MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA @rhema_tv Channel on Telegram

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

@rhema_tv


Rhema Tv Ethiopia

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA (English)

Welcome to the world of Rhema TV Ethiopia! This dynamic Telegram channel, known as 'MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA' is your go-to destination for all things related to Ethiopian culture, entertainment, and news. Whether you are a fan of Ethiopian music, movies, or want to stay updated on the latest events in the country, this channel has got you covered

Rhema TV Ethiopia is a platform that aims to showcase the rich and diverse culture of Ethiopia to a global audience. With a focus on uplifting and empowering content, the channel provides a mix of entertainment, educational, and inspirational videos that celebrate the beauty of Ethiopian heritage

Who is it for? Rhema TV Ethiopia is for anyone who appreciates Ethiopian culture and wants to stay connected with the latest happenings in the country. Whether you are a proud Ethiopian living abroad or someone who simply loves learning about different cultures, this channel is for you

What can you expect? By joining 'MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA', you can expect to discover a treasure trove of videos that highlight the best of Ethiopian music, movies, traditional dances, and more. You will also get access to exclusive interviews with Ethiopian artists, behind-the-scenes glimpses of cultural events, and thought-provoking discussions on important issues affecting the country

Don't miss out on this opportunity to immerse yourself in the vibrant world of Ethiopian culture. Join Rhema TV Ethiopia today and be a part of a thriving community that celebrates the beauty and diversity of Ethiopia!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

09 Feb, 12:02


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ምክራቸው አይፀናምና አይሆንም!!!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

08 Feb, 15:51


“በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።”
— 2ኛ ቆሮ 6፥2

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

08 Feb, 10:28


የኢየሱስ ፀጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን....!!!

የፊታችን ዕሁድ የካቲት 2 ልዩ የአምልኮና የመዋጀት ጉባኤ ይኖረናል።እንዲሁም ከእግዚአብሔር ዘንድ አዲስ ነገር ይሆንልናል።በዚህ የበረከት ጉባኤ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!!!

“አጥፊው የበኵሮችን ልጆች እንዳይነካ ፋሲካንና ደምን መርጨትን በእምነት አደረገ።”
  — ዕብራውያን 11፥28


ይህን ማስታዋቂያ ለሌሎች share ማድረጋችሁን አትዘንጉ።


እንደተባረካችሁ ቆዩ!!!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

08 Feb, 04:46


ምሳሌ 26
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ ታካች ሰው፦ አንበሳ በመንገድ አለ፤ አንበሳ በጎዳና አለ ይላል።
¹⁴ ሣንቃ በማጠፊያው ላይ እንደሚዞር፥ እንዲሁ ታካች ሰው በአልጋው ላይ ይመላለሳል።
¹⁵ ታካች ሰው እጁን ወደ ወጭት ያጠልቃል፤ ወደ አፉም ይመልሳት ዘንድ ለእርሱ ድካም ነው።
¹⁶ ታካች ሰው በጥበብ ከሚመልሱ ከሰባት ሰዎች ይልቅ ለራሱ ጠቢብ የሆነ ይመስለዋል።

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

07 Feb, 17:47


የተወደዳችሁ የሀያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን ቤተሰቦችና ወዳጆች ፀጋና ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን

ቤተክርስቲያናችን በዚህ የቴሌግራም አገልግሎት ብዙዎች እያገለገለችና እየባረከች ትገኛለች ለዚህ እውነት ደግሞ እናንተ ምስክር ናችሁ።ስለሆነም ቤተክርስቲያናችን በቀጣይነት በዚህ የቴሌግራም platform ብዙዎችን ትድረስ ዘንድ እያንዳንዱ የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን ቤተሰብና ወዳጅ የሆነ ሁሉ ቅዱሳንን ወደዚህ የቴሌግራም ቻናል
Add በማድረግ ለዚህ አገልግሎት መስፋትና ማድግ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

https://t.me/+Ux6uZKADjZxkYjI0

ይህን ስታደርጉ የእግዚአብሔር በረከት ያግኛችሁ!!!

የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

07 Feb, 12:48


የኢየሱስ ፀጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን....!!!

የፊታችን ዕሁድ የካቲት 2 ልዩ የአምልኮና የመዋጀት ጉባኤ ይኖረናል።እንዲሁም ከእግዚአብሔር ዘንድ አዲስ ነገር ይሆንልናል።በዚህ የበረከት ጉባኤ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!!!

“አጥፊው የበኵሮችን ልጆች እንዳይነካ ፋሲካንና ደምን መርጨትን በእምነት አደረገ።”
  — ዕብራውያን 11፥28


ይህን ማስታዋቂያ ለሌሎች share ማድረጋችሁን አትዘንጉ።


እንደተባረካችሁ ቆዩ!!!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

07 Feb, 05:53


መንፈሳዊነት በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ማድረግ እንጂ በእግዚአብሔርና በሰው ላይ ማድረግ አይደለም።በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ማድረግ ጤናማ ዕድገት ሲሆን በእግዚአብሔርና በሰው ላይ ማድረግ አጉል መቀጨት ነው።

“ኢየሱስም ደግሞ በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ያድግ ነበር።ሉቃስ 2፥52

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

07 Feb, 03:26


የኢየሱስ ፀጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን....!!!

የፊታችን ዕሁድ የካቲት 2 ልዩ የአምልኮና የመዋጀት ጉባኤ ይኖረናል።እንዲሁም ከእግዚአብሔር ዘንድ አዲስ ነገር ይሆንልናል።በዚህ የበረከት ጉባኤ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!!!

“አጥፊው የበኵሮችን ልጆች እንዳይነካ ፋሲካንና ደምን መርጨትን በእምነት አደረገ።”
— ዕብራውያን 11፥28


ይህን ማስታዋቂያ ለሌሎች share ማድረጋችሁን አትዘንጉ።


እንደተባረካችሁ ቆዩ!!!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

06 Feb, 20:04


“ሰላም ለናንት ይሁን የተወዳዳቹ ወጣቶች”

“የከበረ ጥሪ ከንጉስ ዘንድ”

አስቴር 1:10-11፤ የመንግሥቱን ዘውድ ጭነው ወደ ንጉሡ ፊት ያመጡአት ዘንድ በፊቱ የሚያገለግሉትን ሰባቱን ጃንደረቦች ምሁማንን፥ ባዛንን፥ ሐርቦናን፥ ገበታን፥ ዘቶልታን፥ ዜታርን፥ ከርከስን አዘዛቸው።

ቅዳሜ 10:30 ጀምሮ የአምልኮና የትምህርት ጊዜ ይኖረናል።

እንደተባረካችሁ ቆዩ!!!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

06 Feb, 04:32


እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሚሰጠው በዋጋ የማይተመን ሀብት ጊዜ ነው።ጊዜን የሚተካ ነገር የለም።ጊዜ ረክሶ አያውቅም ጊዜ የረከሰበት ሰው የሚኖርበት ዓላማ የሌለው ሰው ነው።

ከጊዜ እጅግ ዉድ ጊዜ ደግሞ አሁን ነው
እጅግ በጣም ዉድ ጊዜ አሁን እንጂ በኋላ አይደለም አሁን እንጂ ነገ አይደለም።አሁንን የሚተካ በኃላ የለም አሁን የሚተካ ነገ የለም።

“በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።”
  — 2ኛ ቆሮ 6፥2

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

06 Feb, 03:57


“እነሆ፥ ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው፥ የሆድም ፍሬ የእርሱ ዋጋ ነው።”
— መዝሙር 127፥3

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

05 Feb, 19:04


2ኛ ቆሮ 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አብረንም እየሠራን የእግዚአብሔርን ጸጋ በከንቱ እንዳትቀበሉ ደግሞ እንለምናለን፤
² በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

04 Feb, 12:26


እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔር እናመልካለን!!!

ነገ ዕሮብ ጥር 28 ከ 11:00 ጀምሮ የአምልኮና የፀሎት የእግዚአብሔር ቃልና የቡራኬ ጊዜ ይኖረናል።ስለሆነም የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን ወዳጆችና ቤተሰቦች በሙሉ በዚህ የበረከት ምሽት ከቤተሰቦቻችሁና ከወዳጆቻችሁ ጋር በመገኘት የእግዚአብሔርን በረከት ተካፋዮች እንድትሆኑ ተጋብዛችኋል።

📢ማሳሰቢያ፦ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጡ መፅሐፍ ቅዱስና ማስታወሻ መያዛችሁን አትዘንጉ።

📢እንዲሁም ይህን ማስታወቂያ ለሌሎች share በማድረግ ቤተክርስቲያንን ያገልግሉ!!!


🤚ለበረከት ሁኑ

የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን!!!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

04 Feb, 06:04


መዝሙር 123
¹ በሰማይ የምትኖር ሆይ፥ ዓይኖቼን ወደ አንተ አነሣሁ።
² እነሆ፥ የባሪያዎች ዓይኖች ወደ ጌታቸው እጅ እንደ ሆኑ፥ የባሪያይቱም ዓይን ወደ እመቤትዋ እጅ እንደ ሆነ፥ እንዲሁ እስኪምረን ድረስ ዓይናችን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ነው።

Psalms 123 (KJV)
¹ (A Song of degrees.) Unto thee lift I up mine eyes, O thou that dwellest in the heavens.
² Behold, as the eyes of servants look unto the hand of their masters, and as the eyes of a maiden unto the hand of her mistress; so our eyes wait upon the LORD our God, until that he have mercy upon us.

#Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!!!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

04 Feb, 05:03


ውጤት ሰጪ እግዚአብሔር ነው።

ወጤት ሰጪአችሁ እግዚአብሔር እንደሆነ ስታውቁ በህይወት ውጤታማ ለመሆን ወይም ውጤት ለማምጣት አትፍጨረጨሩም።እንደ እግዚአብሔር መንግስት ውጤት አስጣጥ ውጤት የምትቀበሉት ጉዳይ እንጂ የምትፈጥሩት ጉዳይ  አይደለም።


#መትጋት እና #መታገል ልዩነት አላቸው።በተመሳሳይ #ዕረፍት እና ስንፍና ልዩነት አላቸው።እግዚአብሔር የሚፈልገው #እንድትተጉ እንጂ #እንድትታገሉ አይደለም።እግዚአብሔር የሚፈልገው #እንድታርፉ እንጂ #እንድትሰንፉ አይደለም።

#መትጋት፦ለውጤታማነት ከእናንተ የሚጠበቀውን ሁሉ ያለ መታከት ማድረግ ማለት ሲሆን____#መታገል፦ውጤት ፈጣሪ ለመሆን መፍጋት ማለት ነው።

#ዕረፍት፦ከእናንተ የሚጠበቀውን በማድረግ ውስጥ ያለ የእግዚአብሔርን ውጤት ሰጪነት በመተማመን የሚጠባበቅ የውስጥ ሰላም ማለት ነው።#ስንፍና፦ከመትጋትና ከዕረፍት ውጪ የሆነ ባዶ ተስፋ ማለት ነው።

በእናንተ ህይወት እግዚአብሔር ሁለት ድርጊቶች ውጤት ሰጪ ያደርጉታል እነርሱም ትጋትና ዕረፍት ይባላሉ።በተመሳሳይ ሁለት ድርጊቶች እግዚአብሔር በህይወታችሁ እንዳይሰራ እንቅፋት ይሆኑታል መታገልና ስንፍና ናቸው።

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

03 Feb, 06:44


🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

03 Feb, 01:45


https://t.me/c/2020624729/10444

የተወደዳችሁ የኃያላን መቅደስ ቤተሰቦችእና ወዳጆች

ነገ ሰኞ  ከማለዳ 12:00 ጀምሮ ሳምንቱን የምንዋጅበትና  እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት የቴሌግራም  ቀጥታ ስርጭት ይኖረናል።

ስለሆነም  በኢትዮጲያ ሰአት አቆጣጠር  ከጠዋቱ 12:00 ላይ ከላይ ☝️☝️ "Join" የምትለውን ምልክት በመጫን ሳምንቱን እንዲዋጁና እግዚአብሔርን በውዳሴና በምስጋና በማክበር እንዲጀምሩ ተጋብዘዋል!


#እንደተባረካችሁ ቆዩ!

የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

02 Feb, 12:24


የህይወታችሁ ውጤት ሰጪ እግዚአብሔር ነውና ቀሪ ዘመናችሁ እግዚአብሔር በወሰነላችሁና እግዚአብሔር በለካላችሁ ልክ ይሁን!!!

በኢየሱስ ስም አሜን!!!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

01 Feb, 13:27


ሆሳዕና በአርያም ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ!!!

ስለሆነልን ድንቅ ነገር ብቻ ሳይሆን ስላልሆነብን ክፉ ምክር እግዚአብሔር ይመሰገን!!!

ነገ ዕሁድ ማለዳ ከ3:00 ጀምሮ ልዮ የአምልኮና የበረከት ጉባኤ ከቤተሰቦቻችንና ከወዳጆቻችን ጋር በኃያላን ጉባኤ እንገናኝ!!!


ወደ እግዚአብሔር ቤት ስንመጣ መፅሐፍ ቅዱስና ማስታውሻ መያዛችሁን እንዲሁም ጌጠኛ ልብስ መልበሳችሁን አትዘንጉ!!!

