Ethiopian Health Professionals Association @ehpa1084 Channel on Telegram

Ethiopian Health Professionals Association

@ehpa1084


Ethiopian Health Professionals Association (English)

Are you interested in the latest health news and updates from Ethiopia? Look no further than the Ethiopian Health Professionals Association Telegram channel, also known as @ehpa1084. This channel is dedicated to providing valuable information on various health topics, including healthcare initiatives, medical research, public health campaigns, and more. The Ethiopian Health Professionals Association is a community of dedicated healthcare professionals who are passionate about improving the health and well-being of the Ethiopian population. Through this channel, they share insightful articles, informative videos, and helpful resources to keep their audience informed and educated. Whether you are a healthcare professional looking to stay up-to-date with the latest developments in the field or a concerned citizen interested in learning more about health-related issues in Ethiopia, this channel is the perfect resource for you. Join @ehpa1084 today and become part of a community that is committed to making a difference in the health sector of Ethiopia. Stay informed, stay connected, and stay healthy with the Ethiopian Health Professionals Association Telegram channel. Join us now!

Ethiopian Health Professionals Association

06 Jan, 15:34


የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

መልካም የገና በዓል

Ethiopian Health Professionals Association

22 Dec, 10:53


ዶ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ በ2014 ዓ.ም ከጎንደር ዩኒቨርሲ በሕክምና የተመረቀ ሲሆን ፤ በጠቅላላ ሐኪምነት ስራ ቦታ ላይ እያለ ከጀርባው አካባቢ የሕመም ስሜት ከተሰማው በሗላ ሁለቱም እግሮቹ ይሰንፉበታል።

በተደረገለት ምርመራ ሁለት እግሮቹን ያሰነፈው Paraplegia secondary to Transverse myelitis የተባለ በሽታ መሆኑን ተነግሮታል። አስፈላጊ የሆኑ ሕክምናዎችን አግኝቶም የተወሰነ ለውጥ አሳይቷል፤ ሙሉ በሙሉ እግሮቹን መጠቀም ስላልቻለ ለተሻለ ሕክምና ወደ አዲስ አበባ ሪፈር ተደርጓል።

ባለችው አነስተኛ ደሞዝም ሆነ ቤተሰቦቹ የሕክምና ወጪውን መሸፈን ስላልቻሉ የእናንተን እርዳታ ለመጠየቅ ወደ Social media መውጣት አስፈላጊ ሆኗል።

መርዳት ለምትፈልጉ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)
1000066147626
ሳሙኤል ተስፋዬ ይኸይስ

Ethiopian Health Professionals Association

19 Dec, 12:05


ይህ የሆነዉ በወላይታ ዞን ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ሃላለ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ነው። በጣም በሚያሳዚን ሁኔታ ለ3 ዓመት ሙሉ የትርፍ ሰዓት ክፊያ ሳይከፈለን እንዲሁም 2016 ከሃምሌ ወር ጀምሮ ደመወዝ ተከፍሎልን አያዉቅም።
ድምፃችንን ለኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት አሰማልን። #ጤና ሚንስቴር በህይወት ካለ መብታችንን ያስከብርልን።
https://t.me/EHPA1084

Ethiopian Health Professionals Association

18 Dec, 18:21


ዜና፡ ከ3 ሃኪሞች በስተቀር ሁሉም የ #ካምባ ወረዳ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች ሥራ በመልቀቃቸው ነዋሪዎች ለከፍተኛ እንግልት ተዳረጉ

በ #ደቡብ_ኢትዮጵያ ክልል #ጋሞ ዞን ካምባ ወረዳ የሚገኘው ብቸኛው የካምባ ወረዳ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል፤ በክፍያና ጥቅማጥቅም አለመፈጸም እንዲሁም “በወረዳው አመራር ያልተገባ ድርጊት” ምክንያት የሕክምና ባለሙያዎች ከሥራ በመልቀቃቸው በተከሰተ የባለሙያ እጥረት ህብረተሰቡ ለከፍተኛ እንግልት መዳረጉን ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።

ሆስፒታሉ በአከባቢው ብቸኛ የሕዝብ መገልገያ የጤና ተቋም በመሆን ለካምባና ለጋርዳ ማርታ ወረዳዎች ግልጋሎት ሲሰጥ ቢቆይም አሁን ላይ 3 ሃኪሞች በቻ በመቅረታቸው የሕክምና አገልግሎት ወደ ማቆም ተቃርቧል ሲሉ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ሆስፒታሉ ታካሚዎችን ከካምባ ወረዳ በ105 ኮሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው #አርባምንጭ ሆስፒታል በመንግስት አንቡላንስ  7000 ብር በማስከፈል ሪፈር  ያደርጋል ተብሏል።

የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢዩኤል ቡጋ በበኩላቸው ከ2015 ዓ.ም የካቲት ወር ጀምሮ ችግሮች መኖራቸውን ጠቅሰው፤   ቀዶጥገና ህክምና የሚሰጥ ባለሙያ ባለመኖሩ ሆስፒታሉ መስጠት የሚገባውን አገልግሎት እየሰጠ አለመሆኑን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።
https://t.me/EHPA1084

Ethiopian Health Professionals Association

14 Dec, 05:23


የጤና ባለሙያዎች ማህበራዊ ቀዉስ እንደቀጠለ ነዉ።
ዶ/ር አዕምሮ ይኸይስ በከባድ ሁኔታ ታሟል ወደ ዉጭ ሃገር ሂዶ እንዲታከም ተወስኗል።
ምንችለዉን ሁሉ አድርገን እናሳክመዉ።
1000141795353 ዶ/ር አዕምሮ ይኸይስ

Ethiopian Health Professionals Association

11 Dec, 18:01


በአለርት ኮንፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በአንድ ታካሚ ላይ የተከሰተዉ ብዙዎችን አስደንግጧል ግርምትንም ፈጥሯል ።
ከአንድ ታካሚ ሆድ 110 ብረታ ብረቶች ወጡ በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በተደረገ የአንጀት ቀዶ ህክምና ከአንድ የ46 ዓመት ታካሚ ሆድ 110 ብረታ ብረቶች በተሳካ ሁኔታ ወጦለታል።
በቀዶ ህክምናው እንደ ቁልፍ፣ ሚስማር እና ብሎን ያሉ የተለያዩ ብረታ ብረቶች መውጣታቸው ተጠቅሷል፡፡

የአንጀት ቀዶ ህክምናው ከ3 ሰዓት በላይ የፈጀ እንደነበርም የሆስፒታሉ መረጃ ያመለክታል፡፡
ክብር ይሄን ቀዶ ጥገና በተሳካ መንገድ ላከናወናችሁ ጤና ባለሙያዎች ይሁን።
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

