📚 ከሰለፎች ምክር 📚 @abduselamabumeryem Channel on Telegram

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

@abduselamabumeryem


أبــو مـريـم عــبــدالــســلام
📝🎤አቡ መርየም🎤📝

https://t.me/abduselamabumeryem
👆ሊንኩን ነካ በማድረግ ቻናላችንን ይቀላቀሉ

አስተያየትም ይሁን ምክር ወይም ወቀሳ ካላቹህ ብትልኩልኝ ለኔ ትልቅ ስጦታ 🎁 ነው
👇👇
በቦት ለመላክ 👇
@Abumeryeem_bot
ወይም 👇
@Abumeryeem

ከሰለፎች ምክር 📚 (Amharic)

ከሰለፎች ምክር 📚 የአቡ መርየም እና የስትፈኩህ አቡ መርየም መስራት ጊዜ የፈለጉ እና ተወዳጅ የመስራቷ ስእሊ ነው። ሌሎች መስራቷን ለመተላለፍ ወይም ለመተላለፍ ያስተላልፉን ከትናንት ሊንኩን አገልግሎት አድርጎ እንዲያልፉ መጠቀም እንደሚችል አቡ መርየም መሆኑን ያቀናብራል። ከሰለፎች ምክር 📚 ከሰፈሩት ምክርና ይህን ምርጥ ሰነዶችን ስለ መከላከል በቦት ለማውረድ እና ለማውጣት አቡ መርየም በቦት @Abumeryeem_bot ወይም @Abumeryeem የተለያዩ መተግበሪያዎች ይቀላቀሉ።

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

04 Jan, 12:37



     ይህ ነገር የታዘበው አለ??

  ዐይታችሁ እንደሆነ የሌላ እምነት ተከታይ የሆነ ሰው ወደ ስልጣን ሲወጣ ወይም ከትላልቅ ባለስልጣኖች ጋ የሚያገናኘው መስመር ላይ ሲደርስ እሱም የእምነቱ ተከታይ የሆኑ ወዳጆቹ ይደሰታሉ።

ምክንያቱን፦
  እሱ ስልጣን ላይ በመውጣቱ ከቻለ በቀጥታ በመወሰን: ካልሆነም እንዲወሰን ድምፅ በመሆን ለዛ እምነት ተከታዮች ከመንግስትም ይሁን ከሀገሪቱ የሚፈልጉትን ሁሉ እንዲያገኙ ሽፋን ይሰጣል። ስልጣኑን በመጠቀም እምነቱ እና የእምነቱ ተከታዮች ሀገሪቷ ላይ ፍላጎታቸው እንዲሟላላቸው (ለእምነቱ) ወጥሮ ይሰራል።


  በተቃራኒው አንድ ሙስሊም የሆነ ወንድም ስልጣን ላይ ከተመቻቸ: ወይም ከትላልቅ ባለ ስልጣኖች መቀማመጥ እና መወያየት ከጀመረ ነገሩ ከላይ ባየነው ተቃራኒ ይሆናል። አይደለም እስልምና ወይም ሙስሊሞች ሊረዳ ይቅርና እሱ ለራሱ የራሱን እስልምና በግልፅ ለማራመድ ይሳቀቃል።
  ትላልቅ ወይም "የሀላፊ ቢሮ" የሚባሉ ዐይነት ቢሮዎች ገብታችሁ እዛ ቦታ ላይ የሚቀመጡ ሙስሊሞች ብታዩ ለዚህ ሁነኛ ምስክር ናቸው። ፂማቸው ከመከርከም ጀምሮ ልብሳቸው ለማሳጠር ሁላ ይሳቀቃሉ። አንተ ገብተህ ራሱ "አሰላሙ ዐለይኩም" ስትላቸው: አጠገባቸው ሌላ ሰው አለመኖሩ እርግጠኛ ከሆኑ ብቻ ነው ሰላምታህን ድምፃቸው እየሰማህ የሚመልሱልህ።

ከዚህ ሁሉ የከፋው………
  እነዚህ በሀላፊነት ደረጃ ላይ የተቀመጡ ሙስሊም ባለስልጣኖች ከስሮቻቸው ወዳሉ ተቋሞች ሄደው ሌሎች ሙስሊሞች ላይ ጫና እንዲያደርጉ ይገደዳሉ። እነርሱም ይተገብሩታል።


ለምሳሌ፦
   አካዳሚ እያለን የጁሙዐ ሰላት ከመስገድ ስንከለከል እና እኛም የመስገድ መብታችን ስንጠይቅ "በትምህርት ስርዓት ላይ እስካለን መስገድ እንደማንችል" እንዲነግሩን ይላኩና ይመጡ የነበሩት ወረዳው ላይ የነበሩ ሙስሊም አመራሮች ነበሩ። "እኛ እንደናንተው መስገድ የምንፈልግ ሙስሊሞች ብንሆንም ያለንበት የስራ ህግ ስለማይፈቅድልን ወጥተን እንደ ማንሰግደው ሁሉ: እናንተም ትምህርታችሁ እስክትጨርሱ ድረስ አትስገዱ" ይሉን የነበረችው ማሳመኛ አሁን ድረስ ትታወሰኛለች።


እውነቱን ለማውራት………
   ከላይ የጠቀስናቸው ዐይነት ባለስልጣኖች ትምህርታቸው በሚማሩበት ጊዜ "እንደምንም ተምሬ የሆነች ቦታ ልያዝና ቢያንስ ለእስልምና እና ለሙስሊሞች የሆነ ነገር አደርጋለሁ።" የሚል መልካም ምኞት የነበራቸው ናቸው።የኋላ ኋላ ግን ዕድሜያቸው የጨረሱበት የስልጣን እርከን ላይ ሲደርሱ ያሳለፉት ድካም፣ የወንበሩ ምቾት፣ የገቢው ጥፍጥና እና የተገኘው ዕውቅና ተሰብስበው ይሸነግሉትና ለእስልምና የሆነ ነገር ቢፈይድ ከዚህ ወንበር እንዳይሰናበት እየፈራ ለስልጣኑ ሰስቶ እስልምናውን ይደብቃል። እንዴት ያለ ሙሲባ ነው??

  ለዚህ ሁሉ ውድቀት ምክንያቱ ከተጠየቀ ምላሹ አንድና አንድ ነው………
   እነዚህ ሰዎች በየዋህነት ወደ ፊት እስልምና ለመርዳት አልመው እድሜያቸው በአካዳሚ ጨረሱ እንጂ:
  ሊረዱት የተመኙት እስልምና ምን እንደሆነ ለመረዳት አንድም ቀን ጊዜያቸውን ሰጥተው እስልምናን ተምረው አያውቁም። እስልምናን የተማረው እና ያወቀው ሰውማ አይደለም ስልጣኑን ሕይወቱን ፊዳ ያደርጋል እንጂ በፍጹም እስልምናው ላይ አይደራደርም!!

