ ስራ ላይ ማንንም ጠይቆን አንሾምም፤እንዲሁም ለሷ(ለስራዋ) የሚጓጓን አንሾምም።
وفي لفظ عند مسلم፡"ما تقول يا أبا موسى أو يا عبد الله بن قيس؟"
قال:فقلت:والذي بعثك بالحق ما أطلعاني على ما في أنفسهما، وما شعرت أنهما يطلبان العمل،قال: وكأني أنظر إلى سواكه تحت شفته وقد قلصت. فقال: "لن أو لا نستعمل على عملنا من أراده،ولكن اذهب أنت يا أبا موسى ". فبعثه إلى اليمن،ثم أتبعه معاذا.
📚 مسلم ٣٣
وفي النساءئي: "إنا لا نستعين في عملنا بمن سألنا"
📚نساءئي (٨/١٩٨)
ሙስሊም በዘገቡት ሌላ ዘገባ ደሞ ነቢዩ ኣንተ የሙሳ አባት ወይም ኣንተ አብደላህ ሆይ ምን ትላልህ ? ኣሉት።
እሱም እንዲህ ኣልኳቸው ኣለ"በዛ በሀቅ በላከክ ጌታ እምላለው በውስጣቸው ያለውን አላሳወቀኝም፤ስራ እንደሚፈልጉም አላወቅኩም፤ከዛም እንዲህ ኣለ፦ከንፈራቸው ከፍ ብላ ከስር ወደ መፋቂያቸው ምመለከት ይመስለኛል፤ከዛም እንዲህ ኣሉ:እኛ በስራችን ላይ የሚፈልገውን ሰው አንጠቀምም ነገር የሙሳ አባት ሆይ ኣንተ ሂድ"ኣሉት
ወደ የመን ላኩትና ከዛ ሙኣዝን አስከተሉለት።
📚ሙስሊም 33
በነሳኢ ዘገባ ደሞ እንዲህ ብለዋል"እኛ በስራችን ላይ ስጡኝ ብሎ በጠየቀን ሰው አንታገዝም"
📚ነሳኢ 7/197
ከዛ ትንሽ ዝቅ ብለው።
وعلى كل حال فالإمارة والقضاء من الأمور التي لا بد منها، ولا تقوم حياة المسلمين إلا بها، وبها تعصم الدماء والأموال والأعراض.
ለማንኛውም ስልጣንና ዳኝነት ቅሮት ከሌላቸው ጉዳይ ውስጥ ናቸው፤የሙስሊሞች ሂወት በሷ እንጂ አትቆምም፤የሙስሊሞች ደማቸው፣ገንዘባቸውና ክብራቸው ሚጠበቀው በሷ ነው።
ولاكن يجب أن نسلك في اختيار الأمراء والقضاة منهاج رسول الله صلى الله عليه وسلم فلا تعطى هذه المناصب لمن يسألها، أو يحرص عليها، أو يرشح نفسه لها عن طريق الإنتخابات مثلا، فإن هذا من الحرص عليها، وإنما يختار لها الأكفاء علما وزهدا فيها وتقوى.
ነገር ግን መሪዎችንና ዳኞችን ስንመርጥ የመልክተኛውን መንሃጅ ልንከተል ግድ ይለናል፤እነዚህ ስልጣኖቸ ለሚጠይቃቸው ሰው አይሰጡም፤ለሚጓጓላትም አትሰጥም፤በምርጫ እራሱን ምረጡኝ ብሎ ለሚቀሰቅስ ሰውም አትሰጥም፤ኢሄ በሷ ላይ ከመጓጓት ነው ሚቆጠረው፤ለሷ ሚመረጠው በእውቀትም አላህን በመፍራትም ብቁ የሆነ ሰው ነው።
ثم ينبغي أن نستفيد من هذا المنهج النبوي في التربية، فلا ينبغي أن ننشئ الشباب على حب القيادة والرئاسة والسيادة والإمارة، فلو نشأناهم على حب هذه الأشياء خالفنا هدي رسول الله صلى الله عليه وسلم وأوقعنا الشباب في المهالك، وأي فلاح ننتظره في الدنيا والآخرة إن خالفنا منهج رسول الله صلى الله عليه وسلم ؟
ተርቢያችን ላይ ከነቢዩ መንሃጅ ልንጠቀም ይገባል፤ወጣቶችን ስልጣንና መሪነትን እንዲወዱ አድርገን ልናሳድግ አይገባም፤ወጣቶችን እነዚህን ነገሮች እንዲወዱ አድርገን ከኮተኮትናቸው በእርግጥም የነቢዩን መንገድ ተፃረናል፤ወጣቶችንም ጥፋት ውስጥ ጥለናል፤የነቢዩን መንገድ ተፃረን በዱንያም ባኼራም ምን አይነት ፈላህ ነው ምንከጅለው?።📚ሼኽ ረቢእ መንሃጁል አንቢ ኪታባቸው ላይ
👆ሼኹ አላህ ኸይር ጀዛቸውንያ ይክፈላቸው፣ጉዳን በሚገባ ነው ያብራሩት።
እያንዳንዱን ፊርቃ ብትመለከተው በዚች ርእስ ላይ ወድቆ ታገኘዋልህ።
ኢኽዋን በዚህ ጉዳይ ወድቃልች፤ከተመሰረተች ጀምሮ ስልጣንን ፍጋ ነው ምትንከራተው፤ስልጣን ብያገኙም ፈልገውትና ጠይቀው ስለሆነ አላህ ያዋርዳቸዋል።
ሙመይኣም የነሱን መንገድ እከተላለው ብለው ነው ገደል የገቡት፤ሰፊዮችንም በየ ቦታው ሚያሰቃዩት ለዚችው ስልጣን ብለው ነው።
አዲሶቹም ሙመይኣዎችም ከሰለፊዮች የተለዩት እቺኑ ስልጣን ፈልገው ነው፤የነሱ አላማ መሻይኾቹ እነሱን እየተከተሉ እኛ ለነሱ እያጨበጨብን ልንኖር ነበር የፈለጉት፣ነገር ግን ሰለፊዮች እኛ ምንመራ በመሻይኾች ነው ሲሉ እነሱ መሻይኾችን መሳደብና ሰው ዘንዳ ታማኝነት እንዳይኖራቸው ማረግ ጀመሩ።
አሁንም በማሀከላችን ጥንቃቄ ልናረግ ይገባል፤ዛሬ ትንሽ ነው ያልነው ጉዳይ ነገ ገዝፎ እኛንኑ ያፈርሰናል።
በየ ቦታው ያላቹህ ሰለፊዮች በጀማዓቹህ ውስጥ ለማንኛውም ስራ ወይም ስልጣን እኔ እኔ ሚሉ ሰዎች ካሉ ተጠንቀቁ ፊትናን ሚቀሰቅሱት እንደዚህ አይነት ሰዎች ናቸው።
እኔ መሪ ካልሆንኩ፤እኔ ያልኩት ካልሆነ፤ እኔ ኢማም ካልሆንኩ፤እኔ ካላሰናዳው እያሉ ሚንቀዠቀዡ ሰዎች ካሉ እነሱን ከቦታው ዞር አድርጎ እቺን ስልጣን ማይፈልጉ ሰዎችን መተካት ነው።ልክ ነቢዩ እናዛን ሰዎች ከልክለው አቡ ሙሳ አለ_አሽአሪን እንደላኩት።
በየ ቻናሉ እኔ እንዲህ ካልሆንኩ፤እኔ ካልተናገርኩ ብለው ሚበጠብጡ ከሴትም ከወንድም ካሉ ኢሄንኑ መርሆ ልንጠቀም ይገባል።
ibn awol

t.me/ibnawolllll
t.me/ibnawolllll

Ibn Awol

28 Nov, 05:21


🟢ዘመናዊ ኸዋሪጆቾ

የሆነ የሙስሊም ሀገር ወይም መሪ ጥፋት ሲታይበት ወይም ተፈላፍሎ ጥፋት በማውጣት ማቀነባበር ፣ መንጫጨትና ዜና መስራቱ ረብሻ የሚያስነሳ የኸዋሪጆችና የኢስላም ጠላቶች አካሄድ ነው:: ህዝብ የማሳመፅ ልዩ ሴራም ነው:: ይህ ደግሞ በሙስሊሞች ላይ ከጭፈራ ፣ ከአስካሪ መጠጥ ፣ ከዝሙት ወዘተ የከፋ መዘዝ እና ውድቀት ያመጣል::

ኢስላማዊ መፍትሄ
በእንዲህ አይነት ሀገርም ሆነ መሪ ላይ ጥፋት ሲታይ ሙስሊም መሪዎችን በግል መምከርና ማስመከር ነው::ዱዓም ማድረግ :: አጥፊዎችንም በሸሪኣው ህግ መቅጣት::

እወቅ: ነቢያቶችም ሆኑ ምርጥ ተከታዮቻቸው በሚመሩት ማህበረሰብ ውስጥ ወንጀሎች ይሰሩ ነበር::

👌ችግሩ ሸሪኣዊ ከሆነ መፍትሄውም ሸሪኣዊ ይሁን:: ጫጫታና ግርግር በራሱ የከፋ ችግር ነው::

https://t.me/Abuhemewiya

Ibn Awol

23 Nov, 14:53


ኣንተ ትጎዳልህ እንጂ ሰለፊያ አትጎዳም

ማንም ሁን፣ኬትም ምጣ ሰለፊያን ለቀህ ስትወጣ ምትጎዳዉ ኣንተ እንጂ ሰለፊያ አይደለችም።

ከሰለፊያ ብዙዎችና ትላልቅ ሚባሉ ሰዎችም ወጥተዋል፣ሰለፊያ ትቀጥላልች እነሱ ግን ተዋርደዋል።
ዛሬም በየ ቦታዉ ምታኮርፍና ምትበጠብጥ ሰዉ ካለህ የነዚህ ሰዎች እጣ ፋንታ እንጂ ሌላ ነገር አትጠብቅ።
ሰለፊያ ሚስትህ አይደለችም እኔ እንደፈለኩ ካላረኳት ምትላት።ሰለፊያ ከአደም ጀምሮ እስከ ቂያማ ድረስ የምትቆይ የአላህ ቀጥተኛዉ መንገድ ነች።በዚህ ማሀል ግን ተራራ ሚያክሉ ኡለሞች መስዋት ሆነዉላታል ይሆኑላታልም።ለዚህ አላህም ቃል ገብቶዋል።
በዚህ መንገድ ፀንተህ ስትሞት አላህ የገባልህን ቃል ይሞላልሃል።ኢሄንን እምቢ ብለህ ግን ዳር ዳር ስትል ዉርደትን ትከናነባልህ።

ዛሬ ላይ ሰለፊዮች ደዕዋቸዉን እንዳያስፋፉ ጠንቅ የሆነባቸዉ ደዕዋዉ ላይ ዘለዉ ሚገቡ ሰዎች ናቸዉ።ኬት መጣ ሳይባል ዘሎ ይገባል ይጮሃል፣ይፅፋል፣ያንንም ኢሄንም ይነካካና ከሁለት ወር ቦሃላ ፊትና ሲያራግብ ታየዋልህ።
ኢዚህ ጋር የሰዉዬዉ ችግር ብቻ ሳይሆን የኛም ችግር ኣለ።ሰዎችበወኔ ስለጮሁ ብቻ እላይ እንሰቅላቸዋልን፣ንግግራቸዉን እናራግብላቸዋልን።ልክ ፊትና ሲፈጥሩ ለነሱ ወግነን ሀቀኛ ሰዎች ላይ እንዘምታለን።ነገር ግን እንደዚህ አይነት ሰዎች ወደ ደዕዋዉ ዘለዉ ሲገቡ ዘለዉ ሊወጡ ይችላሉ ብለን ብንጠነቀቅ ብዙ ኺላፎች ይቀንሱ ነበር።
ነገር ግን እንደዚህ አይነት እርምጃዎችን ማንወዝደዉ አብዛኛዎቻችን ጋር እዉቀት ስለሌለ ወይም እዉቀትን የመማር ዓላማ ስለሌለ ነዉ።እዉቀት የሌላቸዉ ወይም እዉቀትን መማር ማይፈልጉ ሰዎች የደዕዋ ወኔ ሊኖራቸዉ ይችላል፣ኢሄንን ወኔያቸዉን በደዕዋ ሊያረጉት እዉቀት አይኖራቸዉም ስለዚህ ያላቸዉ አማራጭ ኢሄንን ወኔያቸዉን በሌሎች ላይ ይጭኑታል።ልክ ኢሄ ወኔያቸዉን የጫኑበት ሰዉ የሆነ ችግር ሲገኝበት ያንን ችግር በእዉቀት ከመመርመር ይልቅ ለዛ ሰዉ ይሟገታሉ።የዛኔ ሰዉዬዉ የፈለገዉን ስልጣን ይይዛል እነሱ ተስፋ ቆርጠዉ ከደዕዋዉ ሙሉ በሙሉ ወጥተዉ ነጋዴ ይሆናሉ።

ስለዚህ መፍትሄዉ ሰዎች ላይ መንጠልጠልን ትተን በአቅማችን ልክ እዉቀትን ቀስመን ደዕዋዉ ላይ የራሳችንን አሻራ ማኖር ነዉ።የዚህን ግዜ ማንም ይምጣ ማንም ይዉጣ ኣንተ ፈትሸህ ማባረር ነዉ።

ኤገሌ መጣ፣ኤገሌ ሄደ፣አገሌ አኮረፈ ለራሱ ነዉ።መልካም ከሰራ ለራሱ ነዉ መጥፎም ቢሰራ ለራሱ ነዉ።ኣንተ ማረግ ያለብህ አላህ ባሰመረልህ ቀጥተኛ መንገድ እሱን ተከትለህ መታጠፍ ሳይሆን ቀጥ ብለህ መጓዝ ነዉ ያለብህ።