Ethiopian Health Professionals Association

11 Dec, 11:12


ኢትዮጵያ ዉስጥ ጤና ሚኒስቴር ሁነዉ ከተሾሙ ሚኒስተሮች እንደ ዶ/ር ቲወድሮስ አድሃኖም በጤናዉ ዘርፍ ትልቅ ዉጤት ያመጣ ሚኒስትር የለም ።
በአሁኑ ስዓት ዶክተር ቲወድሮስ ያስጀመሯቸዉ ብዙ መልካም ስራዎችን ማስቀጠል እንኳን አቅጦን ብዙዎች ወደኃላ ተመልሰዋል ወይም ተቋርጠዋል።
ከዘመን ጋር መራመድ አለመቻላችን በጣም ያሳዝናል።
አለም አዳዲስ የጤና ግኝቶችን በሚሞክርበት በዚ ዘመን ኢትዮጵያ ዉስጥ
ግን ተቃራኒ ነዉ ጤና ኬላዎች እየፈረሱ ፣ ጤና ጣቢያዎች የህክምና ግብዓቶችን ከማሟላት ይልቅ እየተዘጉ ከቀን ወደ ቀን እየኮሰመኑ ፣ ጤና ባለሙያዎችም ሚወዱትን ሙያቸዉን እየለቀቁ ይገኛሉ ።
https://t.me/EHPA1084

Ethiopian Health Professionals Association

11 Dec, 08:28


ጠ/ሚ አብይ አህመድ ጤና ባለሙያዎች ከስራችሁ ጎን ለጎን ዶሮ አርቡ ብለዋል /ግብርና መር ህክምና/ ንግግራቸዉ ክፋት የለዉም።
ነገር ግን ለኩቡርነታቸዉ እነዚህን ጥያቄዎች እናቀርብላቸዋለን??
1) ዶሮ ለማርባት በትንሹ መኖርያ ቤት እንደሚያስፈልግ ለሳቸዉ የተደበቀ ሆኖ አደለም።
ጤና ባለሙያዉ ቤት ወይም የቤት መስርያ ቦታ ካለዉ ለምን እርስዎን ደሞዝ ይጨመርልኝ ብሎ ያለ እረፍት ይጠይቃል።
2) አንድ ክፍል ዶርም ተከራይቶ የሚኖርን ጤና ባለሙያ ለቤት ኪራይ እንኳን በቅጡ የማይበቃ ደሞዝ እየከፈሉ ዶሮ አርቡ ብሎ መናገር ከማሾፍ የዘለለ ጥቅም የለዉም።
3) ስፋ አድርጎ ዶሮ ለማርባት የደሮ ቀለበብ ፣ የደሮ ማስፈልፈያ ማሽን በትንሹ 400,000 ብርና ከዚያ በላይ ያስፈልጋል አንድ ጤና ባለሙያ አሁን ባለዉ የኑሮ ዉድነት ይሄን ገንዘብ ለማጠራቀም ለ30 አመታት መሰረታዊ ፍላጎቱን ገድቦ መቆጠብ ይኖርበታል።
4) አንድ ጤና ባለሙያ በትንሹ አስራ ሰባት አመት አለፍ ሲልም ሀያ አራት አመታትን አድካሚዉን የህክምና ትምህርት ተምሮ ብቁ ነህ ማገልገል ትችላለህ ተብሎ ሃገሩን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል በማገልገል ላይ ይገኛል ።
5) ደሮ አርብቶ ሂወቱን ለመደጎም ሀያ አራት ከባድ አማታትን ማቃጠል ነበረበት ወይ ???
https://t.me/EHPA1084

Ethiopian Health Professionals Association

11 Dec, 06:53


በአማራ ክልል የማዋላጃ ጓንት ጠፍቶ የሕክምና ባለሙያዎች እናቶችን በፌስታል  እያዋለዱ እንደሚገኙ ተነገረ።
በአማራ ክልል ባለው ግጭት ምክንያት የመድሃኒቶች አቅርቦት እና የነፍስ አድን ሥራዎች በእጅጉ ትኩረት ያስፈልጋቸዋል ሲል የክልሉ የሲቪል ማህበራት ሕብረት ገልጿል፡፡
እንደ ሕብረቱ ገለጻ ከሆነ በክልሉ ለሕጻናት እና ለእናቶች የሚደረገውን የነፍስ አድን ሥራና ሕክምና፤ የመድሃኒትና የአገልግሎት መስጫ ቁሳቁሶች እጥረት እየፈተነው በመሆኑ ያለውን ችግር መፍታት ከሁሉም የቅድሚያ ቅድሚያ የሚፈለግ ነው፡፡
"በክልሉ በረሃብ ምክንያት ሕጻናትን ጨምሮ ሰዎች እየሞቱ ነው" ያለው ሕብረቱ፤ ባለሙያዎች እናቶችን ማዋለጃ ጓንት አጥተው በፌስታል የሚያዋልዱባቸው አካባቢዎች መኖራቸውንም ገልጿል፡፡
ክልሉን ትተው ከወጡት 8 አለም ዓቀፍ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ውጭ በክልሉ ያሉት ተቋማት ለመንቀሳቀስ እና እርዳታዎችን ለመስጠት ቢሞክሩም፤ ችግሩ ተገቢውን ትኩረት ባለማግኘቱ የአቅርቦት እጥረት መኖሩን የሕብረቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ደስታ ተናግረዋል፡
"ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ሳይቀር የእርዳታ ቁሳቁሶችን ይዞ መግባት ይቻላል" ያሉት ዋና ሥራ አስኪያጁ፤ "ነገር ግን ከዚህ በፊት የነበረው መጥፎ ልምድ፣ የሲቪል ማሕበራቱን 'ግጭት ካለ እንገባም' እንዲሉ እና ችግሮቹ ትኩረት እንዳያገኙ አድርጓል" ብለዋል፡፡
አቶ ንጋቱ አክለውም በክልሉ ባለው ግጭት ምክንያት ለጉዳት እየተዳረጉ እና እየሞቱ ያሉት ጦርነቱን ያላስነሱት ሕጻናት እና ሴቶች መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን፤ "ይህን ጉዳይ ፖለቲካዊ ሽፋን ሰጥቶ ትኩረት መንፈግ የትኛውንም የአለም ዓቀፍ የሰብዓዊ ሕግ አይወክልም ብለዋል፡፡
ሁሉንም ጉዳይ ፖለቲካዊ ማድረግ አንዱ የሚስተዋል ችግር ስለመሆኑም አንስተዋል፡፡
በተጨማሪም በክልሉ አምራች ገበሬዎች በምግብ እና በሕክምና እጦት ምክንያት እየሞቱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
"የልማት የእድገትና ሌሎች ሥራዎችን መስራት ቅንጦት ነው" ያለው ሕብረቱ፤ "የነፍስ አድን ሥራዎች በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች ያስፈልጋሉ" ሲል ገልጿል
በዚህም መሠረት የሚመለከታቸው አካላት ችግሩን ለመቅረፍ ሊረባረቡበት እና ቢያንስ እናት የምትወልድበት መሰረታዊ አገልገሎት ልታገኝ ይገባል" ብሏል።
//አሃዱ ራዲዮ//

Ethiopian Health Professionals Association

06 Dec, 10:19


##የስራ ባልደረባችንን እናሳክመዉ!!

