🇪🇹ኢትዮ-News መረጃ @ethiomereja0 Channel on Telegram

🇪🇹ኢትዮ-News መረጃ

@ethiomereja0


Broadcast & media production company

⌛️ አለም አቀፋዊነት 🌐 🌐 🌐

⌛️ ወቅታዊነት ⌚️🕰🎙

⌛️ ተደራሽነት 📲💻📡📺

⌛️ ሚዛናዊነት

ከኛ ጋር ይሁኑ | ያጋሩ

https://t.me/ethiomereja0
https://t.me/ethiomereja0

🇪🇹ኢትዮ-News መረጃ (Amharic)

የ🇪🇹ኢትዮ-News መረጃ ተደርጎ አለም አቀፋዊነት እና ወቅታዊነትን በማስተዋወቅ መረጃዎችን ይገኝ። በተደራሽነት እና ሚዛናዊነት ግንባታዎች በእኛ እንዲታለል በመጠቀም ጋር ይሁኑ። በቴሌግራም ርዕሶ ከኛ ጋር ያጋሩ። ከታች ይመልከቱ።

🇪🇹ኢትዮ-News መረጃ

25 Oct, 22:42


#AU

የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓትን የሰላም ንግግር በተመለከተ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት መግለጫ አውጥተዋል።

በመግለጫው ምን አሉ ?

- የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት #ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት የተገናኙበት የሰላም ንግግር ዛሬ በደቡብ አፍሪካ ተጀምሯል።

- በሰላም ንግግሩ ላይ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (IGAD)
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ፣ የአሜሪካ መንግስት ተወካዮች በታዛቢነት እየተሳተፉ ነው።

- ደቡብ አፍሪካ የሰላም ንግግሩን ለማስተናገድ ፍቃደኛ ስለሆነች ለሀገሪቱ መንግስት እና ለፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፖሳ ምስጋና አቅርበዋል።

- ሙሳ ፋኪ ማሀመት የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የኢትዮጵያን ጥቅም ባስጠበቀ ሁኔታ ሰላምን ለማስፈን እና ለግጭቱ ዘላቂ ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲገኝ ለማስረግ ባሳዩት ቁርጠኝነት ይበልጥ እንደተበረታቱ ገልፀዋል።

- የአፍሪካ ህብረት " የሰላም ንግግር " ተሳታፊ ወገኖች ኢትዮጵያ፤ በኢትዮጵያውያን ባለቤትነት እና በአፍሪካ ህብረት መሪነት ሰላም እንዲሰፍን ፣ የተረጋጋችና አንድነቷ የተጠበቀ እንድትሆን ህብረቱ ድጋፉን እንደሚቀጥል ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል።

https://t.me/ethiomereja0

🇪🇹ኢትዮ-News መረጃ

07 Oct, 17:58


«የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ

- ኢትዮጵያዊያን በግለሰብ ደረጃ ከ100 ሺህ ብር በላይ ለድርጅቶች ደግሞ ከ200 ሺህ ብር በላይ ቤት ውስጥ ማስቀመጥ የተከለከለ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸወል።

- ገንዘብ በባንክ መቀመጥ አለበት ፤ የግብይት ስርዓትም በባንክ ማካሄድ ይቻላል።

- መመሪያው ከሚፈቅደው የገንዘብ መጠን በላይ አስቀምጦ የተገኘን አካል #የጠቆመ ግለሰብ 15 በመቶ የወረታ ክፍያ ይከፈለዋል።

- በውጭ አገራት ገንዘብ ግብይት መፈጸምም ሆነ በህገወጥ መንገድ ይዞ መገኘት አይቻልም።

- ወርቅን በህገወጥ መልኩ ቤት ውስጥ ማከማቸት የማይቻል ሲሆን በህገወጥ መልኩ ወርቅን ያከማቸ ግለሰብ ለጠቆመ ግለሰብ ባንኩ በወቅቱ ባለው ግብይት የ15 በመቶ ወረታ ይከፈለዋል።

- በህገወጥ የሃዋላ የውጭ አገራት የተሰማሩ አካላትን ለጠቆመም እስከ 25 ሺህ ብር ወረታ ይከፈለዋል።

- በህገወጥ ገንዘብ ህትመት የተሰማሩ አካላትን ያጋለጠም ከ20 ሺህ እስከ 200 ሺህ ብር ወረታ ይከፈለዋል።

- ጠቋሚዎች ወረታውና ሽልማቱ የሚበረከትላቸው #ደህንነታቸው እና #ሚስጥራዊነታቸው በተጠበቀ መልኩ ነው።

Credit : ENA»


https://t.me/ethiomereja0

🇪🇹ኢትዮ-News መረጃ

02 Oct, 12:28


አሜሪካ ሱዳንን አስጠነቀቀች።

በሱዳን የአሜሪካ አምባሳደር ጆን ጎድፍሬይ ፤ ካርቱም ሩሲያ በቀይ ባህር ዳርቻ የጦር ሰፈር እንድትመሰርት ከፈቀደች ከባድ መዘዝ እንደሚኖረው አስጠንቅቀዋል።

