የኢፌዲሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለድሬዳዋ አስተዳደር የገጠር ሴት ተማሪዎች ሆስቴል ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አበረከተ
ድጋፉ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ደ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ "የሴቷ ጥቃት የኔም ነው፣ ዝም አልልም" በሚል መሪ ቃል በአገር አቀፍ ደረጃ በድሬዳዋ የተካሄደው 16ቱ ቀናት የጸረ-ጾታዊ ጥቃት ንቅናቄ (የነጭ ሪቫን ሳምንታት) ማስጀመሪያ መርሀግብር ምክንያት በማድረግ በሆስቴሉ ጉብኘት ባደረጉ ጊዜ በገቡት ቃል መሰረት የተደረገ መሆኑ ተገልጿል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሁክሚያ መሀመድ ከሌሎች የቢሮው አመራሮች ጋር በመሆን ድጋፉን ያስረከቡት ሲሆን ለሚኒስቴር መስሪያቤቱ እንዲሁም ለሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በቢሮው ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የሆስቴሉ አስተባባሪ ወ/ሮ አሚና መሀመድ የኢፌዲሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሆስቴሉን ችግር ለመፍታት ቃል በገቡት በአጭር ጊዜ ውስጥ ድጋፉን በማድረጉ በአስተዳደሩና በተማሪዎቹ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የተደረገው ድጋፍም በአይነት፤ የልብስና የገላ ሳሙና፣ ሎሽን፣ ሞደስ፣ አንሶላ፣ የሰንደል ጫማዎች፣ የውስጥ ልብስና ሺቲ በጠቅላላ ከ አምስት መቶ ሺህ ብር (500,000) በላይ የሚገመት በድጋፍ ተበርክቷል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
Facebook፡- https://www.facebook.com/dire.educ?mibextid=ZbWKwL
Telegram፦ https://t.me/DireDawa_14
Tiktok፡- https://www.tiktok.com/@diredawaeducationbureau
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!