ዶክተር አብርሃም ቦቶ ይባላል : የ2014 በወላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ የወርቅ ተሸላሚ ነው : የኢትዮጵያ የህክምና ማህበርም እንዲሁ ተሸላሚ ነው::

በተደረገለት ምርመራ የአንጎል ካንሰር (Brain tumor) ተገኝቶበት በፍጥነት መታከም እንዳለበት ተነግሮናል::

ሁለት ልጅ እና ባለቤቱን ብሎም መላው ቤተስቡን ተስፋ ካስቆረጠው ከዚህ ህመም እንድንታደጋቸው ስንል በእግዚአብሔር ስም እንማጸናለን::

Account number
Commercial Bank 1000664183173
አብርሃም ቦቶ እና ትዕግስት አለሙ

Ethiopian Health Professionals Association

04 Dec, 09:11


የሁለት ዜናዎች ወግ

ዜና 1. በቤንሻንጉል ጉምዝ 6 ጤና ጣቢያዎች ደምወዝ ለሰራተኞች ባለመከፈሉ መዘጋታቸው ተገለጸ። በአራት ክልሎች መምህራን ደመውዝ ስላልተከፈላቸው የስራ ማቆም አድማ አደረጉ። ''ራበኝ የሚሉ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል ገልጹ።

ዜና 2. ከአምስት ዓመት በኋላ አውሮፕላን አምርተን ለአፍሪካ ሀገራት እንሸጣለን - ጠ/ሚ አብይ አህመድ

Ethiopian Health Professionals Association

04 Dec, 07:03


" ልመና አልነበረም ማለት አይደለም ፤ አሁን ግን እየተባባሰ ሄዷል ! ... የኑሮ ውድነቱን መቋቋም አቅቶት ህብረተሰቡ መድረሻ እያጣ ነው " - አቶ አበረ አዳሙ

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ 8ኛ መደበኛ ሰብሰባው አድርጎ ነበር።

በዚህም ወቅት ከም/ቤት አባላት ለንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።

ሚኒስትሩም ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል የሆኑ አቶ አበረ አዳሙ ምን ጠየቁ ?

" 1. በዓለም አቀፍ ተጨባጭ ሁኔታዎች ምክንያት ከውጭ የሚገቡ ሸቀጦች ዋጋ የኑሮ ውድነቱን እያናረው ከመሆኑንም በላይ በተለይ በሀገር ውስጥ ምርቶች ላይ የሚደረገው ምክንያት የለሽ ጭማሪ የህዝቡን ኑሮ እንዲመሰቃቀል አድርጎታል።

ለምሳሌ ፦
- ጤፍ
- ስንዴ
- ምስር ... ሆነ ሌሎች የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶች በሀገር ውስጥ የሚመረቱ ቢሆኑም በጥራት እና በብዛት ገበያ ላይ አይገኙም ፤ ቢገኙም ዋጋቸው እጅግ የተጋነነ በመሆኑ በቀላሉ የሚቀመስ አይደለም።

የችግሩ ምንጭ ደግሞ ሰው ሰራሽ መሆኑ አይካድም።

ህጋዊ ነጋዴው በኮንትሮባንድ ነጋዴዎች እና ለደላላ እየተጠለፈ መስራት ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል።

በዚህ የተነሳ ' ልጆቼን የማበላቸው አጣሁ ' የሚሉ አዛውንቶች፣ ' ጋሽዬ ቁራሽ የዳቦ መግዣ ስጠኝ ራበኝ ' የሚሉ አንጀት የሚበሉ በርካታ ህጻናትን ማየት በከተማችን እየተለመደ መጥቷል።

ልመና አልነበረም ማለት አይደለም አሁን ግን እጅግ እየተባባሰ ሄዷል።

ደላላው ዋጋ ይተምናል ፤ ደላላው ዋጋ ይሰቅላል ቢፈልግም ያወርዳል ለዚህም አንድ ወቅት የሱዙኪ መኪና ዋጋን ሰማይ አድርሶ መሬት አስልሶት የነበረበትን አጋጣሚ ማስታወስ ይቻላል።

በአጭር አነጋገር ደላላ የንግዱን ስርዓት /ሲስተም እንደ ተባይ ወሮታል። በዚህም የኑሮ ውድነቱን መቋቋም አቅቶት ህብረተሰቡ መድረሻ እያጣ ነው።

ጥቅሙን የሚያገኘው  በጋ ከክረምት ደም ታፍቶ ያመረተው አርሶ አደሩ ቢሆን መልካም ነበር።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶ ህገወጥ ነጋዴዎች እና ደላላዎችን ስርዓት ሊያሲዝ የሚችል ዘላቂነት ያለው ስራ ከመስራት ይልቅ አልፎ አልፎ ወይም የሆነ አጋጣሚ ሲፈጠር ' ይሄን ያህል የንግድ ድርጅቶችን አሽኩ / ልናሽግ ነው ' እያሉ በመገናኛ ብዙሃን ማስታወቂያዎችን ከማስተጋባት የዘለለ ፦
° የንግድ ተቋማቱ በምን ምክንያት እንደታሸጉ
° ምን አይነት ህጋዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸው
° የማሸጉ እርምጃ ምን ውጤት እንዳስገኘ
° የንግድ ድርጅቶቹ ከታሸጉ በኃላ የመጣንው ለውጥ ለህዝቡ ሲያሳውቅ አይታይም።

በኑሮ ላይ ጠብ የሚል ለውጥ አይስተዋልም።

ታዲያ የሀገራችንን ገበያ እየመራ ያለው ንግድ ሚኒስቴር ነው ወይስ ደላላና ህገወጥ ነጋዴ ?

2. ለንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተጠሪ የሆነው የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን ከሚቆጣጠራቸው ተቋማት አንዱ መብራት ኃይል ነው። (በየጊዜው የመዋቅር መቀያየር ለውጥ ካለ ይቅርታ ጠይቃለሁ!)

ይሁን እንጂ የመብራት ተደራሽነት እና አግልግሎት አሰጣጥ በእጅጉ የተበላሸ ነው።

👉 ተደራሽነቱ ፍትሃዊነት የጎደለውና ለማዳረስ የተሞከረው ለረጅም አመታት የተተከሉ ፖሎች ሳይቀር ያለ አገልግሎት የቆሙበት፤

👉 ተዳረሰ የተባለውም በኃይል መቆራረጥ ችግር ተጠቃሚውን የሚያሰቃይ፤

👉 አገልግሎቱን ለማግኘት ያለ እፍረት በእጅ መንሻ / ጉባ ካልሆነ በቀር የማይሰራ ሰራተኛ የበዛበት ነው።

የሚያሳዝነው ደግሞ ጉቦ ወንጀል መሆኑ ቀርቶ መብት እስኪመስል ድረስ ዋጋ ተምነው ' ይህን ያህል አምጣ ' የሚሉ ሰራተኞች መብዛታቸው ነው።

በዚህ ከቀጠለ ምናልባትም ፓርላማውን ' የምቀበለው ጉቦ አንሶኛል እና ህግ አውጡልኝ ' ማለት የቀራቸው ይመስላል።

ይህ የእርሶን ተቋም ብቻ የሚመለከት አይደለም በርካታ ተቋማትን የሚያካትት ነው።

ክቡር ሚኒስትር ለመሆኑ ለእርሶ ተጠሪ የሆነው ባለስልጣን መ/ቤት ህዝቡን እያስለቀሰ የሚቀጥለው እስከመቼ ነው ? ይህንን ተቋም መቆጣጠርና ስርዓቱን ማስያዝ ያልተቻለው ለምንድነው ?

3. የኑሮ ውድነቱን ከሚያባብሱ ምክንያቶች አንዱ ነዳጅ ነው።

የዋጋው ማሻቀብ ምክንያቱ የሚታወቅ ቢሆንም ከዋጋው በላይ ሰልፉ ህዝቡን እያማረረ ይገኛል።

ከእጥረቱም በላይ ነዳጅ ለመቅዳት በሚደረግ ረጃጅም ሰልፍ ምክንያት የስራ ሰዓት ያለ አግባብ እየባከነ፣ የትራፊክ ፍሰቱን እያስተጓጎለ፣ እንዲያውም ሲል በህገወጥ መንገድ ነዳጅ ከሀገር እንዲወጣ ሰፊ በር እየከፈተ መሆኑን እማኝ መጥቀስ የሚያስፈልግ አይመስለኝም።

Ethiopian Health Professionals Association

27 Nov, 20:24


የተከበሩ ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ስለ ደሞዝ ጭማሬዉ ፣ ስለ ኑሮ ዉድነቱ ለፓርላማዉ ያቀረቡት ድንቅ ጥያቄ እና ማብራርያ ።
"የመንግስት ሰራተኛዉ ጎዳና እየወጣ ነዉ"።
https://www.facebook.com/100045749884970/posts/pfbid0sLKsnU3PqVcHS4ST8vn49WBq3BjMe8cyD5qYS5yaCqrGoBTzTUKc3yNttKuPjTzgl/?app=fbl

Ethiopian Health Professionals Association

27 Nov, 12:20


#ከዜናዎቻችን| የጤና ባለሙያዎች ለአመታት ለጠይቀናቸው ችግሮቻችን መፍትሄ ካልተሰጠን ራሳችንን ወደ ማጥፋት እንሄዳለን ብለው አስጠነቀቁ

(መሠረት ሚድያ)- መሠረት ሚድያ የተመለከተው እና እነዚህ የጤና ባለሙያዎች ውስጥ ለውስጥ በቴሌግራም መላላክያ የተቀባበሉት ደብዳቤ "በአንድነት ራስን በማጥፋት ተቃውሟችንን እናሰማ" የሚል መልዕክት ያለው ደብዳቤ እየተቀባበሉ ይገኛሉ።

"በሀገራችን ኢትዮጵያ ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ በመጣው ጭንቀት ምክንያት ብዙዎች 'ብንሄድ ይሻለናል' በማለት በግለሰብ ደረጃ ራሳቸውን ሲያጠፉ ማየት የተለመደ ሆኗል" የሚለው ደብዳቤው እነዚህ ሰዎች ድርጊቱን የሚፈፅሙት በግለሰብ ደረጃ በመሆኑብ ምክንያቱ ሳይጣራ እና ሳይፈታ እስካሁን ቆይቷል ይላል።

በመቀጠልም "በሀገሪቱ ለረጅም አመታት ከባዱን ስልጠና ወስደን የህክምና ሙያ ላይ የተሰማራን ሀኪሞች ግን ከመሄድ ይልቅ እናክማቸው በማለት ስናገለግል ቆይተናል። አሁን ግን ይበቃልናል፣ መኖር አልቻልንም። ኩላሊታችንን እንኳን እንሽጥ ብለን ብንሞክር በሀገራችን ያለው የንቅለ ተከላ ልምድ ከዘመድ በመሆኑ ለብዙዎቻችን አልተመቸንም" የሚለው የጤና ባለሙያዎቹ ደብዳቤ ያለባቸው ችግር ቀን ከቀን እየተባባሰ እንደመጣ ይጠቅሳሉ።

ደብዳቤው በመቀጠልም "በሀኪሞች ላይ የሚደረገው ስም የማጥፋት ሴራ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ስለዚህ ቀን ከለሊት የምንሰራው ኑሯችንን ሊደጉም ካልቻለ ለሰጠነው አገልግሎት አገልግሎት ደግሞ ከምስጋና ይልቅ ስድብ ከወረደብን እንዲሁም መንግስት ባላቀረበው መድሀኒት እና ቁሳቁስ እኛ ከተደበደብን፣ የመልካም አስተዳደር እጦቱ እየባሰ ከሄደ፣ በሰላም መኖር ህልም ሆኖ ከቀረ ከመንግስትም ተሰሚነት ካጣን እስከ መቼ ነው የምንቆየው?" በማለት ጥያቄያቸውን አቅርበው ሀኪሞች ቀጠሮ ይዘን እና በአንድነት ተነጋግረን ተቃውሟችንን ገልፀን ራሳችንን ማጥፋት የሚለው ከብዙዎች ዘንድ ተነስቷል ይላል።