ከ25 ዓመታት በኋላ በሱዳን የመጀመርያው የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ጎድፍሬይ እንዲህ ዓይነት ውሳኔ ሱዳንን ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ መነጠል ብቻ ሳይሆን ጥቅሟን የሚጎዳ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።

አምባሳደር ጎድፍሬይ ከሱዳን አል ታይያር ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ፤ "ሩሲያ በቀይ ባህር ላይ የጦር ሰፈር ለመመስረት እ.ኤ.አ. በ2017 ከስልጣን ከተወገዱት ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ጋር የተፈራረመችውን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ እየሞከረች ነው የሚሉ አንዳንድ ሪፖርቶች አሉ"  ብለዋል።

አልበሽር ለወራት የዘለቀን ተቃውሞ ተከትሎ ከስልጣን የተወገዱት በሚያዝያ 2019 እንደነበር ይታወቃል።

የአሜሪካው ዲፕሎማት " የሱዳን መንግስት የጦር ሰፈሩ (የሩስያ) እንዲቋቋም እንዲቀጥል ከወሰነ ወይም እንደገና ለመደራደር ከወሰነ ለሱዳን ጥቅም ጎጂ ነው " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

" ሁሉም አገሮች ከየትኞቹ አገሮች ጋር አጋር እንደሚሆኑ የመወሰን ሉዓላዊ መብት አላቸው " ያሉት አምባሳደሩ " ነገር ግን እነዚህ ምርጫዎች በእርግጥም መዘዝ አላቸው " ሲሉ አፅንዖት ሰጥተዋል።

እንደ ዲፕሎማቱ ገለጻ አሜሪካ በሱዳን አዲስ በሲቪል የሚመራ መንግስት እና ሀገሪቱን ወደ ዲሞክራሲያዊ ጎዳና የሚመልስ የሽግግር ማእቀፍ ለማየት ትፈልጋለች።

እ.ኤ.አ ህዳር 2017 ሱዳን እና ሩሲያ በወታደራዊ ስልጠና፣ የልምድ ልውውጥ እና የጦር መርከቦችን ወደ ሁለቱ ሀገራት ወደቦች ለማስገባት የትብብር ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/Sudan-Tribune-09-29

ምንጭ፦ ሱዳን ትሪቢዩን

https://t.me/ethiomereja0

🇪🇹ኢትዮ-News መረጃ

02 Oct, 11:02


#ጋምቤላ

የጋምቤላ ክልል መንግስት የኢሰመኮን ሪፖርት "ለጠላት የወገነ ነው " ሲል ገልጾ ሪፖርቱን እንደማይቀበለውና እንደሚያወግዘው ገለፀ።

የጋምቤላ ክልል፤ "ኢሰመኮ ሰኔ 7/2014 ዓ.ም በጋምቤላ ክልል ጋምቤላ ከተማ ላይ ተፈጥሮ በነበረው ውጊያ ተከትሎ በክልሉ ልዩ ኃይሎች፣ ሚሊሽያ እና ተባባሪ ወጣቶችን ሲመሩ የነበሩ አመራሮች አማካይነት ደረሰ ባላቸው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ላይ ያወጣውን ሚዛናዊነት የጎደለውና የአንድ ክልል የፀጥታ ተቋምን ከተራ የአሸባሪ ቡድን ተላላኪ ጋር በአንድነት ያየ" ነው ሲል ገልጿል።

ሪፖርቱ "ከሁሉ በላይ በክልልና በአገር ላይ ይደርስ የነበረ ከፍተኛ ጥቃት በመቀልበስ ሂደት የህይወት መስዋዕትነት የከፈለውን የፀጥታ ተቋማችንን በጅምላ የፈረጀና የተገኘውንም ድል በዜሮ ያባዛ ሆኖ አግኝቶታል" ብሏል።

በዚህም የጋምቤላ ክልል መንግሥት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የምርመራ ሪፖርት እንደማይቀበለውና አጥብቆ እንደሚያወግዘው ገልጿል።

አክሎም "የክልሉ መንግሥት ምንም እንኳን አንድም የዜጋ ህይወት እንዲጠፋ የሚፈቅድ ባይሆንም በጥፋት ቡድኖቹ በተከፈተብን ጥቃት ከንፁሃን ዜጎች እንዲሁም የፀጥታ አካላት ህይወት መጥፋት ጋር ተያይዞ ኮምሽኑ ያወጣው የምርመራ ሪፖርት ግኝት እጅግ የተጋነነ እና በወቅቱ መሬት የነበረውን ጥሬ ሀቅ ያላገናዘበ" ነው ብሏል።

