Gedeo Tube🇪🇹 @gedeotube Channel on Telegram

Gedeo Tube🇪🇹

@gedeotube


መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ!

@Gedeotube

Gedeo Tube (Amharic)

የGedeo Tube ቤተሰብ የሚገመገሙ ሥራዎች በሌሎች ለማሳደግ ሼርን በአገልግሎት ያድርገዋል። ይህ ሼር በታላቅ ቻናላችን ከሚገኙ ለሌሎች ወቅታዊ መረጃዎች እና ቴዎድሮች ላይ ስለ ሼር እና ሌሎች አገለግሎት ለመረጃት እና ስለ ሼር ደግመት በቆዳን እና ወቅታዊ ሚስጥሮችን አስከተልን። Gedeo Tube በታክስ መሠረት አጠቃላይ መረጃዎችን ይመልከቱ።

Gedeo Tube🇪🇹

11 Nov, 12:58


ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጌዴኦ ዞን የቡና ምርት አሰባሰብና ዝግጅት ስራን የመስክ ምልከታ በማድረግ ላይ ይገኛሉ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጌዴኦ ዞን በዲላ ዙሪያ፣ ወናጎ እና ይርጋጨፌ ወረዳ ተዘዋውረው የቡና ምርት አሰባሰብና ዝግጅት ያለበትን ደረጃ ምልከታ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

በዞኑ የ2017 ምርት ዘመን የቡና አሰባሰብና ዝግጅት በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን በተያዘው ምርት ዘመን 34 ሺ ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝም ተጠቁሟል።

Gedeo Tube🇪🇹

28 Oct, 06:19


በጌዴኦ ዞን ጮርሶ ወረዳ ቂሻ ቀበሌ የአስፓልት ቱቦ በመናዱ ምክንያት በንብረት ላይ ጉዳት ያስከተለው ስሆን የአካባቢው ነዋሪዎችንም አፈናቅሏል

ጉዳቱ የደረሰው ከአድስ አበባ ወደ ኬኒያ በሚወስደው ዋና ሀገር አቋራጭ መንገድ ላይ ስሆን በጌዴኦ ዞን ጮርሶ ወረዳ ቂሻ ተብለው በሚጠራበት አከባቢ ነው።

ከዚህ ቀደም የምንጭ ውሀዎች ከአስፓልቱ ስር በተሰራው ቱቦ ውስጥ ያልፍ የነበረው ሲሆን አሁን በአስፓልት ናዳ ምክንያት የውሀ መተላለፊያ ቱቦዎች ተዘግተው ውሀው መተላለፊያ መንገድ በማጣቱ በአቅራቢያው በሚገኙ ማበረሰብ ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል።

በጉዳቱም 7 አባወራና 45 የቤተሰቡ አባላት ከአከባቢ ተፈናቅለው ቀበሌ ተጠልለው እንደሚኖሩ ተገልፃል።

Gedeo Tube🇪🇹

26 Oct, 12:33


የዲላ መካከለኛ አግሮ ኢንዲስትሪ ፓርክ ለመጀመሪያ ጊዜ 22 ሺህ ሊትር የአቮካዶ ዘይት ለውጭ ገበያ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የዲላ መካከለኛ አግሮ ኢንዲስትሪ ፓርክ ለመጀመሪያ ጊዜ ያመረተውን 22 ሺህ ሊትር የአቮካዶ ዘይት ምርት ለውጭ ገበያ ማቅረቡን ገለጸ። በኢንዱስትሪ ፓርኩ የሲይዝ አግሮ ኢንዱስትሪ ማህበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ጌቱ ፥ በአንድ ፈረቃ የተመረተ 22 ሺህ ሊትር የአቮካዶ ዘይት ለመጀመሪያ ጊዜ ለውጭ ገበያ መቅረቡን ገልጸዋል፡፡ በቀጣይ…

Gedeo Tube🇪🇹

08 Oct, 15:57


#UpdateNews
ትምህርት ሚኒስቴር የ2017 የሬሚዲያል መግቢያ ውጤትን ይፋ አደረገ፡፡

ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ውሳኔን ፋ አድርጓል፡፡

የሬሚዲያል ፕሮግራም በ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡትን አነስተኛ የተማሪዎች ቁጥር ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ ውጤት መቀነስ በትምህርት ዘርፉ እና በአጠቃላይ በሀገር ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ማህበራዊ፣ ስነ ልቦናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እንዲሁም ተዛማጅ ችግሮችን ከግምት ውስጥ በማስገባት የተዘረጋ አሰራር መሆኑንም ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

