Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa) @eiptc13579 Channel on Telegram

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

@eiptc13579


Ethio-Italy Poly Technic College (Dire Dawa) (English)

Welcome to the Ethio-Italy Poly Technic College (Dire Dawa) Telegram channel, where innovation meets education! Our channel, with the username @eiptc13579, is the perfect place for students, educators, and anyone interested in the field of polytechnic education. As a leading institution in Dire Dawa, Ethiopia, we offer a wide range of programs and courses designed to provide students with the knowledge and skills needed to succeed in today's competitive job market. Whether you are interested in engineering, technology, or any other polytechnic discipline, our college has something for everyone. At Ethio-Italy Poly Technic College, we pride ourselves on our commitment to excellence in education. Our experienced faculty members are dedicated to providing students with a supportive learning environment where they can thrive and achieve their academic goals. With state-of-the-art facilities and hands-on training opportunities, our students graduate with the practical skills and knowledge needed to excel in their chosen field. Join our Telegram channel to stay up-to-date on the latest news, events, and updates from Ethio-Italy Poly Technic College. Whether you are a current student, an alumni, or simply someone interested in polytechnic education, our channel is the perfect place to connect with like-minded individuals and stay informed about all the exciting things happening at our college. Who is it? Ethio-Italy Poly Technic College (Dire Dawa) is a leading institution in Ethiopia offering a wide range of programs in the field of polytechnic education. With a focus on hands-on training and practical skills development, our college prepares students for successful careers in engineering, technology, and other polytechnic disciplines. What is it? Our Telegram channel, @eiptc13579, is dedicated to providing students, educators, and anyone interested in polytechnic education with the latest news, events, and updates from Ethio-Italy Poly Technic College. Join us today and become a part of our vibrant community of learners and professionals!

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

19 Feb, 14:07


በአስተዳደሩ ከአራቱም ክላስተሮች ለተወጣጡ ወጣቶች በ Sanitation Concrete Slab ላይ ስልጠና ተሰጠ::

ስልጠናው በጤና ቢሮ አማካኝነት ከአራቱም የገጠር ክላስተሮች ለተወጣጡ 20 ሰልጣኞች በMarketing Based Sanitation Concrete Slab Training የተሰጠ ሲሆን ሰልጣኞችም ለሰባት ተከታታይ ቀናት በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮንስትራክሽን ዲፓርትመንት በአጫጭር ስልጠና ማዕቀፍ የተሰጠውን ስልጠና በአግባቡ ተከታትለው አጠናቀዋል::

በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ ለሰልጣኞች የእውቅና ሰርተፊኬቱን ያበረከቱት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ሲሆኑ በእለቱ ባስተላለፉት መልዕክትም ሰልጣኞች እዚህ በኮሌጁ የወሰዱትን ስልጠና መሰረት እድርገው በየአካባቢያቸው የሚስተዋለውን የመፀዳጃ ቤት ችግሮችን ለመቅረፍ መስራት እንደሚገባቸውም ተናግረዋል::


የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
የካቲት 12/2017 ዓ.ም

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

11 Feb, 16:10


#ዜና | የፀሀይ ታዳሸ ሀይልን ለወጣቶች የስራ አድል ፈጠራ ያለው አበርክቶት ከፍተኛ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ተባለ።

ADRA ኢትዮጵያ ግብረሰናይ ድርጅት 5.2 ኪሎ ዋት የሚያመነጭ የፀሀይ ሀይል ኤሌትሪክ መሳሪያ ለኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለገሠ። በ2001 ወደ ስራ የገባው የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከደረጃ 1-5 በማንፋክቸሪንግ ኤሌክትሪክ አውቶ እና ሰርቬይንግን ጨምሮ በ9 የትምህርትና የስልጠና ዲፓርትመንቶች እያሰለጠነ ይገኛል።

ኮሌጁ ADRA ኢትዮጵያ ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጀት ጋር በመተባበርና በፀሀይ የኤሌትሪከ ሀይል ማምረቻ ተከላ እና ጥገና ዙሪያ ወጣቶችን እያሰለጠነ ይገኛል። ለሁነቱ የተግባር መማሪያ የሚያስፈልግ 5.2 ኪሎ ዋት የሚያመነጨ የፀሀይ ሀይል ማመንጫ መሳርያ ለኮሌጁ ለግሶል።