"የኢትዮጵያ ህዝቦች በጋምቤላ ከተማ ውስጥና ኦነግ ሸኔና ጋነግ የፈፀሙት ወረራና ጥቃት ብዥታ ተፈጥሮ የክልሉን መንግሥት እና ህዝብ በወቅቱ የተደረገውን ተጋድሎና ለዚህም የተከፈለውን መስዋዕትነት በዜሮ ያባዛ፤ ከሁሉ በላይ የክልሉን የፀጥታ ኃይል ሞራል የሚያዳክም፤ ፀረ-ሠላም ኃይሉንና መንግሥትን በአንድ ሚዛን ላይ አድርጎ ያየ በአጠቃላይ ለጠላት የወገነ ሪፖርት ሆኖ አግኝተነዋል" ሲል አሳውቋል።
https://t.me/ethiomereja0

🇪🇹ኢትዮ-News መረጃ

28 Sep, 08:50


#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጳጉሜ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል፣ ሆሮጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ በሲቪል ሰዎች ላይ የደረሰን ግድያ አስመልከቶ ባወጣው መግለጫ በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች ተጨማሪ የጸጥታ ሥጋቶች በመኖራቸው በታጠቁ ቡድኖች በሲቪል ሰዎች ላይ ብሔርን መሰረት ያደረጉ ተጨማሪ ጥቃቶች እንዳይፈጸሙ ለመከላከል በትኩረት እንዲሠራ ማሳሰቡን ይታወሳል።

ኢሰመኮ በአካባቢው ሲቪል ሰዎችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶች አሁንም ተሰፋፍተው መቀጠላቸው ገልጾ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን አስገንዝቧል።

በዞኑ በአሙሩ፣ በሆሮ ቡልቅ እና በጃርደጋ ጃርቴ ወረዳዎች ከነሐሴ 25 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት ሦስት ሳምንታት ውስጥ ብቻ በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ ኦነግ ሽኔ)፣ በአማራ ኢመደበኛ ታጣቂ ኃይሎች እና ግለሰቦች በተከታታይ በተፈጸሙ ጥቃቶች ከ100 በላይ ሲቪል ሰዎች የተገደሉ መሆኑ ታወቋል ሲል ኢስመኮ ገልጿል።

እንዲሁም የግል ንበረት እና የቁም ከብቶች መዘረፋቸውን ፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችም ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ያለበቂ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ የሚገኙ መሆኑን ኮሚሽኑ ከተጎጂ ቤተሰቦች፣ ከአካባቢው የፍትሕና የአስተዳደር አካላት እንዲሁም በአካባቢው ከሚንቀሳቀሱ የእርዳታ ድርጅቶች ያሰባሰብኳቸው መረጃዎች እና ማስረጃዎች ያሳያሉ ብሏል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ " የክልሉ አና የፌዴራል መንግሥታት በአካባቢው ብሔርን መሰረት አድርገው የሚፈጸመው ጥቃቶችን ለመከላከል በመወሰድ ላይ የሚገኙትን እርምጃ ችግሩን በሚመጥን ደረጃ በማሳደግ የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል" ሲሉ በድጋሚ አሳስበዋል።

https://t.me/ethiomereja0

🇪🇹ኢትዮ-News መረጃ

18 Sep, 21:39


#EthioTelecom

ኢትዮ ቴሌኮም የ " ኢ-ሲም " አገልግሎት መጀመሩን ገልጿል።

" ኢ-ሲም " በቀላሉ ከስልክ ቀፎ ጋር በማናበብ ብቻ የሞባይል ስልክ አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል አዲስ ቴክኖሎጂ ሲሆን ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ ፤ " ቸርችል ጎዳና " በሚገኘው የፕሪሚየም አገልግሎት ማዕከሉ ማግኘት እንደሚቻል አሳውቋል።

በቅርቡ ፤ በሁሉም የአገልግሎት መስጫ ማዕከሎቹ አገልግሎቱን መስጠት እንደሚጀምር ገልጿል።

የኢ-ሲም አገልግሎት የሚሰጣቸው ጥቅሞች ምንድናቸው ?

- ቀላል እና ብቁ የኔትወርክ ግንኙነት፤

- በአንድ ስልክ ከአንድ በላይ የአገልግሎት ቁጥር መጠቀም የሚያስችል፤

- ሲም ካርድ እየቀያየሩ መጠቀምን ያስቀራል፤

- ላፕቶፕ ፣ ስማርት ሰዓት ፣ ታብሌት የመሳሰሉትን በቀላሉ ለማገናኘት ፣ ለአምራቾች፣ አከፋፋዮች እና አገልግሎት ሰጪዎች፣ ለትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች እንዲሁም የተለያዩ ዲጂታል ዲቫይሶችን በቀላሉ በማገናኘት ቀልጣፋ አገልግሎት የማግኘት ፍላጎት ላላቸው ሁሉ የቀረበ መሆኑን ኢትዮ ቴላኮም ገልጿል።

በኢ-ሲም የሚሰሩ ስልኮች የትኞቹ ናቸው ?