መዝሙር
150
¹ ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን በመቅደሱ አመስግኑት፤ በኃይሉ ጠፈር አመስግኑት።
² በችሎቱ አመስግኑት፤ በታላቅነቱ ብዛት አመስግኑት።
³ በመለከት ድምፅ አመስግኑት፤ በበገናና በመሰንቆ አመስግኑት።
⁴ በከበሮና በዘፈን አመስግኑት፤ በአውታርና በእምቢልታ አመስግኑት።
⁵ ድምፁ መልካም በሆነ ጸናጽል አመስግኑት፤ እልልታ ባለው ጸናጽል አመስግኑት።
⁶ እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን፦ ሃሌ ሉያ።

የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን!!!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

18 Jan, 09:06


#Holy_communion_service

#የበረከት_ፅዋ

ፀጋና ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን፦ነገ ዕሁድ ጥር 11 ከ3:00 ጀምሮ ልዩ የአምልኮና የጌታ ራትን በአንድነት የምንካፈልበት የበረከት ጉባኤ ይኖረናል።እንዲሁም የህይወትን ቃል ከመንፈስ ቅዱስ የምንማር ይሆናል።

ስለሆነም የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን ቤተሰቦችና ወዳጆችበሙሉ በዚህ የበረከት ማለዳ ከቤተሰቦቻችሁና ከወዳጆቻችሁ ጋር በመሆን ጌታን ከእኛ ጋር እንዲያመልኩ ተጋብዛችኋል!!!

እንደተባረካችሁ ቆዩ!!!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

18 Jan, 05:36


<<እግዚአብሔር ብርሃን ብቻ ነው!>>

እግዚአብሔር የጨለማ ደራሲ አይደለ የብርሃን እንጂ።እግዚአብሔር ከክፉ ነገሮች ጀርባ ብትፈልጉት አታገኙትም ምክኒያቱም ክፋት ማድረግ ባህሪው አይደለምና።በተመሳሳይ ሰይጣንን ከመልካም ነገሮች ጀርባ ብትፈልጉት አታገኙትም።በህይወት የሚመጡባችሁ ማንኛውም አይነት መከራና ችግር ፈተናና ግራ መጋባት ከእግዚአብሔር አይደሉም።ምክኒያቱም እግዚአብሔር ማንንም በክፉ አይፈትንም።የእግዚአብሔር ፈተና ሙከራ እንጂ ፈተና አይደለም።የእግዚአብሔር ፈተናዎች በሙሉ መውጫ መንገዶች አሉአቸው።

“ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል።1ኛ ቆሮንቶስ 10፥13


Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

17 Jan, 15:43


https://t.me/+Ux6uZKADjZxkYjI0

የተወደዳችሁ የኃያላን መቅደስ ቤተሰቦች

ዛሬ አርብ  ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ ልዩ የሆነ የፀሎትና የቃል ጊዜ ይኖረናል።

🕎ፕሮግራሙን ለመካፈል ☝️ "Join" የምትለውን ምልክት በመጫን ኘሮግራሙን  ይካፈሉ!
🕎 በቴሌግራም ላይ ያሉ ቤተሠብና ጓደኞችዎን በመጋበዝ ቤተክርስቲያንን ያገልግሉ!

እንደተባረካችሁ ቆዩ!

የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን.

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

17 Jan, 11:36


የምናወራውን ሁሉ አይደለንም።የምናውቀውን ሁሉ አይደለንም።እኛ የምንኖረውን ነን።ሰው ማለት የንግግሩና የእውቀቱ ውጤት ሳይሆን የኑሮው ውጤት ነው።ሰውን በንግግርህና በእውቀትህ እበልጠዋለሁ አትበል የበለጠ በመኖር የበለጠ ነው።

2ኛ ቆሮ 11
²³ እንደ እብድ ሰው እላለሁ፤ እኔ እበልጣለሁ፤ በድካም አብዝቼ፥ በመገረፍ አብዝቼ፥ በመታሰር አትርፌ፥ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ።
²⁴ አይሁድ አንድ ሲጎድል አርባ ግርፋት አምስት ጊዜ ገረፉኝ።
²⁵ ሦስት ጊዜ በበትር ተመታሁ፤ አንድ ጊዜ በድንጋይ ተወገርሁ፤ መርከቤ ሦስት ጊዜ ተሰበረ፤ ሌሊትና ቀን በባሕር ውስጥ ኖርሁ።


Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

17 Jan, 04:41


#Holy_communion_service

#የበረከት_ፅዋ

ፀጋና ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን፦የፊታችን ዕሁድ ጥር 11 ከ3:00 ጀምሮ ልዩ የአምልኮና የጌታ ራትን በአንድነት የምንካፈልበት የበረከት ጉባኤ ይኖረናል።እንዲሁም የህይወትን ቃል ከመንፈስ ቅዱስ የምንማር ይሆናል።

ስለሆነም የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን ቤተሰቦችና ወዳጆችበሙሉ በዚህ የበረከት ማለዳ ከቤተሰቦቻችሁና ከወዳጆቻችሁ ጋር በመሆን ጌታን ከእኛ ጋር እንዲያመልኩ ተጋብዛችኋል!!!

እንደተባረካችሁ ቆዩ!!!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

16 Jan, 10:42


“ከመጥምቁም ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች፥ ግፈኞችም ይናጠቋታል።”ማቴዎስ 11፥12

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

16 Jan, 04:25


መልካም ለመስራት እንትጋ

ባንዝልም በጊዜው እናጭዳለንና መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት (ገላቲያ 6፡9)

በአሁኑ ጊዜ ለሌሎች መልካም ላለመሆን የወሰኑ አሉ፡፡ ለምን? ጥሩ ያልሆነ ተሞክሮ ስለነበራቸው ወይንም ሌሎችን ለመርዳት ሲሞክሩ የተጎዱ ሰዎችን ስላስተዋሉ ሊሆን ይችላል፡፡

ህብረተሰባችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ ነው የመጣው፤ ስለሆነም ብዙዎች ለምህረት እና ለርህራሄ እራሳቸውን ዝግ አድርገዋል፡፡ ከብዙ አመታት በፊት መኪናችሁን እየነዳችሁ የተጎዳ ሰው ብታዩ፣ ለመርዳት ትፈጥኑ ነበር፡፡ ነገር ግን አሁን በዚህ አለም ካለው የበዛ ክፋት የተነሳ፣ ብዙዎች የሚጨነቁት እንግዳ ሰዎችን መርዳት ሊያመጣ ስለሚችለው አደጋ ነው፡፡ ይህ የጥፋት ልጅ ያመጣው ነው፡፡
ክፉ የብዙዎች ልብ እንዲደነድን አድርጓል፡፡

መርዳትን ይፈልጋሉ፣ ነገር ግን በመጨረሻ ተጎጂ መሆንን አይፈልጉም፡፡ ነገር ግን እናንተ መልካምን ለማድረግ ወደ ኋላ አትበሉ፡፡ ለመርዳት አታወላውሉ፡፡ ምክንያቱም በእናንተ ውስጥ ያለው ኃይል በአለም ላይ ካለው የክፋት ሃይል በሙሉ ቢደመር እንኳን እጅግ የላቀ ነው፡፡

በእናንተ ውስጥ ያለው በአለም ካለው ይበልጣል፡፡ ረዳት አልባ አይደላችሁም፡፡ ስለ ኢየሱስ እስቲ አስቡ፡- የካህናት አለቃው አገልጋይ ሊያስረው መጣ፣ መጽሐፍ እንደሚነግረን “ኢየሱስም የሚመጣበትን ሁሉ አውቆ ወጣና፦ ማንን ትፈልጋላችሁ አላቸው” (ዮሐንስ 18፡4)፡፡ እነርሱም “የናዝሬቱ ኢየሱስን” አሉ፡፡ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር ኃይል ተለቀቀ፣ ሁሉም በተለቀቀው ኃይል ወደቁ! ይህ እንዴት ሊከሰት ቻለ?
ይህ ከመከሰቱ ከትንሽ ጊዜ በፊት በማቲዎስ 26 ላይ ኢየሱስ በጌተሰማኒ የአትክልት ስፍራ እየጸለየ ነበር፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በውስጡ በሙላት ነበር፡፡ “እርሱ እኔ ነኝ” ሲል ቃሉ በኃይል ነበር የወጣው፡፡

እርሱ ባዶ አልነበረም፡፡ እናንተም ላይ ተመሳሳይ ነው የሚሆነው፣ ቃላቶቻችሁ በኃይል የተሞሉ ናቸው፣ ምክንያቱም መለኮትን በውስጣችሁ ተሸክማችኋል፡፡
የሚያስፈልጋችሁ በኤፌሶን 5፡18 የተገለጸውን የመንፈስ መሞላት ነው፣ “መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና” በመንፈስ ስትሞሉ መልካም ነገር ሰርቼ ልጎዳ እችላለሁ ብላችሁ ፈጽሞ አታስቡም፡፡

ስለሆነም መንገድ ከመጀመራችሁ በፊት እና የእለቱን ስራችሁን ከመጀመራችሁ በፊት በመንፈስ ተሞሉ፡፡ በልባችሁ ያስቀመጠውን መልካም ነገር እንድታከናውኑ እርሱ ይመራችኋል፣ ማንም ሊጎዳችሁ እና ሊያስቆማችሁ አይችልም፡፡ ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን!

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

15 Jan, 03:42


ኢየሱስን የምንከተለው እንዲለውጥልን ሳይሆን እንዲለውጠን ነው፡፡

ብዙዎች ጌታን የሚከተሉት እንዲለወጣቸው ሳይሆን እንዲለውጥላቸው ነው፡፡በዚህም ምክኒያት ሳይለወጥላቸውም ሳይለወጡም በእግዚአብሔር መንግስት ይጨርሳሉ፡፡እርግጠኛ መሆን ያለባችሁ ነገሮች መለወጣቸውን ሳይሆን እናንተ መለወጣችሁን ነው፡፡የእናንተ መለወጥ ሁሉን ነገር ይለውጠዋልና፡፡

በጌታ ለመሆናችሁ ማስረጃ የሚሆናችሁ የተለወጠው ነገራችሁ ሳይሆን የተለወጠው ማንነታችሁ ነው፡፡ማለትም የእናንተ መለወጥ እንጂ የኑሮአችሁ መለወጥ አይደለም፡፡እናንተን ሳይለወጥ ኑሮአችሁን የሚለውጥ ወንጌል አይደለም፡፡ወንጌል ወደ ልጁ ወደ ኢየሱስ መልክ የሚለወጥ ሀይል ነውና፡፡

“መልካም፣ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በአእምሮአችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።”
  — ሮሜ 12፥2

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

14 Jan, 10:06


የጌታ ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን!

ወድ የኃያላን ቤተክርስቲያን ቤተሰቦች እና ወዳጆች በሙሉ የፊታችን ነገ ዕሮብ ጥር ገ ከ11:00 ጀምሮ የአምልኮ እና የትምህርት ጊዜ ይኖረናል። የእግዚአሔርን ቃል ከመንፈስ ቅዱስ በተከፈተ ሰማይ እንማራለን እንዲሁ የፀሎትና ሀይልን የመቀበል ጊዜ ይኖረናል።

በመሆኑም በዚህ የአምልኮ እና የትምህርት ጊዜ  ተገኝታችሁ ጌታ ኢየሱስን ከእኛ ጋር እንድታመልኩና የህይወትን ቃል እንድትካፈሉ ተጋብዛችኋል።

ማሳሰቢያ፦ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጡ መፅሐፍ ቅዱስና ማስታወሻ መያዛችሁን አትዘንጉ።

👉ይህን ማስታወቂያ ለሌሎች እንዲደርስ Share በማድረግ ያገልግሉ!!!

እንደተባረካችሁ ቆዩ።

የኃያላን መቅደስ  ቤተክርስቲያን

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

14 Jan, 04:10


የመጨረሻው ኪሳራ ራስን መክሰር ነው፡፡ነገሮችን አትርፍችሁ ራሳችሁን እንዳትክስሩ ተጠንቀቁ፡፡በእግዚአብሔር መንግስት እግዚአብሔር ላልፈጠራችሁ ዓለማ እንደመኖር ያለ ኪሳራ የለም፡፡ስኬት መትረፍረፍ ሳይሆን ስኬት ለተፈጠራችሁለት ዓላማ መኖር ነው፡፡

የህይወታችሁ ስኬት መሆን ያለበት ለተፈጠራችሁለት እውነት መኖር እንጂ በምታገኙት ዕድልና በምታገኙት አጋጣሚ ሁሉ መዘፈቅ አይደለም።የሆናችሁትን ባለመሆን ማርፈድ ኪሳራ ያስከትላል።የሆናችሁትን አለመሆን ያለሆናችሁትን እንድትሆኑና ከተፈጠራችሁበት ዓላማ ውጪ እንድትሆኑ ያደርጋችኋል።

እግዚአብሔር ናችሁ ያላችሁን ጥሪ ትታችሁ ሰዎች ሁኑልን በሚሉአችሁ ተስባችሁ የኪሳራ ሳጥን ውስጥ እዳትገኙ ተጠንቀቁ።ምክኒያቱም ኢየሱስ የዓለም ቤዛ ለመሆን መጥቶ ንጉስ ሁንልን ብለውት ነበርና።ስኬታችሁ ያለው የተፈጠራችሁለትን በመኖር ውስጥ ነው።ከዚህ ውጪ ከፍታ ላይ ብትወጡ ወይም ዝቃታ ላይ ብትወረዱ ከስራችኋል።

ዮሐንስ 6
¹⁴ ከዚህ የተነሣ ሰዎቹ ኢየሱስ ያደረገውን ምልክት ባዩ ጊዜ፦ ይህ በእውነት ወደ ዓለም የሚመጣው ነቢይ ነው አሉ።
¹⁵ በዚህም ምክንያት ኢየሱስ ያነግሡት ዘንድ ሊመጡና ሊነጥቁት እንዳላቸው አውቆ ደግሞ ወደ ተራራ ብቻውን ፈቀቅ አለ።

👉ለሌሎች share በማድረግ የእግዚአብሔርን ቃል ያገልግሉ!!!