በኩነቱ ላይ የተገኙት የአስተዳደሩ ስራ ከህሎት አና ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል አና የቴክኒክ ሞያ ኤጀንሲ ሀላፊ ወይዘሮ ፈጡም ሙስጠፋ በአስተዳደሩ ስራ አጥነትን ለመቅረፍ በሚደረገው ጥርት ወጣቶችን ስልጠናውን እንዲወስዱ እየተደረገ ይገኛሉ ብለዋል።በተለይም የገጠር ቀበሌዎችን የኤሌትሪክ ሀይል ተጠቃሚ ከማድረግ ጎን ለጎን ወጣቶችን በማደራጀት የስራ እድል ተጠቃሚ አንዲሆኑ ያደርጋል ሲሉ ገልፀዋል።

የADRA ኢትዮጵያ የፕሮጀከት ዳይሬክተር ዶክተር ዘሪሁን ሀዋኖ በበኩላቸው ከኮሌጁ ጋር በመተባበር ባለፉት 2 አመታት 90 ወጣቶችን በዘርፉ ማሰልጠናቸውን ገልፀው እርዳታው ሰልጣኞች በዘረፉ በቂ እውቀት እንዲጨብጡ እንዲሁም የራሳቸውን ስራ እንዲፈጥሩ ያደረጋል ብለዋል።


#DireTv አማርኛ የካቲት 4/2017

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

07 Feb, 17:03


ኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 በጀት አመት መደበኛ ስራ 6ወር አፈፃፀምና የEASE ፕሮጀክት የሩብ አመት አፈጻጸምን ለኮሌጁ የቦርድ አባላት ቀረበ፡፡

የተቋሙን የስራ አፈፃፀም ሪፖርት እንዲሁም የEASE ፕሮጀክት አፈጻጸም በኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አማካኝነት ለቦርዱ የቀረበ ሲሆኑ በዚህም ኮሌጁ ከዝግጅት ምእራፍ ጀምሮ በ6ወሩ ውስጥ የነበረውን የእቅድ አፈፃፀምና የተሰሩ ስራዎችን እንዲሁም የተገኙ ውጤቶችን የገለፁ ሲሆን አያይዘውም በቀጣይ በተቋሙ ሊሰሩ በእቅድ የተያዙ ስራዎችን ለቦርድ አባላት አቅርበዋል፡:

በመድረኩ የቀረበውን ሪፖርት መነሻ በማድረግም የቦርድ አባላቱ ሀሳብ አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን በተጨማሪም ኮሌጁ በቀጣይ በሚኖረው እንቅስቃሴ ላይ ምክረ-ሃሳባቸውን አስቀምጠዋል::

በመጨረሻም የኮሌጁ ቦርድ ሰብሳቢ እንዲሁም የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ በኮሌጁ እቅድ አፈፃፀም እንዲሁም በፕሮጀክቱ ትግበራ አፈጻጸም ላይ ማጠቃለያ እና የቀጣይ ስራ አቅጣጫና መመሪያም ሰጥተዋል፡፡

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ጥር 30/2017 ዓ.ም

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

18 Jan, 18:02


እንኳን አደረሳችሁ!!

ለኮሌጃችን ማህበረሰብ እንዲሁም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሀነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን እያልኩ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታ እና የአብሮነት እንዲሆንልን እመኛለሁ::

#መልካም_የጥምቀት_በዓል!!

አቶ ታደለ አሰፋ
በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

17 Jan, 15:40


ከጋንቤላ አፔኖ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እና ከደቡብ ምዕራብ ቴፒ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የተወጣጣ ልኡካን ቡድን ኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ልምድ ልውውጥ አደረ፡፡

ኮሌጆቹ በነበራቸው የልምድ ልውውጥ ጉብኝት መርሃ-ግብር ወቅት የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ በEASE ፕሮጀክት ያለውን የላቀ አፈፃፀም ሂደት በዝርዝር የተመለከቱ ሲሆን በተጨማሪም ኮሌጁ በተለያዩ ተግባራት እያከናወናቸው የሚገኙ ስራዎችም በኮሌጁ ዲኖች አማካኝነት ሰፋ ያለ ገልፃ ተደርጎላቸዋል::

ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ ባደረጉት ምልከታና የተደረገላቸው ገለፃን መነሻ በማድረግ በተካሄደው የጋራ ውይይት ወቅትም የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጁ እያደረገው ያለው እንቅስቃሴ አስደናቂ መሆኑን ገልፀው በተለይም ኮሌጁ በEASE ፕሮጀክት አተገባበር ላይ እያሳየ ያለው የላቀ አፈፃፀም ለሌሎች አቻ ተቋማትም ምሳሌ መሆን የሚችልበት የአፈፃፀም ደረጃ ላይ እንደሚገኝም በውይይታቸው ወቅት አንስተዋል::