#Samsung

📱Samsung Galaxy S20
📱Samsung Galaxy S20+
📱Samsung Galaxy S20 Ultra
📱Samsung Galaxy S21
📱Samsung Galaxy S21+ 5G
📱Samsung Galaxy S21+ Ultra 5G
📱Samsung Galaxy S22
📱Samsung Galaxy S22+
📱Samsung Galaxy Note 20
📱Samsung Galaxy Note 20 Ultra 5G 
📱Samsung Galaxy Fold
📱Samsung Galaxy Z Fold2 5G
📱Samsung Galaxy Z Fold3 5G
📱Samsung Galaxy Z Flip

#iPhone

📱iPhone XR
📱iPhone XS
📱iPhone XS Max
📱iPhone 11
📱iPhone 11 Pro
📱iPhone SE 2 (2020)
📱iPhone 12
📱iPhone 12 Mini
📱iPhone 12 Pro
📱iPhone 12 Pro Max
📱iPhone 13
📱iPhone 13 Mini
📱iPhone 13 Pro
📱iPhone 13 Pro Max
📱iPhone SE 3 (2022)

#Google

📱Google Pixel 3a XL
📱Google Pixel 4
📱Google Pixel 4a
📱Google Pixel 4 XL
📱Google Pixel 5
📱Google Pixel 5a
📱Google Pixel 6
📱Google Pixel 6 Pro.
📱Google Pixel 3 XL
📱Google Pixel 2 XL

#Huawei

📱Huawei P40
📱Huawei P40 Pro
📱Huawei Mate 40 Pro

#Motorola

📱Motorola Razr 2019
📱Nuu Mobile X5
📱Gemini PDA
📱Rakuten Mini

#Oppo

📱Oppo Find X3 Pro
📱Oppo Reno 5A
📱Oppo Reno6 Pro 5G

#eSIM #DigitalSIM #EthioTelecom

https://t.me/ethiomereja0

🇪🇹ኢትዮ-News መረጃ

17 Sep, 17:39


"ህይዎት በፈረቃ ናትና ታገስ"

ምድራዊ ህይዎት ተፈጥሮዋ ፈረቃ ነው።ፍፁም ተድላና ፍፁም ችጋር የሚባል ነገር የለም።

ደስታና ሀዘን፣ረሃብና ጥጋብ፣ህይዎትና ሞት፣ብርሃንና ፅልመት፣ትዳርና ፍቺ፣ጤና እና ህመም፣ልፋትና እረፍት፣ጦርነትና ሰላም፣ትርፍና ኪሳራ፣ክረምትና በጋ፣መውደቅና መነሳት፣ዕውቀትና ድድብና፣ሁከትና ፀጥታ፣ችኮላና እርጋታ፣..........የዚች አለም የፈረቃ ገፆች ናቸው።

ትናንት ድሃ የነበሩ አገሮች ዛሬ በሃብታቸው አለምን እየገዙት ነው።ተሰብረው የነበሩት ተጠግነው መራመድ ችለዋል።የተጣሉት ታርቀው ወዳጅ ሆነዋል።የተናቁ የነበሩት ዛሬ አለም እየሰገደላቸው ነው።መካኖች ልጅ ወልደው ስመዋል፣ሃያላን ተሰባብረው ጎዳና ላይ ወድቀዋል፣.............

ዋናው ነገር ሁለቱንም ፈረቃዎች በትዕግስትና በጥበብ ማስተናገድ ነው።የክረምቱ ወጀብ ተገልጦ የበጋው ፀሃይ እንደሚበሰረው ሁሉ ዛሬ ያለንበት የችግር ዶፍ አባርቶ የብልፅግናችንን ፀደይ የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይደለም።

ዛሬ ላይ ጠላት ቢበዛም ነገ መበተኑ አይቀሬ ነው።የዛሬው መጥፎ ገጠመኝ ለነገው ብሩህ ተስፉ ቦታውን ለቆ መሄዱ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ግደታ ነው።ዛሬ በጥጋብ የፈነጩብን ነገ እንደማያፍሩ ዋስትና የላቸውም።

የዛሬ መከረኛ ሌሊቶች በነገ የማለዳ ጮራዎች ተገፈው ያነቡ አይኖች ይታበሳሉ።ያስቸገሩን ኮረብታዎች ሁሉ በተባበረ ክንዳችን ይደረመሳሉ።የወጋን ቡዳ ማርከሻውን ሲያገኝ ይረክሳል።ሊፈጀን ያሰፈሰፈው ባቀጣጠለው እሳቱ ተቃጥሎ አመድ ሆኖ ይበናል።

ሰውና ትዕግስት አብሮ አደግ ናቸው።ከስልጣን ያወረዱትን፣ከማህበራዊ መስተጋብሩ ያገቱትን፣በኢኮኖሚ ማዕቀብ አሳምመው የቀጡትን፣በቀዬው ባይታወር ያደረጉትን ሁሉ በትዕግስት ትቷቸው እያለፈ ዛሬ ላይ ደርሷል።