በዚህ መሰረት የ2017 የትምህርት ዘመን የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን በተፈጥሮ ሳይንስና ማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ያላቸዉን የቅበላ አቅምን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ተጠቃሚዎች በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የሬሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 31% ከመቶ እና ከዚያ የተቆረጠ መሆኑን አስታውቋል።

የተየፈጥሮ እና የማሀበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ600 የተፈተኑት 204 እና ከዛ በላይ ማምጣት እንዲሁም ለሴት ተማሪዎች ደግሞ 600 እና ከዛ በላይ 192 ማምጣት ይጠበቅባቸዋል ተብሏል፡፡

የታዳጊ ክልልና አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮና ማሀበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ600 የተፈተኑ ከሆነ 192 እና ከዛ በላይ ማምጣት ሲጠበቅባቸው ሴቶች ደግሞ ከ600ው 186 እና ከዛ በላይ ማምጣት አለባቸው ተብሏል፡፡

ማሀበራዊ ሳይንስ ዓይነስውራን ወንድ ተማሪዎች ከ500ው 160 እና ከዛ በላይ፣ እንዲሁም ሴቶች ደግሞ 155 እና ከዛ በላይ ሆኖ ተቆርጧል፡፡

በፕሪፓራቶሪ ፕሮግራም የተየፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ700ው 238 እና ከዛ በላይ በተመሳሳይ በሴቶች ደግሞ 224 እና ከዛ በላይ ማምጣት አለባቸው ተብሏል፡፡

Gedeo Tube🇪🇹

22 Sep, 05:30


በቤሩት እስራኤል በፈጸመችው የአየር ጥቃት የሟቾች ቁጥር 31 ደረሰ

በሊባኖስ ቤሩት ደቡባዊ ክፍል እስራኤል ባደረሰችው የአየር ጥቃት የሟቾች ቁጥር 31 ደርሷል።

የሊባኖስ ጤና ሚኒስትር ፊራስ አቢያድ እንደገለጹት ከሟቾች ውስጥ ሦስት ህጻናትና ሰባት ሴቶች ይገኙበታል፡፡ የእስራኤል የአየር ጥቃት በሊባኖስ መዲና ሁለት ሕንጻዎችን ያፈራረሰ ሲሆን 68 ሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሱንም ሚኒስትሩ አክለዋል።

የከተማዋ ትራንስፖርት ሚኒስትር አሊ ሃሜህ እስራኤል በመኖርያ ሕንጸዎች ላይ ያደረሰችው ፍንዳታ የጦር ወንጀል መሆኑን እና ቀጣናውን ወደለየለት ጦርነት የሚገፋ መሆኑን ተናግረዋል።

እስካሁን 23 ሰዎች በፍርስራሹ ውስጥ ጠፍተዋል ማለታቸውን አልጄዚራ ዘግቧል፡፡ የእስራኤል ጦር ግን ጥቃቱ የሄዝቦላህ ከፍተኛ አመሮችን ኢላማ ያደረገ ነበር ብሏል፡፡ ሄዝቦላህም ኢብራሂም አቂል እና አህመድ መሀመድ ዋሀቢ የተባሉ የጦር አዛዥ ኮማንደሮቹ በጥቃቱ እንደሞቱበት አረጋግጧል።

Gedeo Tube🇪🇹

10 Sep, 05:46


#ሙሉ በሙሉ ተማሪዎች አልፏል!

የዳውሮ ሂዶታ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሙሉ በሙሉ ተማሪዎችን አሳለፈ

የዳውሮ ሂዶታ ያስፈተናቸው ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ያለፉ ሲሆን ከፍተኛ 552 ሲሆን ዝቀተኛ 306 ሆኖ ተመዝግቧል። ከ500 በላይ ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር 4 ሲሆን ሌሎች አብዛኞች ከ400 በላይ ውጤት አስመዝግበዋል።

እንደስሙ የዳውሮ ተስፋ የሆነው የዳውሮ ሂዶታ ትምህርት ቤት ቢደገፍ ለዳውሮ ትልቅ ተስፋ ነው እንላለን። ይህ ውጤት እንዲመዘገብ አስተዋጽኦ ያደረጉ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ትልቅ ምስጋና ይገባችኋል።

የዳውሮ ልማት ማህበር በትምህርት ዘርፍ እየሰራ ያለው ተግባር ውጤት እያመጣ መሆኑን ከዳውሮ ትዩቢ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

Gedeo Tube🇪🇹

10 Sep, 05:43


ሊቃ ትምህርት ቤት ሙሉ በሙሉ ተማሪዎችን አሳልፏል

የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት በ2016 ዓ.ም ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ ያስፈተናቸዉን ሁሉንም ተማሪዎች አሳልፏል።

የትምህርት ቤቱ ከፍተኛዉ ዉጤት 544/600 ሲሆን ዝቅተኛዉ 361/600 ሆኖ ተመዝግቧል።

በታከለ ቶማ

Gedeo Tube🇪🇹

09 Sep, 11:56


የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በኦንላይን እና በወረቀት የተሰጠ ሲሆን፤ ፈተናውን በኦንላይን ከወሰዱት መካከል 26.6 በመቶ የሚሆኑት የማለፊያ ውጤት አምጥተዋል።

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

Gedeo Tube🇪🇹

09 Sep, 11:51


ከፍተኛ ውጤት ስንት ተመዘገበ ?