እንደዚህ በየ ጊዜዉ ለመበጥበጥ ምትሞክሩ ሰዎችም ካለፉት አምሳያዎቻቹሁ ተማሩ፤በገዛ እጃቹህ አላህ እንዲያዋርዳቹሁ አትፈልጉ።
ምክሩ ለሁላችንም ነዉ አላህ ከሚጠቀሙት ያርገን።


t.me/ibnawolllll
t.me/ibnawolllll

Ibn Awol

18 Nov, 17:22


👆👆👆👆ኢቺን የኡስታዝ ባህሩ ተካን ሙሃደራ በደንብ አዳምጧት።

ሴጣንና አጋሮቹ ደዕወቱ ሰለፊያን ለመበተን ምን ያህል ርቀት እንደሚጓዙ በደንብ ታያላቹህ።

ለዚህ መፍትሄዉ ደሞ ኢኽላስ፣ሹራ፣ሰብር በደንብ ያስፈልገዋል።
ከሰዎች ጋር ስትሰራ በቡዙ ሀሳብ ጊዜ ላትግባባ ትችላልህ።ለዚህ ትልቁ መፍትሄ በሹራ ተቀምጦ መነጋገር ነዉ።ስንነጋገር አሸናፊና ተሸናፊ እንዲኖር ከሆነ መቼም ስምምነት አይኖርም።

ቡዙ ግዜ ስምምነት እንዳይኖር ሚያረጉትም ሰዎች ለደዕዋዉ ጥቅም ሳይሆን ለነፍሲያቸዉ መበቀል ሚፈልጉ ወይም አሸናፊና ተሸናፊ እንዲኖር ሚፈልጉ ሰዎች ናቸዉ።

ምትሰራዉ ለአላህ ከሆነ አሸናፊ መሆን ያለብህ አላህ ዘንድ እንጂ ሰዎች ዘንድ መሆን ዬለበትም።ሀቅ ያለዉ ኣንተ ጋር እንኳን ቢሆን እራስህን ለደዕዋዉ ጥቅም ብለህ ተሸናፊ ማድረግ ነዉ ያለብህ።
ለአላህ ብለህ ሰዎች ዘንድ ዝቅ ስትል አላህ ዘንድ ከፍ ትላልህ።በአልሸነፍ ባይነት ድርቅ ብለህ ስሜትህን ምትከተል ከሆነ አላህ ያዋርድሃል።ቡዙ እንደዚህ አይነት ሰዎችን አላህ ሲያዋርድ አይተናል።

እዩን እዩን፣እኛን ብቻ ስሙን ብለዉ መጨረሻቸዉ ዉርደት ሆኖዋል።
አሁን ላይ ትልቁ ችግር የሆነብን የሰዎችን ወሬ ሳያጣሩ መቀበል፣ነገሩን ሳያጣሩ አቋም መያዝ፣የግል ጉዳይን ከመንሃጅ ጋር አያይዞ መበቀል፣መስለሃና መፍሰዳን ሳያገናዝቡ መጓዝ፣እኔ አዋቂ ነኝ እኔ አዋቂ ነኝ ብሎ የሌሎችን ሀሳብ አለመቀበል።

እንደ አጠቃላይ እንደዚህ አይነት ሰዎች ካሉ በተሻሉ ሰዎች እንዲመከሩ ማድረግ ይገባል።


t.me/ibnawolllll
t.me/ibnawolllll

Ibn Awol

18 Nov, 03:52


አዲስ ሙሓዳራ

ርዕስ ("የሱረቱል ዓስር " መልዕክት)

በውስጡ ብዙ ምክሮችን የያዘ በጣም ጠቃሚና መሳጭ ሙሓደራ

🎙በኡስታዝ ባህሩ ተካ (ሀፊዙሁሏህ)

🕌 በአዳማ በኢብኑ ተይሚያ መስጂድ የተደረገ ሙሓደራ

📅 በቀን 08/03/2017

https://t.me/abuabdurahmen

Ibn Awol

17 Nov, 11:07


የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة

Ibn Awol

17 Nov, 09:26


Live stream finished (51 minutes)

Ibn Awol

17 Nov, 09:26


የቀረዉን በኡስታዝ በራሱ ቻናል አዳምጡ ዐፍወን ራቅ ብያለሁ

Ibn Awol

17 Nov, 09:25


ፕሮግራሙ በዚህአብቅቶዋል

Ibn Awol

17 Nov, 08:36


ኡስታዝ በህሩ ጀምሮዋል

Ibn Awol

17 Nov, 08:35


Live stream started

Ibn Awol

17 Nov, 07:36


ኡስታዝ አቡ ሀመዊህ ጀምሮዋል

Ibn Awol

11 Nov, 08:22


ታላቅ_የሙሃደራ_ግብዣ በአዳማ ከተማ
==========================

በጣም አጓጊ እና ተናፋቂው የሰለፊዮች የደዕዋ ድግስ በጣም ተናፋቂ በሆኑ ኡስታዞች ለየት ባለ እና በማረ መልኩ ተደግሶ ይጠብቀናል


🪑ተጋባዥ እንግዶች

1ኛ  ተወዳጁ ኡስታዝ ባሕሩ ተካ ((ሀፊዘሁሏህ)

2 ተወዳጁ ኡስታዝ አቡ ሀመዊየህ ሸምሱ ጉልታ ( ሀፊዘሁሏህ)

3ኛ አቡ አብዲረህማን አብዱልቃዲር ( ሀፊዘሁሏህ)

ሌሎችም ተጋባዥ እንግዶች ይጠበቃሉ


    📅  የፊታችን እሁድ 08/03/2017

🕌ቦታ አዳማ 01 ቀበሌ በኢብኑ ተይሚያ መስጂድ

ሰዓት ከ 🕰2:30 ጀምሮ እስከ ዙህር

https://t.me/abuabdurahmen

Ibn Awol

10 Nov, 04:10


ሰሞኑን የተቋረጠዉ ደርሳችን ሰኞ በሳዐቱ ይጀምራል

Ibn Awol

07 Nov, 03:58


  👉 በዲን ጉዳይ ዑለሞችን ማስቀደም

" عمر بن يحيى عن أبيه قال : كنا نجلس على باب عبد الله بن مسعود قبل صلاة الغداة، فإذا خرج مشينا معه إلى المسجد، فجاءنا أبو موسى الأشعري فقال: أخرج إليكم أبو عبد الرحمن بعد؟ قلنا: لا، فجلس معنا حتى خرج، فلما خرج قمنا إليه جميعاً فقال له أبو موسى: يا أبا عبد الرحمن؛ إني رأيت في المسجد آنفاً أمراً أنكرته ولم أر والحمد لله إلا خيراً، قال: فما هو؟ فقال: إن عشت فستراه، قال: رأيت في المسجد قوماً حلقاً جلوساً ينتظرون الصلاة في كل حلقة رجل وفي أيديهم حصا فيقول: كبروا مائة فيكبرون مائة، فيقول: هللوا مائة، فيهللون مائة، ويقول: سبحوا مائة، فيسبحون مائة، قال: فماذا قلت لهم؟ قال: ما قلت لهم شيئاً انتظار رأيك أو انتظار أمرك، قال: أفلا أمرتهم أن يعدوا سيئاتهم وضمنت لهم أن لا يضيع من حسناتهم، ثم مضى ومضينا معه حتى أتى حلقة من تلك الحلق فوقف عليهم فقال: ما هذا الذي أراكم تصنعون، قالوا: يا أبا عبد الرحمن، حصى نعد به التكبير والتهليل والتسبيح، قال: فعدوا سيئاتكم، فأنا ضامن أن لا يضيع من حسناتكم شيء، ويحكم يا أمة محمد ما أسرع هلكتكم! هؤلاء صحابة نبيكم صلى الله عليه وسلم متوافرون، وهذه ثيابه لم تبل، وآنيته لم تكسر، والذي نفسي بيده إنكم لعلى ملة هي أهدى من ملة محمد. أو مفتتحوا باب ضلالة؟! قالوا: والله يا أبا عبد الرحمن ما أردنا إلا الخير، قال: وكم من مريد للخير لن يصيبه. إن رسول الله صلى الله عليه وسلم حدثنا أن قوما يقرؤون القرآن لا يجاوز تراقيهم. وأيم الله ما أدري لعل أكثرهم منكم، ثم تولى عنهم، فقال عمرو بن سلمة: رأينا عامة أولئك الحلق يطاعنونا يوم النهروان مع الخوراج "

وقد صحح هذا الأثر بهذا الإسناد الشيخ الألباني رحمه الله في "الصحيحة" (2005) .

🔹 በዚህ አሰር ላይ ዐብዱላሂ ኢብኑ መስዑድ ዘንድ ይማሩ ከነበሩ ታቢዒኖች በተጨማሪ ሶሓቦችም ይገኙ ነበር ። ከእነዚህ ሶሓቦች ውስጥ የአቡ ሙሰል አሽዓሪይ – ረዲየላሁ ዐንሁ – ገጠመኝን ነው ከዚህ አሰር ከምናገኘው ቁም ነገር ውስጥ ማስታወስ የምፈልገው ።
የዐብዱላሂ ኢብኑ መስዑድ ተማሪዎች ከቤቱ እስኪወጣ ጠብቀውት አብረው ወደ መስጂድ ይሄዱ ነበር ። አንድ ቀን ተማሪዮቹ ቁጭ ብለው እየጠበቁ ሳሉ አቡ ሙሰል አሽዐሪይ ይመጣል ። አቡ ዐብዱራሕማን አልወጣም ወይ ብሎ ይጠይቅና አልወጣም ሲባል ቁጭ ብሎ መጠበቅ ይጀምራል ። ጠብቆ ሲወጣ ሁሉም ተነስተው ወደ መስጂድ መሄድ ይጀምራሉ ። እየሄዱ እያለ አቡሰል አሽዐሪይ ለዐብዱላሂ ኢብኑ መስዑድ ቅድም መስጂድ ላይ ደስ የማይል ነገር አየሁኝ ይለዋል ። ምን አየህ ብሎ ሲጠይቀው ሰዎች ተሰብስበው ሶላት እየተጠባበቁ ሳሉ በተለያየ ቦታ ክብ ክብ ሰርተው ከመካከላቸው አንዱ መቶ ጊዜ አላሁ አክበር በሉ, መቶ ጊዜ ላሂላሃ ኢልለላህ በሉ, መቶ ጊዜ ሱብሓነላህ በሉ ይላቸውና በጀማዓ ሲሉ አየሁ ይለዋል ። ኢብኑ መስዑድም ለአቡ ሙሳ ምን አልካቸው ይለዋል ። አቡ ሙሳም ምንም አላልኳቸውም አንተ የምትለውን እስክሰማ አለው !!! ……"
እኔ ይህን የሰለፎች አዳብና ስነስርኣት ለራሴና ለአሁኑ ሙፍቲ ነን ባይ ተማሪዮች ማስታወስ ነው አላማዬ ። አቡ ሙሰል አሽዐሪይ ከዓሊም ሶሓብዮች አንዱ ነው ። ባየው ነገር ላይ ብይን መስጠት አቅቶት ወይም መረጃ አጥቶ አልነበረም ምንም እንዳይል የከለከለው ። ነገር ግን ዐብዱላሂ ኢብኑ መስዑድ ከሱ ስለሚበልጥ እሱ የሚለውን ሳይሰማ በራሱ ብይን መስጠት አልፈለገም ። በዒልምና በእድሜ የሚበልጠው ስላለ ጉዳዩን ወደበላዩ አስተላለፈ ።
እኛ በተለይ ሰለፍይ ነን የሰለፎችን መንገድ ነው የምንከተለው የምንል ወንድሞች ከአቡ ሙሳ ምን እንማራለን እስኪ ራሳችንን እንፈትሽ እላለሁ ።

አላህ በሙግት ሳይሆን በተግባር ሰለፎችን የምንከተል ያድርገን ።

https://t.me/bahruteka

Ibn Awol

06 Nov, 07:48


👉 የነሲሓዎች ጥረት ዲን ማስፋፋት ወይስ በዲን መነገድ ?