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

13 Jan, 06:55


ሰላም የተወደዳችሁ የኃያላን መቅደስ ቤ/ክ ቤተሰቦችና ወዳጆች በሙሉ ፀጋና ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን!!!

ዛሬ ሰኞ ጥር 05 ከምሽቱ 11:30 - 01:30 የሚቆይ  በእህቶች ህብረት የሚዘጋጅ      "ልባምዋ ሴት" የተሰኘው  ፕሮግራማችን ይደረጋል፣ በዕለቱ ሁላችሁ የእግዚአብሔር ሴት ልጆች ትገኙ ዘንድ ተጋብዛችኋል!!!

እንደተባረካችሁ ቆዩ!!!
ከእህቶች ህብረት የአገልግሎት ዘርፍ

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

13 Jan, 05:47


ያለ እምነት ዕረፍት የለም፡፡ያለ ዕረፍት እምነት የለም፡፡እያመናችሁ አለማረፍ አትችሉም እያረፍችሁ አለማመን አትችሉም፡፡የእምነት ማረጋገጫው እረፍት ነው የዕረፍት ዋስትናው ደግሞ እምነት ነው፡፡እምነት የሌለው ዕረፍት ስሜት ነው፡፡ዕረፍት የሌለው እምነት ሙት ነው፡፡እግዚአብሔር የሚሰራላችሁ በእምነት በሆነ ዕረፍት ውስጥ ስትሆኑ ነው፡፡በኢየሱስ ድንቅ ስም በእምነት የሆነ ፍፁም ዕረፍት ውስጥ መግባት ይሁንላችሁ!

"፤ ሥራው ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ምንም እንኳ ቢፈጸም። እንዲህ። ወደ ዕረፍቴ አይገቡም ብዬ በቁጣዬ ማልሁ እንዳለ፥ እኛስ ያመንን ወደ ዕረፍቱ እንገባለን። "
(ወደ ዕብራውያን 4: 3)

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

12 Jan, 12:02


“ከመጥምቁም ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች፥ ግፈኞችም ይናጠቋታል።ማቴዎስ 11፥12

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

11 Jan, 13:26


ልዩ _የቅባት_ማለዳ

እግዚአብሔር በስራ ላይ ነው ሁላችንም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች በታላቅ መጠባበቅ በልዑል በእግዚአብሔር ፊት እንገኝ!!!

“በተናገረኝም ጊዜ መንፈስ ገባብኝ በእግሬም አቆመኝ፥ የሚናገረኝንም ሰማሁ።ሕዝቅኤል 2፥2


ለበረከት ናችሁ!!!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

11 Jan, 04:34


ትላንትን ትተን፥ ነገን አይተንና ተመልክተን፥ ዛሬን እንጀምር!!!

መልካምን ሥራ ሁሉ ለመጀመርና ለመፈጸም፥ ለማሰብና ለማድረግ፥ ለመዝራትና በጊዜው ለማጨድ አልረፈደብንምና!!!

እግዚአብሔር ለሰዎች የሚሰጣቸው የጊዜ መቁጠሪያ ተስፋ ይባላል፥ የሚመጣው እንጂ ያለፈውን አይቆጥርምና፥ ሊሆን ያለውን እንጂ የሚታየውን አያይምና፤

በተመሳሳይ

ሰይጣን ለሰዎች የሚሰጣቸው የጊዜ መቁጠሪያ ቁጭት ይባላል፥ ያለፈውን እንጂ የሚመጣውን አይቆጥርምና፥ የሚታየውን እንጂ ሊሆን ያለውን አያይምና።

📜 ፊልጵስዩስ 3፥13c

በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ፤

📜 ዘፍጥረት 15:3-4

³ አብራምም፦ ለእኔ ዘር አልሰጠኸኝም፤ እነሆም፥ በቤቴ የተወለደ ሰው ይወርሰኛል አለ።
⁴ እነሆም፥ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጣለት፦ ይህ አይወርስህም፤ ነገር ግን ከጉልበትህ የሚወጣው ይወርስሃል።

📜 ሮሜ 4:18-19

¹⁸ ዘርህ እንዲሁ ሊሆን ነው እንደ ተባለ፥ ተስፋ ባልሆነው ጊዜ የብዙ አሕዛብ አባት እንዲሆን ተስፋ ይዞ አመነ።
¹⁹ የመቶ ዓመትም ሽማግሌ ስለ ሆነ እንደ ምውት የሆነውን የራሱን ሥጋና የሳራ ማኅፀን ምውት መሆኑን በእምነቱ ሳይደክም ተመለከተ

📜 ዕብራውያን 11፥11

ተስፋ የሰጠው የታመነ እንደ ሆነ ስለ ቈጠረች፥ ሣራ ራስዋ ደግሞ ዕድሜዋ እንኳ ካለፈ በኋላ ዘርን ለመፅነስ ኃይልን በእምነት አገኘች።

📜 ኢሳይያስ 54፥1

አንቺ ያልወለድሽ መካን ሆይ፥ ዘምሪ፤ አንቺ ያላማጥሽ ሆይ፥ እልል በዪ፥ ጩኺም፤ ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆነቺቱ ልጆች በዝተዋልና፥ ይላል እግዚአብሔር፤

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

10 Jan, 12:05


የቅባት_ቀን/Day of Anointing

የፊታችን ዕሁድ ጥር 4 ከ3:00 ጀምሮ የአምልኮ እና የቅባት አገልግሎት አገልግሎት ይኖረናል።እንዲሁም በተከፈተ ሰማይ የእግዚአብሔርን ቃል እንማራለን።

ስለሆነም በዚህ የቅባት አገልግሎት ቀን ከቤተሰቦቻችሁና ከወዳጆቻችሁ ጋር በመገኘት ጌታን ከእኛ ጋር እንዲያመልኩ ተጋብዛችኋል።

ማሳሰቢያ፦ወደ እግዚአብሔር ቤት ስንመጣ መፅሐፍ ቅዱስና ማስታወሻ መያዛችሁን አትዘንጉ!!!

👉እንዲሁም ይህን ማስታወቂያ ለሌሎች እንዲደርስ share በማድረግ ቤተክርስቲያንን ያገልግሉ!


እንደተባረካችሁ ቆዩ!!!

የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን.

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

10 Jan, 05:21


እምነት የሚሰራው በፍቅር ነው፡፡ያለ ፍቅር የሚሰራ መፅሐፍ ቅዱሳዊ እምነት የለም እምነትን እንዲሰራ የሚያደርገው ብቸኛ ሀይል ፍቅር ነው፡፡ፍቅር የሌለው ሰው እምነት የለውም፡፡እምነት የሌለው ሰው ደግሞ ህይውት የለውም፡፡ህይውት የሚኖራችሁና የሚስራ እምነት ሊኖራችሁ የሚችለው በፍቅር መኖር ከቻላችሁ ብቻ ነው፡፡ትልቁ መንፈሳዊ ኪሳራ የሚጀመረው ፍቅር ከመጣል ነው፡፡ፍቅር የክርስትና መጀመሪያም መደምደሚያም ነውና እግዚአብሔር ፍቅር ያብዛላችሁ!

“በክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ፥ በፍቅር የሚሠራ እምነት እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና።”ገላትያ 5፥6

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

09 Jan, 18:13


ሰው ሆነህ በሰው ላይ ቂም መያዝ የሰይጣን ባህሪ ማርገዝ ነውና ልብህ ቂምን ሲያስብ ናቀው እንጂ አክብረህ አትያዘው።

ቂም አፍን የሚያመር ልብን የሚያነቅዝ ነፍስን የሚያዝል የዲያብሎስ መውጊያ ነው።ቂመኛ ሰዎች ደስታቸውን በተበድያለሁ የተቀሙ መራራ ህይወት የሚኖሩ ሰዎች ናቸው።

በእናንተ የውስጥ ሰውነት ውስጥ ከእግዚአብሔር ደስታና ሰላም ውጪ ማንንም በቂም ገመድ አስራችሁ ማኖር የለባችሁም።ወጫዊ ዓላማችሁ በውስጣዊ ዓለማችሁ በምታኖሩት አካል ይወሰናልና ውጫዊ ገጽታችሁ የተዋበ ይሆን ዘንድ ዛሬ በውስጣችሁ በቂም በቀል ገመድ ለአመታት ያሰራችኋቸውን ሰዎች በሙሉ በነፃ ፍቱና ልቀቋቸው ይህን ስታደርጉ የእግዚአብሔር አብሮነትን ታገኛላችሁ።

እግዚአብሔር በፍጹም ይቅር ባይነት ፀጋ ይደግፍችሁ።በኢየሱስ ስም አሜን።

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

09 Jan, 10:17


Channel photo updated

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

09 Jan, 10:05


በዚህ ጥር ወር በጽድቅና በታማኝነት እንደዘራችሁት መጠን እግዚአብሔር መከሩን ያሳጭዳችሁ!!!

በብዙ ለቅሶና በብዙ መከራ ለዘራችሁት መልካም ሥራ በኢየሱስ የተባረከ ስም የመከር አምላክ እግዚአብሔር የተረፈረፈ ነዶ ያሸክማችሁ!!!

ይህ ጥር ወር ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ ብድራት ወደ ቤታችሁ የሚገባበት የምስክርነት ወር ይሁንላችሁ!!!

መዝሙር 126
⁵ በልቅሶ የሚዘሩ በደስታ ይለቅማሉ።
⁶ በሄዱ ጊዜ፥ ዘራቸውን ተሸክመው እያለቀሱ ተሰማሩ፤ በተመለሱ ጊዜ ግን ነዶአቸውን ተሸክመው ደስ እያላቸው ይመጣሉ።


በኢየሱስ ስም አሜን!!!

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!!!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

09 Jan, 05:42


“ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።”
— ኢሳይያስ 9፥6

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

08 Jan, 19:16


አዝመራውን ለመቀየር ዘሩን መቀየር ጥበብ ነው።ጠቢብ ክርስቲያን አዝመራውን ለመቀየር አይታገልም ዘሩን በመቀየር የአዝመራውን መልክ ይቀይራል።

መጪው ዘመናችሁ ምን ይመስላል ካላችሁኝ መጀመሪያ እግዚአብሔር ያለውን አይነት ይመስላል በመቀጠል ዛሬ የምትዘሩትን ዘር ይመስላል።የማንም ሰው ነገ ከእነዚህ ውጪ ሊሆን አይችልም።

1ኛ ጴጥሮስ 3
¹⁰ ሕይወትን ሊወድ መልካሞችንም ቀኖች ሊያይ የሚፈልግ ሰው፥ መላሱን ከክፉ ከንፈሮቹንም ተንኰልን ከመናገር ይከልክል፤
¹¹ ከክፉ ፈቀቅ ይበል፥ መልካምንም ያድርግ፥ ሰላምን ይሻ ይከተለውም፤

በህይወት መጨነቅ ያለባችሁ ለአዝመራው ሳይሆን ለዘሩ ነው።ምክንያቱም የምትዘሩት ዘር መልካም ከሆነ አዝመራችሁ መልካም ይሆናል።በቀሪ ዘመናችሁ አዝመራችሁ ወይም ውጤታችሁ ያማረ እንዲሆን እግዚአብሔር በሚሰጣችሁ ዛሬ መልካም የሆነውን ሁሉ ዝሩበት።

“አትሳቱ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና፤”
— ገላትያ 6፥7


Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

07 Jan, 12:40


የመዋጀት ምሽት / Night of Redemption.

የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የጌታ ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን!!!

ነገ ዕሮብ ታህሳስ 30 ከ11:00ጀምሮ የአምልኮና ወር የመዋጅት ትንቢታዊ ጉባኤ ይኖረናል በመሆኑም በዚህ የበረከት ምሽት ከቤተሰቦቻችሁና ከወዳጆቻችሁ ጋር በመሆን የመለኮታዊ በረከት ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ ተጋብዛችኋል።

ኤፌሶን 5
¹⁵ እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤
¹⁶ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ።


የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን.

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

07 Jan, 04:02


ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመሰገን!!!

ዉድ የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን ቤተሰቦችና ወዳጆ በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ!!!

“ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።ኢሳይያስ 9፥6

እንደተባረካችሁ ቆዩ።

የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን!!!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

06 Jan, 03:34


https://t.me/c/2020624729/10444

የተወደዳችሁ የኃያላን መቅደስ ቤተሰቦችእና ወዳጆች

ነገ ሰኞ  ከማለዳ 12:00 ጀምሮ ሳምንቱን የምንዋጅበትና  እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት የቴሌግራም  ቀጥታ ስርጭት ይኖረናል።

ስለሆነም  በኢትዮጲያ ሰአት አቆጣጠር  ከጠዋቱ 12:00 ላይ ከላይ ☝️☝️ "Join" የምትለውን ምልክት በመጫን ሳምንቱን እንዲዋጁና እግዚአብሔርን በውዳሴና በምስጋና በማክበር እንዲጀምሩ ተጋብዘዋል!


#እንደተባረካችሁ ቆዩ!

የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

05 Jan, 13:18


MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA pinned «የዓለምን ሃጢያት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ ተወለደልን!! “በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።” — ዮሐንስ 1፥29 #Emmanuel!!!»

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

05 Jan, 13:18


የዓለምን ሃጢያት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ ተወለደልን!!

“በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።”
— ዮሐንስ 1፥29

#Emmanuel!!!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

04 Jan, 19:31


እናንተ መኳንንቶች በሮችን ክፈቱ ይህ የክብር ንጉስ ይገባ!!!