በመሆኑም…………
  አካዳሚም ይሁን ሌላ ዐይነት መስክ ላይ መሰማራት የፈለገ ሙስሊም: ከምንም ነገር በፊት እስልምናውን መማር እና ማወቅ አለበት።

ወላጅ ሆይ!!
   "ልጆ ተምሮ ቦታ ይያዝና እስልምና ላይ የሆነ አሻራ ያሳርፋል" ብለህ አካዳሚ ላይ የምትማግደው ልጅህ ነገ ያሰብክለት ደረጃ ላይ ሲደርስ ለእስልምና አሻራ ሊያሳርፍ ሳይሆን የራሱ እስልምና እንዳይንሸረሸር ከዚህ ትምህርት ውሰድና ቆም ብለህ አስብ!!


📖{قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ}
{ሰላቴንም እርዴንም መኖሬንም መሞቴንም የዐለማት ጌታ ለሆነው አላህ ነው በል።}



🖊ሐምዱ ቋንጤ ከፉርቃን ሰማይ ስር!!
https://t.me/hamdquante
👆
👇https://t.me/abduselamabumeryem/5376

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

03 Jan, 03:05


🚨 ትክክለኛው የሴት ልጅ ሂጃብ 🚨
ቁጥር 01

🤝 ለብዙ እህቶች ኒቃብ ለመልበስ ሰበብ የሆነው ከአስር አመት በፊት የተደረገ ሙሓደራ።

🔁 አላህ ስለ ሴት ልጅ ሂጃብ በቁርዓን ምን ብሏል?

🔁 ትክክለኛው የሴት ልጅ ሂጃብ ምንድ ነው?

🔁 ሴት ልጅ መሸፈን ያለባት ከየት እስከየት ነው?

🔁 አንድ አንድ አጥማሚ ፈትዋ ሰጪዎች ስለ ሂጃብ ምን አይነት አመለካከት ነው ለህብረተሰቡ ሚያስገነዝቡት?

📮 በሚል ርዕስ ስለ ሴት ልጅ ሂጃብ በሰፊው የተዳሰሰበት ተከታታይ የሆነ እጅግ በጣም ማራኪ እና ወሳኝ የሆነ ሙሓደራ።

🎙በኡስታዝ አቡ ዐብድረህማን አብራር {ኢብራሂም} ቢን ሙሓመድ አላህ ይጠብቀው።

🕌 ከአስር አመት በፊት በታላቁ አንዋር መስጂድ {አዲስ አበባ} ።

ـــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ👇👇👇
📎 https://t.me/Al_Furqan_Islamic_Studio/17538

♡ㅤ   ❍ㅤ     ⎙ㅤ     ⌲
ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ     ˢʰᵃʳᵉ

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

30 Dec, 13:09


የሆነን ኢባዳ ለማድረግ አስበህ ግን ነፍስያህ ከከበዳት

ጀነት እኮ ከዚም በላይ ይገባታል በላት ።



https://t.me/abduselamabumeryem/5370

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

30 Dec, 06:05


🚪ባንተና በአላህ መሀል ሁሌም ክፍት የሆነ እራስህ ከዘጋሀው እንጂ የማይዘጋው በር ምን እንደሆነ ታውቃለህ

መልስ👇

👌 ዚክር ማለት አላህን ማስታወስ

ኢብኑል ቀይም እንዲህ ይላሉ

‏" الذكر .. هـو باب الله الأعظم المفتوح بينه وبين عبده، ما لم يُغلقه العبد بغفلته ".

مدارج السالكين (٢٠٨/٣)


ዚክር ማለት በአላህና በባሪያው መሀል ያለ ክፍት የሆነ ትልቅ በር ነው ባሪያው እራሱ ካልዘጋው ።


🔐 ዚክር ካቋረጥክ ዘጋሀው ማለት

ዚክር በማለትህ ደግመህ ትከፍተዋለህ

በተከፈተው በር ብዙ መጠየቅና ብዙ ማግኘት ትችላለህ

https://t.me/abduselamabumeryem/5369

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

28 Dec, 16:24


👉 ሲከፋን ወይም ስናዝን ከኢባዳ መሳነፍ የለብንም

👌 ህፃን ልጅ ሲከፋው ወደ እናቱ ተጠግቶ እንደሚያለቅሰው እኛም መጠጊያችን ወደ ሆነው ጌታችን በኢባዳ ተጠግተን ማልቀስና መለመን ነው ያለብን

ምንም አይነት ሀሳብና ጭንቀት ላይ ብንሆን ከሱ ውጪ ማንም ሊረዳን አይችልም መፍትሄው እሱ ዘንድ ነውና ።


https://t.me/abduselamabumeryem/5368

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

28 Dec, 13:16


ድንግል ሆና ያለ ወንድ እንዴት አርግዛ ትወልዳለች ?

እንዴት ልጅ ይኖረኛል ብላ ጠየቀች

{ { قَالَتۡ أَنَّىٰ یَكُونُ لِی غُلَـٰمࣱ (٢٠)
[سُورَةُ مَرۡيَمَ: ٢٠-٢١]

መልሱም አጭር ነበረ
፡ هُوَ عَلَیَّ هَیِّنࣱۖ
እሱ በኔ ላይ ቀላል ነው

ቢከብድህም ለአላህ ቀላል ነው
ችግር የሆነብህ መራቅህ ነው

ቅረብ ጌታህ ቅርብ ነው
፡ فَإِنِّی قَرِیبٌۖ
እኔ ቅርብ ነኝ

አላህ ላንተ ከማንም በላይ ቅርብ ነው

እየጎዳን ያለው የኛን መራቅ ነው

፡ { وَٱسۡجُدۡ وَٱقۡتَرِب }
ስገድ ቀረብ በል


https://t.me/abduselamabumeryem/5367

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

28 Dec, 04:07


👉 ሁሉም ለኸይር ነው በል

ለምን ምን አጥፍቼ ከማለት ጌታዬ ወስኖት ነበረና ሆኗል ማለት ይልመድብህ

ልጅ ቢሞትህ የልጅህ መሞት ላንተ ኸይር ስለሆነ ይሆናልና ወደ ጌታህ ተመለስ

👌 የልጅህ መሞት ኸይር እንደሆነ ለማወቅ ገዳዩ ኸድር መሆን የለበትም

{ فَٱنطَلَقَا حَتَّىٰۤ إِذَا لَقِیَا غُلَـٰمࣰا فَقَتَلَهُۥ }
[سُورَةُ الكَهۡفِ: ٧٤]