ከሶሓባ ስም ምርጡን የዐብዱላሂ ኢብኑ መስዑድ ከሐዲስ ስም ደግሞ ምርጡ የሆነውን አድዲኑ ነሲሓ ከሚለው ስም ወስደው በዲን የሚነግዱት ነሲሓዎች እነሞር ወይም ሞት ያሉ ይመስላል ። ምክንያቱ ደግሞ ከላይ እስከታች በድርጅታዊ አሰራር ኔትወርክ ሰርተው የሚበዘብዙት የሀገር ውስጥና የሀገር ውጪ የእነሞር ተወላጅ ምን እየሰራችሁ ነው የሚለው ጥያቄ ይመስላል ።
ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ለመግለፅ እንደሞከርኩት ያኔ ከእነርሱ ጋር በነበርኩበት ጊዜ እነሞር ላይ ከነበሩት 72 ቀበሌዎች ውስጥ በ2ቱ ላይ በወር 400 ብር ደሞዝ እየከፈሉ ሁለት ኡስታዝ ቀጥረው 3ተኛ ስጠይቃቸው ማለትም በወር 1200 ሊያወጡ ማለት ነው አንተ የተቋሙን ባጀት እንዳለ ወደ እነሞር ልትወስደው ነው የምትፈልገው ብለውኝ ነበር ። ይህ ማለት እነርሱ በወር ከእነሞር ተወላጆች የሚሰበስቡት ገንዘብ በወር ከ100 ሺህ ብር ይበልጥ ነበር ። !!! በዚህ መልኩ ወደ እነሞር ለማሰብ የማይፈልጉ የነበሩ አካላት ዛሬ ላይ ያለ የሌለ ሀይላቸውን ተጠቅመው በዲን ስም እነሞር ላይ መነገድ ይፈልጋሉ ።
የዚህ እንቅስቃሴ ዋነኛው መሪ አቶ አዩብ ደርባቸው ነው ። አቶ አዩብ ማለት ያብሬት ሼይኽ የሴት ልጅ ልጅ ነው ። አያቱ ስልጤንና ጉራጌን በእስልምና ስም ሲያስገብሩት ነበር ። በልጆቻቸው አማካይነት አሁንም እየገበረ ነው ። አቶ አዩብ የከተማውን የጉራጌና ስልጤ ተወላጅ ዘመናዊ ሙሪድ አድርጎ እያስገበረው ሲሆን ገጠሩ ላይ ባሰበው መልክ አልተሳካለትም ። በተለይ እነሞር ላይ በዲን ስም መነገድ የህልም እንጀራ እየሆነበት ነው ። ይሁን እንጂ ከጎኑ ፖለቲከኞችን ፣ አክቲቪስቶችን ፣ ክ/ሀገር ላይ ኪዮክስ ከፍተው የከሰሩ ፣ ከመምህርነት በብድር ወደ ዱባይ ነጋዴነት ሞክረው ያልተሳካላቸው ፣ መካ ላይ ከ20 በላይ ግሩፕ ከፍተው እህቶችን ሲዘርፉ ቆይተው እዚህ መጥተው የተሸሸጉ አካላትን አሰልፎ እንዲሁም ስለሱ ማንነት የማያውቁ ለዲን ነው በሚል ጎራውን የተቀላቀሉ በሞያቸው ህዝባቸውን መጥቀም የሚችሉ አቅም ያላቸው ወንድሞችን ይዞ የማይቆፍረው ጉድጓድ የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም ግን አይሳካም ። ምኞቱ ረፍት ነስቶት እንጂ እንደማይሳካ በተደጋጋሚ አይቶታል ።
የአዩብና ግብረአበሮቹ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የሆነው ነሲሓ በተውሒድና ሱና ስም የሰበሰበውን ወጣት ከኢኽዋን ጋር ተደምሮ ካስረከበ በኋላ በዱንያ ጉዳይ ከኢኽዋን ጋር አልሰራም ብሎ እነሞር ላይ ሌላ ቡድን አቋቋመ ። ኢኽዋኖች ቀደም ብለው ያቋቋሙት ወሄ ሜያ የሚል ቡድን እነሞር ላይ የሚንቀሳቀስ የነበረ ቢሆንም በዐቂዳ አንድ ነን ብሎ የተደመረው የነሲሓ ቡድን በገንዘብ ግን አንድ አይደለንም ብሎ ሂዳያ የሚል ቡድን አቋቁሞ እንቅስቃሴ ጀምሯል ። ከልምድ እንዳየነው ይህ ስብስብ እርስ በርሱ ተበላልቶ የሚበታተን ስብስብ ነው ። ምክንያቱም በዲን ስም ለዱንያ የተሰባሰበ ስብስብ በረካ አይኖረውም ። አውቃለሁ ባይ በበዛ ቁጥር ስራ አይሰራም ። የሁሉም ፍላጎት የተለያየ ስለሆነ ሁሉም ፍላጎቱን ለማሳካት መጓተት መገፈታተር ይመጣል ። ማንም ለውድቀቱ ተጠያቄ መሆን አይፈልግም አንዱ ሌላውን አንተ ነህ ምክንያቱ ይላል ። ይህ በተጅሩባ የተረጋገጠ ነው ። አሁንም ይህ የአዩብ ደርባቸው ስብስብ መጨረሻው ክስረት ነው ። ምክንያቱም አቶ አዩብ የእነሞር እናትና አባት በሽርክ ወደ አኼራ መሄድ አሳስቦት አይደለም እየሮጠ ያለው ። ይልቁንም ሩጫው መቶ ሺህ ብር አውጥቶ የሆነ ነገር ሰርቶ ዶክመንተሪ በማሳየት በመቶ አባዝቶ ብር መሰብሰብ ነው ። ለእነሞር እናትና አባት ወይም ትውልድ አስቦ እንዳልሆነ ከላይ ለማሳየት ሞክሬያለሁ ። ሌላው ማሳያ ሶሞኑን ጉንችሬ አንዋር መስጂድ ላይ ባደረጉት ንግግር ነሲሓዎች እነሞር ላይ እንደ ተብሊጝ የወረደ እንደ ባሕሩም ወሰን ያለፈ ሳይሆን ለዘብተኛ ትውልድ መቅረፅ እንደሚፈልጉ ገልፀዋል ። የባሕሩ ወሰን ማለፍ ማለት ያብሬት ሸይኾችን ማምለክ እንደማይቻል ስም ጠርቶ መናገሩ ነው ። እነርሱ ደግሞ ኡሱሉ ሰላሳንና ኪታቡ ተውሒድ ለተበሩክ ወጣቱን ለመያዝ እያስቀሩ ከነባራዊው ሁኔታ ጋር ሳያገናኙ ትውልዱን ማለዘብ ነው ። ለዚህ ነው አይሳካም የምንለው አቶ አዩብ ተሸወደ እንጂ እነሞር ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ከባሕሩ በጣም የሚሻሉ የአላህ ባሮች ተፈጥረዋል እየተፈጠሩም ነው ። ከዚህ በኋላ ከእነሞር ላይ የተውሒድን ብርሃን አደበዝዛለሁ ማለት የፀሀይን ብርሀን በመዳፌ እከልላለሁ እንደማለት ዘበት ነው ። በስሙ የሚነገድበት ትውልድ አይኖርም ተውሒድ ማለት ከሽርክና ከሙሽሪክ መራቅና ማስጠንቀቅ እንደሆነ የተረዳ ትውልድ ቦታውን ተረክቧል ። በተለይ በእነሞር ምድር ላይ በሰልባጅና በትርፍራፊ ዲኑን የሚሸጥ አይኖርም ።
የተውሒድ ብርሃን ቸሓ ላይ ፣ እዣ ላይ ፣ ጉመር ላይ ፣ ጌቶ ላይም አድማሱን እያሰፋ ነው ። የተውሒድን ባንዲራ ከፍ አድርገው የሚያውለበልቡ የአላህ ባሮች እየወጡ ነው ። ይህን ለማጥፋት የሚደራጅ አካል ራሱ እንደሚጠፋ እርግጠኛ ይሁን ። የተውሒድና ሱና እሳት አንዴ ከተለኮሰ እንደማይጠፋ የማያውቅ ምስኪን ትንፋሽ እስከሚያጥረው እፍ ይበል ።
ለማንኛውም ወንድማዊ ምክር የእነሞር ተወላጅ የሆናችሁ በአዩብ የአል ሂዳያ ቡድን ውስጥ ያላችሁ ቅጥረኛ ተጫዋቾች ጫወታችሁን እንድታቆሙና ማህበረሰባችሁን በምትችሉት ነገር እንድትጠቅሙት እንመክራችኋለን ። በተለይ ከተለያየ ቦታ ከስራችሁና ተደብቃችሁ በመምጣት እዚህ ቡድን ውስጥ የገባችሁ አካላት እንቢ ብላችሁ የምትቀጥሉ ከሆነ ስማችሁን ከነፕሮፋይላችሁ በመዘርዘር ከናንተ የምናስጠነቀቅ መሆናችንን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ ። አቅም ያላችሁ በተለያየ ሞያ የተመረቃችሁ ወንድሞችን በተመለከተ ያላችሁበት ቡድን እናንተን የማይመጥን የወረደ ግብ ይዞ የሚንቀሳቀስ ቡድን በመሆኑ ራሳችሁን አርቃችሁ አላህ በሰጣችሁ እውቀት ማህበረሰባችሁን የሚጠቅም ስራ እንድትሰሩ አደራ እላለሁ ። በዚህ አጋጣሚ ለሞያችሁ ታማኝና ለዲናችሁ ክብር ያላችሁ እስከሆነ ሁሌም የማከብራችሁና በምችለው ማህበረሰባችሁን ጠቃሚ እንድትሆኑ አላህን የምለምንላችሁ መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ ።
ከተማ ያላችሁ ከትንሽ እስከ ትልቅ አንዳችሁ የሌላውን ሳያውቅ በኔት ወርክ ተጠልፋችሁ እየተበዘበዛችሁ ያለችሁ ነጋዴዎች እኛ ከናንተ የምንፈልገው ነገር እንደሌለና ግን አላህ በሰጣችሁ ገንዘብ የምትጠየቁ ስለሆነ የት ለምንና ለማን እንደምትሰጡ እወቁ ለማለት እወዳለሁ ። ዐረብ አገር የምትኖሩ ሁሉም እንደወተት ላም ሊያልባችሁ የሚመኛችሁ እህቶች ባጠቃላይ ነሲሓ የሚዘርፋችሁ እህቶች በተለይ ለዲን ማውጣት ወደ አላህ መቃረቢያ ሲሆን በዲን ሰም የሚለምን ሁሉ ለዲን አይደምና ተጠንቀቁ እላለሁ ።

አላህ ለመልካሙ ሁሉ ይወፍቀን ።

https://t.me/bahruteka

Ibn Awol

01 Nov, 17:57


በኒቃብ ፖለቲካ


የሰሞኑን የኒቃብ ፕሮፖጋንዳ ለፖለቲካ ፍጆታ ሊያዉሉት ፈልገዉ አዉቀዉ ያደረጉት ይመስላል።

መጀመሪያዉንም አነሳሱንና በአስራ አምስት ቀናት ብቻ የተሰራጨበትን ሁኔታ ለተመለከተ ሰዉ የሆነ ሰዉ እጅ እንዳለበት ግልፅ ነዉ።

እስቲ እንጠይቅ።፦ትምህርት ቤቱ ኒቃብ መልበስ ሚከለክል ከሆነ ለምንድነዉ ሁለት ወር ከምናምን በኒቃብ አስተምሮ አሁን ከለከለ?
↪️ለምንድነዉ ለፓርላማ ስብሰባ አስራ አምስት ቀን ሲቀረዉ መራገብ የተጀመረዉ?
↪️ለምንድነዉ መጅሊሱ ለፓርላማ ስብሰባ ኣንድና ሁለት ቀን እስኪቀረዉ ድረስ መግለጫ ከመስጠት ዝም ያለዉ?
↪️እንደሚታወቀዉ የፓርላማ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስቴሩ የሚጠይቁትን ጥያቄ ለፓርላማ ስብሰባዉ ሳምንትና ከዛ በላይ ሲቀሩት ነዉ ጥያቄያቸዉን ወደ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ሚልኩት፣ስለዚህ ካሚል ሸምሱ ትላንት ለጠቅላይ ሚኒስቴሩ የጠየቀዉን ጥያቄ ከሳምንት በፊት አስገብቶታል ማለት ነዉ።ለምንድነዉ መጅሊሱ ምንም ኣይነት እንቅስቃሴ ሳያደርግ በፊት ካሚል ሸምሱ ቀድሞ ጥያቄዉን ያስገባዉ?
↪️ለምንድነዉ ልክ የፓርላማዉ ስብሰባ ቀን በኒቃብ እንዳትማሩ የተባሉ ተማሪዎች መማር ትችላላቹህ ተባሉ?፤ማለትም ለምንድነዉ ክልከላዉ እስከዚያች ቀን ድረስ እንዲረዝም የተፈለገዉ?
ልክ እንደዚህ ቡዙ ጥያቄዎችን መጠየቅ ይቻል ነበር።

ወደ ነጥቡ ስገባ ኢሄ አጀንዳ የተፈለገዉ ለሁለት ሰዎች ሊሆን ይችላል።
ኣንደኛዉ ካሚል ሸምሱ ነዉ።የፓርላማ አባል እንደመሆኑ መጠን የሆነ አጀንዳ ኢዞ ቀርቦ ኢሄንን ለጠቅላይ ሚኒስቴሩ በመጠየቅና ከዛ መፍትሄ አምጥቻለሁ በማለት የሙስሊሙን ማህበረሰብ ዉዳሴ ማግኘት......።

ሁለተኛዉ ሰዉ ጠቅላዩ ራሳቸዉ ናቸዉ፤ኢሄንን አጀንዳ ካስነሱ ቦሃላ ወደ ፓርላማዉ እንዲቀርብና እሳቸዉም መልስ ሰጥተዉበት መፍትሄ እንደተገኘ በማረግ የሙስሊሙን ድጋፍ ማግኘትና ሙስሊሙ በሳቸዉ ተስፋ እንዲያደርግ።

ይህም ሆነ ያ ኢሄንን አጀንዳ የቀሰቀሰዉ አካል የራሱን ጥቅም አግኝቶዋል፣ነገር ግን በዚ ጉዳይ ልባቸዉ የተጎዱ ኒቃቢስት እህቶች ግን ለዛ ጉዳታቸዉ ምንም ካሳ አላገኙም።

ምናልባት ካሚል ሸምሱ ሙስሊም ሆኖ እንዴት ኢሄንን ያረጋል ካልክ ኢኽዋን መሆኑን አስታዉስ፣ኢኽዋኖች ኣንድ ነገር ይጠቅማል ካሉ ያንን ነገር ከማረግ ወደ ኋላ አይሉም።

እናም ሙስሊሞች ኣንድ ነገር ሲከሰት ከስር መስረቱ ማጥናት ኣለብን፣ማንም አምጥቶ የሰጠንን አጀንዳ ማራገብ ዬለብንም።ችግሩም ካለ ከስር መሰረቱ እንዲፈታ መታገል ነዉ እንጂ የሆነ ሰዉ ቆመ ሲለን መቆም ጀመረ ሲለን መጀመር ዬለብንም።


t.me/ibnawolllll
t.me/ibnawolllll

Ibn Awol

30 Oct, 07:33


👆👆👆ድንበር አላፊዉና ነዉረኛዉ ኢብን ሙነወርና ተከታዮቹ

ኢሄን ያልኩት እኔ አይደለሁም እራሱ ኢብን ሙነወር የተናገረዉ ነዉ።

ስለ ሀጁሪ በፃፈዉ ፁሁፍ ላይ"ኣንድ ሰዉ ተዉበት ያረገበትን ነገር አንስቶ መዉቀስ በሱ ላይ ድንበር ማለፍና ነዉረኝነት ነዉ"ብሏል።