ነገ ዕሁድ ከ3:ዐዐ ጀምሮ፦ ስግደት ለንጉሳችን


ሉቃስ 2
⁸ በዚያም ምድር መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ እረኞች ነበሩ።
⁹ እነሆም፥ የጌታ መልአክ ወደ እነርሱ ቀረበ የጌታ ክብርም በዙሪያቸው አበራ፥ ታላቅ ፍርሃትም ፈሩ።
¹⁰ መልአኩም እንዲህ አላቸው፦ እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤
¹¹ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።
¹² ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ።
¹³ ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ፦
¹⁴ ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ አሉ።

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

04 Jan, 06:33


ህፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና!

ዉድ የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን ቤተሰቦችና ወዳጆች በሙሉ ነገ ዕሁድ ታህሳስ 27 ከ3:00ጀምሮ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ፕሮግራሞች ይከበራል በመሆኑም በዚህ ልዩ የአምልኮ ቀን ከወዳጆቻሁና ከቤተሰቦቻችሁ ጋር በመሆን የነገስታት ንጉስ የሆነው ጌታ ኢየሱስን እንዲያመልኩት ተጋብዛችኋል!!!


ማሳሰቢያ፦ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጡ ጌጠኛ ልብሳችሁን መልበሳችሁን አትዘንጉ!!!

👉ይህ ማስታወቂያ ለቅዱሳን እንዲደርስ share በማድረግ ቤተክርስቲያንን ያገልግሉ!!!

እንደተባረካችሁ ቆዩ!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

03 Jan, 12:19


ህፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና!

ዉድ የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን ቤተሰቦችና ወዳጆች በሙሉ የፊታችን ዕሁድ ታህሳስ 27 ከ3:00ጀምሮ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ፕሮግራሞች ይከበራል በመሆኑም በዚህ ልዩ የአምልኮ ቀን ከወዳጆቻሁና ከቤተሰቦቻችሁ ጋር በመሆን የነገስታት ንጉስ የሆነው ጌታ ኢየሱስን እንዲያመልኩት ተጋብዛችኋል!!!


ማሳሰቢያ፦ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጡ ጌጠኛ ልብሳችሁን መልበሳችሁን አትዘንጉ!!!

👉ይህ ማስታወቂያ ለቅዱሳን እንዲደርስ share በማድረግ ቤተክርስቲያንን ያገልግሉ!!!

እንደተባረካችሁ ቆዩ!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

03 Jan, 12:18


Channel photo updated

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

03 Jan, 03:46


ህፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና!

ዉድ የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን ቤተሰቦችና ወዳጆች በሙሉ የፊታችን ዕሁድ ታህሳስ 27 ከ3:00ጀምሮ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ፕሮግራሞች ይከበራል በመሆኑም በዚህ ልዩ የአምልኮ ቀን ከወዳጆቻሁና ከቤተሰቦቻችሁ ጋር በመሆን የነገስታት ንጉስ የሆነው ጌታ ኢየሱስን እንዲያመልኩት ተጋብዛችኋል!!!


ማሳሰቢያ፦ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጡ ጌጠኛ ልብሳችሁን መልበሳችሁን አትዘንጉ!!!

👉ይህ ማስታወቂያ ለቅዱሳን እንዲደርስ share በማድረግ ቤተክርስቲያንን ያገልግሉ!!!

እንደተባረካችሁ ቆዩ!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

03 Jan, 03:24


ነፃነት

አንድ ጥቁር አሞራ ነበረ አሉ፡፡ በጣም የምታምር ነጭ እርግብ ያይና ይቀናል፡፡ ሰዎች እኔን አይወዱኝም፤ እሷን ግን የሰላም ምልክት አርገው ይጠቀሟታል፤ ደስታ የለኝም ብሎ ወደሷ ሄደና በኑሮው ደስተኛ እንዳልሆነ ነገራት፡፡ ነጯ ወፍም በጣም ተክዛ ለጥቁሩ አሞራ "እኔ ደስተኛ አደለሁም ከኔ የምትበልጥ ማራኪ ፒኮክ የምትባል አለች እሷ በጣም ታምራለች በጣም ውብ ናት ሰዎች ይወዷታል ከኔ ይልቅ በሷ ይማረካሉ፡፡ እኔ አላምርም" አለችው፡፡

አሞራውም ፒኮክ ያለችበትን ጠይቆ እየበረረ ሄደ ፒኮክ ፓርክ ውስጥ ተቆልፎባት ሰዎች ሲጎበኟት አያትና ጠጋ ብሎ አናገራት፡፡ "ፒኮክ ሆይ አንቺ በጣም ታምሪያለሽ፤ በጣም ውብ ነሽ፤ ሰዎች ይወዱሻል እኔ ግን እንደምታይኝ ነኝ እድለ ቢስ ነኝ" አላት፡፡ ፒኮክ ሆዬ ምን ብትለው ጥሩ ነው ፈገግ ብላ "አንተ አሞራ አንተ እድለኛ ነህ፡፡ እኔ ሰዎች ታምራለች ብለው ኢኸው እዚህ ሳጥን ውስጥ ቆልፈውብኝ የነሱ መዝናኛ ሆኛለሁ፤ አንተ ወደ ፈለክበት በነፃነት ትበራለህ፤ እኔ ግን እዚሁ ተቀምጬ የነሱ ፎቶ ማድመቂያ ከመሆን ውጪ ወደፈለኩበት የመንቀሳቀሱ ነፃነት የለኝም፤ እድለኛ ነህ ነፃነትን የመሰለ ምንም ነገር የለም፡፡ ይህ የምታየው ሰማይ ያንተ ነው፤ በነፃነት ብረር፤  ነፃነትን የመሰለ ደስታ የለም ሌሎችን ለመምሰል ስትጥር ነው ደስታህን የምታጣው" አለችው አሉ!!!

ነፃነትን የመሰለ ሀብት የለም፡፡

መልካም ቀን!

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

02 Jan, 11:37


ህፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና!

ዉድ የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን ቤተሰቦችና ወዳጆች በሙሉ የፊታችን ዕሁድ ታህሳስ 27 ከ3:00ጀምሮ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ፕሮግራሞች ይከበራል በመሆኑም በዚህ ልዩ የአምልኮ ቀን ከወዳጆቻሁና ከቤተሰቦቻችሁ ጋር በመሆን የነገስታት ንጉስ የሆነው ጌታ ኢየሱስን እንዲያመልኩት ተጋብዛችኋል!!!


ማሳሰቢያ፦ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጡ ጌጠኛ ልብሳችሁን መልበሳችሁን አትዘንጉ!!!

👉ይህ ማስታወቂያ ለቅዱሳን እንዲደርስ share በማድረግ ቤተክርስቲያንን ያገልግሉ!!!

እንደተባረካችሁ ቆዩ!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

02 Jan, 05:37


የተወደዳችሁ የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን ቤተሰቦችና ወዳጆች በሙሉ የጌታ ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ እያልን ይህን ማስታወቂያ በምትጠቀሙባቸው social ሚዲያዎች በሙሉ profile በማድረግ ቤተክርስቲያንን ያገልግሉ።

እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይባርካችሁ!!!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

02 Jan, 04:07


#አቋም፦

#አቋም እግዚአብሔር እናንተን ለመረዳት ወደ ህይወታችሁ #እንዲመጣ ከሚያደርጉ #መንፈሳዊ #መርሆዎች መካከል #አንዱ ሲሆን #መወላወል ደግሞ የእግዚአብሔርን #ዕርዳታ እንዳታዩ ከሚያደርጉ #መጋረጃዎች መካከል #አንዱ ነው።#ዛሬን #በእግዚአብሔር #ነገን #በስጋ #ለባሽ የሚታመን #ሰው ከእግዚአብሔር የሆነውን #ዕርዳታ #መቼም አያይም።

📜“ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው።”ያዕቆብ 1፥7-8


#እግዚአብሔር #ደባል ዕረዳት #አይደለም ብቸኛ ዕረዳት ነው።በእናንተ ቤት #እግዚአብሔር #እና #እግዚአብሔር እንጂ #እግዚአብሔር እና #ሌላ አይፈልግም።

እግዚአብሔር #የሚረዳው #አማራጭ #የሌለውን #ሰው ነው።#አማራጭ ያጣችሁበት #ወቅት #የጭንቅ ጊዜ #ሳይሆን #የህይወታችሁ #ዉዱ #ጊዜ ነው።#ምክንያቱም #የእግዚአብሔርን #ዕርዳታ #የምታዩበት #ጊዜ #ስለሆነ #ነው።


📜መዝሙር 121
¹ ዓይኖቼ ወደ ተራሮች አነሣሁ፤ ረዳቴ ከወዴት ይምጣ?
² ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።

ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነውን ዕርዳታ የምታዩበት ጊዜው አሁን ነው!!!

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

01 Jan, 19:06


“በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም፤ በፍርድም በሚነሣብሽ ምላስ ሁሉ ትፈርጂበታለሽ። የእግዚአብሔር ባሪያዎች ርስት ይህ ነው፥ ጽድቃቸውም ከእኔ ዘንድ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር። ኢሳይያስ 54፥17

🤚ተወዳጆች በእናንተ ላይ የተሰራ ማንኛውም የጨለማ ሥራ በኢየሱስ ስም ከዚህ ምሽት ጀምሮ አይከናወንም።።።።።።።።።።።በኢየሱስ የተቀባ ስም በእግዚአብሔር መንፈስ ተቀደሙምክራቸውን እጃቸው እንዳይፈፅመው የተኮለኞችን ሃሳብ ከንቱ አደርጋለሁ ያለ እግዚአብሔር በኢየሱስ ስም በዚህ ሌሊት ምክራቸው ይፍረስ ሃሳባቸው ላይሰበሰብ ይበተን🤚🤚🤚

ተፈፀመ አሜን!!!!

እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!!!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

01 Jan, 04:21


ህፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና!

ዉድ የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን ቤተሰቦችና ወዳጆች በሙሉ የፊታችን ዕሁድ ታህሳስ 27 ከ3:00ጀምሮ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ፕሮግራሞች ይከበራል በመሆኑም በዚህ ልዩ የአምልኮ ቀን ከወዳጆቻሁና ከቤተሰቦቻችሁ ጋር በመሆን የነገስታት ንጉስ የሆነው ጌታ ኢየሱስን እንዲያመልኩት ተጋብዛችኋል!!!


ማሳሰቢያ፦ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጡ ጌጠኛ ልብሳችሁን መልበሳችሁን አትዘንጉ!!!

👉ይህ ማስታወቂያ ለቅዱሳን እንዲደርስ share በማድረግ ቤተክርስቲያንን ያገልግሉ!!!

እንደተባረካችሁ ቆዩ!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

01 Jan, 04:08


ሌላ ሰው ሊያስቆማችሁ እንደሚችል ታስባላችሁ? ማንም ሊያስቆማችሁ አይችልም! ተግዳሮቶች ሊያስቆማችሁ አይችሉም፤ እናንተን ሊያቆማችሁ የሚችለው ብቸኛ ሰው ራሳችሁ ብቻ ናችሁ።

       እግዚአብሄር ለበለጠ ነገር እያዘጋጃችሁ ነው!ጠላት እናንተን ወደኃላ ሊያስቀራችሁ የሚችለውን ተግዳሮቶች እየተጠቀመ እንዳለ ያስባል፤ እውነታው ግን ወደፊት እንድትቀጥሉ እግዚአብሄር እየተጠቀመበት መሆኑ ነው። እግዚአብሄር የዲያብሎስን ስራ መልሶ ማጥቃት ላይ አይደለም ይልቁኑ ከዛ ውስጥ መልካም እንዲወጣ እያደረገ እንጂ። ዲያብሎስ ነው እግዚአብሄር ታላቅ ነገር ሲያደርግ ሲያይ በክፉ ምላሽ የሚሰጠው ነገር ግን አትጨነቁ፤ ቃሉን ማድረግ ቀጥሉ።

          አስታውሱ እግዚአብሄር ብርሀንን ከጨለማ ውስጥ አወጣው እንጂ ብርሃንን ለጨለማው አላመጣለትም። ራሳችሁን ቀና አድርጉ እግዚአብሄር ጠንካራ ውጊያዎችን ለጠንካራ ወታደሮች ይሰጣል።

         በህይወት ውስጥ የሚያጋጥማችሁ ተግዳሮቶች የበታች እንደሆናችሁ እንዲያስባችሁ አትፍቀዱ። አንድ ቀስት የሚወነጨፈው ወደኃላ በተለጠጠ መጠን ነው። ሕይወት በተግዳሮቶች ወደኃላ እየለጠጠቻችሁ በሚመስልበት ጊዜ ወደ አንድ የላቀ ነገር  እየተወነጨፋችሁ እንደሆነ አስቡና ለራሳችሁ ትኩረት መስጠትን አስተምሩት!