በዚህ መልኩ "እኛ ባንኖር ለሚኖሩት መፍትሄ እንሁን" በማለት ደብዳቤው ይጠቅሳል።

ይህን መረጃ ወደ መሠረት ሚድያ ያመጡት አንድ የጤና ባለሙያ ሲሆኑ ድርጊቱ ከተፈፀመ እጅግ አስደንጋጭ መሆኑ ስለማይቀር መፍትሄ እንዲፈለግ ወደ ሚድያ ማምጣት እንደፈለጉ ተናግረዋል።

ይህን ደብዳቤ ከሚቀባበሉ ሪዝደንቶች በአዲስ አበባ፣ ወላይታ፣ ሀዋሳ፣ አዳማ እና ሌሎች ቦታዎች የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች እንደሚገኙበት ታውቋል።

አደጋ ከደረሰ በኃላ ከንፈር ከመምጠጥ ምናልባት መፍትሄ ከተገኘለት በማለት መሠረት ሚድያ ወደ ህዝብ ሊያቀርበው ችሏል።

(#ከዜናዎቻችን በሳምንቱ በቪድዮ ዩትዩብ ላይ ያቀረብናቸውን የተመረጡ መረጃዎች ቆየት ብለን በድጋሜ በፅሁፍ የምናቀርብበት አምድ ነው)

መረጃን ከመሠረት!

Via Meseret Media

Ethiopian Health Professionals Association

26 Nov, 05:14


https://www.facebook.com/SafeRoadsAddis/videos/1121119482912846/?mibextid=9sIWoBpUEZes3HRB

Ethiopian Health Professionals Association

26 Sep, 15:03


የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም፣የጤናና የፍቅር  እንዲሆንላችሁ ምኞቱን ይገልጻል፡፡

Ethiopian Health Professionals Association

19 Sep, 17:13


የደሞዝ ጭማሬ ቅሬታዉን በሚመለከት የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዚዳንት ከአሻም ቲቪ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ "የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር" ፕሬዚዳንት ተብሎ የተገለፅዉ በጋዜጠኞች የአገላለፅ ስህተት መሆኑን እንገልፃለን ።
https://t.me/EHPA1084

Ethiopian Health Professionals Association

18 Sep, 12:47


የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዚዳንት ተጨመረ ተብሎ በተለቀቀዉ ደሞዝ ዙርያ ከአሻም ቲቪ ጋር ያደረጉት ቃለ መጠየቅ!!
https://youtu.be/OkO4-21Gdog?si=snBcVzjU6XPOQMKp

Ethiopian Health Professionals Association

02 Aug, 16:31


#Update

የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ በቅርቡ እንደሚጸድቅ የገንዝብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ተናግረዋል።

" ለታችኛው የደመወዝ ተከፋይ ሠራተኛ የተሻለ ደመወዝ እንዲያገኝ የሚያችል ጭማሪ ተሰርቷል " ብለዋል።

ዝርዝሩ በቅርብ ይጸድቃል ሲሉም አሳውቀዋል።

ከዓለም አቀፍ ተቋማት ከተገኘው ድጋፍ ውስጥም አንዱ የሚውለው ለሠራተኛው ደመወዝ ጭማሪ / በድጎማ መልኩ እንደሆነ አመልክተዋል።

ትላንትና በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ፖሊሲ ላይ ማብራሪያ የሰጡት ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ፤ መንግሥት በወር 1,500 ብር የሚበላ ሠራተኛ እንዳለው በመግለፅ ጭማሪ እንደሚደረግ ተናግረው ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሁኑ የደመወዝ ማሻሻያ ከ90 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ሃብት እንደጠየቀና ፤ ከታች ያለው 1,500 ብር የሚበላው የመንግሥት ሠራተኛ 300% ደመወዙ እንደሚጨመር በይፋ መናገራቸው አይዘነጋም።
https://t.me/EHPA1084
@tikvahethiopia

Ethiopian Health Professionals Association

01 Aug, 13:43


‹‹ ኢትዮጵያ ደሃ የማይኖርባት ሀገር እየሆነች ነው ›› - የአዲስ አበባ ነዋሪዎች

አሻም ዜና | ሐምሌ 25 ቀን 2016 ዓ.ም

ከባለፈው ሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የውጭ ምንዛሪ ተመን ማሻሻያ ‹‹ የኑሮ ውድነቱን ሰማይ ጠቀስ እያደረገው መሆኑን ›› አሻም በተለያዩ የመዲናዋ የገበያ ስፍራዎች ተገኝታ ያነጋገረቻቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

አንድ ሸማች ከውጭ ምንዛሪ ተመን ማሻሻያው በኋላ ስላለው የገበያ ሁኔታ ሲያስረዱ ‹‹ የዘይት ዋጋ በእጥፍ ጨምሯል፤ በአንድ ጊዜ ነው ዋጋው የናረው፤ እንደኔ ያለ ደሃ መኖር አይችልም ›› ሲሉ ብለዋል፡፡

ሌላው ለአሻም ምልከታቸውን ያጋሩ ሸማች በበኩላቸው ‹‹ በውድ ዋጋ እንኳን ለመግዛት አቅርቦት የለም፣ አጥተናል ›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ አክለውም ‹‹ ዕቃውን የት እንዳደርሱት አናውቅም፤ ዘይት ፈልጌ መጥቼ ነበር፤ ግን ሁሉም ቦታ የለም ›› ብለዋል፡፡

በገበያ ዋጋ ላይ የተመሰረተ ተመን ይወጣል ከተባለ በኋላ በአጠቃላይ የዋጋ ንረቱ አይሏል ሲሉ አቤቱታቸውን ለአሻም ያሰሙት ሸማቾች ብቻ ሳይሆኑ ነጋዴዎችም ጭምር ናቸው፡፡

ለአሻም አስተያየታቸውን የሰጡ አንድ ነጋዴ ‹‹ ከጅምላ አከፋፋዮች እጅ እቃ ማግኘት አልቻልንም፤ መርካቶ ስንሄድ እቃ የለም ነው እያሉን ያሉት ›› ሲሉ የገጠማቸውን አስገንዝበዋል፡፡

በመጨረሻም ‹‹ መንግስት ቁጥጥሩን ከላይ ካላደረገ የችርቻሮ ሽያጩ ምንም ማድረግ አይችልም ›› በማለት መፍትሔ ይሆናል ያሉትን ምክረሃሳብ ለግሰዋል፡፡

ህሊና ተክሌ

(በምሽት የዜና እወጃችን ዝርዝር ዘገባውን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን)

አሻም ለኢትዮጵያችን!!