በእንደዚህ አይነት አስነዋሪ ስራዉ ሚታወቀዉ ደሞ እሱና ተከታዮቹ ናቸዉ።
ዬቱጋና በማን ላይ እንደዚህ አይነት ስራ ሰራ ካላቹሁኝ መልሱ በሼኽ አብድል ሃሚድ ላይ ነዉ።

ሼኽ አብድል ሃሚድ ዱሮ ራያ አባ ሜጫና ጥቂት ኢኽዋኖችን አወድሰዉ ነበር ነገር ግን ከቆይታ ቦሃላ ከዚህ አቋማቸዉ ተመልሰዉ ባደባባይ ተመልሻለሁ ማለታቸዉ የታወቀ ነዉ።

ኢሄንን እያወቁና እሳቸዉም ተመልሻለሁ ያሉበት ድምፅ እያለ ኢብን ሙነወርና ተከታዮቹ በዚህ ጉዳይ ሲወቅሷቸዉ ነበር፣አሁንም ተከታዮቹ በየ ቦታዉ እያራገቡት ነዉ።

ስለዚህ የተከበሩ አክቲቪት ኢብን ሙነወር እባካቹሁን ከዚህ ነውራቹሁ መመለሳቹሁን ብታሳወቁን?።
እንዲሁም በዚህ ስራ ላይ የተሰማሩ አስነዋሪ ተካታዮቻቹሁንም ከዚህ ድርጊታቸዉ እንዲታቀቡ ብትነግሩልን?።

እንዲሁም ግራ የተጋባዉ ጓደኛቹህ እያራገበ ያለዉን የሼኹን ቪዲዮ እነዲያቆም ብትነግሩልን?።ምክኒያቱም በፁሁፋቹህ ወረድ ብላቹህ በፊቂህ ጉዳይ ላይ ያለ አግባብ መጮህ እንደሌለብን ለመጦቀም ሞክራቹሃል።ስለዚህ የጮሀበትን ሪከርድ እንዲያጠፋ ብትነገሩልን?።



በተረፈ ስለ ሀጁሪይ የፃፈዉ ፁሁፍ ሙሉ በሙሉ ኢጅማል ነዉ።ኢሄ ደሞ አደገኛ የሆነ የሙብተዲዖች አካሄድ ነዉ።ኢብን ሙነወር ባአሁን ጊዜ በተፍሲል ሚናገረዉ ሰለፊዮችን በተመለከተ ብቻ ነዉ።ሌላዉ ፁሁፉ ባጠቃላይ ኢጅማል ነዉ።ኢሄንን ሚያረገዉ ባአንድ በኩል ሲቲይዙት በሌላ በኩል ለማምለጥ ነዉ



t.me/ibnawolllll
t.me/ibnawolllll

Ibn Awol

27 Oct, 18:11


የኒቃብ አጀንዳ



ኢሄ የኒቃብ ጉዳይ ግን በስነ ስርኣት መመርመር ኣለበት።
ለምንድነዉ በየ ዓመቱ እንደ አዲስ እየቀሰቀሱ ሙስሊሙን ሚረብሹት?።

ሙስሊሙስ እራሱን ሚወክል ተቋም ዬለዉም?።ወይስ ኢሄ ተቋም ለዚህ ነገር ዘላቂ መፍትሄ ማምጣት አይችልም?።
ኣንድ ትልቅ የሀገር ተቋም ኢሄን ችግር ፈቶ ዘላቂ የሆነ መፍትሄ ካላመጣ ስራዉ ምንድነዉ?።

በዚህ ተቋም ያልተገኘ መፍትሄ እንዴት ነዉ በፌስቡክና በቲክቶክ ጩሀት መፍትሄ ሚመጣዉ?።

ህዝቡም ለምንና እንዴት ብሎ አይጠይቅም፣ኣንድ አጀንዳ አምጥተዉ ይሰጡታል እሱ ተቀብሎ ያራግባል።ያ ያራገበዉ ጉዳይ መፍትሄ አገኘ አላገኘም አያጣራም።ለጥቂት ቀን ይጮሃል ከዛ በሌላ አጀንዳ ይጠምዱታል ከዛ መጀመሪያ የያዘዉን አጀንዳ መፍትሄ ሳያገኝ በሌላዉ ይጠመዳል የመጀመሪያዉን ይረሳዋል።

የሰሞኑም የኒቃብ ጉዳይ እንደዚህ አይነት አሻጢር ሳይኖረዉ አይቀርምና በደንብ ሊጠና ይገባዋል።የሆነ የፖለቲካ አጀንዳቸዉን ሊያስቀይሩ ያስነሱት ረብሻ ይመስለኛል።

ኢሄ ችግር ካለም የሚመለከተዉ አካል ጣልቃ በመግባት ዘላቂ የሆነ መፍትሄ ማምጣት ይኖርበታል።በየ ዓመቱ በየ ሚዲያዉ መንጫጫት ብቻ ሆኖ መቅረት ዬለበትም።
ኢሄ ህዝብ አይደለም አጀንዳ ሰጥተሀዉ ሆዱና የኑሮ ዉድነቱ ተጨማምሮ ራሱ ከአጀንዳ አልፎ በጭንቅ ተወጥሮ ነዉ ያለዉ።

ጉዳዬን ያስፈፅምልኛል ብሎ ያቋቋመዉ ተቋም እያለ ለምንድነዉ መልሳቹህ ወደ ቤቱ ምታመጡለት?።


t.me/ibnawolllll
t.me/ibnawolllll

Ibn Awol

27 Oct, 09:09


🔷  ሱፍይና አሕባሾች የዼንጤ ድልድዮች

      በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ዼንጤዮች ጌታዋን የተማመነች ጊደር ጅራትዋን ውጪ ታሳድራለች እንደሚባለው የልብ ልብ ተሰምቷቸው እየዘመቱ ነው ። የአክፍሮት ዘመቻቸው በዋነኝነት ቀብር አምላኪዮችን ትኩረት ያደረገ ነው ።
      ኢስላም ከጅምሩ የተዋጋው ኩፍር ቢኖር ቀብር አምልኮትን ነው ። የሚያሳዝነው ግን አሕባሽና ሱፍዮች ቀብር አምልኮትን ኢስላም አድርገው ለማህበረሰቡ በማቅረብ ዘጠና ከመቶ የሚሆነው ሙስሊም ቀብር አምላኪ እንዲሆን አድርገውታል ።
     አሕባሽና ሱፍዮች ይህን ቀብር አምልኮ የሚቃወምን ከእስልምና የሚያስወጣ ተግባርና ክልክል መሆኑን የሚያስተምሩ የተውሒድ ሰዎችን ካፊር ይላሉ ። ማህበረሰቡ የዚህ አይነቱን አስተምሮ እንዳይሰማ በዚህ የተውሒድ ዳዕዋ የተሰማሩ የነብያት ወራሾችን ወሀብዮች በማለት እንደጭራቅ እንዲታዩ ያደርጋሉ ። ከዚህ አልፎ ተርፎ የተለያዩ አጋጣሚዮችን በመጠቀም እድሉን ሲያገኙ በማሳሰር በማስገረፍ የቻሉትን ይሰራሉ ።
     የሱፍይና የአሕባሽ መሪዮች ወሀብዮች ከአባታችሁ የወረሳችሁትን እምነት ሊያስለቅቁዋችሁ ነው በምትችሉት ታገሏቸው ብለው የተውሒድ ሰዎችን እንዲገሉ ያበረታቱዋቸዋል ። ሞራል ይሰጡዋቸዋል ። ምስኪኖቹ የቀብር አምላኪዮች እስልምናችንን ሊያጠፉብን ነው ብለው የህይወት ዋጋ እስከመክፈል ራሳቸውን ያዘጋጃሉ ።
    አላህን በብቸኝነት ተገዙ የሚሉ ዱዓቶችን ከከሀዲያን የበለጠ ይጠላሉ ። የሚሉትን ለመስማት ቀርቶ ማየት አይፈልጉም ። 124 ሺህ ነብያት ሊዋጉት የተላኩበትን ቀብር አምልኮ ኢስላም ነው ብለው የነብያት ተከታዮችን ይዋጋሉ ። ነብዩ የተወጉለትን ፣ ደማቸው የፈሰሰለትን ፣ የተራቡለትና የተጠሙለትን ፣ የተሰደዱለትን ፣ ሶሓቦች የሞቱለትን ፣ ሰባ ሰማኒያ ቦታቸው የተወጉለትንና የተሰየፉለትን ተውሒድ ኩፍር ነው ይላሉ ።
    በተቃራኒው ያወገዙትና ኩፍር ነው ያሉትን ቀብር አምልኮ ኢስላም ነው ይላሉ ።
     ይህ የሱፍይና የአሕባሽ መሪዮች አስተምሮና ተግባር ለዼንጤዮች ወርቃማ እድል ሆኖላቸዋል ። ይህን ክፍተት ተጠቅመው ቀብር አምላኪ ምስኪኖች ጋር ቀርበው እናንተ ሞቶ የበሰበሰን ከምታመልኩ ዒሳ ጌታ ነው ብላችሁ ለምን አትድኑም ቀናቶችን ከፋፍላችሁ ቁጭ ብላችሁ ጫት በመቃም እድሜያችሁን ከምትጨርሱ የሙታን መንፈስ እያመለካችሁ የሲኦል ከምትሆኑ እየሱስ ጌታ ነው ብላችሁ ለምን አትድኑም ይሏቸዋል ።
    ምስኪኖቹ አንድ ቀን ተውበት አድርገው ወደ አላህ ተመልሰው ዘላለማዊ ሕይወት የሚወርሱበትን እድል ትተው የዘላለማዊ ጀሀነም መሆንን ይመርጣሉ ።
     ዒሳ ሁሉን ቻይ የሆነው ጌታ ኣደምን ያለ አባትና እናት ፣ ሓዋን ያለ እናት እንደፈጠረው ሁሉ ያለ አባት ከእናት ብቻ ሁን በሚለው ቃሉ ፈጥሮ ነብይ ያደረጋቸው መሆኑን የሚያስተምረውን ኢስላም ትተው በመርየም ማህፀን ውስጥ ማንኛውም ህፃን የሚያልፈውን ሂደት አልፈው ተረግዘው የተወለዱትን ዒሳን ፈጣሪ ብለው ይከፍራሉ ።
    እነዚህ ምስኪኖች ዒሳ በመርየም ማህፀን ውስጥ ከረጋ ደም ጀምሮ የነበሩ ሂደቶችን አለረፈው ደሙ ስጋ ሆኖ ፣ ስጋው አጥንት ለብሶ ፣ ስጋና አጥንቱ ቅርፅ ይዞ የተለያየ የሰውነት ክፍል እንደ ልብ ፣ ሳንባ ፣ ጉበት ፣ ኩላሊት ፣ ዐይን ፣ ጆሮ ፣ አፍና አፍንጫ ፣ ጭንቅላትና አእምሮ ፣ እጅና እግር ፣ ሴልና ነርቭ ፣ የውስጥ ሜካኒካል ክፍልና የአእምሮ ኤሌክትሪካል ክፍል ተሟልቶለት ሙሉ ሰው እስኪሆኑ ፍጥረተ ዓለሙን ማን ነበር የሚያስተናብረው ?
    ብለው መጠየቅ አልቻሉም ። እየሱስ ጌታ ነው ሲባሉ እሺ ብለው ተቀበሉ ። ለዚህ የዳረጋቸው ከሱፍያና አሕባሽ የወረሱት የሙታን መንፈስ አምልኮት ነው ።
     እነዚህ የሱፍይና አሕባሽ መሪዮች ወሀብዮችን በሚያስጠቁቁበት ልክ ከዼንጤ አያስጠነቅቁም ። ዼንጤ ልጆቻቸውን ሲከፍር ዱላ ይዘው አይወጡም ። እምነታችሁ ተነጠቀ አይሉም ። ዐቂዳችሁ ተነካ አይሉም ። በምትችሉት ታገሏቸው አይሉም ። የእነርሱ ወኔ በነብያት ወራሽ የተውሒድ ሰዎች ላይ ነው ።
     ለዘህ ነው እነዚህ አካላት የዼንጤዮች ድልድዮች ናቸው ያልኩት ። የአሕባሽና ሱፍዮች የኩፍር ተግባር ነው ምስኪን ቀብር አምላኪያንን ወደ ከፋ ኩፍር ይዟቸው የሚሄደው ።
      በጣም የሚያሳዝነው ነሲሓዎች ከእነዚህ ጋር ነው አንድ ነን ብለው ከኢኽዋንና ሱፍይ እንዲሁም አሕባሽ ጋር አንድነት በመፍጠር እኛ የኢትዮዽያ ሙስሊሞች ነን ያሉት ።
     በየአካባቢያችሁ ያሉትን የነሲሓ ዱዓቶችን ዳዕዋ አዳምጡ የቀብር አፈር በጥብጦ መጠጣት ፣ በአንዬ ፣ ዳንዬ ፣ አልከስዬ ፣ ቃጥባርዬ ፣ አብሬትዬ ፣ አባድርዬ ፣ ሾንክዬ ፣ ሸከና ሑሰይንዬ ፣ ጀማ ንጉስዬ ፣ ከረምዬ ቀብር ላይ ጠዋፍ ማድረግ ከእስልምና የሚያወጣ ሽርክ ነው የሚል የለውም ።
     ይህን ካሉ ከሱፍይና አሕባሽ እንዲሁም ኢኽዋን ጋር ስለሚጣሉ ። እየአንዳንዱን ወልይ ተብለው የሚመለኩ መሻኢኾችን ስም ጠርተው እዱኝ ፣ አክብሩኝ ፣ አሽሩኝ ፣ እጄን ያዙኝ ዋስ ጠበቃ ሁኑኝ ማለት ኩፍር ነው አይሉም ። የአንድነት  ስምምነቱን ስለሚያፈርስ ። በጥቅሉ ሽርክ ከባድ ወንጀል ነው ይላሉ ። ተውሒድ የነብያት ዳዕዋ ነው ይላሉ ። በዚህም ተከታዮቻቸውን ይሸውዳሉ ። የቱ ምን አይነቱ ተግባር ሽርክ እንደሆነ በዝርዝር አይናገሩም ።
     በመሆኑም ሰለፍዮች ሆይ ኡማውን ከቀብር አምልኮና ከአክፍሮት ሀይላት ለማዳን ያለባችሁ ሀላፊነት ከምን ጊዜውም የከበደ ነው ። ከዚህ ጎን ለጎን ይህን የነብያት ተልእኮ ለዱንያዊ ጥቅም ብለው በመተው በኢስላም የሚነግዱትን ነሲሓዎችንና የእንጀራ አባታቸው ኢኽዋኖችን እንዲሁን እንባ ጠባቂዮቻቸው የሙነወር ልጅና ግብረአበሮቹ ማንነት ለሱናው ማህበረሰብ ግልፅ ማድረግ ሌላው ትልቅ ሀላፊነት መሆኑን መዘንጋት የለባችሁም ።
       አላህ ዲኑን ይረዳል ተውሒድም የበላይ ይሆናል ።