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

31 Dec, 09:45


የመለኮታዊ በቀል ምሽት

“እግዚአብሔር የበቀል አምላክ ነው፤ የበቀል አምላክ ተገለጠ።” መዝሙር 94፥1

የተወደዳችሁ የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን ቤተሰቦችና ወዳጆች በሙሉ ነገ ዕሮብ ታህሳስ 23 ከ11:00 ጀምሮ ልዩ የአምልኮና ጨለማዎችን የመበቀል ልዩ የሆነ የመለኮታዊ ፍርድ ጉባኤ ይኖረናል።በመሆኑም በዚህ የመለኮታዊ በቀል ምሽት ከቤተሰቦቻችሁና ከወዳጆቻችሁ ጋር በመገኘት ጌታን ያመልኩ ዘንድ ተጋብዛችኋል።


እንደተባረካችሁ ቆዩ

የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን!!!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

31 Dec, 06:13


ሁሉም ሰው አይጠቅምህም ሁሉም ሰው አይጎዳህም።በህይወት የሚያስፈልገህ ሰዎች ሁሉ ሳይሆኑ አንድ የታመነ ሰው ነው።አንድ ታማኝ ሰው የብዙዎች ዋጋ አይተምነው።በብዙዎች መታጀብ ብዙ ጉልበት እንዳይመስልህ በብዙዎች መክበብ ብዙ ርቅት የሚያስጉዝህ እንዳይመስለህ በብዛቱ ልክ ብክነቱ ያው ነው።እግዚአብሔር በታመኑ ሰዎች ይባርካችሁ።

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

31 Dec, 05:01


sunday service

ዘዳግም 33
²⁶ ይሹሩን ሆይ፥ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥ በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም።
²⁷ መኖሪያህ የዘላለም አምላክ ነው፥ የዘላለምም ክንዶች ከአንተ በታች ናቸው፤ ጠላትህን ከፊትህ አውጥቶ፦ አጥፋው ይላል።

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

30 Dec, 09:19


#በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፕላን የተሳፈረ ሰውዬ የበረራ አስተናጋጇ በሰጠችው ጥቆማ መሰረት የአውሮፕላኑ መጸዳጃ ቤት ውስጥ መጠቀም ይጀምራል። ታዲያ በመሐል አንዲት ቀይ ማብሪያና ማጥፊያ የምትመስል ነገር ያይና ነካ ያደርጋታል። በዚህ ቅፅበት አውሮፕላኑ በሐይል መንገጫገጭና ወደ ጎን ማጋደል ይጀመራል። ሰውዬውም ደንግጦ ወይኔ ሳላውቅ የማይነካ ነገር ነክቼ ሕዝብ ጨረስኩኝ ብሎ በነካት ቀይ ነገር ይጸጸታል። ከጥቂት ቆይታ በኃላ ግን መንገጫገጩ ይቆምና ጨርሶ ከመጸዳጃ ቤት ይወጣል። ሁሉም ሰው "አንተ የማትረባ! ጨርሰኸን ነበር እኮ!" ብሎ ይጮህብኛል ብሎ ቢጠብቅም ዞር ብሎ ያየው ሰው እንኳን አልነበረም።
    
መቀመጫው ላይ እንደደረሰም አጠገቡ የተቀመጠውን ሰው ቀስ እና ስቅቅ ብሎ "ይቅርታ የማይነካ ነገር ነክቼ ጨርሻቹ ነበር አይደል?" ይለዋል።  ሰውዬውም "አረ በፍጹም እንደዛ እንዳታስብ! ይህን ያሕል ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮች እኮ መፀዳጃ ቤት ውስጥ አይደረጉም ...ካፒቴኑ ያለበት ክፍል ውስጥ ነው ያሉት። አጋጣሚ ነው ትንሽ የአየሩ ሁኔታ አስቸጋሪ ስለሆነ ነው አውሮፕላንኑ የተንገጫገጨው" ይለዋል።
    
ብዙ ጊዜ ሰዋች እንደዚህ ያስባሉ። የሆነች ነገር ነክተው ሕይወትህን የሚያንገጫግጩ እና መጨረሻህን የሚወስኑ ይመስላቸዋል። የረሱት ነገር ቢኖር ይህን ያክል ጥንቃቄ የሚፈልገው ነገር እነሱ አጠገብ ሳይሆን የሕይወትህ ካፒቴን ጋር እንዳለ ነው። እንደዛማ ባይሆን ኖሮ ቀይዋን ነገር እየጠቀጠቁ ሕይወታችንን መንገጫገጭ ብቻ ያደርጉት ነበር። ምስጋና ለካፒቴኑ ይሁንና እንደዚሕ አይነት ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮችን በሱ እጅ ብቻ እንዲገኙ አድርጓቸዋል።

ዋና ነገሬ ያለው እኔና ፈጣሪ ጋር ነው በማለት በእረፍት እንኑር።

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

30 Dec, 08:33


ህፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና!

ዉድ የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን ቤተሰቦችና ወዳጆች በሙሉ የፊታችን ዕሁድ ታህሳስ 27 ከ3:00ጀምሮ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ፕሮግራሞች ይከበራል በመሆኑም በዚህ ልዩ የአምልኮ ቀን ከወዳጆቻሁና ከቤተሰቦቻችሁ ጋር በመሆን የነገስታት ንጉስ የሆነው ጌታ ኢየሱስን እንዲያመልኩት ተጋብዛችኋል!!!


ማሳሰቢያ፦ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጡ ጌጠኛ ልብሳችሁን መልበሳችሁን አትዘንጉ!!!

👉ይህ ማስታወቂያ ለቅዱሳን እንዲደርስ share በማድረግ ቤተክርስቲያንን ያገልግሉ!!!

እንደተባረካችሁ ቆዩ!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

30 Dec, 04:07


ዘዳግም 33
²⁶ ይሹሩን ሆይ፥ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥ በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም።
²⁷ መኖሪያህ የዘላለም አምላክ ነው፥ የዘላለምም ክንዶች ከአንተ በታች ናቸው፤ ጠላትህን ከፊትህ አውጥቶ፦ አጥፋው ይላል።

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

29 Dec, 19:58


https://t.me/c/2020624729/10444

የተወደዳችሁ የኃያላን መቅደስ ቤተሰቦችእና ወዳጆች

ነገ ሰኞ  ከማለዳ 12:00 ጀምሮ ሳምንቱን የምንዋጅበትና  እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት የቴሌግራም  ቀጥታ ስርጭት ይኖረናል።

ስለሆነም  በኢትዮጲያ ሰአት አቆጣጠር  ከጠዋቱ 12:00 ላይ ከላይ ☝️☝️ "Join" የምትለውን ምልክት በመጫን ሳምንቱን እንዲዋጁና እግዚአብሔርን በውዳሴና በምስጋና በማክበር እንዲጀምሩ ተጋብዘዋል!


#እንደተባረካችሁ ቆዩ!

የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

29 Dec, 13:46


ህፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና!

ዉድ የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን ቤተሰቦችና ወዳጆች በሙሉ የፊታችን ዕሁድ ታህሳስ 27 ከ3:00ጀምሮ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ፕሮግራሞች ይከበራል በመሆኑም በዚህ ልዩ የአምልኮ ቀን ከወዳጆቻሁና ከቤተሰቦቻችሁ ጋር በመሆን የነገስታት ንጉስ የሆነው ጌታ ኢየሱስን እንዲያመልኩት ተጋብዛችኋል!!!


ማሳሰቢያ፦ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጡ ጌጠኛ ልብሳችሁን መልበሳችሁን አትዘንጉ!!!

👉ይህ ማስታወቂያ ለቅዱሳን እንዲደርስ share በማድረግ ቤተክርስቲያንን ያገልግሉ!!!

እንደተባረካችሁ ቆዩ!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

28 Dec, 12:35


#የመንፈስ_ቅዱስ_ቀን

ነገ ዕሁድ ታህሳስ 20 ከማለዳው 3:00 ጀምሮ ልዩ የአምልኮና የእግዚአብሔርን ሀይል የመቀበል የመንፈስ ቅዱስ ጊዜ ይኖረናል።

በዚህ የተወደድ የመንፈስ ቅዱስ ቀን ከቤተሰቦቻችሁና ከወዳጆቻችሁ ጋር በመገኘት ጌታን በአንድነት እንዲያከብሩ ተጋብዛችኋል!!!

እንደተባረካችሁ ቆዩ!!!

የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

28 Dec, 07:26


ዕውቀት የአዕምሮ ብርሃን ነው!!!

"ዕውቀታችሁ ካልተፈወሰ ሃሳባችሁ አይፈወስም ምክኒያቱም ሃሳባችሁ የዕውቀታችሁ ውጤት ነውና።ሃሳባችሁ ካልተፈወሰ ንግግራችሁ አይፈወስም ምክኒያቱም  ንግግራችሁ የሃሳባችሁ ውጤት ነውና።ንግግራችሁ ካልተፈወሰ ድርጊታችሁ አይፈወስም ድርጊታችሁ የንግግራችሁ ውጤት ነውና።ድርጊታችሁ ካልተፈወሰ ብርሃናችሁ አይታይም።

“መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።”
  — ማቴዎስ 5፥16

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

27 Dec, 12:22


#የመንፈስ_ቅዱስ_ቀን

የፊታችን ዕሁድ ታህሳስ 20 ከማለዳው 3:00 ጀምሮ ልዩ የአምልኮና የእግዚአብሔርን ሀይል የመቀበል የመንፈስ ቅዱስ ጊዜ ይኖረናል።

በዚህ የተወደድ የመንፈስ ቅዱስ ቀን ከቤተሰቦቻችሁና ከወዳጆቻችሁ ጋር በመገኘት ጌታን በአንድነት እንዲያከብሩ ተጋብዛችኋል!!!

እንደተባረካችሁ ቆዩ!!!

የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

27 Dec, 04:37


የማትከብሩበት ቦታ አትቆዩ

አንደ ሊትር ውሃ፦

👉ሱቅ 30 ብር

👉መለስተኛ ሆቴል 50 ብር

👉ትልቅ ሆቴል 150 ብር

👉ኤርፓርት 250 ብር ይሸጣል


አስተውሉ ተመሳሳይ ውሃ በተለያየ ዋጋ ማለት ነው።ለምን? ከሆነ ጥያቂያችሁ፦ጉዳዩ ከውሃው ሳይሆን ውሃው ከተገኝበት ቦታ ነው።

አንድ አይነት ውሃ በተለያየ ቦታ የተለያየ ዋጋ ካለው በተመሳሳይ የሰው ዋጋ አንድ አይነት ሆኖ በተገኝበት ቦታ ይውሰናል።ይህን በመረዳት ዋጋችሁን ከሚያሳንስ ከማንኛውም ዉሎና ቦታ ፈጥናችሁ ውጡና ዋጋችሁ የሚጨምርበት ቦታ ተገኙ።

አንድ ተራ ውሃ ቦታ ስለቀየረ ብቻ ይህን ያህል የዋጋ ልዩነት ካመጣ ማንም ሰው የከበረ ቦታ መርጦ የከሰረና የቀለለ ሊሆን አይችልም።ዋጋ ከማታወጡበት ዉሎና ግንኙነት ሽሹ!!!!

መልካም ቀን!!!

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

26 Dec, 04:27


ጠላትህ ፊትህን ሊያበላሸው ይፈልጋል።አልቃሽና ትኩዝ የተከፋና ሀዘንተኛ ምስኪንና የተረበሸ ፊት እንዲኖርህ ይፈልጋል።እግዚአብሔር የፈጠረውን ፍልቅልቁን ሰው ወስዶ ጨለማ የለበሰ ሰው ሊያደርግህ ያደባል።በማንኛውም እንቅስቃሴህ ደስታህን ይዋጋል።አንተ ግን ውድ የሆነውን የእግዚአብሔር ደስታ ከመጽናናት አምላክ ተቀበለህ የፀሎትና የፆምን ቅባት ተቀብተህ አብራ እንጂ አትጨልም።

“እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።”
  — ዕንባቆም 3፥18

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

25 Dec, 13:47


ሰላም የተወደዳችሁ የኃያላን መቅደስ ቤ/ክ ቤተሰቦችና ወዳጆች በሙሉ ፀጋና ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን!!!

ነገ ሐሙስ ታህሳስ 17 ከምሽቱ 11:30 - 01:30 የሚቆይ  በእህቶች ህብረት የሚዘጋጅ      "ኤልሮኢ" የተሰኘው  ፕሮግራማችን ይደረጋል፣ በዕለቱ ሁላችሁ የእግዚአብሔር ሴት ልጆች ትገኙ ዘንድ ተጋብዛችኋል!!!

እንደተባረካችሁ ቆዩ!!!
ከእህቶች ህብረት የአገልግሎት ዘርፍ

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

25 Dec, 10:26


#ዛሬ_ምሽት_ከ11:00ጀምሮ

     በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን

“የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነውና፤ በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን።መዝሙር 36፥9

#share በማድረግ ቤተክርስቲያን ያገልግሉ!

#Emmanuel-እግዚአብሔር_ከእኛ_ጋር_ነው!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

25 Dec, 03:43


ከያዛችሁ #ችግር የያዛችሁት #እግዚአብሔር ይበልጣል ።ውጫችሁን #ለውስጣችሁ አትንገሩት #የውስጣችሁን ለውጫችሁ ንገሩት።ምክኒያቱም ነገ #የሚወርሳችሁ ከውጪ #የምትሰሙት የውርደት ድምፅ ሳይሆን ከውስጥ የምትሰሙት የክብር ድምፅ  ነው።

ህይወት ያለው ነገር የሚወጣው ከውስጥ ወደ ውጪ እንጂ ከዉጪ ወደ ውስጥ አይደለም ።
ዙሪያችሁ #በፀጥታም ተሞላ #በጩህትም ተሞላ #እግዚአብሔር ከእናንተ ጋራ ነው፡፡


Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

24 Dec, 11:33


#ነገ_ዕሮብ_ታህሳስ 16 ከ11:00ጀምሮ

     በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን

“የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነውና፤ በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን።መዝሙር 36፥9

#share በማድረግ ቤተክርስቲያን ያገልግሉ!