ዛሬና ትናንት ፍፁም አንድ አይደሉም።ፀንፈኝነት፣አግላይነት፣ደሴትነቴ፣ከፋፋይነት፣ስግብግብነት፣በኪነት መግዘፍ፣ቤት ዘግቶ መብላት፣ወዘተ የፍፃሜ ጊዚያቸውን ሊያገኙ የመጨረሻው ትራክ ላይ ደርሰናል።የሚጠበቅብን ሁነቶችን በትዕግስት፣በጥበብና በስራ አጅቦ ማስተናገድ ብቻ ነው።"ቀን አለና ቀና ብለህ ተራመድ "እንዲሉ በዛሬው የችግር ናዳ አንገትህን ደፍተህ ከመራመድ ይልቅ የነገውን የተስፋ ጮራ እያማተርክ ቀና ብለህ ተራመድ።

እናም አብሽሩ!ሁሉም ለበጎ ነው!እርጎ ካልተገፋ ቂቤ አይወጣውም።እንጨት ካልጨሰ አይነዲም።ሻይ ካልተማሰለ ጣዕሙ አይታወቅም።በእርግጥም ከችግር በኋላ ድሎት አለና አይዞን!ነገ የእኛ አንገት ቀጥ ብሎ የግፈኞች አንገት መሰበሩ አይቀሬ ነው።


https://t.me/ethiomereja0

🇪🇹ኢትዮ-News መረጃ

27 Aug, 17:07


መረጃዎች በፍጥነት ለሁሉም እንዲደርሱ ሊንኩ ሼር ማድረግን አይርሱ!

https://t.me/ethiomereja0

🇪🇹ኢትዮ-News መረጃ

27 Aug, 17:05


ሰበር ዜና

አሸባሪው ህውኀት ቆቦ ከተማን ተቆጣጠረ!

🇪🇹ኢትዮ-News መረጃ

13 Mar, 03:54


የሰው ልጅ ይህን ያክል ጭካኔ ጫፍ ላይ የደረሰበት አሳዛኝ ቪድዮ ነው!

ይህ የምታዩት ወንድም ወንድሙን የሚደግልበት ቪድዮ ያሳዝናል! እንደዚህ አይነት ስራ እየተሰራ እንዴት ነው ታዲያ አምላክ ሊያዝንልን የሚችል!

🇪🇹ኢትዮ-News መረጃ

07 Mar, 10:52


ቻናሉን ጆይን ብላቹህ ብትገቡ ብዙ ጥቅም ታገኙበታላቹህ!

🇪🇹ኢትዮ-News መረጃ

10 Feb, 06:53


ወለጋ ላይ ለሚገኙት ወሎዬዎችተወላጆች እና ሰኡዲ አረቢያ ለሚገኙ ንፁሀን ዜጎች ሁላችንም ድምፅ ልንሆን ይገባል የሁላችንም ወገን ናቸው!

ስለዚህ መንግስት የወለጋን አምሀራዎችና የሳኡዲ ታሳሪ ኢትዮጵያዊያኖች ዝምታን እያበዛ ህዝባችን እየተጎዳ ነው። በሁሉም ሀገር ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣት ማውገዝ አለብን!

ሰብዓዊነት ለሚስኪኑ ህዝብ ሊኖረን ይገባል!

https://t.me/ethiomereja0

🇪🇹ኢትዮ-News መረጃ

18 Oct, 12:13


ለስራ ፈላጊዎች በሙሉ
__________________



❖ ሳፋሪ ኮም ኢትዮጲያ አዲስ የስራ ማስታወቂያ በ0 አመት በተለያዩ ፊልዶች
_____________________

Deadline: 28-Oct-2021 

Safaricom Telecom Ethiopia Vacancy Fresh Graduates. Sign up today and get the chance to work with Ethiopia’s newest telecommunications network.

Position 1: Finance

Degree: Finance, Logistics & Supply Chain

Position 2: External Affairs

Degree: Business Administration, Public Policy, Economics, Law, Engineering, Public Relations

Position 3: Enterprise Business Unit

Degree: Business Administration, Technology, Engineering, Legal, Marketing

Position 4: Consumer Business Unit

Degree: Marketing, Data Analytics, HR, Psychology, Economics, Business Administration, Corporate Communication

Position 5: Sales and Distribution

Degree: Business Administration & Data Analytics

Position 6: HR(Human Resource)

Degree: Business Administration, Economics, Finance, HR, Civil Engineering

Position 7: Legal & Risk

Degree: Corporate Law, BBIT (SQL Knowledge; scripts)

Position 8: Technology

Degree:Computer Science, Electrical Engineering, Mechanical Engineering, Mechatronics, Data Science, Data Analytics, Sofware Engineering, Geospatial Engineering, Civil Engineering, Structual Engineering, Architecture, Information Technology, Land Economics, Quantity Survey.