ጠቃሚ ስለሆነ በድጋሚ የተለቀቀ ።

https://t.me/bahruteka

Ibn Awol

21 Oct, 13:35


🔈#ትንሽ ስለ ተብሊግ

🔶ማነው በጥሩ የሚያዘው ከመጥፎ የሚከለክለው ከሚለው ሙሐደራ የተወሰደ አጭር ትምህርት

🎙 በኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን (ሀፊዘውላህ)

🌐 https://t.me/shakirsultan

Ibn Awol

20 Oct, 17:25


የተብሊግ ደእዋ ኢጅቲማእ ሚባለዉ ስብስብ የአህባሽና የሱፊያ መሸሸጊያ ነዉ።
በፍፁም ትክክለኛዉን አሰስልምና አይወክልም።
እንደዉም ኣንዱ ኢሄን ስብስብ የአህባሽ መሸሸጊያ ነዉ ስለዉ። ከተለያዩ ሀገር የመጡት ሰዎች እንዴት አህባሽ ይሆናሉ ብሎኛል።

ሲጀመር ተብሊግ የሆነ ሰዉ ኬትኛዉም ሀገር ቢመጣ ጃሂል ከመሆን አይወገድም። እራሱ አህባሾ ሆኖ ባይመጣም የአህባሽን ፊክራ ኢዞ የመሄድ ቻንሱ የሰፋ ነዉ።
ሲቀጥል የተብሊግ ጀማኣ የተመሰረተዉ በሱፊያ አካሄድ ነዉ።የጀመሩት ሰዎችም ቀብር አምላኪ የነበሩ ናቸዉ።በስም አህባሽ ባይሆኑም በአቂዳ ግን አህባሽ ናቸዉ።


ባጠቃላይ በአቂዳዉ ጤነኛ የሆነ ሰዉ ከነሱ ጋር አይሄድም።ከነዚህ የጃሂልና የቢደዓ ጥርቅሞች ሰዎችን ልናስጠነቅቅ ይገባል



t.me/ibnawolllll

Ibn Awol

20 Oct, 13:06


የማስጠንቀቂያ መልዕክት

ይህ የተብሊግ ስብስብ ሱናን አይወክልም የቢድዓ ሰዎች እና የተውሒድ ጠላቶች ስብስብ ነው ስለሆነም መታደሙም ሆነ ማሰራጨት አይፈቀድም ።

የተብሊግ ስራ የመሀይማን እና የጨለማ ጉዞ

https://t.me/abuabdurahmen

Ibn Awol

15 Oct, 17:45


ዱኒያ ማለት በጣም ርካሽ የሆነች ነገር ነች።
ጀነት ደሞ በጣም ዉድ ነች።


ርካሿን ሽጠህ ዉዷን ለመግዛት ተሯሯጥ።ሸይጣንና አጋሮቹ ርካሿን እዘህ መጨረሻህ እንዲከስር ይታገሉሃል።
ጓደኛህ ሁሌ ስለ ርካሿ ከሆነ ሚያወራህ ራቀዉ፣ጓደኛህ ሁሌ ስለ ዉዷ ሚመክርህ ከሆነ አጥብቀህ ያዘዉ


t.me/ibnawolllll
t.me/ibnawolllll

Ibn Awol

12 Oct, 08:17


አላወቁንም፣ እስኪያቁን እንታገስ።
እንደነሱ ሀገር ጥለን ምንፈረጥጥ መስሎዋቸዉ ነዉ።


ቡዙ ያላወቁን ሰዎች ሞልተዋል።ማንነታችንን ልናሳያቸዉ ይገባል።
ሲነካኩን ምንጠነክር፣ሊያዳክሙን ሲሞክሩ እንደምንበዛ አላወቁም።ፈተናዎች ሲበዙ እንደ ብረት እንደምንጠነክር አላወቁም።

ማንሰራዉና ምንደክመዉ እነሱ ችላ ሲሉን እንደሆነ አልገባቸዉም።እነሱ ሲነካኩን ኣንድ ሆነን ወደ ስራችን እንደምንመለስ አላወቁም።

ስላነቃቃቹሁንና ብዙ ጠላቶች እንዳሉን ስላስታወሳቹሁን እናመሰግናልን።


t.me/ibnawolllll
t.me/ibnawolllll

Ibn Awol

11 Oct, 18:01


የተላለፈዉ የአንድ ቀን ደዕዋ እንጂ ሙሉ የሰለፊያ ደዕዋ አይደለም።
በዚህ የሀቅ ባለቤቶችም ሊያዝኑ አይገባም፣የባጢል ሰዎችም ሊደሰቱ አይገባም።

ነገሮች ተፈፃሚነት ሚያገኙት አላህ ሲፈቅድ ብቻ ነዉ።ሰዎች እቅድ ብቻ ነዉ ሚያወጡት አላህ ከፈለገ ይፈፀማል ካልፈቀደ አይፈፀምም።

ለክስተቶች ሰበብ ሊኖራቸዉ ይችላል፣ከእኛ ሚጠበቀዉ እነዚያን ሰበቦች መፈፀም ነዉ።ሰበቦችን የፈፀምነዉ ለአላህ ብለን ከሆነ ያ ነገር ባይሳካም አላህ አጅሩን ይከፍለናል።

ኢሄ ፕሮግራም ባለመሳካቱ የሚደሰት ጠላተ ካለ የራሱን ድክመት ነዉ ሚያሳየዉ።ምክኒያቱም እኛን በመረጃ ሊያሸንፈን አይችልም ስለዚህ ያለዉ አማራጭ በእንደዚህ አይነት እንቅፋቶች መደሰት ነዉ።

እኛ ደሞ እንቅፋቶች በበዙ ቁጥር የበለጠ ጠንክረን፣በጥንቃቄ መጓዝ ይኖርብናል።

የጀመርነዉ ለአላህ ብለን ከነበረ የተላለፈዉም በአላህ ፍቃድ ነዉና ሰብር አድርገን ቀጣዩን ቀን በጉጉት ልንጠብቅ ይገባል።

የሚናደድ ሰዉ ካለ ከሰዎች ጋር እልህ ዉስጥ ስለገባና እነዛን ሰዎች ለማስቆጨት ብሎ የገባ ነዉ፣የሚናደደዉ እነዛ ሰዎች ስላልተናደዱ ነዉ ሚሆነዉ።ስለዚህ እንደዚህ አይነት ሰዎች ካለን ኢኽላሳችንን ልናስተካክል ይገባል።ስኬታችንና ዉድቀታችን በሰዎች ልንመዝነዉ አይገባም።

ኢሄ ክስተት ለሰለፊዮች ትልቅ ተአምር ሊያሳያቸዉ እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ፣ተእዊሉን ስለማናቀዉ ነዉ ቅር ሚያሰኘን።

በተረፈ ቀጣዩ ፕሮግራም ቀኑ ታዉቆ እንዲሳካ በያለንበት ለፕሮግራሙ አዘጋጆች ዱዓ እናድርግላቸዉ።እኛ ተጠርተን ባለመሄዳችን ነዉ ቅር ያለን እነሱ ጊዜያቸዉን አቃጥለዉ፣ተጨንቀዉ እየተሯሯጡ ባለመሳካቱ ምን ያህል እንደሚሰማቸዉ አስቡት እስኪ።ስለዚህ ነሽጠን እነሱንም አነሽጠን ለቀጣዩ እንዘጋጅ፣ሙእሚን ተስፋ አይቆርጥም።ድክመታችንን ወደ አላህ እናስጠጋ፣ድክመታችንን ማንም ላይ አናላክክ።
አላህ ደዕወቱ ሰለፊያን ሀበሻ ላይ አብባ ከሚያዩት ሰዎች ያድርገን።

t.me/ibnawolllll
t.me/ibnawolllll

Ibn Awol

10 Oct, 08:25


በፍፁም ሊያመልጠን ማይገባ ፕሮግራም።


እሁድ የኢትዮጵያ አህለሱና ወል ጀማዕ ማህበር በሚሊኒየም አዳራሽ ሚያዘጋጀዉ ፕሮግራም በአመት ኣንዴ ሚገኝ እድል ነዉ።ስለዚህ በፍፁም ሊያመልጠን አይገባም።

የባጢል ሰዎች ለባጢላቸዉ ብለዉ ቡዙ ጊዜያቸዉን ያጠፋሉ፣ቡዙ ገንዘባቸዉንም ያፈሳሉ።
ተብሊጎች ምንም ሳይኖራቸዉ ለአርባና ለሶስት ወር ሲዞሩ ይከርማሉ።እኔ እንደ ተብሊግ ቤትንና ስራህን ጥለህ ዙር እያልኩህ አይደለም፣ነገር ግን ከነሱ አንፃር ኣንተ ምን ያህል ወኔ ኣለህ ለማለት ያክል ነዉ።
በተለይ የሰለፎቻችንን ታሪክ ብናይ ከእንደዚህ አይነት ምሳሌዎች ሚያብቃቁ ታሪኮች ሞልተዋሉ።

ዓለም በዚህ ወቅት ወደ ለዬለት ቀዉስ እየገባች ነዉ።ሰዎች ለምንና በምን ምክኒያት እንደሚሞቱ አያቁም።ግማሹ በጦርነት፣ግማሹ በመኪና አደጋ፣ግማሹ በረሀብ፣ግማሽ በመሬት መንሸራተት፣ግማሹ ..........እያለቀ ነዉ፣እኛን ነጌ ምን እንደሚያጋጥመን አይታወቅም።ስለዚህ ዛሬ ያገኜነዉን እድል በአግባቡ እንጠቀም።

ነብሲያችንን እናሸንፋት፣ለሰለፊያ ደእዋ ኣንድ ሺ ብር አላህ ላገራለት በጣም ትንሽ ነዉ።
ካለህ አትሰስት።ከሌለህ ተበደር።ኣንድ ሺ ብር ማለት ቁርስ፣ምሳ፣እራት በልተሀባት ትንሽ ቢቀርህ ነዉ።
እያወራሁ ያለሁት ስለ ሚስኪኖቹ ነዉ።ሀብታሞቹ አይደለም ለራሳቹህ ለሌሎችም መሸፈን ኣለባቹህ።ለተራ የመንግስት ሰራተኛ ከምትሰጡት ለነዚህ ሚስኪን ወንድሞቻቹህ ሰጥታቹህ አላህ እነዚያን እንዲይዝላቹህ ዱዓ ብታረጉ የበለጠ ትርፋማ ትሆናላቹህ።

በተረፈ ነቃ ነቃ በሉ፣ማስታወቂያዉን ደጋግማቹህ ሼር አድርጉት እስካሁንም ያልሰሙ ቡዙ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ።

t.me/ibnawolllll
t.me/ibnawolllll

Ibn Awol

09 Oct, 18:16


ኢብን ሙነወር አክቲቪቱ በጣም እናመሰግናልን።

የሙነወር ልጅ ቶሎ ቶሎ ብትፅፍ ደስ ይለናል።ምክኒያቱም የሙሃደራዉ ቀን በጣም ቅርብ ስለሆነ ማስታወቂያዉ ቡዙ ሰዉ ጋር መድረስ ኣለበት።ለዚህ ደሞ የናንተ ተሳትፎ ከተጨመረበት የበለጠ ይሰራጫል።


ኣንተ ረድ ያረክ መስሎሃል ነገር ግን አላህ ነዉ በጥበቡ እንድትናገር ያደረገህ።በዚች ንግግር ስንት የተኙ የነበሩ ሰለፊዮችን እንደቀሰቀስክ አላህ ነዉ ሚያቀዉ።

በነገራችን ላይ ኣንተ አላወክም እንጂ በዚህ ወቅት እንዳንተ የከሸፈ ዬለም።በቅናት፣በምቀኝነት፣በኩራት፣በኢብሪተኝነት ተወጥረህ ብዙ ሚወዱህና ሚከተሉህን ሰዎች አጥተሃል።እኔ ምኖርባት አዳማ ላይ ኣንድ እንኳን ያንተን ተከታይ ማግኘት ከባድ ነዉ።ይህ ሚገርምህ ድሮ የነበሩህን ተከታዮች ስታቅ ብቻ ነዉ።