በተጨማሪም ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ የሚገኙ የተለያዩ የትምህርትና ስልጠና ክፍሎች እንዲሁም ዎርክ ሾፖችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን እዚህ በኮሌጁ ያገኙትን በርካታ ልምዶችንም ቀምረው በመጡባቸው ኮሌጆች ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰሩም ገልፀዋል::

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ጥር 9/2017 ዓ.ም

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

17 Jan, 14:24


የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በድሬዳዋ አስተዳደር ከሚገኘው የስራ አመራር ኢንቲትዩት ጋር በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ::

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከ ኢንቲትዩቱ ጋር በመተባበር እየሰራቸው ከሚገኙ ተግባራቶች በተጨማሪ ዘላቂነት ባለው መልኩ ውጤታማ ስራዎችን ለማከናወን እንዲረዳ ሁለቱ ተቋማት የመግባቢያ ስምምነቱን ተፈራርመዋል::

የመግባቢያ ስምምነቱን የፈረሙት የኮሌጁ ዲን እቶ ታደለ አሰፋ እንዲሁም የስራ አመራር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አወቀ ለገሰ ሲሆኑ ስምምነቱም በአቅም ግንባታ ስልጠናዎች፣በጥናቶች እንዲሁም በማማከር ዙሪያ በትብብር ለመስራት ያለመ ሲሆን በቀጣይ በመግባቢያ ስምምነቱ መሰረት ወደ ትግበራ እንደሚገባም ትግልፇል::

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ጥር 9/2017 ዓ.ም

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

14 Jan, 11:11


የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ስራ ሂደት አዲሱን እሳቤ እና የጥራት ስራ አመራር ስርዓት መሠረት አድርጎ በተከለሰው እቅድ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ::

በመድረኩ አዲስ በተከለሰው እቅድ ዙሪያ ተሻሽለው የመጡና አዲስ በተጨመሩ የአዲሱ እሳቤዎች እና የጥራት ስራ አመራር ስርዓት መነሻ በሆነው እቅድ ላይ ለትምህርትና ስልጠና ክፍል ተጠሪዎች ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል::

የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው በዘርፉ አዲሱ እሳቤዎች ዓላማ ከሰው ሀይልና ቴክኖሎጂ ልማት አኳያ ያሉ ተግዳሮቶችን በመፍታት የታለመውን ጥራቱን የጠበቅና የተሟላ ስልጠና መስጠት እንዲቻል ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑም ተገልፇል::

በመድረኩ በተሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሳታፊዎች በቀረበው የተከለሰ እቅድ ዙሪያ ያላቸውን አስተያየትና ምክረ-ሃሳብ በማቅረብ ሰፊ ውይይትም ተደርጎበታል::

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
ጥር 6/2017 ዓ.ም

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

06 Jan, 12:58


እንኳን ለ2017 ዓ.ም የገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ::

በቅድሚያ ለኮሌጃችን ሰራተኞች እንዲሁም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል(ገና) በሰላም አደረሳችሁ እያልኩኝ በዓሉ የሰላም፣የፍቅር፣የጤና፣የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እየተመኘሁ በዓሉን ስናከብርም የተቸገሩትን በመርዳትና ያለንን በማካፈል በዓሉን በበጎ ተግባር ማሳለፍ ይኖርብናል እያልኩ በድጋሚ በኮሌጁ ስም እንኳን አደረሳችሁ ማለት እወዳለሁ::

#መልካም_የገና_በዓል!!

አቶ ታደለ አሰፋ
ኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

29 Nov, 17:56


የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሰራተኞች በአለም ለ37ኛ ጊዜ እንዲሁም በሀገራችን ለ36ኛ ጊዜ የሚከበረውን የዓለም ኤች.አይ.ቪ ኤድስ ቀን በዛሬው ዕለት አክብረዋል::


"ሰብዓዊ መብትን ያከበረ የኤች.አይ.ቪ አገልግሎት ለሁሉም" በሚል መሪ ቃል በፖናል ውይይት የተከበረ ሲሆን መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ እንዳሉትም በተቋሙ ያሉ ሰራተኞች በአብዛኛው ወጣት ከመሆናቸው አኳያ ለቫይረሱ ተጋላጭ ከሚያደርጉ ሁኔታዎች ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግና ተቋሙ ለሚያሰለጥናቸው ሰልጣኞችም ተገቢውን ግንዛቤ በመፍጠር እንደ ሀገር የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸው አፅእኖት ሰተው ተናግረዋል::