Ethiopian Health Professionals Association

29 May, 10:58


https://www.linkedin.com/posts/tedros-adhanom-ghebreyesus_g20-g7-wha77-ugcPost-7201502023496650752-_zRq?utm_source=share&utm_medium=member_android

Ethiopian Health Professionals Association

24 May, 20:30


የኢትዮጽያ ጤና ባለሙያዎች ማሕበር ከጤና ሚኒስቴር በ ቀን 6/2016 ዓ.ም በቀረበዉ ጥሪ መሰረት ከ ጤና ሚንስቴር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እና ሌሎች ሀላፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት አካሂዷል። የ ኢትዮጵያ ጤና ሚንስተር የሆኑት ዶ/ር መቅደስ ዳባ የ 90 ቀን እቅዳቸዉ ውስጥ ባለሙያውን ይዘን እንዴት አድርገን እንስራ በማለት እና ከጤና ማሕበራት ፕሬዜዳንቶች ጋር ለመተዋወቅ ጭምር ፕሮግራም ይዘዉ እንደተገኙ ገልፀዋል። ቀጣይ መሰራት በሚገባቸዉ ስራዎች ላይ ከማሕበራት ምን ይጠበቃል እኛስ ምን እናግዝ የሚሉ ጥያቄዎች ላይ ሰፊ ምክክር አካሂደዋል። አያይዘዉም በቀጣይ በቅርበት ከ ጤና ማሕበራት እና ሌሎች አካላት ጋር ለመስራት እንዳቀዱና የጤና ማሕበራት በጤናዉ ዘርፍ ትልቅ አስተዋፆ እንዳለቸዉ የገለፁ ሲሆን ከማሕበራቱ የተነሱ ሀሳቦችንም እንደግብአት በመውሰድ ሰፊ ዉይይት አካሂደዋል።
የኢትዮጵያ ጤና ማሕበርም ሁሉንም ባለሙያ እንደሚወክል በመግለፅ ለሁሉም ጤና ማሕበራት ማሕበሩን እንዲቀላቀሉ እና ተቀራርበን በመነጋገር በአንድነት ትልቅ ስራ እንስራ በማለት ጥሪ ያቀረበ ሲሆን አብዛኞቹም የማሕበራት መሪዎች ጉዳዩን እንደሚደግፍት እና በቀጣይ ሁኔታዎች ተመቻችተዉ በአንድነት ተቀናጅተን እንስራ ሲሉ አሳስበዋል። የኢትዮጵያ ጤና ማሕበርም ለጤና ሚኒስትር አንዳንድ ትኩረት ሊሰጥባቸዉ የሚገቡ ሀሳቦችን አቅርቧል። ከተነሱት ሀሳቦች መካከል፦
1. ባለሙያዉ ካለዉ ነባራዊ ሁኔታ ብዙ አመት የለፍበትን ስራዉን ትቶ ወደ ሌላ ስራ እየገባ ይገኛል። ስለዚህ በዚ ዙሪያ ምን ታስቧል?
2. ባለሙያዉ የሚያነሳቸዉን ጥያቄ በአንድ ጊዜ መመለስ ስለማይቻል በየጊዜዉ ከማሕበራት ጋር ተቀራርቦ በመወያየት ችግሮቹን የምንፈታበትን መፍትሄ ብንፈልግ የሚል ሀሳብ፣
3. ቡዙ ስራ ተጀምሮ ሳይጠናቀቅ እየቀረ ቡዙ የታካሚዎችን እንግልት ስለሚፈጠር በሁሉም እቅዶች ላይ ቀጣይነት ያለዉ ክትትል ቢደረግ የሚል ሀሳብ ፣
4. የሕክምና ጥራት ላይ ስንሰራ በሁሉም የጤና ዘርፍ ከታካሚ ቅበላ ፣ካርድ ማዉጣት ጀምሮ ሕክምናዉን ጨርሶ እስኪያጠናቅቁ ያለዉን ሁሉ ማካተት እንዳለብን እና በቀጣይ ተግባራዊ ቢደረግ የሚሉ ጥያቄዎችን እና
5. ጤና ሚንስተር ካሉት ቀጣይ እቅዶች በተጨማሪ Diagnostic Service ላይ ትኩረት አድርጎ ቢሰራ አብዛኛዉ የመንግስት ጤና ተቋም የሚታከሙ ታካሚዎችን እንግልት የሚቀንስ መሆኑን ማሕበሩ ሀሳብ ሰቷል።
ከጤና ሚንስትር በተሰጠዉ ማብራሪያ ሚኒስቴር መስራቤቱ ከባለሙያ ጋር ተቀራርቦ መስራት እንዳለበት በማመን አዳዲስ ግኝቶችን ጭምር ከጤና ባለሙያዉ ለመስማት ጥሩ ዕድል እንደሚፈጥር ገልፀዋል። ባለሙያዉን ለማስደሰት ከሚመገብበት እና Night አዳር ላይ ከሚያረፍበት ቦታ ጀምሮ ፅዱ እና ምቹ እንዲሆኑ ለመስራት እንዳቀዱም ገልፀዋል። አያይዘዉም የጤና ጉዳይ ከተነሳ ባለሙያዉ ከሚሰራበት መስራቤት ሆስፒታሎችን ፅዱ እና ለአገልግሎት ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ለማድረግ ቀጣይ በሚጀመረዉ የፅዳት ዘመቻ ሁሉም ጤና ባለሙያ ተሳታፊ እንዲሆን መልክት አስተላልፈዋል። ከጤና ባለሙያ በተደጋጋሚ ለሚነሱም ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ የጤና ባለሙያ Health Insurance ጥያቄ ትኩረት በመስጠት እስከ ሕዝብ ተወካዮች ድረስ ጥያቄዉን በማቅረብ እየተወያየን እንገኛለን በማለት በትግስት እንድትጠብቁ ሲሉ ማብራሪያ ሰተዋል። ለሕብረተሰቡ ከሚሰጡ የጤና አገልግሎቶች ጋር ተያይዞ በሽታ የመከላከል ስራችንን አጠንክረን መቀጠል አለብን ሲሉ ገልፀዋል። የሕክምና አሰጣጡን ጥራት በሚመለከት ከባለሙያ የትምሕርት ስልጠና ጋር ተያይዞ የተሻለ የሕክምና ደረጃ ያላቸዉን ባለሙያዎች እስከታች ድረስ በመመደብ ጤና ሚኒስቴር እንደሚሰራ ገልፀዋል። የጤና ባለሙያ ኬሪየር በሚመለከት need based or Demand based ነዉ የሚለዉን ጨምሮ አጠቃላይ Health Care Finance መታየት ያለበት ጉዳይ መሆኑን ገልፀዋል።