ዛሬ በፃፍካት ፁሁፍ ቡዙም አልተገረምኩም።በፁሁፍህ ያዬዉት በዉስጥህ ለሰለፊዮች የያዝከዉን ስር የሰደደ ጥላቻ ነዉ።እንጂማ እንዲህ ልትናገር ሚያበቃህ ነገር እኮ አልነበረም።ከዚህ በፊት ከኛ መሻይኾች ዉስጥ እናንተ ወይም ሙመይዓዎች ብር ሰብስባቹህ ደዕዋ በማረጋቹህ ብቻ የተናገራቹህ ማንም አልነበረም።ኣንተ ግን ተከታዮችህን ለማስተኛት በማሰብ ብቻ እኛ ለደዕዋ ብር መሰብሰብን ምንቃወም አስመስለህ ለማቅረብ ሞክረሃል።
ቆይ እንደዉ አላህን አትፈራም ሰዎችን ስለጠላህ ብቻ እንዲህ ባደባባይ ትዋሻልህ?፣ትልቅ ሰዉ አይደለህም?፣ከጓደኞችህ መሃከል ተዉ ሚልህ ዬለም?።
ቆይ ከዚህ በፊት ሰለፊዮች ያደረጓቸዉ ሙሃደራዎች ያለ መዋጮ ነዉ የተደረጉት?።ያለ መዋጮ የተደረገ የሰለፊዮችን ኣንድ ፕሮግራም ታዉቃልህ?።
እኛ እኮ በደዕዋ ስም የምንነግደዉ ንግድ ወይም ገቢ ዬለንም አመት በመጣ ቁጥር የራሳችንና የሚስኪን ወንድሞቻችንን ኪስ ነዉ ምንዳብሰዉ።ለምን በዚህ ልክ ልታብድ ቻልክ?።
ለምን በመዋጮ መስጊድ ስንሰራ አልተናገርከም?።ዛሬ ነዉ ጥፋት ሆኖ የታየህ?።

እዉነታዉ ግን ኢሄን የተናገርከዉ ተካታዮችህን ለማስተኛት ብቻ ነዉ፣ምክኒያቱም ተከታዮችህ ኢዚህ ፕሮግራም ላይ እንዳይገኙ ሌላ አማራጭ ዬለህም።
ነገር ግን ምስጋና ለአላህ ይገባዉ ኣንተ ተንኮል ብታስብም አላህ የበለጠ ፕሮግራሙን በናንተ አስተዋዉቆልናል።

ሰለፊዮች ግን ኣንድ ነገር በደንብ ልብ በሉ።እነኚህ ሰዎች ዝም ሲሉ ደክሟቸዉ እንዳይመስላቹህ እኛ እየሰራን ስላልሆነ ነዉ።እኛ መስራት ስንጀምር ቀለማቸዉን አሹለዉ እንቅልፋቸዉን ትተዉ ነዉ ሚያድሩት።
ስለዚህ በስራ ላይ በደንብ እንበርታ፣በማሀከላችን ያሉ ቀዳዶችን በደንብ እንዝጋ፣እንተጋገዝ አላሀም ያግዘናል።

ኢሄንንም ፕሮግራም ያቅማችንን ሁሉ በማረግ እናሳካዉ።


t.me/ibnawolllll
t.me/ibnawolllll

Ibn Awol

09 Oct, 16:02


ሰው በህመሙ ልክ ነው የሚጮኸው

አይግረማችሁ የኢኽዋን እንባ ጠባቂ የነሲሓ የእንጀራ ልጆች ይህ ፕሮግራም ቢያሳምማቸው ምን ይገርማል ? ሰለፍዮች ውጤታማ ስራ በሰሩ ቁጥር ያቅለሸልሻቸዋል ። ያስታውኩት ዝም በሏቸው ። ዝቅጠትን በጩኸት መሸፈን የሽንፈት ምልክት ነው ። ለማንኛውም በአላህ ፈቃድ ሰለፍዮች በወሬ ሳይሆን በተግባር ተውሒድና ሱናን የበላይ ያደርጋሉ ። የታመሙትን ህመማቸው በተውሒዱ ዳዕዋ የሚፈወሱ ያድርጋቸው ነው የምንለው ።

http://t.me/bahruteka

Ibn Awol

07 Oct, 08:55


ጥያቄ ለኸድር አህመድ አል_ደሲይ


ሰሞኑን እርቅ ይሻላል የሚል ፁሁፍ ፅፎ አዬሁትና ለምን ኣንድ ነገር አልልም ኣልኩ።
ማንም ሰዉ እርቅ የሚጠላ አይመስለኝም።ነገር ግን በምንና እንዴት ሚለዉ ነገር ግን መታየት ኣለበት።ኺላፍ ደረጃዎች እንዳሉት ግልፅ ነዉ።የኺላፍ አይነት ግን በደንብ መጤን ኣለበት።

በፁሁፉ ብዙ መልስ ዬላቸዉም ያላቸዉ ነገር ግን እኛጋ መልስ ያላቸዉን ነገሮች ኣሉ።ግን እሱን ትተነዉ ወደ ጥያቄ ልግባ።

ኣንደኛ፦እናንተ መሻይኾቻችን ላይ ኣለ ብላቹህ ያነሳቹሁት ችግር የመንሃጅ ነዉ ወይስ የዱኒያ ችግር ነበር?።

እናንተ ከዚህ በፊት ያላቹሁን የመንሃጅ ነዉ ብላቹህ ነበር።ታዲያ ችግሩ የመንሃጅ ከሆነ እንዴት ነዉ በሱልህ(በእርቅ)ሚፈታዉ?።
የመንሃጅ ችግር ካለበት ሰዉ ምትታረቀዉ ወይ ያ ችግር ኣለበት ያልከዉ ሰዉ ያንን ኣለበት ያልከዉን ችግር ትቶ ወደ ሀቅ ሲመለስ ነዉ ወይ ያንን ሰዉ የመንሃጅ ችግር ኣለበት ብሎ የከሰሰዉ ሰዉ ችግሩ የመንሃጅ አይደለም ተሳስቼ ነዉ የመንሃጅ ችግር ነዉ ያልኩት ሲል ነዉ።

ስለዚህ እዚህ ጋር መሻይኾቹ ኣለባቸዉ ካላቹሁት የመንሃጅ ችግር ተመልሰዉ ነዉ?።
ወይስ እናንተ የመንሃጅ ነዉ ያላቹሁት ነገር ስህተት ሆኖ ነዉ?።

ሁለተኛ፦በመሻይኾች ያነሳቹሁት ነገር የመንሃጅ ካልሆነ ለምን አደባባይ አወጣቹሁት?።
ያኔ ተዉ ነገሮችን አረጋጉ ፊትና አትፍጠሩ ስትባሉ ለምን አሻፈረኝ ኣላቹህ?።
ከኤገሌ የሚለየን ነጥብ እያላቹህ ያዙኝ ልቀቁኝ ለምን ኣላቹህ?።
የመንሃጅ ካልሆነ ለምን አዲሶችን ሙመይዓዎች ይቅርታ እስከመጠየቅ ደረሳቹህ?።
ወይስ የሀጃዊራዎችን አይነት ሱልህ ነዉ የፈለጋቹሁት?።


በመጨረሻም ኣንድ ምክር ልምከራቹህ፣የፈለጋቹሁት አጥፍተናል እንመለስ ከሆነ ስህተታቹሁን በያን አድርጋቹህ ወደ ነበራቹሁበት(አቋም) ተመለሱ።ለዚህ ምንም አይነት የወረቀትና የፊርማ ሱልህ አያስፈልገዉም።


t.me/ibnawolllll
t.me/ibnawolllll

Ibn Awol

04 Oct, 13:29


👆👆👆በተለይ ሰለፊይ የሆነ ሰዉ ከእንደዚህ አይነት ባህሪ ሊርቅ ይገባል።

ሀሜትና ወሬ ማመላለስ በአሁን ሰዓት በሰለፊዮች መሀከል ሰርፆ የሚገኝ አደገኛ በሽታ ነው።
አብዛኛዉ በማሀከላቸዉ የሚመጣዉ ኺላፉ ከእነዚህ ሁለት በሽታዎች ነዉ።
ለአኼራዉ ሚጨነቅ ሰዉ ማንኛዉንም ወሬ ሳያጣራና ከባለቤቱ ሳያረጋግጥ ማውራት ዬለበትም።
አብዛኛዉ ሰዉ እያረገ ያለዉ ግን በተቃራኒዉ ነዉ፣የሆነ ሰዉ የሆነ ወሬ ይሰጠዋል እሱ ከባለቤቱ ሳያረጋግጥ ቶሎ ብሎ እርምጃ ይወስዳል።

ኤገሌ እንዲህ ብሎዋል ወይም ኤገሌ እንዲህ አድርጎዋል ስትባል የነገሩን ምንጭ በደንብ ማጥናት ይኖርብሃል።ኢሄ ያለዉ ሰዉ ለምንና ከምን አንፃር እንደተናገረዉ ሳታቅ ወደ አቋም መያዝ አትሂድ።

እንደዉም አብዛኛዉ ሰዉ የመንሃጅና የዱንያን ልዩነት ለይቶ አያቅም።ኣንድ ወንድምህ በሆነ ነገር ሲሳሳት ያ የተሳሳተበት ነገር ዱንያዊ ጉዳይ ነው ወይስ መንሃጃዊ ብለህ መለየት ግድ ነው።
ወደድንም ጠላንም ከአንድ ወንድማችን በሆነ ነገር ባንስማማና ያ ነገር መንሃጃዊ እስካልሆነ ድረስ ከሶስት ቀን በላይ መኮራረፍ አይቻልም።
ታዲያ ከማሀላችን ስንቱ ነዉ መንሃጃዊ ባልሆነ ነገር ከሶስት ቀን በላይ ሚኮራራፈዉ?።ከዚህም አልፎ መንሃጃዊ ባልሆነ ነገር ደእዋዉን ለመጉዳት ሚንቀሳቀስ ስንት ኣለ!?።

ከሆኑ ሰዎች ጋር በሆነ ነገር ስላልተስማማህ ብቻ ደዕዋ ለመጉዳት መንቀሳቀስ ወይም ደዕዋዉን ለመጉዳት ማሰብ አላዋቂነት ነዉ።
እንደዚህ ሚያረጉ ሰዎች እንደዉም ደዕዋ ሰለፊያ ካለማወቅ ይመስለኛል።ሰለፊያ ጠንቅቆ ሚያቅ ሰዉ እያንዳንዱ ንግግሩ፣እያንዳንዱ አካሄዱ በጥንቃቄ የተሞላ ነዉ።
ኣንድን ንግግር መቼና ዬት ለምን እንዴት መናገር ወይም መተግበር እንዳለበት ያቃል።

ባጠቃላይ ሰለፊያን በትክክል ሚያቅ ሰዉ ስሜቱን ከሰለፊያ ደዕዋ አያስቀድምም።
እያንዳንዱ እንቅስቃሴዉ ወይም ንግግሩ ከሰለፊያ ጥቅምና ጉዳት ጋር ያመዛዝናል።ለግለሰቦች ጥቅም ሳይሆን ለደዕዋዉ ጥቅም ይንቀሳቀሳል።


ምክሩ ለራሴም ጭምር ነው።

t.me/ibnawolllll
t.me/ibnawolllll
t.me/ibnawolllll

Ibn Awol

04 Oct, 12:59


ሐሜትና ወሬ አመላላሽነት መልካም ስራን ባዶ ያደርጋል
———
ሰዒድ ኢብን ጁበይር (ረሂመሁላህ) እንዲህ አለ:-
“በእለተ ትንሳዔ ለአንድ ባሪያ የስራው መዝገብ ይመጣና ይከፈትለታል፣ መዝገቡ ላይም የሶላትም ሆነ የፆም ውጤት አይመለከትበትም፣ ወደሰራው መልካም ስራም ቢመለከት የለም፣ ይህን ጊዜ "ጌታዬ ሆይ ይህ እኮ የሌላ ሰው መዝገብ ነው፣ የኔ የስራ መዝገብ አይደለም፣ ምክንያቱም ለኔ መልካም ስራዎች ነበሩኝ እዚህ መዝገብ ላይ ደግሞ የሉም።" ይላል፣ ለእርሱም ምላሹ እንዲህ ይባላል:- ጌታህ አይስትም አይረሳም፣ ስራህ እንዳለ ሰዎችን በማማትህ ጨርሶ ሄዷል። ይባላል፣
አደራ!! ወንድም እህቶቼ ሐሜትንና ወሬ አመላላሽነትን ተጠንቀቁ!! ሁለቱም ዲንን ይጎዳሉ!! የመልካም ሰሪንም ስራ ያበላሻሉ!!። አላህ ይጠብቀንና በሙስሊሞችም መካከል ጥላቻን ያስወርሳሉ።”
[በህር አድ-ዱሙዕ ሊብን አል-ጀውዚ 133]
✍🏻ኢብን ሽፋ
#join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

Ibn Awol

01 Oct, 14:49


ደእዋ ላይ ስሜትን መቀላቀል


በዬትኛዉም የደዕዋ እንቅስቃሴያችን ላይ ስሜታችንን መቀላቀል ዬለብንም።
ደዕዋዉ ላይ ምትንቀሳቀሰዉ ለአላህ ብለህ እስከሆነ ድረስ፣ለአላህ የገባሀዉን ቃል ለሰዎች ወይም ለስሜትህ ብለህ መተዉ ወይም ችላ ማለት ዬለብህም።

ደዕዋዉ ላይ ኣንተ ማትወደዉ ወይም ማይመችህ ሰዉ መኖሩ በአንተ በደዕዋህ እንቅስቃሴ ላይ ምንም ተፅዕኖ ሊያሳድርብህ አይገባም(ችግሩ የመንሃጅ እስካልሆነ ድረስ)።