{ وَأَمَّا ٱلۡغُلَـٰمُ فَكَانَ أَبَوَاهُ مُؤۡمِنَیۡنِ فَخَشِینَاۤ أَن یُرۡهِقَهُمَا طُغۡیَـٰنࣰا وَكُفۡرࣰا
(٨٠) فَأَرَدۡنَاۤ أَن یُبۡدِلَهُمَا رَبُّهُمَا خَیۡرࣰا مِّنۡه زَكَوٰةࣰ وَأَقۡرَبَ رُحۡمࣰا (٨١) }
[سُورَةُ الكَهۡفِ: ٨٠-٨١]

በሱረቱ አልከህፍ የተነገረን
ኸድር የገደለው ልጅ ወላጆች ኸይራቸው የነበረው በልጁ መኖር ሳይሆን በልጃቸው መሞት ላይ ነበረ


👌ኸድር ባይገድላቸው በሌላ ምክንያት የሞቱ ልጆች መሞታቸው ኸይር የሆነ ብዙዎች ይኖራሉ

https://t.me/abduselamabumeryem/5366

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

24 Dec, 14:59


ወረኛ ወሬ ይዞልህ ሲመጣ ጆሮህን ከመስጠትህ በፊት እነዚህ ሶስት ጥያቄዎችን ጠይቀው

1⃣ይህ ነገር አንተ እራስህ ሰምተሀዋል ወይ ?

2⃣ የሰማሀው ነገር ጥሩ ነገር ነው ወይስ መጥፎ ?

3⃣ ይሄ ነገር ከነገርከኝ ለኔ ጥቅም ያለው ነገር ነው ወይ ?

ከሶስቱ አንዱን ከጎደለ ጆሮህን አታቁሽሽ ።

https://t.me/abduselamabumeryem/5365

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

23 Dec, 05:50


በቀንዱ ይነፋል !

ቂያማ በሸረኞች ላይ እንጂ አትቆምም

👌 ከአላህ ጋር ያለህ ሁኔታ ጥሩ ከሆነ ቀብርም ላይ ደስተኛ ነህ

07 : ደቂቃ

https://t.me/abduselamabumeryem/5364

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

21 Dec, 13:00


አ ብ ሽ ር

በድንገት ብትከስር
በድንገት ገቢህን ቢቋረጥ

በድንገት ብትከዳ
በድንገት ብትፈቺ

በድንገት .....

🤝 ተስፋ አትቁረጥ

👉 አንዳንዴ ስኬታማ መሆኛ መንገድ ጨለማ ሊሆን ይችላል

👉 ዩሱፍ የግብፅ ንጉስ የሆነበት መንገድ አበባ የተነጠፈ አልነበረም

1⃣ ጎድጓድ ውስጥ ተወርውሯል
2⃣ ባሪያ ነው ተብሎ ተሽጧል
3⃣ ሴትም ለመድፈር ሞከረሀል
ተብሎ ስሙ ጠፍቷል
4⃣ ታስሯል
5⃣ ሌባም ነበረ ተብሎ ተዋሽቶበታል

👌 ውጤቱ ግን እሱ ንጉስ ሆኖ ግፍ የፈፀሙበት ሁሉ ከሱ እርዳታ ጠያቂዎችና ለሱ ሱጁድ አድራጊዎች መሆን ነበረ


👌 መከራ ከደረሰብህ አላህ ሌላም የተሻለ ነገር እንዳለ ሊያሳይህ ፈልጎ ይሆናልና
ተስፋ አ ት ቁ ረ ጥ

በመጨረሻም👇
አማኝ አመስጋኝና ትእግስተኛ ከሆነ ነገሩ ሁሉ ለሱ ኸይር ነው

قَالَ رَسُولُ الله ﷺ: عَجَباً لأمْرِ الْمُؤْمِنِ إِنَّ أَمْرَهُ كُلَّهُ لَهُ خَيْرٌ

إِنْ أَصَابَتْهُ سَرَّاءُ شَكَرَ فَكَانَ خَيْراً لَهُ
وَإِنْ أَصَابَتْهُ ضَرَّاءُ صَبَرَ فَكَانَ خيْراً لَهُ
رواه مسلم

https://t.me/abduselamabumeryem/5362

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

20 Dec, 15:08


ምርጥ ሚስት ለምርጥ ባል

👌ሰዎችጋ ሰራተኝነት እየሰራች አስራ ስምንት (18) አመት ታሞ የነበረውን ባለቤትዋን እየቀለበች ኖራለች

ሰዎች ሁሉ ተፀይፈውት ከጎኑ እሷ ብቻ ነበረች

👆የነብይ አዩብ ባለቤት

ዱንያ ላይ ውዱ ነገር መልካም ሚስት ነች

👉 በነገራችን ላይ ሴቶች ወንዶችን ሲተቹ ሷሊህ ሷሊህ ትላላቹህ እንጂ ሷሊህ ነው ብለን አግበትን የተሸወድንበትም አጋጣሚ አለ መጀመሪያ እራሳቹህን አስተካክሉ ይላሉ

እውነትም አንተ እንደሀጃጅ ሆነህ የአዩብ ሚስት አይነት የምትፈልግ ከሆነ ችግር ነው

ላንተ የምትኖረዋ ሚስትህን አመስጋኝ መሆን መቻል አለብህ

፡ الطيبات للطيبين
መልካም ሴቶች ለመልካም ወንዶች ተብሏል


👌 ሂወት በሁለት ሷሊሆች ስትገፋ ታምራለች

ምርጫቹህን አሳምሩ

قال ابن كثير

فَكَانَتْ تَخْدُمُ النَّاسَ بِالْأُجْرَةِ وَتُطْعِمُهُ وَتَخْدُمُهُ نَحْوًا مِنْ ثَمَانِي عَشْرَةَ سَنَةٍ


https://t.me/abduselamabumeryem/5361

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

20 Dec, 12:31


💊በኛና በሸይጣን መሀል
💊በኛና በደጋሚዎች መሀል
💊በኛና በሀሲዶች መሀል

🏗 መገንባት የምንችለው የመከላከያ አጥር አዝካር ብቻ ነው

👌 ዚክር አብዛ ከአላህ ውጪ ማንንም አትፍራ

👉 ሰማይ ዝቅ ምድር ከፍ ብትል
አላህ ከወሰነብህ ውጪ የሚደርስብህ ነገር የለም ።

https://t.me/abduselamabumeryem/5360

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

19 Dec, 11:10


ስላፈቀርሽው ብቻ አታግቢ
ስላፈቀርካት ብቻ አታግባት

ምክንያቱም ፍቅር ያሳውራል ማየት የነበረባቹህ ነገር እንዳታዩ ያረጋቹሀል

ዋናው ጉዳይ
ለምን ወደድኳት
ለምን ወደድኩት
የሚለው ጥያቄ ነው

የትዳር ምክንያቱ
ዲንና አኽላቅ ከሆነ እሰየው

قال النبي ‏ﷺ: "إذا جاءكم من ترضون دينه وخلقه فزوجوه

በዲኑና በአኽላቁ የሚያስደስታቹህ ወንድ ከመጣ ዘውጁት ብለዋሉ ነብያችን ﷺ

قال النبي ‏ﷺ تنكح المرأة لأربع: لمالها، ولجمالها، ولحسبها، ولدينها؛ فاظفر بذات الدين تربت يداك