#Emmanuel-እግዚአብሔር_ከእኛ_ጋር_ነው!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

24 Dec, 03:57


“የብርሃኑ ፍሬ በበጎነትና በጽድቅ በእውነትም ሁሉ ነውና ለጌታ ደስ የሚያሰኘውን እየመረመራችሁ፥ እንደ ብርሃን ልጆች ተመላለሱ፤”
— ኤፌሶን 5፥9-10

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

23 Dec, 15:28


                 ስኬት/Success/

ስኬት የበለፀገ አስተሳሰብ ነው፡፡የስኬት መጀመሪያ ወፍራም ገንዘብ ሳይሆን የተፈወሰ አስተሳሰብ ነው፡፡ትክክለኛ ስኬት የሚጀመረው ከትክክለኛ አስተሳሰብ ነው፡፡

ስኬት መሰብሰብ ወይም ማከማቸት ሳይሆን ስኬት መለወጥ ነው፡፡ስኬታችሁ የሚወሰነው በሰበሰባችሁት ነገር ወይም ባከማቻችሁት ነገር ልክ ሳይሆን በለወጣችሁት ነገር ልክ ነው፡፡

ስኬት ምድር ላይ መድመቅ ሳይሆን ስኬት ለሰማይ አክሊል መሮጥ ነው፡፡ስኬታችሁ ምድር የምታጨበጭብለት ብቻ ከሆነ በስተመጨረሻ ኪሳራችሁ ይሆናል፡፡ስኬታችሁ ሰማይ የሚያጨበጭብለት ከሆነ በስተመጨረሻ ብድራታችሁ ይሆናል፡፡ስለዚህ ለስኬት ስትሮጡ ለምድር ሳይሆን ለስማይ ይሁን!

ሰኬት ከሰዎች ተሽሎ መገኝት አይደለም፡፡ስኬት ከትናቱ ማንነታችሁ ዛሬ ቅድማችሁ መገኘት ነው፡፡ትክክለኛ ስኬት ከራስ ጋር የሚድረግ ዉድድር ነው፡፡

ስኬት መሆን የምትፈልጉትን ማለም ሳይሆን መሆን የምትፈልጉት መኖር ነው፡፡ስኬት ስታልሙት ሩቅ ነው ስትኖሩት ቅርብ ነው፡፡

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

23 Dec, 06:06


ማንኛውም እንቅስቃሴአችሁ ውስጥ የእግዚአብሔር ሞገስ ካልተጨመረበት ውጤታችሁ የጥረታችሁ ብቻ ይሆናል፡፡

🤚በዚህ ሳምንት የእግዚአብሔር ሞገስ ህይወታችሁን ለማቅናት ከእናንተ ጋር ይሁን!በኢየሱስ የተቀባ ስም የእናንተ የሆነውን ሁሉ የእግዚአብሔር ሞገስ ያግኘው!!!

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

22 Dec, 13:58


የተወደዳችሁ የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን ቤተሰቦችና ወዳጆች በሙሉ የጌታ ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ እያልን ይህን ማስታወቂያ በምትጠቀሙባቸው social ሚዲያዎች በሙሉ profile በማድረግ ቤተክርስቲያንን ያገልግሉ።

እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይባርካችሁ!!!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

22 Dec, 05:21


ዛሬ ዕሁድ ታህሳስ 13 ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ወንድሞች ህብረት እንፍጠር!!!

ወደ ቤተክርስቲያን ሄዳችሁ ነፃ የምትወጡት በሰይጣን የሆነባችሁን ሲነገራችሁ ሳይሆን በክርስቶስ የሆነላችሁን ሲነገራችሁ ነው፡፡


“እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው።ዮሐንስ 8፥32

🤚መልካም የበረከት ዕሁድ!

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

22 Dec, 03:54


Channel photo updated

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

21 Dec, 12:03


የበረከት ጽዋ -


ነገ ዕሁድ ታህሳስ 13 ከ3:00 ጀምሮ ልዩ የአምልኮ የጌታ ራት ፕሮግራም!!!

1ኛ ቆሮንቶስ 10
¹⁶ የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን?
¹⁷ አንድ እንጀራ ስለ ሆነ፥ እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን፤ ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና።

የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን ቤተሰቦችና ወዳጆች በሙሉ ዕሁድ ለአምልኮና ለበረከት እንገናኝ።

#Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው።

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

21 Dec, 03:31


የበረከት ጽዋ -


ነገ ዕሁድ ታህሳስ 13 ከ3:00 ጀምሮ ልዩ የአምልኮ የጌታ ራት ፕሮግራም!!!

1ኛ ቆሮንቶስ 10
¹⁶ የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን?
¹⁷ አንድ እንጀራ ስለ ሆነ፥ እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን፤ ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና።

የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን ቤተሰቦችና ወዳጆች በሙሉ ዕሁድ ለአምልኮና ለበረከት እንገናኝ።

#Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው።

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

21 Dec, 03:21


እግዚአብሔር ሁለተኛ ረዳት ሆኖ አያውቅም ብቸኛ ረዳት እንጂ።እግዚአብሔርን መጠጋት ምርጫችሁ ከሆነ ሌሎች አማራጮችን መተው ግዴታችሁ ይሆናል።በእግዚአብሔር ነገር ለመኖር ከእናንተ ነገር መውጣት አለባችሁ።ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ለመልበስ የራስን ነገር ማውለቅ ተገቢ ነው።

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

20 Dec, 12:02


እግዚአብሔር የሚያሳርፍችሁ ሁሉን ነገር እየሰጣችሁ አይደለም፡፡እግዚአብሔር የሚያሳርፍችሁ በምንም የማይተካውን ነገር ግን ሁሉን ነገር መተካት የሚችለውን ህልውናውን በመስጠት ነው፡፡ነፍሳችሁ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የምታርፈው የእግዚአብሔርን አብሮት ስታይና በህልውናው ስትነካ ብቻ ነው፡፡በጌታ በኢየሱስ ስም በእግዚአብሔር ህልውና ውስጥ መሰወርና ማረፍ ይሁንላችሁ!

"፤ በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል። " (መዝሙረ ዳዊት 91: 1)

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

20 Dec, 04:26


የበረከት ጽዋ -


የፊታችን ዕሁድ ታህሳስ 13 ከ3:00 ጀምሮ ልዩ የአምልኮ የጌታ ራት ፕሮግራም!!!

1ኛ ቆሮንቶስ 10
¹⁶ የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን?
¹⁷ አንድ እንጀራ ስለ ሆነ፥ እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን፤ ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና።

የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን ቤተሰቦችና ወዳጆች በሙሉ ዕሁድ ለአምልኮና ለበረከት እንገናኝ።

#Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው።

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

20 Dec, 03:56


ሰው የሚኖረው ባለው ልክ ሳይሆን ባየው ልክ ነው:: አንዳንዶች ከአንተ በላይ እያላቸው ነገር ግን ከአንተ በታች ሊኖሩ ይችላሉ::

የኤልሳዕ ሎሌ ያየው የሶርያ ጭፍራና ፈረሶች ሰረገሎችን ነው:: ኤልሳዕ ደግሞ ያየው ከእርሱ ጋር ያሉትን የእሳት ፈረሶችና ሰረገሎችን ነበር::የኤልሳዕ ሎሌ ቦታውን አልቀየረም ነገር ግን እይታው ተቀየረ::

"የሰውነት መብራት ዓይን ናት። ዓይንህ እንግዲህ ጤናማ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ይሆናል" የማቴዎስ ወንጌል 6:22

"እይታችን አይበላሽብን" "ነገር በዓይን ይገባል"

"የእግዚአብሔር ሰው ሎሌ ማለዳ ተነሥቶ በወጣ ጊዜ፥ እነሆ፥ በከተማይቱ ዙሪያ ጭፍራና ፈረሶች ሰረገሎችም ነበሩ። ሎሌውም፦ ጌታዬ ሆይ፥ ወዮ! ምን እናደርጋለን? አለው። እርሱም፦ ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ አለው። ኤልሳዕም፦ አቤቱ፥ ያይ ዘንድ ዓይኖቹን፥ እባክህ፥ ግለጥ ብሎ ጸለየ። እግዚአብሔርም የብላቴናውን ዓይኖች ገለጠ፥ አየም እነሆም፥ በኤልሳዕ ዙሪያ ያሉት የእሳት ፈረሶችና ሰረገሎች ተራራውን ሞልተውት ነበር" መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 6:15-17

- እይታ የሚንሄድበትን ርቀት ይወስናል

- እይታ አቅጣጫን ያስቀይራል

ላየኸው ነገር ለመሮን ሞክር እንጂ ለሰው ለማስረዳት አትድከም:: ምክንያቱም አንተ ያየኸውን ሌሎች ላያዩት ላይረዱት ይችላሉ:: ራዕይ ይተገበራል እንጂ አይሰበክም:: ያየኸውን የሰበክ ዕለት እንደ ዮሴፍ ስደትና መከራ በራስህ ላይ ልትጋብዝ ትችላለህ:: ዘፍጥረት 37:4-11

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

19 Dec, 13:20


እግዚአብሔርን ለሰዎች ከምታሳዩበት ድንቅ ብርሃን መልካም ሥራ ይባላል።

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

30 Nov, 09:13


ነገ ዕሁድ ህዳር 22 ከ3:00 ጀምሮ

#ልዩ_የአምልኮና_የመለኮታዊ_ምሪት_ቀን

ሁላችንም በኃያላን ጉባኤ እንገናኝ!!!

#እንደተባረካችሁ_ቆዩ


የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን!!!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

30 Nov, 04:41


በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ።ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል።ከቀደሙህ መቅዳት፣ከተጎዱ መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ።የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር አይጠበቅብህም።ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትህትና መጠየቅ ይበቃሃል።

ካላየሁ አላምንም አትበል ልታየው የምትናፈቀውን ዓለም አስቀድመው ባዩት ሰዎች በተከፈተ ጆሮ ተመልከተው።ይህ ደግሞ ከብክነት የምታመልጥበት መፅሐፍ ቅዱሳዊ ጥበብ ነው።


📜“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ እነርሱ ግን፦ አንሄድባትም አሉ።”
  — ኤርምያስ 6፥16

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

29 Nov, 18:11


https://t.me/+Ux6uZKADjZxkYjI0

የተወደዳችሁ የኃያላን መቅደስ ቤተሰቦች

ዛሬ አርብ  ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ ልዩ የሆነ የፀሎትና የቃል ጊዜ ይኖረናል።

🕎ፕሮግራሙን ለመካፈል ☝️ "Join" የምትለውን ምልክት በመጫን ኘሮግራሙን  ይካፈሉ!
🕎 በቴሌግራም ላይ ያሉ ቤተሠብና ጓደኞችዎን በመጋበዝ ቤተክርስቲያንን ያገልግሉ!

እንደተባረካችሁ ቆዩ!

የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን.

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

29 Nov, 18:01


MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA pinned Deleted message

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

29 Nov, 11:08


እግዚአብሔር እረኛዬ ነው

“እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።”
መዝሙር 23፥1

የፊታችን ዕሁድ ህዳር 22 ከ3:00 ጀምሮ

#ልዩ_የአምልኮና_የመለኮታዊ_ምሪት_ቀን

ሁላችንም በኃያላን ጉባኤ እንገናኝ!!!

#እንደተባረካችሁ_ቆዩ


የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን!!!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

29 Nov, 05:38


ልጆቻችን

Sunday school

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

29 Nov, 03:54


ኒውዮርክ ከካሊፎርኒያ በ 3 ሰዓት ትቀድማለች ነገር ግን ይህ ካሊፎርኒያን ቀርፋፋ  አያደርጋትም !ምክንያቱም የራሷ ጊዜ አላትና ፡፡

አንዳንድ ሰዉ በ22 አመቱ ይመረቃል ነገር ግን አሪፍ ስራ ለመያዝ 5 አመት ይፈጅበታል።
አንዳንዱ በ25 አመቱ የድርጅት ሃላፊ ሆኖ በ50 አመቱ ሲሞት ሌላዉ በ50 ዓመቱ ሃላፊ
ሁኖ እስከ 90 ዓመት ይኖራል።

ኦባማ በ55 ዓመቱ ኘሬዝዳንትነቱን ጨረሰ ነገር ግን ትራምፕ በ70 ዓመቱ ኘሬዝዳንትነቱን
ጀመረ! ይሄ ትራምፕን ኅላ ቀር
አያደርገዉም።ጊዜ በሕይወታችን ወሳኝ ነገር ነዉ ፡፡

ፈጣሪ በግዜዉ ሁሉን ነገር ዉብ ያደርጋል ፡፡
ስለዚህ.... ከሁሉ በኋላ የቀረን ወይም ወደፊት የቀደምን አይምሰለን!
ሁሉም ሰዉ የራሱ የሆነ የኑሮ ሩጫና የተፈጠረበት አላማ አለዉ!
ሁላችንም የራሳችን የሆነ የጊዜ ክልል አለን!


Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

28 Nov, 03:32


የእግዚአብሔር ክብር ጥጋብ የሚሆነው የእግዚአብሔር ክብር ርሃብ ለሆነው ሰው ብቻ ነው።ያልጠማችሁ የእግዚአብሔር ክብር መቼም ርካታ አይሆናችሁም።የእግዚአብሔር የክብሩን ጥጋብን የሚያመጣ ብቸኛ ምክንያት ርሃብ ይባላል።

እግዚአብሔር የተጠማ የእግዚአብሔርን ክብር ይረካል።እግዚአብሔርን የተራበ የእግዚአብሔር ክብር ይጠግባል።


መዝሙር 63
¹ አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፤ ነፍሴ አንተን ተጠማች፥ ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች እንጨትና ውኃ በሌለበት በምድረ በዳ።
² ኃይልህንና ክብርህን አይ ዘንድ እንዲሁ በመቅደስ ውስጥ ተመለከትሁህ።

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

27 Nov, 18:29


MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA pinned «#ክብርህን #ሳይ #እጠግባለሁ የሰው ልጅ የነፍስ ጥጋብ የእግዚአብሔር ክብር ነው።ምክንያቱም ሰው የተፈጠረው በሌላ ነገር እንዳይረካ በእግዚአብሔር ብቻ እንዲረካ ተደርጎ ስለሆነ ነው።በቀሪ ዘመናችሁ እግዚአብሔር ከክብሩ ያጥግባችሁ። “እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤ ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ።መዝሙር 17፥15 #Emmanuel የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.»

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

27 Nov, 18:29


#ክብርህን #ሳይ #እጠግባለሁ

የሰው ልጅ የነፍስ ጥጋብ የእግዚአብሔር ክብር ነው።ምክንያቱም ሰው የተፈጠረው በሌላ ነገር እንዳይረካ በእግዚአብሔር ብቻ እንዲረካ ተደርጎ ስለሆነ ነው።በቀሪ ዘመናችሁ እግዚአብሔር ከክብሩ ያጥግባችሁ።

“እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤ ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ።መዝሙር 17፥15


#Emmanuel

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

27 Nov, 12:53


ሰላም የተወደዳችሁ የኃያላን መቅደስ ቤ/ክ ቤተሰቦችና ወዳጆች በሙሉ ፀጋና ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን!!!

ነገ ሐሙስ ህዳር 19 ከ11:30 - 01:30 የሚቆይ ልዩ የእህቶች ህብረት የመክፈቻ ፕሮግራም ይኖራል ሁላችሁ የእግዚአብሔር ሴት ልጆች ተጋብዛችኋል!!!

እንደተባረካችሁ ቆዩ!!!
ከእህቶች ህብረት የአገልግሎት ዘርፍ

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

27 Nov, 10:13


ስጦታዬዬዬዬዬዬዬ!!!!

🙏🙏🙏🙏

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

26 Nov, 11:23


ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ

“እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤ ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ።መዝሙር 17፥15

#ነገ_ዕሮብ ህዳር 18 ከ11:00ጀምሮ

#የትምህርትና #የአምልኮ #የፀሎት_ምሽት

#ሁላችሁም_ተጋብዛችኋል

የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

26 Nov, 06:00


#የዕሁድ_አገልግሎት


ሐዋርያት 2
¹ በዓለ ኀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ፥
² ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፥ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው።
³ እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፤ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው።
⁴ በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር።

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

16 Nov, 16:19


ነገ ዕሁድ ህዳር 8 ከ3:00ጀምሮ

መለኮታዊ መጋረድ

#Holy_communion_service-የጌታ ራት ፕሮግራም

👉ነገ ዕሁድ ለቡራኬ በእግዚአብሔር ፊት እንገኝ።

እግዚአብሔር በስራ ላይ ነው።


የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን!!!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

15 Nov, 18:00


https://t.me/+Ux6uZKADjZxkYjI0

የተወደዳችሁ የኃያላን መቅደስ ቤተሰቦች

ዛሬ አርብ  ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ ልዩ የሆነ የፀሎትና የቃል ጊዜ ይኖረናል።

🕎ፕሮግራሙን ለመካፈል ☝️ "Join" የምትለውን ምልክት በመጫን ኘሮግራሙን  ይካፈሉ!
🕎 በቴሌግራም ላይ ያሉ ቤተሠብና ጓደኞችዎን በመጋበዝ ቤተክርስቲያንን ያገልግሉ!

እንደተባረካችሁ ቆዩ!

የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን.

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

15 Nov, 12:26


Holy communion service

የፊታችን ዕሁድ ህዳር 8 ከ3:00 ጀምሮ

#ልዩ_የአምልኮና_ወርሃዊ_የጌታ_ራት_ፕሮግራም


“ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ።ዮሐንስ 6፥56

#ሁላችንም ለበረከት በኃያላን ጉባኤ እንገናኝ!!!


#Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!!!

የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን.

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

15 Nov, 03:48


Holy communion service

የፊታችን ዕሁድ ህዳር 8 ከ3:00 ጀምሮ

#ልዩ_የአምልኮና_ወርሃዊ_የጌታ_ራት_ፕሮግራም


“ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ።ዮሐንስ 6፥56

#ሁላችንም ለበረከት በኃያላን ጉባኤ እንገናኝ!!!


#Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!!!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

13 Nov, 19:08


ኢየሱስ ለሰዎች ባገኝነው አጋጣሚ ሁሉ የምናወራው መልካም ዜናችን ነው።

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

13 Nov, 06:28


🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

13 Nov, 04:41


ክርስትና መብሰልሰል ሳይሆን መብሰል ነው፡፡በመብሰል ውስጥ መድረስ አለ።በመብሰል ውስጥ መጥቀም አለ።በመብሰል ውስጥ መፈለግ አለ።

በእግዚአብሔር መንግስት የምትበስሉትበመንግስቱ ሰለቆያችሁ በእግዚአብሔር ቃል ስለተሰራችሁ ነው፡፡

"፤ ከጊዜው የተነሳ አስተማሪዎች ልትሆኑ ሲገባችሁ፥ አንድ ሰው ስለ እግዚአብሔር ቃላት መጀመሪያ ያለውን የሕፃንነትን ትምህርት እንዲያስተምራችሁ እንደ ገና ያስፈልጋችኋልና፤ የሚያስፈልጋችሁም ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም። " (ወደ ዕብራውያን 5: 12)


Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

12 Nov, 11:47


የጌታ ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን!!!

ነገ ዕሮብ 11:00 ጀምሮ ልዩ የትምህርትና የሀይል ምሽት!

የተወደዳችሁ የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን ቤተሰቦችና ወዳጆች ነገ ዕሮብ  ጀምሮ ለተከታታይ ዕሮቦች የጀመርነው የማስታረቅ አገልግሎት ክፍል ሁለት  በተከፈተ ሰማይ የእግዚአብሔርን ቃል እንቀጥላለን  እንዲሁም ሀይልን እንቀበላለን።

በመሆኑም በእነዚህ የበረከትና ሀይል ምሽቶች በመገኝት ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነው ብርሃን እንድትካፈሉ ይሁን!!!

2ኛ ቆሮ 5
¹⁸ ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤
¹⁹ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ።


እንደተባረካችሁ ቆዩ!

#Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

12 Nov, 09:24


እግዚአብሔር የእደገና አምላክ ነው።እግዚአብሔር የእደገና አምላክ ባይሆን ኑሮ የከሰርነው ድሮ ነበር።በእግዚአብሔር እንደገና ከወድቅንበት ተነስተናል ከድካማችን በርትተናል።

🤚በዚህ በእግዚአብሔር የማይነጥፍ ባህሪ ልባርካችሁ የእንደገና አምላክ እንደገና ይጎብኛችሁ፣እንደገና ይያችሁ፣እንደገና ይስማችሁ፣እንደገና ያባከናችሁን ዘመን ይካሳችሁ፣እንደገና ያፅናናችሁ፣እንደገና ከጥፋት መንደር ነጥቆ ያውጣችሁ!!!

በኢየሱስ የተባረከ ስም አሜን!!!

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

12 Nov, 04:50


#የማይቀለበስ_ሀቅ

ወፍ በርራ በርራ አውሮፕላንም በርሮ በርሮ   ከመሬት   እንደማይቀሩ  ሁሉ ሰውም ኖሮ ኖሮ ከመሬት አይቀርምና እንደሚሞት ሆነህ የእውነት ኑር፡፡ኖርህ ኖርህ የማትጨርሰውን የዘላለም ህይውት ሁለት ጊዜ በማትኖረው የሀሰት ዓለም እንዳታበላሽው ተጠቀቅ፡፡

ክርስትና በሀሰት ዓለም የእውነት መኖር ነው፡፡

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

11 Nov, 16:33


#የዕሁድ_አገልግሎት

ሮሜ 3
²⁴ በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።
²⁵ እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው፤ ይህም በፊት የተደረገውን ኃጢአት በእግዚአብሔር ችሎታ ስለ መተው ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው፥
²⁶ ራሱም ጻድቅ እንዲሆን በኢየሱስም የሚያምነውን እንዲያጸድቅ አሁን በዚህ ዘመን ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው።

Romans 3 (KJV)
²⁴ Being justified freely by his grace through the redemption that is in Christ Jesus:
²⁵ Whom God hath set forth to be a propitiation through faith in his blood, to declare his righteousness for the remission of sins that are past, through the forbearance of God;
²⁶ To declare, I say, at this time his righteousness: that he might be just, and the justifier of him which believeth in Jesus.

#Emmanuel.

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

11 Nov, 07:37


መልካም ዜና

ህዳር 2017 ዓ.ም ትንቢታዊ ቃል፦

<<በበጉ ደም ድል የመንሳት ወር>>

🤚በዚህ ወር ከበጉ ደም የተነሳ ማንኛውንም መንፈሳዊ ሰልፍ ድል መንሳት ይሁንላችሁ!!!

🤚የትኛውም በህይወታችሁ ላይ የሰለጠነ የጨለማ አሠራር ከበጉ ደም የተነሳ በዚህ ወር ከእግራችሁ በታች የወደቀ ይሁን!!!

የእግዚአብሔር ቃል አጥፊው ፈፅሞ ጠፍቶአልና ከእንግዲህም ወዲህ በአንተ ዘንድ አያልፍምና ይሁዳ ሆይ አመትባሎችህን አድርግ እንደሚል በኢየሱስ ጌታ ስም በእናንተ ላይ የቆሙ አጥፊዎች በሙሉ በዚህ ወር ይጥፋ እግዚአብሔርም በዙሪያችሁ ካሉ ጠላቶች ያሳርፍችሁ!!!

ራእይ 12
¹⁰ ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ አሁን የአምላካችን ማዳንና ኃይል መንግሥትም የክርስቶስም ሥልጣን ሆነ፥ ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና።
¹¹ እነርሱም ከበጉ ደም የተነሣ ከምስክራቸውም ቃል የተነሣ ድል ነሡት፥ ነፍሳቸውንም እስከ ሞት ድረስ አልወደዱም።  
          
Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!!!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

11 Nov, 04:12


በዚህ ሳምንት ከእግዚአብሔር ቤት እንዲህ ባረክናችሁ!!!

🖐 "እግዚአብሔር ባሪያውን ያዕቆብን ታድጎታል በሉ።" ተብሎ እንደተፃፈ እንዲሁ የእግዚአብሔርን ትድግና የሚያውጅ የእልልታ ድምፅ ከጓዳችሁ ይሰማ! እስከ ምድር ዳርቻ የሚነገር የምስክርነት ቃል የሚሆን የምታመልኩት አምላክ ድንቅን ነገር በዚህ ሳምንት ያድርግላችሁ!!!

🖐 ይህ ሳምንት ከክርስቶስ ኢየሱስ ከደሙ ምልክት የተነሳ የሞት አዋጅ አልፎ ይሂድ፣ ማንኛውም በሕይወታችሁ ከተዘረጋ ወጥመድ የእግዚአብሔር አምላክ ኃይል ይታደጋችሁ፣ እናንተና የእናንተ የሆነው ሁሉ በመለኮት ጥበቃ ስርም ይሁን!!!

🖐 በፊታችሁ ባሉ ሰባት ቀናት እግዚአብሔር ይምራችሁ፣ የክርስቶስ ኢየሱስ ደም ስለ እናንተ ይጩኽላችሁ፣ ከጠላቶቻችሁም ይልቅ ያበርታችሁ! ውድቀታችሁን ሲጠብቁ እናንተ ግን በድል እና በከፍታ መራመድ ይሁንላችሁ፣ መርገማችሁን ወደ በረከት ይለውጥላችሁ፣ የአንበሶችን መንጋጋ ይስበርላችሁ!!!

🖐 " እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፥ ስሙም እግዚአብሔር ነው፥" ተብሎ እንደተፃፈ በዚህ ሳምንት ተዋጊው አምላክ ሰልፋችሁን ይሰለፍላችሁ፣ ውጊያችሁን ይዋጋላችሁ፣ ሙግታችሁን ይሟገትላችሁ፣ ከጠላትን ወጥመድ ያስመልጣችሁ፣ የክፋት ፍላፃ ይስበርላችሁ፣ በእናንተ ላይ የሚመከር ክፉ ምክር ከንቱ ያድርግላችሁ፣ ጠላቶቻችሁም እያዩ ራሳችሁን በዘይት ይቀባ፣ እየተመለከቱም ከፍ ከፍ ማለት ይሁንላችሁ!!!

🖐 ከበጉ ደም የተነሳ ከምስክርነታችሁም ቃል የተነሳ ድል የምትነሱበት የድል ሳምንት ይሁንላችሁ፣ "ሥራውም የተከናወነለት ሰው ሆነ" ተብሎ እንደተፃፈ ለምታምኑ ለእናንተ እግዚአብሔር አምላክ በሥራችሁ፣ በመውጣትና በመግባት መከናወን ይስጣችሁ!!!

ይህ የበረከት ቃል በኢየሱስ ክርስቶስ ክቡር ደም በእናንተ ላይ የፀና ይሁን!!! አሜን!!!

መልካም ሳምንት ይሁንላችሁ!!!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

10 Nov, 13:51


በኢየሱስ ደም ከእግዚአብሔር ቁጣ ያመለጠ ሰው የኢየሱስን በከበረ ምስጋና ያክብረው!!!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

10 Nov, 05:09


ቅዱሳን ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ወንድሞች ህብረት እግሮቻችን ይፍጠኑ!!!

“ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሄድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ። መዝሙር 122፥1

መልካም የመዋጅት ማለዳ!!!

ህዳር ወር እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!!!

#Emmanuel#Emmanuel#Emmanuel

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

09 Nov, 09:31


ነገ ዕሁድ ህዳር 1 ከ3:00 ጀምሮ

#ህዳርን_ወር_የመዋጅት_ትንቢታዊ_ጉባኤ

#የአምልኮና_የፀሎት_ጊዜ

#የኢየሱስን_ደም_ሀይል_መግለጥ

“የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።”
  — ዕብራውያን 12፥24

👉ዕሁድ ማለዳ በኃያላን ጉባኤ ለበረከት እንገናኝ

#Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!!!

የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን!!!

#ለቅዱስ share በማድረግ ያገለገሉ!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

09 Nov, 03:41


ለሰዎች መልካም ስታደርግ ራስህን እንደ ልዩ ፍጥረት እንዳትቆጥር ተጠንቀቅ።ምክንያቱም መልካም ማድረግ ልዪ መለያህ ሳይሆን ከእግዚአብሔር የተቀበልከው ማንነትህ ነው።ስለዚህ መልካም ስታደርግ ከባህሪህ እያካፈልክ እንጂ ልዩ ፍጥረት እየሆንክ አይደለም።

ከመልካም ተግባራቶችህ ጎን ለጎን ክርስቶስ እንዲታይ አድርግ እንጂ ራስህን ለሽያጭ አታቅረብ።ፎቶና ጡሩባዋ ዋጋ ታስከፍላለችና ለመልካም ተግባር ስትነሳ ጡሩባ አታስነፋ።

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

08 Nov, 14:42


የፊታችን ዕሁድ ህዳር 1 ከ3:00 ጀምሮ

#ህዳርን_ወር_የመዋጅት_ትንቢታዊ_ጉባኤ

#የአምልኮና_የፀሎት_ጊዜ

#የኢየሱስን_ደም_ሀይል_መግለጥ

“የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።”
  — ዕብራውያን 12፥24

👉ዕሁድ ማለዳ በኃያላን ጉባኤ ለበረከት እንገናኝ

#Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!!!

የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን!!!

#ለቅዱስ share በማድረግ ያገለገሉ!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

08 Nov, 13:44


https://t.me/+Ux6uZKADjZxkYjI0

የተወደዳችሁ የኃያላን መቅደስ ቤተሰቦች

ዛሬ አርብ  ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ ልዩ የሆነ የፀሎትና የቃል ጊዜ ይኖረናል።

🕎ፕሮግራሙን ለመካፈል ☝️ "Join" የምትለውን ምልክት በመጫን ኘሮግራሙን  ይካፈሉ!
🕎 በቴሌግራም ላይ ያሉ ቤተሠብና ጓደኞችዎን በመጋበዝ ቤተክርስቲያንን ያገልግሉ!

እንደተባረካችሁ ቆዩ!

የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን.

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

08 Nov, 12:53


የጌታ ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን!!!

ነገ ቅዳሜ 10:30 ጀምሮ ልዩ የትምህርትና የአምልኮ ጊዜ ይኖረናል !

የተወደዳችሁ የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን ወጣቶች ነገ ቅዳሜ ጥቅምት 30 “ለእኛ በዚህ መሆን መልካም ነው” በሚል ርዕሰ የእግዚአብሔርን ቃል እንማራለን ።

እንደተባረካችሁ ቆዩ!

#Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

08 Nov, 06:52


የፊታችን ዕሁድ ህዳር 1 ከ3:00 ጀምሮ

#ህዳርን_ወር_የመዋጅት_ትንቢታዊ_ጉባኤ

#የአምልኮና_የፀሎት_ጊዜ

#የኢየሱስን_ደም_ሀይል_መግለጥ

“የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።”
— ዕብራውያን 12፥24

👉ዕሁድ ማለዳ በኃያላን ጉባኤ ለበረከት እንገናኝ

#Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!!!

የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን!!!

#ለቅዱስ share በማድረግ ያገለገሉ!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

08 Nov, 03:25


ሰላማችሁ የሚወሰነው ነገ በሚሆንላችሁ ነገር ሳይሆን አሁን ከእናንተ ጋር ባለው ጌታ ነው፡፡ምክኒያቱም የእናተ ሰላም ከሚመጣ ነገር ጋር አብሮ የሚመጣ ከሚሄድም ነገር ጋር አብሮ የሚሄድ አይደለም፡፡የእናንተ ሰላም ለዘላለም ከእናንተ ጋር ነው እርሱም ኢየሱስ ነው፡፡

🤚በኢየሱስ የተቀባና የተባረከ ስም ከዚህ ቀን ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ ራሱ በውስጣችሁ በሁኔታዎች የማይደፈረስ ስላምና ደስታ ይሁናችሁ!!!

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

07 Nov, 04:11


የማስታረቅ አገልግሎት ተቀብለናል

📢ዛሬ በተሰጠን አዲስ ቀን ከእግዚአብሔር ከአምላክና ከአባታችን የተቀበለውን ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር የማስታረቅ አደራ እንፈፅም።

👉ዛሬ ጥቅም 28 ለአንድ ሰው የምስራቹን የእግዚአብሔር ማዳን መናገራችሁን አትዘንጉ ይህን ስታደርጉ የእግዚአብሔር እጅ ከእናንተ ጋር ትሰራለች።

2ኛ ቆሮ 5
¹⁸ ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤
¹⁹ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ።

#Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!!!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

06 Nov, 18:26


መዝሙር 96
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ለእግዚአብሔር አዲስ ምስጋናን አመስግኑ፤ ምድር ሁሉ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑ።
² እግዚአብሔርን አመስግኑ ስሙንም ባርኩ፥ ዕለት ዕለትም ማዳኑን አውሩ።
³ ክብሩን ለአሕዛብ ተኣምራቱንም ለወገኖች ሁሉ ንገሩ፤
⁴ እግዚአብሔር ታላቅ ምስጋናውም ብዙ ነውና፥ በአማልክትም ሁሉ ላይ የተፈራ ነውና።

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

06 Nov, 07:23


Don't miss it'

ዛሬ ምሽት ከ11:00 ጀምሮ

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

06 Nov, 04:44


🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

06 Nov, 04:38


ኢየሱስ የማያልቅ ፍቅር፣የማይደ ፈርስ ሰላም፣የማይቆም ደስታ ነው!!!
❤️
በዚህ ቀን በጌታ ደስ ይበላችሁ!!!

Emmanuel

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

05 Nov, 15:53


እግዚአብሔር ፀሎትህን ከሰማህ እምነትህም በዚያኑ ልክ ይጨምራል፡፡የፀሎትህ መልስ ካረፈደ ደግሞ ትዕግስትህን ይጨምረዋል፡፡ሙሉ በሙሉ ምላሽ ካልሰጠህ ግን በጣም የተሻለ ነገር አዘጋጅቶልሃል ማለት ነው፡፡የተሻለ ነገ እንጂ የተበላሸ ነገ የለህም፡፡
     
ለጻድቁ መልካም ይሆንልሃል በሉት!!!

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

05 Nov, 12:27


የጌታ ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን!!!

ነገ ዕሮብ 11:00 ጀምሮ ልዩ የትምህርትና የሀይል ምሽት!

የተወደዳችሁ የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን ቤተሰቦችና ወዳጆች ከነገ ዕሮብ ጥቅምት 27 ጀምሮ ለተከታታይ ዕሮቦች የማስታረቅ አገልግሎት በሚል ርዕሰ በተከፈተ ሰማይ የእግዚአብሔርን ቃል እንማራለን እንዲሁ ሀይልን እንቀበላለን።

በመሆኑም በእነዚህ የበረከትና ሀይል ምሽቶች በመገኝት ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነው ብርሃን እንድትካፈሉ ይሁን!!!

2ኛ ቆሮ 5
¹⁸ ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤
¹⁹ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ።


እንደተባረካችሁ ቆዩ!

#Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

31 Oct, 04:00


ነገዎቻችሁ ብድራት ወይም ደመወዝ የሚኖራቸው ዛሬዎቻችሁ በእግዚአብሔር ፊት ሲኖሩ ብቻ ነው።

መኖራችሁ በመጨረሻ ብድራት ያለውና በረከት የሚያመጣ የሚሆነው ዛሬ በእግዚአብሔር ፊት ከተኖረ ብቻ ነው።ከዚህ ውጪ መኖር ትርጉም የሌለው ቁጥር ነው።

በእግዚአብሔር ፊት የተኖሩ ዛሬዎች ነገ በአደባባይ ካሳ ሆነው ይመጣሉና ካሳ ያላቸው ዛሬዎች ይኑራችሁ።

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

30 Oct, 07:08


ዛሬ ምሽት 11:00 ጀምሮ

ልዩ የትምህርትና የፀሎት ምሽት

ሁላችንም በተዘጋጀ ልብ እግዚአብሔርን ለመገናኘት እንገኝ!

እግዚአብሔር በስራ ላይ ነው

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

30 Oct, 04:21


አንድ ፕሮፌሰር ፊኛ ለእያንዳንዱ ተማሪ ሰጡና ፣ አየር ሞልተው ስማቸውን በላዩ ላይ ከጻፉ በኋላ ወደ ኮሪደሩ እንዲያከማቹት አዘዟቸው።  ፕሮፌሰሩ ከዚያም ሁሉንም ፊኛዎች ቀላቅለው አሰባጠሯቸው። ተማሪዎቹ የራሳቸውን ፊኛ ፈልገው እንዲያገኙ 5 ደቂቃ ተሰጧቸው። እያንዳንዱ ተማሪ የራሱን ፊኛ ፈልጎ ማግኘት አቃተው። 

ፕሮፌሰሩ ተማሪዎቹን ሌላ አማራጭ ሰጧቸው። ይሄውም እያንዳንዱ ተማሪ መጀመሪያ ያነሳውን ፊኛ ወስዶ ስሙ ለተጻፈበት ሰው እንዲያስረክብ አዘዟቸው። በ 5 ደቂቃ ውስጥ ሁሉም ሰው የራሱ የሆነውን ፊኛ ደረሰው።

ፕሮፌሰሩም ለተማሪዎቹ እንዲህ አሏቸው:- “እነዚህ ፊኛዎች እንደ ደስታ ናቸው። ሁሉም ሰው የራሱን የሚፈልግ ከሆነ በጭራሽ አያገኘውም። ነገር ግን ለሌሎች ሰዎች ደስታ የምንጨነቅ ከሆነ የእኛን እናገኛለን።"

ለሌሎች ደስታ የማንጨነቅ ከሆነ የእኛ ደስታ ተፈልጎ አይገኝም ቢገኝም ዘለቄታ ያለው ደስታ አይሆንም።

🤚በቀን ለአንድ ሰው መደሰት ምክንያት ሁኑ ምክንያቱም የእናንተ ደስታ ያለው በዚያ ውስጥ ነውና።እግዚአብሔር ፀጋ ያብዛልን!!!

Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

29 Oct, 12:05


#የትምህርትና_እና #የፀሎት_ጊዜ

የጌታ ፀጋ እና ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን!!

ነገ እሮብ ጥቅምት20 ከ11:00 ጀምሮ #ጌታን #እናመልካለን እንዲሁም#የህይወትን #ቃል #ከእግዚአብሔር #መንፈስ #እንማራለን #በፀሎት #መለኮታዊ #ሀይልንን እንቀበላለን።

ስለሆነም በዚህ የትምህርት እና ፀሎት ምሽት ከቤተሰቦቻችሁና ከወዳጆቻችሁ ጋር በመገኝት የእግዚአብሔር ረደኤት ተካፋይ ይሁኑ።


📜“ነገር ግን ቃሉን የሚማር ከሚያስተምረው ጋር መልካምን ነገር ሁሉ ይከፋፈል።ገላትያ 6፥6

@👉ወደ እግዚአብሔር ቤት ሲመጡ መፅሐፍ ቅዱስና ማስታወሻ ማያዛችሁን አትዘንጉ!!!

እንደተባረካችሁ ቆዩ!!!

የኃያላን መቅደስ ቤተክርስቲያን!!!

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

29 Oct, 04:13


የሌሊትና የቀኑ መፈራረቅ ልማድ እንዳይመስልህ፡፡የታላቁ የእግዚአብሔር ቸርነት ውጤት እንጂ፡፡ነግቶ የሌሉ ብርሃን ወጥቶ ከአልጋ መውረድ ያልቻሉ ብዙ ወገኖችህ አሉና፡፡ስለነጋልህና ከአልጋ መውረድ ስለቻልህ ቸሩ እግዚአብሔርን ልታመሰግንና ቀኑን ሙሉ  መዘመር ይገባሃል!

ቀን የቀኑ የእግዚአብሔር የመጀመሪያ ባርኮት ነው።


Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!

የእግዚአብሔር ሰው ቃልአብ ታደሰ.

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
     https://t.me/rhema_tv
     https://t.me/rhema_tv

MIGHTIES' TEMPLE / RHEMA TV ETHIOPIA

28 Oct, 16:57


ኤፍታህ

ኢሳይያስ 35
⁵ በዚያን ጊዜም የዕውሮች ዓይን ይገለጣል የደንቆሮችም ጆሮ ይከፈታል።
⁶ በዚያን ጊዜ አንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘልላል፥ የድዳም ምላስ ይዘምራል፤ በምድረ በዳ ውኃ፥ በበረሀም ፈሳሽ ይፈልቃልና።

#Emmanuel-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!!!