ትክክለኛ ሰለፊይ ማለት ስሜቱ ወደደዉም አልወደደዉም ለደዕዋዉ የሚጠቅም እስከሆነ ድረስ ሸሪዓን ካልኻለፈ ስሜቱን አሸንፎ ሚታገል ማለት ነዉ።

የሆነ ሰዉ የሆነ ድርጊቱ ወይም የሆነ ሰዉ የሆነ ንግግሩ..... አልተመቸኝም ተብሎ ደዕዋን የሚጎዳ ተግባር አይፈፀምም።

ሁላችንም በሁሉም ቦታ የምንገኝ የሰለፊያ ወንድሞች ችግሮች ሲከሰቱ ስሜታችንን በመተዉ፣በመነጋገር፣ቅድሚያ ሚሰጠዉን ቅድሚያ በመስጠት፣እርስ በእርስ በመደማመጥ፣ጥቅምና ጉዳትን በማመዛዘን፣የዲንና የዱኒያ ነገሮችን በመለየት፣በወንድማችን ሀቅ እንኳን ቢኖረን በመሸነፉ ኣንድነታችንን ልናጠናክር ይገባል።
ሁሌ እኔ ያልኩት ካልሆነ ማለት ዬለብንም፣ኣንድ ኣንዴ ብንበደል ራሱ ለአላህ ብለን መተዉ ትልቅነት ነዉ።

ሸይጣንን በዐቂዳ፣በመንሃጅ አሸንፈነዉ በትናንሽ ነገሮች ሊያሸንፈን አይገባም።

አላህ ስሜታችንን ከመከተል ይጠብቀን


t.me/ibnawolllll
t.me/ibnawolllll

Ibn Awol

29 Sep, 17:41


አልሀምዱሊላህ



የዛሬዉ ፕሮግራማችን በሰላም ተጠናቆዋል።

ጥሪያችንን አክብራቹህ የመጣቹህ ባጠቃላይ አላህ ያክብራቹህ።
በሀጃ ምክኒያት የቀራቹህ ደሞ አላህ ሀጃቹሁን ያዉጣላቹህ።


ፕሮግራማችን ከጠበቅነዉ በላይ ያማረ ነበር።እንደዚህ አይነት ፕሮግራሞች ሊበረታቱ ይገባል።
ሁላችንም ዉስጣችን ንፁህ ከሆነ ደዕወቱ ሰለፊያ የበላይ ከመሆን ማንም አያግዳትም።

t.me/ibnawolllll
t.me/ibnawolllll

Ibn Awol

29 Sep, 05:24


👇👇👇ቀጠሮዋችን በሳዐቱ እንደተጠበቀ ነው።እርስ በእርስ አስታዉሱ።

ማስታወቂያ ለአዳማ ሰለፊዮች በሙሉ



እሁድ ቀን 19/1/2017 በአዳማ በሁሉም መድረሳ የምትገኙ ሰለፊዮች አንገብጋቢ ለሆነ ጉዳይ ስለፈለግናቹህ ሁለቹሁም በቀጥርናቹህ ሰዓት እንድትገኙ።

አስር ቀበሌም ያላቹህ፣ቦሌም ያላቹህ፣ግንብ መናሀሪያ አካባቢም ያላቹህ፣ቁዱስ ቁርኣን አካባቢም ያላቹህ፣ኢብን ተይሚያ መድረሳም ያላቹህ፣ሌሎችም ቦታዎች ላይ ያላቹህ ሁላቹሁም ተጠርታቹሃል።
ሴቶችንም ይጨምራል።


የፈለግናቹህ ለአንገብጋቢ ጉዳይ ስለሆነ በፍፁም እንዳትቀሩ።

ቀጠሮን ማክበር የሙእሚን ባህሪ ነው፣ቀጠሮን ማፍረስ የንፍቅና ባህሪ ነው።

ቦታው ኢብን ተይሚያ መድረሳ

ሰዓት 8 ሰዓት

አዳማና አካባቢዋ አህለሱና ወልጀማዕ ማህበር


t.me/ibnawolllll

Ibn Awol

26 Sep, 13:29


👇👇👇ቀጠሮዋችን በሳዐቱ እንደተጠበቀ ነው።እርስ በእርስ አስታዉሱ።

ማስታወቂያ ለአዳማ ሰለፊዮች በሙሉ



እሁድ ቀን 19/1/2017 በአዳማ በሁሉም መድረሳ የምትገኙ ሰለፊዮች አንገብጋቢ ለሆነ ጉዳይ ስለፈለግናቹህ ሁለቹሁም በቀጥርናቹህ ሰዓት እንድትገኙ።

አስር ቀበሌም ያላቹህ፣ቦሌም ያላቹህ፣ግንብ መናሀሪያ አካባቢም ያላቹህ፣ቁዱስ ቁርኣን አካባቢም ያላቹህ፣ኢብን ተይሚያ መድረሳም ያላቹህ፣ሌሎችም ቦታዎች ላይ ያላቹህ ሁላቹሁም ተጠርታቹሃል።
ሴቶችንም ይጨምራል።


የፈለግናቹህ ለአንገብጋቢ ጉዳይ ስለሆነ በፍፁም እንዳትቀሩ።

ቀጠሮን ማክበር የሙእሚን ባህሪ ነው፣ቀጠሮን ማፍረስ የንፍቅና ባህሪ ነው።

ቦታው ኢብን ተይሚያ መድረሳ

ሰዓት 8 ሰዓት

አዳማና አካባቢዋ አህለሱና ወልጀማዕ ማህበር


t.me/ibnawolllll

Ibn Awol

26 Sep, 04:51


📌አላህ ከአንተ ይቅር እንዲልህ፣ ይቅር ባይ ሁን
👉አቡሁረይራ - ረዲዬሏሁ ዓንሁ - ከረሱል - ዓለይሂ ሶላቱ ወሰላም - ሰምቶ የሚከተለውን ሐዲስ አስተላለፈ:-
"كان تاجر يداين الناس ، فإذا رأى معسرا قال لفتيانه : تجاوزوا عنه لعل الله أن يتجاوز عنا ، فتجاوز الله عنه "
"ሰዎችን የሚያበድር አንድ ነጋዴ ነበር ፤ (እዳውን ከመክፈል) የተጨናነቀ ሰው ሲመለከት : 'ከእርሱ ይቅር በሉ - አላህ ከእኛ ይቅር ሊለን ተስፋ እናደርጋለንና' በማለት ለአገልጋዩ ይነግረዋል። አላህም ከእርሱ ይቅር አለው"

ሐዲሱን ቡኻሪ (2078)

https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة

Ibn Awol

23 Sep, 18:04


በነቢዩ ሰም ለሆዳቸው ነው ሚጨነቁት



መዉሊድ አክባሪዎች መዉሊድ ነቢዩ በተወለዱበት ቀን እናከብራል ቢሉም ግን አብዛኛው ቦታ ላይ በፈረቃ ነው ሚያከብሩት።

አዳማ ቁባ ሚባለው መስጊድ ላይ የተለያዩ የመዉሊድ ዝግጅቶች ቢደረጉም መዉሊድ የተከበረው ግን በዚህኛው እሁድ ነበር።ለምን እስካሁን ቆዩ ስል የተሰጠኝ መልስ ሁሌ በሬ ሲገዛ ሁለትና ከዛ በላይ ለብቻው ሚገዛው ሰዉዬ ታሞ ነበር ኣሉኝ፣እናም እስኪሻለው ጠብቀዉት ነው ኣሉ።

አሁን እነዚህ ሰዎች የነቢዩን መዉሊድ አከበሩ ነው ሚባለው ወይስ ሰዉዬው ከህመሙ የዳነበትን ቀን?።
እንደዚህ አይነት ነገሮች ብዙ ቦታዎች ላይ ይደረጋሉ፣እናም ኢሄ ድርጊት ነቢዩን የመዉደድ ሳይሆን ሆድን ከነቢዩ አሰበልጦ የመዉደድ ነው።



t.me/ibnawolllll
t.me/ibnawolllll

Ibn Awol

23 Sep, 17:54


👉 የኸድርና የነብዩላሂ ሙሳ ታሪክ

ክፍል ሶስት

ኸድርም " ብትከተለኝም ለአንተ ከርሱ ማውሳትን እስከምጀምርልህ ድረስ ምንም ነገር አትጠይቀኝ " አለው ። በባሕር ዳርቻም ላይ መጓዝ ጀመሩ ። መርከብ ባጠገባቸው አለፈች ። እንዲያሳፍራቸው ሲጠይቁ ሰዎቹ ኸድር መሆናቸውን ስላወቁ ካለምንም ክፍያ አሳፈሯቸው ። በመርከቧ እየተጓዙ ሳሉ ኸድር የመርከቧን አንድ ክፍል በመጥረቢያ ሲፈልጡ ሙሳ ተመልክተው " ባለቤቶቿን ልታሰምጥ ቀደድካትን ትልቅ ነገር በርግጥ ሰራህ " አሉት ። ኸድርም አንተ ከእኔ ጋር ትእግስትን ፈፅሞ አትችልም አላልኩምን ? አለው " ። ሙሳም " በረሳሁት ነገር አትያዘኝ ከነገሬም ችግርን አታሸክመኝ " አሉት ።
የአላህ መልእክተኛም – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም – ይህ የሙሳ የመጀመሪያው መርሳት ነው " አሉ ።
ሙሳና ኸድር በመርከቧ እየተጓዙ ሳለ አንዲት ወፍ በመርከቧ ጠረፍ ላይ አረፈችና በምቃሯ ከባሕሩ ጠጣች ። ይህን በተመለከቱ ጊዜ ኸድር እንዲህ አለ ። የኔ እውቀትና ያንተ እውቀት ከአላህ እውቀት ጋር ሲነፃፀር ይህች ወፍ ከባሕሩ ውሃ ብትጠጣ እንደማትቀንሰው አይነት ነው " አላቸው ። ወደ ባሕር ዳርቻ ደርሰው ከመርከቧ ወርደው በየብስ ላይ ጉዟቸውን ቀጠሉ ።
ሁለቱም ( ኸድርና ሙሳ ) እየተጓዙ ሳለ ኸድር ከህፃናት ጋር አብሮ የሚጫወት አንድ ህፃን ተመለከተና ጭንቅላቱን ይዞ ከሰውነቱ በእጁ ስቦ በመንቀል ገደለው ። ሙሳም ይህን ተመልክተው " ያለ ነፍስ ( መግደል) ንፁህን ነፍስ ገደልክን ? በርግጥ መጥፎን ነገር ሰራህ " አሉት ። ኸድርም " አንተ ከኔ ጋር ትግስትን ፈፅሞ አትችልም አላልኩህምን? አላቸው ። ሙሳም " ከርሷ ( ከአሁኒቱ ጊዜ ) በኋላ ከምንም ነገር ብጠይቅህ ከኔ የይቅርታን መጨረሻ በርግጥ ደርሰሃል " አሉት ።
ሄዱም ወደ አንዲት ከተማ በመጡ ጊዜ ነዋሪዎቿን ምግብ ጠየቁ ከማስተናገዳቸውም እንቢ አሉ ። በርሷም ውስጥ ለመውደቅ የተቃረበን ግድግዳ አገኙ ። ( ኸድርም) በእጁ አቆመው ። ሙሳም " እነዚህ ሰዎች ወደነርሱ መጥተን ሳለ ምግብ አላበሉንም በእንግድነትም አላስተናገዱንም በሻህ ኖሮ በርሱ ላይ ዋጋን በተቀበልክ ነበር " አለው ። ኸድርም " ይህ በኔና ባንት መለያያ ነው ፣ በርሱ ላይ መታገስን ያልቻልክበትን ፍች እነግርሀለሁ " አለው ።
መርከቢቱም በባሕር ለሚሰሩ ምስኪኖች ነበረች ፣ ከኋላቸውም መርከብን ሁሉ በቅሚያ የሚዝ ንጉስ ነበርና ( እንዳይቀማቸው) ላነውራት ፈቀድኩ ። ወጣቱ ልጅማ ወላጆቹ ምእመናን ነበሩ ( ቢያድግ) ትእቢትና ክህደትንም የሚያያስገድዳቸው መሆኑን ፈራን ፣ ጌታቸውም በንፁህነት ከርሱ በላጭን ከእዝነትም ከርሱ በጣም ቀራቢን ልጅ ሊለውጥላቸው ፈለግን ። ግድግዳውማ በከተማይቱ ውስጥ የነበሩ የሁለት የቲሞች ወጣቶች ነበር ። በስሩም ለእነርሱ የሆነ ( የተቀበረ) ድልብ ነበር ። አባታቸውም መልካም ሰው ነበር ፣ ጌታህም ለአካለ መጠን እንዲደርሱና ከጌታህ ችሮታ ድልባቸውን እንዲያወጡ ፈቀደ ።
በፍቃዴም አልሰራሁትም ይህ በርሱ ላይ መታገስን ያልቻልከው ነገር ፍቺ ነው " አሉት ። የአላህ መልእክተኛም እንዲህ አሉ: – አላህ የሁለቱን ታሪክ እስኪፈፅምልን ድረስ ሙሳ ታግሰው በነበር ወደድን " አሉ ።