የኢትዮጲያ ጤና ባለሙያዎች ማሕበር
ቀን 16/9/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

Ethiopian Health Professionals Association

17 May, 08:33


""በጤና ተቋማት ያለዉ የደም እጥርት እጂግ አሳሳቢ ነዉ""
“ 20 እናቶች በደም እጦት ሕይወታቸው አልፏል ” - ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል

ከ60 ሺሕ በላይ የሚሆኑ ሕዝቦች የሚገለገሉበት የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቲቺንግ ሆስፒታል ባጋጠመው ከፍተኛ የደም እጥረት ሳቢያ በተለይ እናቶች ሕይወታቸው እያለፈ መሆኑን ሆስፒታሉ ገልጿል።

ላጋጠመው የደም እጥረት ምክንያቱ የደም ባንክ አለመኖር መሆኑን የገለጸው ሆስፒታሉ በዚህም ደም የሚሹ ታካሚዎች ለሕልፈተ ሕይወት እየተዳረጉ መሆኑን አስረድቷል።

የዩኒቨርሲቲው የኮሚዩኒኬሽን ባለሙያ አቶ ኢያሱ ታደሰ ለቲክቫህ ኢትዮጵያና ለሌላ አንድ ሚዲያ በሰጡት ቃል ፣ “ በ6 ወራት ውስጥ በተከሰተው የደም እጦት ሳቢያ 20 እናቶች ሕይወታቸው አልፏል ” ብለዋል።

የደም ባንክ እንዲቋቋም ሆስፒታሉ ለጤና ሚኒስቴር ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርብም ደም ባንኩን ማቋቋም እንዳልተቻለ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ከደም እጥረቱ ባሻገር በሆስፒታሉ በርካታ የወባ ታካሚዎች በመኖራቸው መጨናነቅ እንደፈጠረ፣ ሆስፒታሉ የምርመራ ግብአቶችን ጨምሮ የኦክስጂን እጥረት እንደፈተነው ተመላክቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለጉዳዩ ምላሽ እንዲሰጡ የጠየቃቸው አንድ የጤና ሚኒስቴር ፒአር ባለሙያ ጉዳዩን ከሰሙ በኋላ፣ “ እኔ የፒአር ባለሙያ ነኝ የሚመለከተውን ነው እንጂ የማገናኝህ መልስ አልሰጥህም ” ያሉ ሲሆን፣ ሌሎች የተቋሙ አካላት ለጊዜው ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

Ethiopian Health Professionals Association

09 May, 14:25


➡️ " ውላችን ይቋረጥ ፣ ገንዘባችንም ይመለስ ብለው የፈረሙ 4,000 ቆጣቢዎች አሉ " - የቤት እጣ ቆጣቢዎች

➡️ " ከጤና ሚኒስቴርም ከዳሽን ባንክም ጋር የመግባቢያ ሰነድ ስላለን ተመካክረን መልስ እንሰጣለን " - ጎጆ ብሪጂ

ከ7,500 በላይ ለሚሆኑ ጤና ባለሙያዎች ቤት ገንብቶ ለማስረከብ ከጤና ሚኒስቴርና ከዳሽን ባንክ የሦስትዮሽ ውል የፈረመው ጎጆ ብሪጂ ሀውሲንግ፣ እጣውን በወቅቱ እያወጣ ባለመሆኑ፣ ለወጣላቸውም ግንባታ ባለመጀመሩ፣ 4,000 ቆጣቢዎች ገንዘባቸው እንዲመለስ ቢጠይቁም እንዳልተመለሰላቸው ገልጸዋል።

አሁንም ቢሆን እንዲመለስላቸው ጠይቀል።

የቆጣቢዎቹ ኮሚቴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ " በየ 3 ወሩ ለማውጣት እጣው ሳይሰጥ 2 ዙር አልፏል። ለምን ? ተብለው ሲጠየቁ 'የመሬት አስተዳደር ችግር ስላለብን ነው' እያሉ እስካሁን ቆዩ" ብሏል።

" ውላችን ይቋረጥ፣ ገንዘባችን ይመለስ ብለው የፈረሙ 4,000 ቆጣቢዎች አሉ " ያለው ኮሚቴው፣ በደብዳቤ ጭምር ቢጠይቅም መፍትሄ እንዳልተሰጠው አስረድቷል።

ለተየሳው የእጣ መዘግየት ቅሬታ በጎጆ ብሪጅ ሃውሲንግ በኩል ምላሽ እንዲሰጡ የተጠየቁት አቶ አልማው ጋሪ በሰጡት ሞላሽ፣ " የገጠመን ችግር አደረጃጀት ላይ መዘግየቶች ስለነበሩ ነው " ብለዋል።

" የሚያደራጀው የአዲስ አበባ ህብረት ሥራ ኮሚሽን የሚባለው ነው " ያሉት አቶ አልማው፣ " በሌላ ሳይት ላይ በተፈጠረ ክስ ትንሽ ሥራው ስለቆመ እስኪ ውጤቱን እንየው የሚል ሀሳብ ተነስቶ ስለነበረ የመዘግየት ጉዳይ አጋጥሟል " ነው ያሉት።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጠየቁ ለምን ገንዘባቸውን አልመለሳችሁም ? በማለት ለጠየቀው ጥያቄ ፣ " ውሉ የሚያስቀምጣቸው ብዙ ነገሮች አሉ። ይህን ደግሞ ለብቻችን ሳይሆን ከጤና ሚኒስቴርም ከዳሽን ባንክም ጋር የመግባቢያ ሰነድ ስላለን ተመካክረን መልስ እንሰጣለን " ብለዋል።

የመጀመሪያው እጣ ማውጣት ተደርሶ ወደ 300 ሰዎች እጣ የደረሳቸው አሉ። እነርሱን ለማደራጀት በሂደት ላይ ነው ያለነው” ያሉት አቶ አልማው፣ “አንዳንዶች ደግሞ ቅሬታ አላቸው እየመጡ ይጠይቃሉ” ሲሉ ተናግረዋል።

" የቅሬታ አቅራቢዎቹን ጉዳይም ባለፈው ሳምንት ጤና ሚኒስቴር የተቋማት ተወካዮች በተገኙበት ውይይት ተደርጎ አቀረቡ አቅጣጫ ተቀምጧል። ምናልባት በዚህ ሳምንት አንድ ደረጃ ላይ ይደርሳል " ብለዋል።

#TikvahEthinpiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Ethiopian Health Professionals Association