በሀገር ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበው በትግራይ ነው።

በትግራይ ፈተናው ከ700 ነው የተሰጠው።

ከቀላሚኖ 675 ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል። በወንድ ተማሪ። ኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ  ጊዜ ነው ተብሏል።

ሌላ በሀገር ደረጃ ከ600 ከተፈተኑት ውስጥ 575 ከፍተኛው ነው ከተፈጥሮ ሳይንስ፤ ሴት ናት። ከማህበራዊ ሳይንስ 538 ተመዝግቧል።

በተፈጥሮም በማህበራዊ ሳይንስም ትልቅ ውጤት የመጣው በሴቶች ነው።

Gedeo Tube🇪🇹

09 Sep, 11:43


የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናውን ከወሰዱት ተማሪዎች 5.4% ብቻ ማለፋቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል ። 🤯

ጠቅላላ ያለፉ ተማሪዎች ቁጥር 36,409 ተማሪዎች አልፈዋል።

Gedeo Tube🇪🇹

21 Aug, 14:16


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሔቨን እናት የመኖሪያ ቤት እና ሥራ አመቻቸ‼️

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የ7 ዓመት ልጇን ሔቨን በግፍ ተነጥቃ ባለፈው አንድ ዓመት ተገቢ ፍትህ ሳታገኝ ለቆየችው ሲስተር አበቅየለሽ የከተማ አስተዳደሩ አንድ የመንግስት የመኖሪያ ቤት እንዲሁም በሙያዋ እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ እንድትሰራ መመቻቸቱን ገልጸዋል።

የፍትህ ሂደቱን ለመከታተል ፣ ያለችበት ሁኔታ የተሻለ እንዲሆንላት እና ተጋላጭነቷን ለመቀነስ እንዲመች የከተማ አስተዳደሩ ድጋፉ ማድረጉንም ነው የገለጹት።

"የህፃን ሄቨን ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ በመሆኑ ድርጊቱ ተገቢውን ፍትህ ማግኘቱ የሌሎች ህፃናት ተጋላጭነትን ለመቀነስ አስተዋፅዖ ያለው ነው" ሲሉ ከንቲባዋ ተናግረዋል።

አክለውም፥ የዚህ አይነት ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት እንዳይፈፀም የማህበረሰቡ የአመለካከት ለውጥ እንዲመጣ እና ችግሩ የጋራ ጉዳይ በመሆኑ ሁላችንም ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባልም ብለዋል።

Gedeo Tube🇪🇹

13 Aug, 17:56


special news

#TPLF : የህወሓት ጉባኤ የተመለከተ አሁናዊ መረጃ፦

ደብረፅዮን እና ጢቂት ቡድኖች የሚሄዱት አካሄድ ከፍተኛ ተቃውሞ እየገጠመው ቢሆንም ለግል ስልጣን ጥማት ሲሉ የትግራይን ህዝብ ዳግም ወደአላስፈላጊ መንገድ እየወሰዱት ነው። መንግስትን እየተፈታተኑት ይገኛሉ። ይዋጣልን እያሉ ነው። ይህን የአጥፊውን ቡድን አካሄድ የተረዱ አካላት አቋማቸውን እያንፀባረቁ ነው።
1) በርካታ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በግልፅ ጉባኤው መካሄድ እንደሌለበት አቋማቸቅን አንፀባርቀዋል።

2) የድርጅቱ ማእከላዊ ቁጥጥር ኮሚሽን በይፋ ከሂደቱ እራሱን አግልሏል።

3) በርካታ ከፍተኛ፣ መካከለኛና ዝቅተኛ አመራር እራሳቸውን ከጉባኤው አግልለዋል።

4) ነባር እና ተተኪ የማእከላዊ ኮሚቴ ካውንስል በግልፅ ተቃውመዋል።

5) ደቡባዊ ዞን ሙሉ በሙሉ፣ ደቡብ ምስራቅ 12 ወረዳዎች ፣መቀሌ ከተማ አስተዳደር 5 ክፍለ ከተሞች እንዲሁም በሌሎች ዞኖች የሚገኙ አንዳንድ ወረዳዎችና ቀበሌዎች አልተወከሉም።