ሰዎች ሴት ልጅን ለገንዘቧ ለውበትዋ ለዘርዋ ብለው ያጋባሉ
አንተ ግን ዲን ያላትን ምረጥ ብለውሀል ረሱላችን ﷺ

https://t.me/abduselamabumeryem/5359

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

14 Dec, 15:14


👉 የሶሪያ ሙስሊም ወገኖቻችን ድል
ለምን አስደሰተን

👉 ሶሪያውያን የበሻር አልአሰድ አገዛዝ በመጣላቸው ለምን ይሄን ያህል ተደሰትን

👉 በዚ ልክ መደሰቱ ምን ተገኝቶ ነው


https://t.me/abduselamabumeryem/5358

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

14 Dec, 13:12


የሶሪያ ሙስሊሞች ድል ለምን ይሄን ያክል አስደሰተን

👇👇👇

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

12 Dec, 09:47


🎙️مقتطفات

مقتطف بعنوان:
قولة عمر الشهيرة
    "نحن قوم أعزنا الله بالإسلام"

للشيخ الفاضل:
   أبي حذيفة عبدالغني العمري حفظه الله

https://t.me/Al_Furqan_Islamic_Studio

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

11 Dec, 05:12


‏قال الإمام ابن القيِّم -رحمه الله-:

لا شَيء أفسَدُ لِلعَملِ الصَّالِحِ منَ العُجبِ ورُؤيَةُ النَّفس.
« الفوائد (١٥٢/١)

በራስ ከመገረም በላይ መልካም ስራን የሚያበላሽ ነገር የለም ።

ኢብኑል ቀይም

https://t.me/abduselamabumeryem/5355

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

09 Dec, 03:51


እንዴት ነው በአላህ ውሳኔ
ደስተኛ መሆን የምችለው ?

https://t.me/abduselamabumeryem/5352

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

08 Dec, 16:50


قال شيخنا يحيىٰ حفظه الله:

والله أني سجدت لله شكراً فرحاً بسقوط نظام بشار .
    ليلة الاثنين

٨/جماد الثاني/١٤٤٦ه‍ـ

"ወላሂ የበሻር አስተዳደር በመደምሰሱ ለአላህ የምስጋና ሱጁድ ተደፍቻለሁ"
  /ሸይሕ የሕያ አል_ሀጁሪ/ አላህ ይጠብቀው

👇👇

እኛም ሱጁድ ወርደናል
ይህ ድል የሱሪያውያን ብቻ ሳይሆን
የአጠቃላይ ሙስሊሞች ለየት ባለ መልኩ የአህሉ ሱናዎች ድል ነው

ከኢራን እጅ ሱሪያን ነጥቀናል
ኢራቅና የመን ይቀረናል

https://t.me/abduselamabumeryem/5351

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

08 Dec, 13:46


በሻር አል አሰድ በመደምሰሱ ሱጁድ አሽኩር የወረደ ብቻ 👍

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

08 Dec, 03:36


፡ الحمدلله
በኢራን ድጋፍ ህዝቦቹን ሲጨፈጭፍ የኖረው የሶሪያው ፕሬዝዳንት በሻር አልአሰድ በዛሬው ቀን ከስልጣን ወድቋል

የሶሪያ ሙስሊም ወገኖቻችን ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበት እድል በዛሬው ቀን ታውጇል

፡ اللهم لك الحمد

https://t.me/abduselamabumeryem/5347

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

06 Dec, 17:12


ሸይኹ በፉርቃን!!

ነገ ዕለተ ቅዳሜ
ሸይኹ በፉርቃን

ከዝሁር ሰላት በኋላ
ከዐስር ሰላት በኋላ
ከመግሪብ ሰላት በኋላ
እና
እሁድ ከፈጅር ሰላት በኋላ

በተከታታይነት በታላቁ የሰለፍዮች መሰባሰቢያ መስጂድ አል_ፉርቃን ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራማቸው ያካሂዳሉ።

https://t.me/Al_Furqan_Islamic_Studio

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

05 Dec, 17:03


ሁሉም እንደተመቸው የሙስሊሞችን ክብር አዋርዶ ዝቅ አድርጎ የሚዘረጥጠው በዚ ተግባራቸው ጀነት እንገባለን ብለው አስበው ይሁን

ይሄን ተግባር እንደ አዝካር ቆጥረውት ይሁን

🟰 ይሄ ምን አይነት ዲን ነው
🟰 ሰለፎች እንዲህ ነበሩ እንዴ

👌 በብዛት የሚሰሙ ጩሀቶች ምክንያታቸው ስሜታዊ መሆንና ለራስ መበቀል መሆናቸው ልናውቅ ይገባል

👉እልህ ገደል ውስጥ ይከታል
👉እልህ መናገር የሌለብህን ነገር ያስለፈልፈሀል
👉በእልህ አይን የትላንትናው ሀቅ ዛሬ ላይ ባጢል ሆኖ ይታየሀል
👉 በእልህ ትላንትና ያልከውን ዛሬ ትክደዋለህ

👉 ብቻ እልህ ብዙ ዋጋ እንደሚያስከፍል ሰምተናልም አይተናልምም ።

🤲 اللهم ربناأرنا الحق حقاً وارزقنا اتباعه وأرنا الباطل باطلاً وارزقنا اجتنابه

https://t.me/abduselamabumeryem/5345

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

04 Dec, 20:54


የምላስህ ጣጣ ይመዘንልሀል

ላቀናበረው جزاه الله خيرا


https://t.me/abduselamabumeryem/5344

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

22 Nov, 13:45


ሀያ የጁሙአ የመጨረሻው ሰአት ደርሷል


🤲 ሀጃችን ወደ ጌታችን

اللهم صل وسلم على محمد

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

20 Nov, 18:32


ቤተሰቦቿ እንድትፋታ አርገው ከጣሏት አንዲት እህት የተወሰደ ምክር ነው


እንድትፋቺ የሚገፋፉሽ ሁሉ
ከተፈታሽ በኋላ አያስታውሱሽም


የራሷን ትዳር በክራንቻ ጥርሷ አጥብቃ ይዛ አረ ይሄ ትዳር ቢቀርብሽስ የምትልሽ ምቀኝነት ሊሆን ይችላልና ጠንቀቅ በይ


የተፈቱ ሴቶች ውስጣቸው እያረረም ፍች ጥሮ ምርጫ እንደሆነ ሊያንፀባርቁ ይሞክራሉ

በኛ የደረሰው ሁሉም ይቅመሰው ማለታቸው ነው


https://t.me/abduselamabumeryem/5317

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

17 Nov, 15:28


የሱብሂ ሰላት አዛን እንደሰማቹህ ብድግ ብላቹህ አትስገዱ!