በመድረኩ ከጤና ቢሮ በመጣ ባለሙያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ የቀረበ ሲሆን የቀረበውን ሰነድ ጨምሮ ባለው ነባራዊ ሁኔታ ላይ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በዚህም ሰራተኛው የቫይረሱ ስርጭት ላይ ያለውን ግንዛቤ እንዲያሳድግ ረድቶታል::

በተጨማሪም በመድረኩ ሁሉም ማህረሰብ የሚያስፈልጋቸውን የኤች.አይ.ቪ መከላከል እና መቆጣጠር አገልግሎቶች ገደብ ሳይኖር ተደራሽ ማድረግ ተገቢ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በተለይም ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ቅድሚያ መስጠት ተገቢ መሆኑን ተነግሯል፡፡


ኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
ዳር 20/2017 ዓ.ም

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

23 Nov, 09:42


የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ መደበኛ ስልጠና አጠናቃቂ ለሆኑ ሰልጣኝ ተማሪዎች የኢንተርፕሩንርሺፕ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል::

ስልጠናው በዋናነት ሰልጣኝ ተማሪዎች መደበኛ ስልጠናቸውን አጠናቀው ሲወጡ ስራ ፈጣሪነትን ተላብሰው እንዲወጡና በሚፈጥሩትም ስራ ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ከመጥቀም ባሻገር ለሀገር ኢኮኖሚ እንዲተርፉ የሚያስችላቸው የንግድ ስራ ክህሎት ስልጠና እንደሆነም ተገልፇል::

የኢንተርፕሩነርሺፕ ስልጠናውን የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከEntrepreneurship Development Institute(EDI)ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሲሆን ስልጠናው በቀጣዮቹ ቀናትም ቀጥሎ የሚሰጥ ይሆናል::

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
ዳር 14/2017 ዓ.ም

Ethio-Italy Poly Technic College (Dire Dawa)

21 Oct, 12:46


የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2017 ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል፡፡

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ(ደ/ር) የመቁረጫ ነጥቡን አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጻ ሰጥተዋል፡፡

ዶ/ር ተሻለ በመግለጫቸው የሥራ ገበያውን ፍላጎት መሰረት በማድረግ ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ ነጥብ እንደሚዘጋጅ ገልጸው በዚህ ዓመትም የ12 ክፍል የማጠቃለያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 526,683 የሚሆኑት ከደረጃ 1 እስከ 5 በመደበኛ ስልጠና ለመሰልጠን ተቋማቱን ይቀላቀላሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል፡፡

ገበያ ተኮር በሆኑ በአጫጭር ስልጠናዎች ደግሞ ከ3 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ዜጎች በተቋማቱ ስልጠና ለመስጠት ታቅዶ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

ሰልጣኞች በተቋማቱ በቂ ክህሎት ታጥቀው እንዲወጡ በክረምቱ የአሰልጣኞች የአቅም ግንበናታ ስልጠና፣ የማሽነሪዎች ጥገና እና አስፈላጊ የማሰልጠኛ ግብዓቶችን የማሟላት ሥራ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

በሀገሪቱ የሚገኙ የመንግስት እና የግል ማሰልጠኛ ተቋማት ይህንን የመቁረጫ ነጥብ መነሻ አድርገው ሰልጣኞችን መቀበል ይጀምራሉ ብለዋል፡፡

ለማህበራዊ ሳይንስ እና ለተፈጥሮ ሳይንስ የተቀመጡ የመቁረጫ ነጥቦች ዝርዝር ከታች ይመልከቱ

ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥቅምት 11፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols

Ethio-Italy Poly Technic College (Dire Dawa)

19 Oct, 16:55


"የዘንድሮውን የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ለየት ከሚያደርጉት አንዱና ዋነኛው ኮሌጃችን በምስራቅ ኢትዮጵያ የመንግስት ተቋም ሆኖ የአለም አቀፍ የጥራት ደረጃ የሆነውን የISO 9001 2015 QUALITY MANAGEMENT SYSTEM እውቅና ያገኘ የመጀመርያው የመንግስት ተቋም በሆነ ማግስት መደርጉ ልዩ ያደርገዋል"

የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ

1,230

subscribers

2,938

photos

13

videos