How to Apply??
👇👇👇👇👇👇
https://bit.ly/SafaricomVacancy2021

https://effoysira.com/2021/10/16/safaricom-telecom-ethiopia-vacancy-fresh-graduates/

Broadcast & media production company

⌛️ አለም አቀፋዊነት 🌐 🌐 🌐

⌛️ ወቅታዊነት ⌚️🕰🎙

⌛️ ተደራሽነት 📲💻📡📺

⌛️ ሚዛናዊነት

ከኛ ጋር ይሁኑ | ያጋሩ

https://t.me/ethiomereja0
https://t.me/ethiomereja0

🇪🇹ኢትዮ-News መረጃ

16 Oct, 06:43


የአድስ ተመራቂዎች የስራ ማስታወቂያ / job vacancy/ -የግብርና ሚኒስቴር 🔔
👩‍👩‍👦‍👦ተፈላጊ ብዛት: 32 በዜሮ አመት የስራ ልምድ
📚የትምህርት ዓይነት እና ደረጃ: BSc Degree in Plant Science, Computer Science, IT, Animal Science, Accounting, Auditing, Business administration Agribusiness management, Agricultural mechanization, Agricultural science, Agriculture engineering, management, marketing, Rural development, Urban land management, NARM and related.
🇪🇹የስራ ቦታ: አድስ አበባ
🧭የምዝገባ ጊዜ: እስከ ነሃሴ 14 ቀን 2013 ዓ.ም;
🔔ሰለ ሰራው ሙሉ መረጃ ለማየት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ
https://jobs.amazonethiopia.com/ministry-of-agriculture-job-vacancy/
---------------------
🔰ወደፊት የምናወጣቸው የስራ ቅጥር ማስታወቂያዎች በፍትነት እንዲደርስዎ የቴሌግራም ገጻችን እና የፌስቡክ ገጻችን ይወዳጁ!
ቴሌግራም:
Broadcast & media production company

⌛️ አለም አቀፋዊነት 🌐 🌐 🌐

⌛️ ወቅታዊነት ⌚️🕰🎙

⌛️ ተደራሽነት 📲💻📡📺

⌛️ ሚዛናዊነት

ከኛ ጋር ይሁኑ | ያጋሩ

https://t.me/ethiomereja0
https://t.me/ethiomereja0

🇪🇹ኢትዮ-News መረጃ

16 Oct, 06:43


DV 2023 እንዴት ራሳችን መሙላት እንችላለን?
ዲቪ 2023 ለመሙላት መከተል ያለብንን መንገዶች እነሆ
›በመጀምሪያ ዲቪ መሙላት የምንችለዉ ከ መስከረም 27,2014 በኢትዮጵያ ወይም በፈረንጆች ኦክቶበር ሀሙስ 07/2021 ጀምሮ ህዳር 09/2021 ለሊት 6፡00 ድረስ ብቻ ነው።
DV-2023 Program: Online Registration
DV-2023 Program: The online registration period for the DV-2023 Program begins on Wednesday, October 7, 2021 at 12:00 noon, Eastern Daylight Time (EDT) (GMT-4), and concludes on Tuesday, November 09, 2021 at 12:00 noon, Eastern Standard Time (EST) (GMT-5). Individuals who submit more than one entry during the registration period will be disqualified.
DV-2023 Program Instructions