ትክክለኛ ወቅቱ ሳይገባ ነው አዛን የሚለው

ተጠንቀቁ

6:50

https://t.me/abduselamabumeryem/5315

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

15 Nov, 17:56


ለአዚሮች ማስረጃ መልስ ቁ.5

👉 አልኢማም ሙሀመድ ኢብኑ አብዲልወሀብ አዚር አይደሉም

https://t.me/abduselamabumeryem/5314

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

15 Nov, 17:08


👇

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

09 Nov, 11:15


ሁላችንም ከነፍስያችን ጋር ትንቅንቅ ላይ ነን

በተለይ ጌታህ አታድርግ ያለህን ነፍስያህ ደሞ አድርግ ብላ ስትወተውትህ

ለማንን ነው ቅድሚያ የምትሰጠው
ማንን ነው የምታስበልጠው


ያንተን ማንንት ከፈተናው በኋላ ነው የሚታወቀው

{ وَأَمَّا مَنۡ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِۦ وَنَهَى ٱلنَّفۡسَ عَنِ ٱلۡهَوَىٰ } [ النَّازِعَاتِ: ٤٠]

ጌታውን ፊት መቆምን ፈርቶ ነፍሱን ከስሜቷ የከለከለ ሰው

ከለከለ
ከለከለ ይሰመርበት

ሽልማቱ ታላቋን ጀነት ነው


https://t.me/abduselamabumeryem/5310

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

09 Nov, 10:42


ሁለት ወንጀል በአንድ እይታ


አይንም እኮ ዝሙት ይሰራል
የአይን ዝሙት ማየት ነው

የተራቆተችን ሴት ማየትህ የአይን ዝሙት ይሆንብሀል

በዛ መደሰትህ ገና ሌላ ወንጀል ነው


https://t.me/abduselamabumeryem/5309

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

08 Nov, 17:29


♻️ ሰባቱ አላህ የቂያማ ቀን የሚያጠላቸው ⤵️

🔘 በሚል ርዕስ የተደረገ ገሳጭ እና መካሪ የሆነ ሙሓደራ።

🎙️ በኡስታዝ አቡ ሱፍያን ሙኽታር ሙሀመድ አላህ ይጠብቀው።

📅 ሀሙስ 28/02/2017E.C 📅

🕌 በፉርቃን መስጂድ {አለም-ባንክ}

📎
https://t.me/Al_Furqan_Islamic_Studio/17354

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

08 Nov, 15:25


👌 ከፊሎች ለተስሚያ ኡዝር ቢልጀህል የለም ማለት ለሙስጠፋ ዲፋዕ ማድረግና የሙስጠፋን አጋር መሆን አድርገው ያዩታል


👉 ይህ ነጥብ ሙስጠፋ ወደዚች ዱንያ ገና ብቅ ከማለቱ በፊት አኢማዎች ብዙ ያወሩበትና የፃፉበት የሆነ መስአላ ነው ።


ሌላው ለአዚሮች
ማስረጃ መልስ መስጠትም የኡለሞችን ክብር መንካት አይደለም

አልባኒ ሴት ልጅ ፊቷን መሸፈን ዋጂብ አይደለም ሲል እኮ ሌሎች ዋጂብ ነው ያሉት እሱ ማስረጃ ያለው ማስረጃ አይሆንም ብለው መልስ ሰጥተዋሉ


ለዲን ያገለገለ ሁሉ ክብር ይገባዋል

ነብያችን ﷺ እውራ ዶሮ ለሰላት ይቀስቅሳልና አትስደቡት አሉ

ተመልከቱ ዶሮ እንኳ ጩሀቱ ለሰላት ለመነሳት ሰበብ ስለሚሆን ተከብሯል

ማይሳሳት የለም ማንም ሊሳሳት ይችላል


عن زيد بن خالد الجهني قال نهى رسولُ اللهِ - صلَّى اللهُ عليهِ وسلَّمَ - عن سبِّ الدِّيكِ، وقال : إنهُ يؤذِّنُ للصلاةِ رواه أبو داود وصححه الألباني

قال الحليمي: كما في فيض القدير:
فيه دليل على أن كل من استفيد منه خير لا ينبغي أن يسب ولا يستهان به بل حقه الإكرام والشكر ويتلقى بالإحسان

https://t.me/abduselamabumeryem/5307

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

07 Nov, 14:39


💯 የነብዩ ﷺ እዝነት ⤵️

🔘 በሚል ርዕስ የተደረገ ገሳጭ እና መካሪ የሆነ ሙሓደራ።

🎙 በኡስታዝ አቡ በከር አብድረህማን ቢን ሸምሱ አላህ ይጠብቀው።

📅 ሰኞ 25/02/2017E.C 📅

🕌 በፉርቃን መስጂድ {አለም-ባንክ}

📎
https://t.me/Al_Furqan_Islamic_Studio/17351

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

06 Nov, 15:27


👆👇

ፊትና አይደለም❗️❗️

👉ለአዚሮች መልስ ብሎ መልቀቅ ወንጀል ወይም ሙኻለፋ አይደለም

ትንሽ ወደ ኋላ ብንመለስ
👉ኡዝር አለመስጠት ይቅርና ኺላፍ አለው ያለ እንኳ ተክፊሪ ተብሏል የዛኔ

👉ጃሂሎች
👉የኡለሞች ንንግር የማይረዱ
👉ኮፒ አንባቢዎች
👉የተክፊር ፊትና የነካቸው
👉 አህሉ ሱናዎች የማያውቁት መንሀጅ

ስንቱን ተብሏል

👌 የዛኔ ማን ምን እንዳለ እናውቃለን

አሁን ግን መስአላው ገፍቶ ስለመጣና አዚር የሆኑ መሻይኾችም ኺላፍ አለው ሲሉ

እንደበፊቱ ለማለት ሞራሉ ባይኖራቸውም በዛው አቋማቸው ያሉ ሰዎች አሉ

ስለዚህ መስአላ ማውራት ለተክፊሪዮች ማገዝና ከነሱ እንደ መሆን አድርገው የሚያወሩት በድሮው አቋማቸው ላይ ለመሆናቸው ምልክት ነው


