🔤ሀገርከ ደጋ ወስምከ ወርቄ🔤
ከልክ የተረፈውን ባለቅኔ አለቃ ዘመደ ብርሃንን ጎጃም ደጋማ ክፍል ይኖሩ የነበሩ አንድ ቅኔ የማያውቁና ቄስ ወርቁ የተባሉ ካህን በደንገት ያገኙትና ለሰው ሁሉ ቅኔ ስትዘርፍ ለእኔም ምናለ ብትዘርፍልኝ ይሉታል።ዘመደ ብርሃንም በዚያው ቅጽበት
🔻ሀገርከ ደጋ ወስምከ ወርቄ፣
በጊዜ ማኅሌት በግዕ ወበጊዜ መብልዕ አንቄ። ብሎ ዘረፈባቸው።
🔵ትርጉም:-ሀገርህ ደጋ ፣ስምህ ወርቄ የምትባል ቄስ በማኅሌት ጊዜ በድን ቃል የማትተነፍስ፣ዜማ የማታውቅ፣በመሐራ ጊዜ ደግሞ ጭልፊት ፣አሞራ ነህ ብሎ በጓደኞቻቸው ፣ካህናት መካከል ተቀኘባቸው ይባላል።
😄የቅኔውን ምሥጢር ስለማይሰሙትና ያመሰገናቸው ስለመሰላቸው በጣም ደስ ብሏቸው አንድ ጠገራ ብር ሸለሙት።
ብሂል ቅኔ እንማር🤓