›የዲቪ ፎርሙን ከመሙላታችን በፊት ማሟላት ያሉብን ነገሮች፦
እያንዳንዱ የ DV አመልካች የትምህርት / የሥራ ልምድ ማሟላት አለበት
ማለትም
በ ፕሮግራሙ መሰረትም-
• ቢያንስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ወይም ተመጣጣኝ, የ 12 ዓመት ትምህርት
በሚገባ ያጠናቀቀ / ያጠናቀቀች።
ወይም
• ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የሁለት አመት የሥራ ልምድ ያለው።
•ጉርድ ፎቶ ግራፍ
በመቀጠልም
www.dvlottery.state.gov በሚለው ዌብ ሳይት መግባት
›ዌብ ሳይቱ ዉስጥ ገብተን Entry ሚለውን በመጫን መቀጠል
በፎቶ መልክ የተቀመጠልንን Authentication code በድጋሚ በመጻፍ ወደ
ፎርም መሙያዉ መግባት።
ፎርም አሞላል
1. Name - ስም - Last/Family Name (የመጨረሻ/የቤተሰብ ስም ወይም
የአያት ስም) ፣ Middle Name- (የመካከለኛ ስም ወይም የአባት ስም) ፣
First Name (የመጀመሪያ ስም ወይም የእርሶን ስም) በፓስፖርትዎ ላይ
ያለውን ስም ሳያሳስቱ በእንግሊዝኛ መጻፍ።
2. Gender - ፆታ - ወንድ (Male) ወይም ሴት(Female) መምረጥ።
3. Birth date - የልደት ቀን - መጀመሪያ Month (ወር) ፣ Day (ቀን) ፣ Year
( ዓመት) በፈረንጆች አቆጣጠር በተሰጠው ቦታ መጻፍ።.
4. City Where You Where Born - የተወለዱበትን ከተማ.
5. Country Where You Were Born - የተወለዱበትን ሀገር
6. Country of Eligibility for the DV Program - ለ DV መርኃ-ግብር
ብቁ የሆነ ሀገር ማለትም yes ሚለዉ ላይ በመተው ማለፍ
7. Entrant Photograph - የመግቢያ ፎቶግራፍ ማስገባት
- የቅርብ ጊዜ ጉርድ ፎቶግራፍ -ፎቶ ግራፉ በደንብ የሚታይ ልኬቱ 600ፒክስል
* በ600 ፒክስል የሆነ መጠኑ ከ 240 ኪሎባይት የማይበልጥ ከለር ፎቶ ግራፍ
፣JPEG Format መሆን አለበት።
8. Mailing Address - የፖስታ መላኪያ አድራሻ መሙላት
9. Country Where You Live Today - አሁን የምንኖርበትን ሀገር መምረጥ
10. Phone Number - ስልክ ቁጥር ማስገባት ለኢትዮጲያ +251 ብለን
በመጀመር ስልካችንን ማስገባት / አለማስገባትም ይቻላል
11. E-mail Address - የ ኢሜል አድራሻንን ማስገባት
12. What is the highest level of education you have achieved,
as of today?
የትምህርት ደረጃችንን መምረጥ
13. What is your current marital status?- በአሁን ሰአት ያለን የትዳር
ሁኔታ መምረጥ
14 . Number of Children - የልጅ ብዛት በቁጥር መጻፍ
እያንዳንዱ የተወለዱ ሕጻናት እንዲሁም የማደጎ ልጆች፣ የእንጀራ ልጆች
በእርስዎ ፎርም ውስጥ እያንዳንዱ ያላገቡ ህጻናት, ምንም እንኳን ልጅዎ
ከእርስዎ ጋር አብረው ባይኖሩም መሞላት አለባቸዉ።
»በመጨረሻም continue በማለት Confirmation Number ያለበትን
ወረቀት ፕሪንት በማድረግ ማስቀመጥ እና በ Confirmation Number ን
DV-2023 ሲወጣ ማየት እንችላለን።
DV-2023 Submission Confirmation : Entry success
በዚ መሰረት ፎርሙን በመሙላት እድላችሁን መሞከር ትችላላችሁ ፔጃችንም
መልካም እድል ይመኝላቹሀል
ይሄን መረጃ ለወዳጆ ሼር ያርጉ
Broadcast & media production company

⌛️ አለም አቀፋዊነት 🌐 🌐 🌐

⌛️ ወቅታዊነት ⌚️🕰🎙

⌛️ ተደራሽነት 📲💻📡📺

⌛️ ሚዛናዊነት

ከኛ ጋር ይሁኑ | ያጋሩ

https://t.me/ethiomereja0
https://t.me/ethiomereja0

🇪🇹ኢትዮ-News መረጃ

11 Oct, 15:32


የቀረቡት የሚኒስትሮቹ ዝርዝሩ ፦

1. ግብርና ሚኒስቴር - ዑመር ሁሴን
2. የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር - መላኩ አለበል
3. የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር - ገ/መስቀል ጫላ
4. የማዕድን ሚኒስቴር - ታከለ ዑማ
5. የቱሪዝም ሚኒስቴር - ናሲሴ ጫሊ
6. የስራና ክህሎት ሚኒስቴር - ሙፈሪያት ካሚል
7. የገንዘብ ሚኒስቴር - አህመድ ሽዴ
8. የገቢዎች ሚኒስቴር - ላቀ አያሌው
9. የፕላንና ልማት ሚኒስቴር - ፍፁም አሰፋ
10. የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር - በለጠ ሞላ
11. የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር - ዳግማዊት ሞገስ
12. የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር - ጫልቱ ሳኒ
13. የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር - ሀብታሙ ኢተፋ
14. የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር - አይሻ መሐመድ
15. የትምህርት ሚኒስቴር - ብርሀኑ ነጋ
16. የጤና ሚኒስቴር - ሊያ ታደሰ
17. የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር - ኤርጎጌ ተስፋዬ
18. የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር - ቀጄላ መርዳሳ
19. መከላከያ ሚኒስቴር - አብረሀም በላይ
20. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር - ደመቀ መኮንን
21. የፍትህ ሚኒስቴር - ጊዲዮን ጢሞቲዎስ
22. የሰላም ሚኒስቴር - ብናልፍ አንዳለም

🇪🇹ኢትዮ-News መረጃ

28 Aug, 08:02


#SaudiArabia

በጄዳ የሹሜሲ ዲፖርቴሽን ማዕከል ከገቡ በኃላ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በተለያዩ ሆስፒታሎች ውስጥ ህይወታቸው ያለፈ የኢትዮጵያ ዜጎችን የሚያውቃቸው ቤተሰብ ፣ ዘመድ እና ጎደኞች ሪፖርት እንዲያደርጉ ተጠየቀ።

ከዚህ በታች የሟቾች ስም አስክሬናቸው የሚገኝበት ሆስፒታል የተገለፀ ሲሆን የምታውቋቸው ሰዎች በቢሮ ቁጥር 13 ቀርባችሁ ሪፖርት እንዲያደርጉ በጄዳ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅ/ቤት አሳውቋል።