አማ ሙስጠፋን በተመለከተ ታላቁ አርቆ አሳቢውና ኣቢዱ ወንድማቸን ኡስታዝ አቡ የህያ ባወጣው በያን ላይ ምንም የምጨምረው ነገር የለም

የኔም አቋም ስለሆነ እላይ ለቅቄዋለሁ

🤝 والسلام عليكم


https://t.me/abduselamabumeryem/5305

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

06 Nov, 13:32


ለአዚሮች ማስረጃ መልስ ቁ.4


اجْعَلْ لَنَا ذَاتَ أَنْوَاطٍ كَمَا لهم ذَاتُ أَنْوَاطٍ

ዛት አንዋጥ( ሰይፎቻችን ማንጠልጠያ አርግልን)

ለሚለው ሀዲስ ማስረጃ ማድረጋቸው መልስ ነው


https://t.me/abduselamabumeryem/5304

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

06 Nov, 13:26


👇

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

05 Nov, 11:06


ጥያቄ 👇
መስአላው ኺላፊይ ነው ወይስ  አይደለም 

👉 መስአላው ኺላፊይ ነው ወይስ አይደለም ብላቹህ ለምትጨቀጭቁኝ ወንድሞቼ


ፍላጎታቹህ ገብቶኛል

መልስ👇
ጥያቄያቹህ በጥያቄ ልመልሳላቹህ


👌 ኢጅማዕ ነው ኺላፍ የለውም ያሉ ታላላቅ ኡለሞች ላይ ያላቹህ አቋም ምንድን ነው

https://t.me/abduselamabumeryem/5302

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

04 Nov, 13:05


አንድ ውንድማችን በሱ ቤት ለማወዛገብ የላከው ጥያቄ ነው

👉 ድሮ ሳላውቅ ሽርክ እሰራ ነበረ የዛኔ እኔ ምን ነበርኩኝ

መልስ 👇
👉የአኼ ሽርክ የሰራ በዛሂሩ ሙሽሪክ ነው ሲባል ሽርክ የሚሰራን ሁሉ ያካትታል

👇እኔ እራሴ ቃጥባሬ ሄጄ ያሸይኽ ብዬ ስጣራ በነበርኩኝ ጊዜ ሙሽሪክ ነበርኩኝ ጌታዬ አዳነኝ ከዛ ጨለማ አወጣኝ

{ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ ٱلَّذِی هَدَنَا لِهَـٰذَا وَمَا كُنَّا لِنَهۡتَدِیَ لَوۡلَاۤ أَنۡ هَدَىٰنَا ٱللَّهُۖ لَقَدۡ جَاۤءَتۡ رُسُلُ رَبِّنَا بِٱلۡحَقِّۖ } [سُورَةُ الأَعۡرَافِ: ٤٣]


👉 እኔ ዘንድ ከ 14 አመት በፊት ሽርክ ላይ ያለ ሰው ሙሽሪክ ነው የዛኔ እንኳ ገጠር ስገባ ሽርክ እንደሚሰሩ የማቃቸው ሰዎች ያረዱት አልበላም ነበር

ለአረፋ ሄጄ ስጋ ሳልቀምስ የተመለስኩበት አጋጣሚም አለ

👉 ስለዚህ መስአላ አንድም ሰው ሳያወራ በፊት አዳማ ሳስቀራ በነበርኩበት ሰአት የሲልሲላ ደርስ ላይ ሸይኽ ፈውዛን በገፅ 236 ያሰፈሩትን በግልፅ አብራርቼዋለሁ


👌 የኖርኩበት አቂዳዬ ስለሆነ ነው ከሁለት አመት በፊት የኡዝር ቢልጀህል መስአላ ሲነሳ ከመጀመሪያውኑ ገለፃ ማድረግ የጀመርኩት


👌 ለማንም ተቅሊድ አድርጌ ወይም ወግኜ አይደለም ወግኜማ ቢሆን ዙሪያዬ ያሉት አዚሮች ስለሆኑ ለአዚሮች ነበረ የምወግነው ነገር ግን ዲን ነው የኔ ወንድም


አቅጣቻ ለማስቀየር በውስጥ መስመር ጥያቄ የምታበዙ ባትለፉ ይሻላል ሀቅ ከሆነ የምትፈልጉት ሸይኻችን ሸይኽ አብዱል አዚዝ አራጂሂ እጠይቅላቹሀለሁኝ

ምን ማውራትና ስለምን ማውራት እንዳለብኝ አውቃለሁ

https://t.me/abduselamabumeryem/5301

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

04 Nov, 03:20


ለአዚሮች ማስረጃ መልስ ቁ.3

إِذْ قَالَ الْحَوَارِيُّونَ يَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ هَلْ يَسْتَطِيعُ رَبُّكَ أَنْ يُنَزِّلَ عَلَيْنَا مَائِدَةً مِنَ السَّمَاءِ قَالَ اتَّقُوا اللَّهَ إِنْ كُنْتُمْ مُؤْمِنِينَ

https://t.me/abduselamabumeryem/5300

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

02 Nov, 19:14


ለአዚሮች ማስረጃ መልስ ቁ.2


ስሞት አቃጥላቹህ በትኑኝ ያለው ሰውዬ ሀዲስ

ለቀብር አምላኪዎች ባለማወቃቸው ኡዝር ለመጠት ማስረጃ አይሆንም

https://t.me/abduselamabumeryem/5299

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

02 Nov, 16:30


👇

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

31 Oct, 09:51


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ብቻ እንድታውቁልኝ ብዬ ነው

👌በምንም አይነት መልኩ አላህን በብቸኝነት ያላመለከና
የሙታኖች አምልኮ ላይ ያለን ሰው ምላሴ ታዞልኝ ህሌናዬ ፈቅዶልኝ ሙስሊም ልለው አልችልም

👉 ሀቅን ስለምፈልግ የአዚሮችን ማስረጃ በደንብ አይቻለሁ አንድም ማስረጃ ላገኝ አልቻልኩም

👌 የአላህ ኡሉሂያና ሩቡቢያ ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ ወይም ጃሂል ስለሆነ ምናምን የሚያስብል ነገር አይደለም

👆
👉ሰዎች የተፈጠሩለት ትልቁ አላማ የእስልምና ዋናው መሰረት የጀነት መግቢያ ቁልፍ አላህን በብቸኝነት ማምለክ እሱን በአምልኮ መነጠል ነው
ያለዚህ መሰረት አንድ ሰው ሙስሊም ሊሆን አይችልም