6) በጉባኤ ለመሳተፍ የተመረጡ የተለያዩ ከተሞችና ወረዳዎች ተወካዮች አንሳተፍም በማለት ቀርተዋል።

7) ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያልተገኘበትና እውቅና የለውም ብሎ መግለጫ አውጥቷል።

8) ህወሓት ህገመንግስቱና ህገመንግስታዊ ስርአቱ፣ የፌዴራል ተቋማት እንዲሁም የፕሪቶርያው ስምምነት እንዲያከብር በፌዴራል መንግስት ጥሪ አስተላልፏል። ይህ የማይሆን ከሆነ ተገዶ ወደ ማይፈልገው እርምጃ ሊገባ እንደሚችል ከዚህ ቀደምም አመላክቷል።

8) በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የስቪክ፣ የሃይማኖትና የቢዝነስ ተቋማት ያላቸውን ተቃውሞ በግልፅ አመላክተዋል።

9) በሀገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የትግራይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ትክክል አለመሆኑን እየገለፁ ነው።

10) በውጭ ሀገራት የሚንቀሳቀሱ ስቪክ ማህበራት ማሳሰቢያ ሰጥተዋል። በአጠቃላይ የተለያዩ የትግራይ ማህረሰብ አካላት ምክረ-ሐሳብ የሰጡበት ሲሆን በጎሳ እና በትውልድ አካባቢ የተቧደነው የነ ዶ/ር ደብረፅዮን ቡድን ይህን ሁሉ የትግራይ ህዝብ ተቃውሞ ችላ በማለት እንዋጣልን እያለ ነው። መላው የትግራይ ህዝብ ይህን ሊያውቅ ይገባል።

Gedeo Tube🇪🇹

31 Jul, 14:35


የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ብልጽግና ፓርት ቅ/ጽ/ቤት አመራሮች ጋር መግባቢያ ውይይት አደረጉ

#ዲላ #ሐምሌ /2016 ዓ/ም
የበጀት አመቱ መግቢያ የዝግጅት ምዕራፍ ተግባራት ላይ መግባቢያ መፍጠርን ዓላማ ያደረገ መድረክ በጌዴኦ ዞን በዲላ ከተማ ተካሂዷል።

አጠቃላይ መንግስታዊና የፓርቲ ሥራዎች በታቀደ መሠረት ግቡን እንዲመታ ፊት ሆነው የሚመሩት አመራሮች ሰፊ ሥራ መሥራት እንደሚጠበቅባቸው ነው በመድረኩ የተጠቆመው።

አቶ አበባየሁ ኢሳያስ የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ በመድረኩ እንደገለጹት በየሰክቴሩ የሚከናወኑት ዜጋ ተኮር የሆኑ ተግባራትን በተሳለጠ መልኩ ለማሳካት በዚህ መድረክ የተለየ አቋም የሚያዝ መሆኑን ተናግረዋል።

በግብርና የመኼር እርሻ መሬት ዝግጅት፣ በትምህርት የቀጣይ የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ቅበላ፣ በጤና ሁሉንም የዞኑን ቀበሌያት ከአይነምድር የጸዳ እንዲሆን የማድረግ ዘመቻ፣ በወጣቶችና ስፖርት የክረምት ወራት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲሁም ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የማጣራት ሥራዎች እና ሌሎች ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰሩ ሥራዎችን የፓርቲ አመራሮች አቅደው መደገፍ እንዳለባቸው ነው አቶ አበባየሁ ያብራሩት።

የአካባቢውን ሠላም ከማስጠበቁ ረገድ በሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች አመራሩ ነቅተው በማንቃት በቀን ቅኚትም ሆነ በምሽት ሮንድ ሥራዎች ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት መሆኑንም በመድረኩ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ውይይት ተደርጎበታል።

በ2016 ዓ/ም በጀት ዓመት ዞኑ በሁሉም ረገድ ግንባር ቀደም በመሆን አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡ በመድረኩ የተገለጸ ሲሆን አሁን የተጀመረው የሥራ ዘመንም የበለጠ ውጤታማ ተግባር ለማከናወን ከወድሁ በዝግጅት ምዕራፉ ስልት ቀይሶ መንቀሳቀስን ይጠይቃል ተብሏል።

መድረኩን የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና ዋና የመንግስት ተጠሪ ክቡር አቶ አበባየሁ ኢሳያስና የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊና ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ተስፋጽዮን ዳካ በጋራ በመሆን መርተውታል።