- ሂክመት መሀመድ (የአስክሬን መገኛ👉 ሸርቅ ጂዳ ሆስፒታል)
- ከዲጃ ማህመድ (የአስክሬን መገኛ👉ሸርቅ ጂዳ ሆስፒታል)
- ሮዳስ ሙሉ (የአስክሬን መገኛ 👉 ሸርቅ ጂዳ ሆስፒታል)
- ጀማል ከማል (የአስክሬን መገኛ 👉 ሸርቅ ጂዳ ሆስፒታል)
- ቢንያም ምሩፅ ሃጎስ (የአስክሬን መገኛ 👉 ሰግር ሆስፒታል)
- የኢንዲያ ተማም /ህፃን ልጅ/ (የአስክሬን መገኛ 👉 ሰግር ሆስፒታል)
- መሃሪ ኃይሌ (የአስክሬን መገኛ 👉 ንጉስ አብዱላአዚዝ ሆስፒታል)
- ሱልጣን ሙሀመድ (የአስክሬን መገኛ 👉 ንጉስ አብዱላአዚዝ ሆስፒታል)
- በህታ ነጋሲ አፈወርቂ (የአስክሬን መገኛ 👉 ንጉስ አብዱላአዚዝ ሆስፒታል)
- ሰለሞን ሀዱሽ ተካ (የአስክሬን መገኛ 👉 ንጉስ አብዱላአዚዝ ሆስፒታል)

በዚሁ አጋጣሚ በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎችን የመመለስ ስራ ዳግም የተጀመረ መሆኑ ቢታወቅም አሁንም ከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ያሉ ዜጎች በርካታ በመሆናቸው ልዩ ትኩረት ሊደረግ ይገባል።

🇪🇹ኢትዮ-News መረጃ

20 Aug, 14:04


"..የኢኮኖሚ አሻጥሮችን በመፍጠር ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን" - ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ፥ " የኢኮኖሚ አሻጥሮችን በመፍጠር ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ፣ ሰዉ ሰራሽ የምርት አቅርቦት እጥረት በሚፈጥሩና የህዝቡን የተረጋጋ ኑሮ ለማወክ ብሎም አገር ለማፍረስ በሚሰሩና በሚተባበሩ የህዝብና የአገር ጠላቶች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን" አሉ።

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች ይህንን ተግባር በበላይነት የሚመራና የሚከታተል በፌዴራል መንግስት እና በከተማ አስተዳደሩ የተዋቀረ ግብረሃይል አቋቁመናል ሲሉ ገልፀዋል።

መላው የከተማው ነዋሪ በዚህ ህገወጥ ተግባር ላይ እየተሳተፉ ያሉ ተቋማትና ግለሰቦችን በመጠቆምና በማጋለጥ እንደከዚህ ቀደሙ አብሮን እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል።

🇪🇹ኢትዮ-News መረጃ

20 Aug, 07:00


የአድስ ተመራቂዎች የስራ ማስታወቂያ / job vacancy/ -የግብርና ሚኒስቴር 🔔
👩‍👩‍👦‍👦ተፈላጊ ብዛት: 32 በዜሮ አመት የስራ ልምድ
📚የትምህርት ዓይነት እና ደረጃ: BSc Degree in Plant Science, Computer Science, IT, Animal Science, Accounting, Auditing, Business administration Agribusiness management, Agricultural mechanization, Agricultural science, Agriculture engineering, management, marketing, Rural development, Urban land management, NARM and related.
🇪🇹የስራ ቦታ: አድስ አበባ
🧭የምዝገባ ጊዜ: እስከ ነሃሴ 14 ቀን 2013 ዓ.ም;
🔔ሰለ ሰራው ሙሉ መረጃ ለማየት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ
https://jobs.amazonethiopia.com/ministry-of-agriculture-job-vacancy/
---------------------
🔰ወደፊት የምናወጣቸው የስራ ቅጥር ማስታወቂያዎች በፍትነት እንዲደርስዎ የቴሌግራም ገጻችን እና የፌስቡክ ገጻችን ይወዳጁ!
Broadcast & media production company

⌛️ አለም አቀፋዊነት 🌐 🌐 🌐

⌛️ ወቅታዊነት ⌚️🕰🎙

⌛️ ተደራሽነት 📲💻📡📺

⌛️ ሚዛናዊነት

ከኛ ጋር ይሁኑ | ያጋሩ

https://t.me/ethiomereja0
https://t.me/ethiomereja0

🇪🇹ኢትዮ-News መረጃ

17 Aug, 04:09


የ2013 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ የ2013 የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ይፋ መደረጉን አሳውቋል።

ፈተናው ካለፉት አመታት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበበት ሆናል ተብሏል።

ከነገ ነሃሴ 11 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ተማሪዎች ውጤታቸውን በየትምህርት ቤቶቻቸው መመልከት እንደሚችሉ ተገልጿል።