👉ይሄ እምነቴ ነው ኢልም ደግሞ አማና ነው የያዝኩትን አማና መደበቅ አይቻልልኝም

👉ስድቦች👇
👉የተክፊር ጅራት
👉መፍቱን ለማትረፍ
👉ሊታወቅ የሚፈልግ ጎረምሳ
👉በተክፊር የተመታ
👉የፊትና ሰው ወ ዘ ተ
ስላላቹኝ ፈርቼ ማቆም መስሏቹህ ከሆነ ተሳስታቹሀል

እንደውም ይሄ ለኔ ብርታት ነው ሰዎች ብዙ ማወቅ ያለባቸው ነገር እንዳለ ማስረጃ ነው

👇👇
👉በነገራችን ላይ በባለፈ ስለ ዘረኝነት ከተናገርኩኝ ጊዜ አንስቶ ቂም የያዙብኝ አሉ ምክንያቱም ዘረኞቹ የነ ማን ጓደኞች ከነማን ጋር እንደሚቀማመጡ ተልእኮ ከነማን እንደሚወስዱ ስለታወቀ ህመማቸው የቱ ጋ እንደሆነ ተረድቻለሁ

አሁንም እየተሳደቡ ያሉት እነሱ ናቸው

ይሄን መስአላ ሽፋን አርገው ሂሳብ ለማወራረድ ነው

🫵 ሁላቹም ምስክሮቼ ናቹህ አንድም ሰው ስሙን ጠርቼ እከሌ ብዬ የፃፍኩበትም ይሁን የተናገርኩበት ሰው የለም

👉 በኔ ተበሳጭተው የሚሳደቡበት ሌላው ምክንያት ትልቁን ሽርክ የሰራ ሰው ሙስሊም አለማለቴ ነው
ይሄ ደሞ በማስረጃ የታጠረ የአኢማዎች የሰለፊዮች እምነት ነው

ግፍ ጥሩ አይደለም
ፍትህ ይኑረን

በማስረጃ ስላመንኩበት ነጥብ ማውራት መብቴ ነው

በመጨረሻም👇
የምጠላውና ቂም የያዝኩበት
አንድም ዳዒ ይቅርና ተራ ሰለፊ እንኳን የለም ለሰደባቹኝ ሁሉ አፍው ብያለሁ

🤲 በሀቅ አኖሮን በጀነት ይሰብስበን


https://t.me/abduselamabumeryem/5297

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

30 Oct, 17:42


👇

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

30 Oct, 09:39


አሁንም የጥያቄው መልስ እንጠብቃለን

ማንቋሸሽና መሳደብ ለኔ አዲስ አይደለም እንተዋወቃለን

በእውቀት የተገነባ መልስ ልቀቁ እኔም ሼር አረግላቹሀለሁኝ


አንድ ሰው ሽርክ ላይ ሆኖ እንዴት ነው እስልምና በዛሂርም በባጢንም የተቀበለ ሙስሊም የምትሉት
፡ لا حول ولا قوة إلا بالله

ኡለሞች አህሉሱናዎች ዘንድ ኺላፍ የለውም ስላሉት መስአላ ማውራት የኛ አዚሮች ጋ መፍቱኖችን ማትረፍ ይሉታል


ኢብኑ ተይሚያና ሙሀመድ ቢን አብዱልወሀብ ኡዝር ይሰጣሉ ማለት ስህተት ነው እመለስበታለሁ


https://t.me/abduselamabumeryem/5294

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

30 Oct, 09:30


👆ለዚህ ጥያቄ የመለሱት መልስ ነው👇

ምን አህነት በጭፍንነት እና በዘርኝነት ስሜት እንደሚያወሩ ተመልከት በተለይ እቺን መስአላ ሰበብ አድርገው ወንድሞች መሃል ተህሪሽ ለማድረግ እና ለሙብጥሎች : ኦለማዖችናን ደዕዋን ዱዓቶችን በመዎረፍ የተጠመዱ መፍቱን አህለል ፊትናነዎችን ለማትረፍ የመረባረብ ስራ ላይ የተሰማሩ በደዕዋ ሳይሆን በፊትና ግዜ የሚታወቁ ሙለቢሶች ። አንድ ሙስሊም የሆነ የሚሰግድ የሚፆም እስልምናን በዛህርም በባጢንም የተቀበለ እሄ ሽርክ ነው ተው ሲባል አሺ የሚል አካል ሽርክ መሆኑን ሳያቅ አንድ ተግባር ከፈፀመ ሽርክ መሆኑን ሳይበይንለት ሁጃ ሳይቆምበት አናከፍረም ሲባል: የሸይክ ኢስላም እብን ተይሚየህ የሙሀመድ እብን አብድልወሃብ የሌሎችም ትልልቅ ኡለማዎች ቀውል እንደሆነው ሲባል :ኢነዚህ ሙተረቢሶች ይመጡና ኣዚር : የአህባሽ ጠበቃ ፣: ሙርጂዕ አንዳንዴ ደግሞ አብሬት አምላኪዎችን የማያከፍሩ አንዳንዴ ወሃቢዮች ብለው ስለሚሉት ግልፅ ሁጃ ደርሷቸው አህለሱና ላይ ስሊሚያላግጡት ሙሽሪኮች ያወራሉ : አንዳንዴ ሙሽሪክ ሙሽሪክ በው ይለሃል ማን ሙሽሪክ ሙስሊም ነው አለ ሙስሊም ሙስለም ነው ነው በግልፅ ያለ ኡዝር እስኪከፍር አልሀምዱ ሊላህ ከእናንተ በፊትም ከእናንተ በሃላም አህለሱና ቁጭ ብለው ተውሂድን ፈትፍተው ያስተምራሉ : ተክፊንን ይጠነቀቃሉ: ተክፊርል ኡሙምና ኹሱስንም በደምብ ይለያሉ: መሻይይኾች ላይ ረድ ለማስደረግ ሂዝብዮች ጋ መሀፀድ አይተበቅብንም መጀመሪያ ከወገንተኝነት ሀዋ ተላቀቅ: ወይቁጭ ብለው ከኡለማች አልተማሩ ወይ ኡለማዎችን አክብረው ምክራቸውን አልተቀበሉ ወይ ኡለማዕ ሆነው በኡለመዎች ግንዛቤ ልክ መስአላውን ተረድተው አልሄዱወይ ዝም ብለው ኢልምና ደዕዋውን ለአህሉ ትተው ወደ ተቀጣጩበት አልተቀጣጩ ።