ቡኻሪይ ዘግበውታል ።

ተፈፀመ ።

ክፍል አንድን ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/bahruteka/5370

ክፍል ሁለትን ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/bahruteka/5375

https://t.me/bahruteka

Ibn Awol

23 Sep, 17:54


👉 የኸድርና የነብዩላሂ ሙሳ ታሪክ

ክፍል አንድ

ቁርኣን ላይ ትኩረት ከተሰጣቸው አስተማሪ ታሪኮች ውስጥ የነብዩላሂ ሙሳና የኸድር ታሪክ ነው ። በዚህ ታሪክ ውስጥ ትልቁ አስተማሪ ነገር ማንም ቢሆን በእውቀት ጥግ ደርሻለሁ ማለት እንደሌለበት አላህ ከባሮቹ ውስጥ ለሚሻው ሰው ጥበቡ ባስፈረደው የእውቀት አይነት ለየት እንደሚያደርገው ።
በዚህ ታሪክ ውስጥ ነብዩላሂ ሙሳ ረሱልና ከዛም ከፍ ባለ ደረጃ ዑሉል ዐዝም ከሚባሉት ውስጥ ናቸው ። ኸድር ደግሞ በቀደምት የኢስላም ሊቃውንቶችና እስካለንበት ዘመን ባሉ ተከታይ የኢስላም ሙሁራኖች እንደተረጋገጠው ነብይ መሆናቸው ነው ። በመሆኑም ኸድር ማለት ከነብያቶች ውስጥ አንዱ ናቸው ። ይህ ማለት በደረጃ ነብዩላሂ ሙሳ ይበልጣሉ ማለት ነው ። ምክንያቱም የረሱልነት ደረጃ ከነብይነት ደረጃ የሚበልጥ መሆኑ የተረጋገጠ ስለሆነ ። ነብዩላሂ ሙሳ ደግሞ ከረሱልም በላይ አምስቱ ዑሉል ዐዝም የተባሉት ውስጥ ናቸው ።
ነገር ግን የጥመት አንጃ የሆኑት ሱፍዮችና ሺዓዎች ይህን አስተምሮ በማስተባበል ኸድር ወልይ ነው አሉ ። እዚህ ጋር ቢቆሙ አንድ ነገር ነበር ነገር ግን ከዚህም አልፈው ሄዱ ። ወልይ ከነብይም ከረሱልም ከዑሉል ዐዝም ይበልጣል አሉ ። ለዚህህ ስህተታቸው መነሻው ደግሞ አላህ ነብዩላሂ ሙሳን ኸድር ጋር ሄደህ ተማር ማለቱ ነው ። ይህ ማለት ኸድር አላህ ዘንድ በደረጃ ከሙሳ ከፍ ያለ ስለሆነ ነው ልዩ እውቀት ሰጥቶት ከሱ ተማር ያለው አሉ ። በመሆኑም የኸድር እውቀት የውስጥ እውቀት ( ዒልመል ባጢን) ነው የሙሳ እውቀት ደግሞ የውጭ እውቀት ( ዒልመ ዛሂር ) ነው የሚል ፍልስፍና ውስጥ ገቡ ።
ከዚህ በመነሳት በእነርሱ እምነት የነብያት ተከታዮች የውጪውን እውቀት ነው የሚያውቁት የወልይ ተከታዮች ደግሞ የውስጡን ነው የሚያውቁት በመሆኑም የነብያት ተከታዮች የሸሪዓን ሚስጥር አያውቁም ላዩን ነው የሚከተሉት እኛ ደግሞ የሸሪዓን የውስጥ ሚስጥር ስለምናውቅ የውስጡን ነው ምንከተለው አሉ ። በዚህም ነብዩን ጨምሮ ሶሓቦችንና አጠቃላይ ቁርኣንና ሐዲስን የሚከተሉ የኢስላም ሊቃውንቶችን አላዋቂ መሀይማን አደረጉ ።
ይህ እምነታቸው ነው ዛሬ ላይ እየታየ ያለውን የኩፍርና የሽርክ ተግባር እንዲፈፅሙ ያደረጋቸው ። ምነው ሲባሉ እናንተ ስለማታውቁ ነው ኩፍር የሚመስላችሁ ነገር ግን የሙታን መንፈስ ማምለክ ፣ በቀብር ላይ ጠዋፍ ማድረግ ፣ ወደ እነርሱ የተለያዩ ቁሩባን በማቅረብ እነርሱን መለማመን ፣ እርዱኝ ፣ አክብሩኝ ፣ ድረሱልኝ ፣ አሽሩኝ … ወዘተ ማለት ተውሒድ ነው አሉ ።
ይህ በተሳሳተ መነሻ ላይ የተመሰረተ የተሳሳተ እምነት ነው ። የዚህ ማሳያው እንደሚከተለው ነው : –
1ኛ – ኸድር ነብይ እንጂ ወልይ አይደለም ።
የነብይነትና የወልይነት ደረጃ አይገናኝም ። የነብይነት ደረጃ በጣም የላቀ ነው ።
2ኛ – አንድ ሰው ሄደህ ከእገሌ ተማር መባሉ ያ
አካል ከሱ መብለጡን አያሳይም ። ይበልጣል ቢባልም በዛ በሚያስተምረው ጉዳይ ነው ሊሆን የሚችለው ። ይህን ወደ ታሪኩ ስንገባ በግልፅ የምናየው ይሆናል ።
3ኛ – የነብዩላሂ ኸድር እውቀት ለራሱ የተሰጠው
እንጂ ሸሪዓ ሆኖ ሊሰራበት አይደለም ። ሸሪዓ ቢሆን እንኳን ለነብዩ ተከታዮች ከዛ በፊት የነበሩ ነብያቶች ሸሪዓ ከቁርኣንና ሐዲስ ወይም ከነብዩ ሸሪዓ ጋር ከተጋጨ አይሰራበትም ሸሪዓም አይሆንም ።
ሱፍዮችና አሕባሾች እያጨማለቁት ላለው ኩፍርና ሽርክ የነብዩላሂ ሙሳና የኸድር ታሪክ በፍፁም መረጃ ሊሆን አይችልም ። ምክንያቱም በባጢል ላይ የተመሰረተ ነገር ባጢል ነውና ።
አላህ ለነብዩላሂ ሙሳ ከኸድር እንዲማሩ የፈለገው እሱ ዘንድ ካለው እውቀት ለሳቸውም ይሁን ለኸድር የተሰጠው በጣም ኢምንት መሆኑን ለማሳየት ነው ። ለዚህ ማሳያ በታሪኩ ላይ ከባህር ላይ የምትጠጣዋን ወፍ ምሳሌ እንዳደረገው ሁሉ ።
የነብዩን ሸሪዓ በፍልስፍና ውድቅ ያደረጉና ኩፍርና ሽርክ ያነገሱ ሱፍዮችና አሕባሾች ታሪኩ በእነርሱ ላይ እንጂ ለእነርሱ መረጃ አይሆናቸውምና በደንብ እንወቀው ። አላህ ካለ ሠዒድ ኢብኑ ጁበይር ከዐብዱላሂ ኢብኑ ዓባስ ዐብዱላሂ ከኡበይ ኢብኑ ካዕብ ይዘው ባስተላለፉትና ኢማሙል ቡኻሪይ በዘገቡት ሐዲስ ላይ እንደተዘገበው ሙሉ ታሪኩን የምናይ ይሆናል ። በሱረቱል ካህፍ ላይ ይህ ታሪክ ሰፊ ሽፋን የተሰጠው ሲሆን በአቀማመጥ ሐዲሱ ላይ የመጣው ይበልጥ ቀለል ስለሚል የሐዲሱን እናያለን ።

አላህ ካለ ይቀጥላል ።

http://t.me/bahruteka

Ibn Awol

23 Sep, 17:54


👉 የኸድርና የነብዩላሂ ሙሳ ታሪክ

ክፍል ሁለት

ሰዒድ ኢብኑ ጁበይር እንዳስተላለፉት " ለኢብኑ ዓባስ (ረ · ዐ) " ነውፍ አል ቢካሊይ የተባለው ሰው ሙሳ የኸድር ባለንጀራ ናቸው እንጂ ከኢስራኤላዊያን ልጆች መካከል አይደሉም እያለ ያወራል " አልኳቸው ኢብኑ ዓባስም የአላህ ጠላት ዋሽቷል ኡበይ ኢብኑ ካዕብ እንደነገረኝ የአላህ መልእክተኛ – ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም – እንዲህ ሲሉ ሰምቷል ። " ሙሳ በእስራኤላዊያን ልጆች ፊት ንግግር ሊያደርግ ተነሳ " የተኛው ሰው ነው አዋቂ "? ተብሎ ተጠየቀ ። እሱም " እኔ ነኝ " አላቸው ። አላህም እውቀትን ሁሉ ወደርሱ ስላላስጠጉ ሙሳን ገሰፃቸው ። አላህም መለኮታዊ ራዕይ ወደ ሙሳ እንዲህ ሲል ላከ ፣ " በሁለት ባሕሮች መተላለፊያ ላይ ካንተ በላይ አዋቂ የሆነ ባሪያችን አለ ። " ሙሳም " ጌታዬ ሆይ እንዴት ልገናኘው እችላለሁ "? ሲል ጠየቀ ። እንዲህም ተባለ አሳ ውሰድና ቅርጫት ውስጥ አድርገህ መንገድህን ቀጥል ። " አሳውን ስታጣ እሱን ታገኘዋለህ "። ሙሳም አሳ ቅርጫት ውስጥ ካደረጉ በኋላ ዩሹዕ ኢብኑ ኑን ከተባለ ወጣት ጋር አብረው ጉዘዟቸውን ቀጠሉ ። አንድ ቋጥኝ አጠገብ ደርሰው ደገፍ ብለው ተኙ ። አሳው ቅርጫት ውስጥ እያለ ተንቀሳቀሰና ከቅርጫት ውስጥ በመውጣት ባሕር ውስጥ ገባ በዚያውም በባሕሩ ውስጥ ቀዳዳ አድርጎ ያዘ ። አላህም የባሕሩን መፍሰስ በአሳው ሰበብ አቆመው ። !!!!! እንደ ቦይም አድርጎ ቀጥ ባለው ውሃ አሳው ጉዞዉን ቀጠለ ።
ከእንቅልፋቸው ሲነቁ ባለንጀራቸው ስለ አሳው የሚነግራቸውን ነገር ረሳውና የተቀሩትን ለሊቶችና ቀናት ተጓዙ ። በሚቀጥለው ቀን ጠዋት ሙሳ ይህን ወጣት " ምሳችንን ስጠን ከዚህ ጉዟችን በርግጥ ድካምን አግኝቶናልና አሉት ። ወጣቱም: – አየህን ወደ ቋጥኟ በተጠጋን ጊዜ እኔ አሳውን ረሳሁ ፣ ማሳታወሱንም ሰይጣን እንጂ ሌላ አላስረሳኝም ። በባሕሩም ውስጥ መንገዱን አስደናቂ አድርጎ ያዘ " አሉ ። ለአሳው መንገድ ነበር ። ለሙሳና ለወጣቱም አስደናቂ ነገር ነበር ። ሙሳም ይህ እንፈልገው የነበርነው ነው አለው ፣ በፈለጎቻቸውም ላይ እየተከተሉ ተመለሱ " ። ሁለቱም ወደ ኋላ ተመለሱ ። ወደ ቋጥኙ እስኪደርሱም ተጓዙ ።
እንሆ አንድ በጨርቅ የተሸፋፈነ ሰውም አገኙ ። ሙሳም ለሰውየው ሰላምታ ሰጡት ። ኸድርም ለሙሳ በጣም በመገረም ሁኔታ " በምድራችሁ ላይ እንዲህ አይነት ሰላም አለ ወይ ብሎ ጠየቃቸው ። ሙሳም " እኔ ሙሳ ነኝ አሏቸው ። " ሙሳ የእስራኤላዊያን ልጆች ? " ሲል አሁንም ኸድር ሙሳን በመገረም ጠየቁ ። ሙሳም አዎ ነኝ ። ከተማርከው ቀጥተኛን ( እውቀት) ታስተምረኝ ዘንድ ወዳንተ መጥቻለሁ " አሉት ። ኸድርም አንተ ከኔ ጋር መታገስን በጭራሽ አትችልም ። ሙሳ ሆይ ፣ እኔ አንተ የማታውቀው ነገር ግን አላህ ያሳወቀኝ እውቀት አለኝ ። አንተ ደግሞ አላህ ያሳወቀህ ነገር ግን እኔ የማላውቀው እውቀት አለህ " አላቸው ። ሙሳም አላህ የሻ እንደሆነ ታጋሽና ላንተ ታዛዥ ሆኜ ታገኘኛለህ አሉት ። ኸድርም ብትከተለኝ ለአንተ ከሱ ማውሳትን እስከምጀምርልህ ድረስ ምንም ነገር አትጠይቀኝ አላቸው ። በባሕር ዳርቻም ላይ መጓዝ ጀመሩ ።

አላህ ካለ ይቀጥላል ።

https://t.me/bahruteka

Ibn Awol

17 Sep, 07:13


📌قال العلامة ربيع بن هادي المدخلي حفظه الله

- اليوم يأتي دعاة السوء ودعاة الفتن يضربون عن هذا التوحيد بأدلته، التوحيد يفرِّق في نظرهم، يقولون بلسان حالهم أو مقالهم إذا نادينا إلى التوحيد من يأتي معنا؟ نحن نريد أن نصل إلى الكراسي بسرعة، فإذا قلنا التوحيد التوحيد ذهب الناس عنا، ما نصل نريد أن نجمع الناس الرافضي أخونا، النصراني أخونا، الخرافي القبوري أخونا كلهم إخواننا حتى نصل بسرعة، طيب وصلوا بسرعة ماذا فعلوا؟ وحدة أديان، ومؤتمر وحدة الأديان وغيرهت هذا يكفيكم، أنه لما وصل جماعة من أهل هذه الدعوات إلى الكراسي أداروا ظهورهم لما كانوا يمنّون به الناس، لا يعطونك شريعة، ولا عقيدة...

[المجموع ١ /٧٦-٧٧].

t.me/ibnawolllll
t.me/ibnawolllll

Ibn Awol

16 Sep, 05:04


ልዩ ኮርስ

                  ክፍል ②

ርእስ:-
الصدق منجاة
እውነት መዳኛ ነው!!

🎙በሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ)

በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል

የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://t.me/DarASSunnah1444
https://t.me/DarASSunnah1444

2,320

subscribers

155

photos

147

videos