Subject: Precaution
The Ministry of Health has announced that there is an outbreak of an infectious disease that has similar symptoms with common cold, but much more serious, in our City. It is said that the disease becomes more severe, even fatal, when it comes to children. We are thus taking every humanly possible precautions to prevent our children from the plague. As is the case with most contagious diseases, one of the preventive measure is to isolate a child who shows the symptom(s). We would therefore like to kindly inform you, not only to keep your child at home if he/she shows signs such as cough and/or fever, but also to take him to hospital immediately. Please also try to understand us and not be offended with us if we refuse to let a child with such signs enter into, or stay at, the Center.
With kind regards
Fasika Childcare Center
የተወደዳችሁና የተከበራችሁ ወላጆች
ሰሞኑን የጤና ሚኒሰቴር በከተማችን ዉስጥ የጉነፋን የሚመስሉ ምልክቶች ያሉት፣ ነገር ግን በጣም አደገኛ የሆነ ተላላፊ በሽታ፣ የገባ መሆኑን አስታዉቆ አስፈላጊዉ ጥንቃቄ እነዲደረግ አሳስቧል፡፡ በሽታዉ በሕጻናት ላይ የበለጠ የከፋ ጉዳት ሊያስከትል እነደሚችልም ገልጽዋል፡፡ እኛም ልጆቻችንን ከመለከፍ ለመከላከል በሰዉ አቅም ሊደረግ የሚቻለዉን ሁሉ እያደረግን ነዉ፡፡ እነደማንኛዉም ተላላፊ በሽታ አንዱ የመከላከያ ዘዴ የበሽታዉ ምልክቶች (ሳልና ትኩሳት) የታየባቸዉን ልጆች እስኪሻላቸዉ ድረስ እቤታቸዉ እንዲቆዩ ማድረግ ነዉ፡፡ ስለዚህ ልጅችዎ እነዚህን ምልክቶች ካሳዩ እቤት እንዲቆዩ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ወደ ሐኪም ቤትም እንዲሄዱ ማድረግ እንዳይዘነጉ እናሳስባለን፡፤ እኛም ምልክቶቹን ያየንባቸዉን ልጆች ወደቤት እንዲመለሱ ብናደርግ ቅር እንዳትሰኙብን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
ከማክበር ሰላምታ ጋር
ፋሲካ የሕጻናት እንክብካቤ ማዕከል!