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

25 Oct, 18:34


ከሁለት አመት በፊት ጀምሬ ስለ ኡዝር ቢልጀህል መስአላ አልፎ አልፎ እያወራሁኝ ነው

ዛሬ የጀመርኩት ነገር አይደለም

ከፉላንና ከእከሌ የተያያዘም ነገር አይደለም


አዚር የሆናቹህ ወንድሞች እየፃፋቹህ እየገለፃቹህ ለዚህም ብላቹህ አዳዲስ ቻናሎችም እየከፋቱችህ ነው

አንዳንዶች እኔ ስናገር ለምን እንደሚበሳጩ አላቅም


ለማንኛውም ዋናው ጭንቀታችን በፊት ለያዝነው አቋም መሟሟት ሳይሆን መረጃዎችን ለመረዳትና ለመከተል ይሁን


https://t.me/abduselamabumeryem/5290

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

24 Oct, 15:25


👉 ጥያቄ ለአዚሮች

ሽርክ ላይ የወደቁ ሰዎች
የ لا إله إلا الله ትርጉም አውቀውት ነው ወይስ ሳያውቁት ቀርተው ነው

ትርጉሙን ካወቁ በኋላ ከሆነ ሽርክ የሚሰሩት በራሳቸው ላይ ሁጃ አቁመዋል ማለት ነው

ትርጉሙን ሳያውቁት ቀርተው ከሆነ ሽርክ የሰሩት ይህ ሲጀመር ሙስሊም ላለመሆናቸው ማስረጃ ነው ምክንያቱም ሙስሊም ለመሆን
የ لا إله إلاالله ትርጉም አውቆ አላህን በብቸኝነት ማምለክ መስፈርት ነው

በቁርአንና በሱና በሙስሊሞችም ኢጅማዕ ሙስሊም ለመሆን
የ لا إله إلا الله ትርጉም ማወቅን መስፈርት ተርጎ እያለ

አዚሮች ግን የ لا إله إلا الله ትርጉም አለማወቅን ሙስሊም ለመሆን መስፈርት እያደረጉት ነው

እንዴት ከተባለ
ባለማወቁ ሽርክ የሰራ ሙሽሪክ ሙስሊም ነው ሲሉ ሙስሊም ነው ያሉበት ምክንያት አለማወቁ እኮ ነው

{ فَمَن یَكۡفُرۡ بِٱلطَّـٰغُوتِ وَیُؤۡمِنۢ بِٱللَّهِ } [سُورَةُ البَقَرَةِ: ٢٥٦]


https://t.me/abduselamabumeryem/5289

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

21 Oct, 11:04


https://t.me/abduselamabumeryem/5287

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

20 Oct, 17:49


ከየትኛው ቀዳዳ ገብቶ ነው ሙስሊም የሆነው

https://t.me/abduselamabumeryem/5286

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

18 Oct, 14:23


👉 ይድረስ 👇

ለቤተሰብ ብለው ዲሽ ለሚገዙ

https://t.me/abduselamabumeryem/5283

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

16 Oct, 07:55


ክብረ ንፅህናዬን ከነጠቀኝ በኋላ ፈታኝ
ልቤ ተሰብሯል ለቤተ ሰው ምን ማለት እንዳለብኝ ግራ ገብቶኛል ምክር ያስፈልገኛል


ይድረስ ለወንዶች

ም ን ጭ
🔻 🔻 🔻 🔻
https://t.me/abduselamabumeryem/5282

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

15 Oct, 15:49


ንግግራችን እንደ ንብ ነው

ወይ ማር
ወይ እሾክ

በመጨራም መልካም ንግግር ሰደቃ
መሆኑን አንዘንጋ

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

14 Oct, 06:32


{ وَٱلَّذِینَ صَبَرُوا۟ ٱبۡتِغَاۤءَ وَجۡهِ رَبِّهِمۡ وَأَقَامُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَأَنفَقُوا۟ مِمَّا رَزَقۡنَـٰهُمۡ سِرࣰّا وَعَلَانِیَةࣰ وَیَدۡرَءُونَ بِٱلۡحَسَنَةِ ٱلسَّیِّئَةَ أُو۟لَـٰۤىِٕكَ لَهُمۡ عُقۡبَى ٱلدَّارِ } [سُورَةُ الرَّعۡدِ: ٢٢]


ከዚች አንቀፅ ምርጥ ፉኢዳ

ለሰው ጥሩ መሆን

https://t.me/abduselamabumeryem/5280

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

14 Oct, 05:26


https://surahquran.com/aya-38-sora-5.html

👆👆👆👆
በዚህ ሊንክ የምትፈልጉትን የቁርአን አንቀፅ በተለያዩ ቃሪኦች ድምፅ ማውረድ ትችላላቹህ

https://t.me/abduselamabumeryem/5279

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

12 Oct, 09:17


« وفي أنفسكم أفلا تبصرون »

الشيخ عبدالحميد الحجوري

https://t.me/abduselamabumeryem/5278

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

10 Oct, 05:57


👌 ፍች ከመጠየቅሽ በፊት አስቢበት

🫵 ልጆች ከአባቶቻቸው ለሚያጣሉ ሚስቶችንም ምክር አለበት

https://t.me/abduselamabumeryem/5277

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

06 Oct, 10:42


ሙስሊሞችና ከሀዲያኖች የሚለያቸው ዋናው ጉዳይ
አላህን በብቸኝነት ማምለክ ነው

አላህን በብቸኝነት ያመለከ ሰው ሙስሊም ሲሆን

ተቃራኒው ደሞ ካፊር ነው


ጥሎብኝ ወደ ተውሂድ የሚጠራ ሁሉ ማንም ይሁን ማን ያስደስተኛል جزاه الله خيرا እላለሁኝ


👉 ምድርና ሰማይ
👉 ጂኑም ኢንሱም
👉 ጀነትም ይሁን ጀሀነም
የተፈጠረው ለ ተ ው ሂ ድ ነው ።

https://t.me/abduselamabumeryem/5274

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

02 Oct, 03:06


قال الحسن البصري /رحمه الله :

التوبة النصوح :

أن تُبغِض الذنب كما أحببته،
وتستغفر منه إذا ذكرته.
تفسير ابن كثير (١٦٩/٨)

ትክክልኛና ንፁህ ወደ ወንጀል ማይመለስበት ተውበት ማለት ወንጀሉን ወዶት እንደነበረ ሁሉ መጥላቱና ሲያስታውሰው ኢስቲግፋር ማድረጉ ነው

አል ሀሰኑል በስሪ

https://t.me/abduselamabumeryem/5271

📚 ከሰለፎች ምክር 📚

30 Sep, 11:21


https://t.me/abduselamabumeryem/5267

5,008

subscribers

355

photos

126

videos