01 May, 08:43


ከታች በምስሉ የምትመለከቷት እህታችን ዶ/ር ቤቴል ገርማሞ ትባላለች። ከጥቂት አመታት በፊት ከጅማ ዩኒቨርስቲ የህክምና ዶክትሬት ድግሪ ተመርቃ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርቲ በህክምና እና በማስተማር ሲታገለግል ቆይታ በመጨረሻም አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በመቀላቀል የራዲዮሎጂ ስፔሻሊት ስልጠና ከጨረሰች ገና 3ኛ ወሯ ትዳር ከመሰረተች ደግሞ ገና 2ኛ ወሯ ነው።
  
ዶ/ር ቤቴል የመመረቋን እና የማግባቷን ደስታ ገና ሳታጣጥም እንደቀልድ ለቶንሲል ህመም ምርመራ ለመደረግ በሄደችበት  ያልጠበቀችውን መጥፎ ዜና ተረዳች።
 
ቤቲ  የደም ካንሰር በአይነቱም acute lymphoblastic leukemia የሚባል በፓቶሎጂ ምርመራ ተረጋገጠባት።
የጥቁር አንበሳ ሜዲካል ቦርድ አፋጣኝ የሆነ የመቅኔ ንቅለ ተከላ (Bone Marrow Transplant) ከሀገር ውጭ እንዲደረግላት ወስኗል።
  
የደም ካንሰር ምንም እንኳን አጣዳፊ እና አስደንጋጭ ቢሆንም በጊዜ ከታከመ እና የመቅኔ ንቅለ ተከላ ከተደረገ የመዳን ዕድል ያለው በሽታ በመሆኑ ፣ እናንተ ኢትዮጲያዊያ የዚህችን ምስኪን ሀኪም ህይወት በደጋግ እጆቻችሁ ተባብራችሁ እንድትታደጉ ስንል በፈጣሪ ስም እንለምናችኋለን።
  
ዶ/ር ቤቴል በወላይታ ዞን በዴሳ በምትባል ከተማ ተወልዳ ያደገች እና በቤተሰቦቿ እና በአከባቢው ማህበረሰብ እንደምሳሌ የምትጠቀስ ብርቱ ሴት ናት።

እንደ አብዛኛው ኢትዮጲያዊ ቤተሰቧም ሆነ ባለቤቷ  አቅማቸው እሷን ለማሳከም የሚበቃ አይደለም። ቤቲ የምታገለግላችሁ እናንተ ኢትዮጲያዊያን፣ እናንተ ቤተሰቦቿ ናችሁ እና በፈጣሪ ስም የመልካምነት እጃችሁን ዘርግታችህ የቤቲን ሀዘን የቤተሰቦቿን ድንጋጤ እንድትመለከቱ እንላችኋለን።

CBE- 1000105102384 Bethel Germamo Ganebo

GoFundMe: https://gofund.me/fdc9a0b3

Ethiopian Health Professionals Association

01 May, 08:40


እንኳን ለዓለም አቀፍ የላብአደሮች ቀን አደረሳችሁ!
Happy International Labour Day!

Ethiopian Health Professionals Association

30 Apr, 09:56


" የተጠየቀው የህክምና ወጪው በመንግሥት የሀኪም ደመወዝ እና በቤተሰቦቼ አቅም የሚቻል አይደለም - ዶ/ር ሳምሶን ይስሀቅ

ዶ/ር ሳምሶን ይስሀቅ ላጋጠመው የጤና እክል መታከሚያ ደጋግ ኢትዮጵያውያን እንዲተባበሩት ጠየቀ።

ዶክተሩ 2015 ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በህክምና ሙያ ትምህርት ነው የተመረቀው።

ከተመረቀ በኃላም ለ6 ወራት በጠቅላላ ሀኪምነት ወገኑን ሲያገለግል ቆይቷል።

በድንገት ግን ሚዛኑን ስቶ መውደቅ እና ሌሎችም ምልክቶችን በማሳየቱ ወደ ጤና ተቋም ሄዶ ምርመራ ካደረገ በኋላ የጭንቅላት እጢ እንዳለበት ተነግሮታል። የናሙና ምርመራ ተደርጎ GradeIII Astrocytoma እንዳለበት ተገልጾለታል።

" ትልቅ ቦታ ደርሼ ማየት ለሚመኙት ቤተሰቦቼና ከኔ በታች ላሉት እህት ወንድሞቼ ዜናው በጣም ትልቅ ዱብዳ ነው የሆነባቸው " ያለው ዶክተር ይስሃቅ " የጥቁር አንበሳ የጭንቅላት ቀዶ ጥገና ሀኪሞች ወደ ውጪ ሀገር ሄጄ ህክምና ማድረግ እንዳለብኝ ወስነዋል ሲል ገልጿል።

ለህክምናው ወጪው እስከ 2.3 ሚሊዮን ብር  እንደሚያስፈልግም እንደተነገረው አስረድቷል
ይህን ከፍተኛ ወጪ በመንግስት ሰራተኛ የሀኪም ደሞዝም ሆነ በቤተሰቦቹ አቅም የሚቻል ባለመሆኑ ሁላችሁም የቻላችሁትን እንድትረዱት ተማጽኗል
ዶ/ር ይስሃቅ  በየሃይማኖታችሁ ፈጣሪ በመንገዴ ሁሉ እንዲረዳኝ በጸሎታችሁ አስቡኝ  ሲልም ጠይቋል።
ከዶክተሩ የተላከ የህክምና ማስረጃን መመልከት የቻልን ሲሆን  ወላጅ እናቱን ብርሃኔ በየነን በስልክ ቁጥ ር +251911353752 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል
እገዛ ለማድረግ የምትፈልጉ
ዶክተር ሳምሶን ይስሃቅ በየነ
ንግድ ባንክ ፦ 1000139965691
ብርሃኔ በየነ ሚደቅሳ (እናት)
ንግድ ባንክ ፦ 1000549927681
GoFundMe
https://gofund.me/618fc8ee

Ethiopian Health Professionals Association

26 Apr, 15:46


እንዴት አደራችሁ

ጎጆ ብሪጂ ሀውሲግን በተመለከተ

ቴሌግራም ግሩፕ ከፍታችሁ ገንዘብ እናስመልሳለን እያላችሁ ገንዘብ ምትሰበስቡ አካላት እንዳላችሁ እየሰማን እንገኛለን ። በዚ ምክንያት ባለሙያው ገንዘቡ ይመለስልኛል ብሎ እየጠበቀ ይገኛል:: ስለዚህ ሁሉም ባለሙያ ሂደቱን በንቃት መከታተል አለበት። እናስመልሳለን ብላችሁ ገንዘብ ምትሰበስቡ አካላትም ምን ላይ እንደደረሳችሁ በየጊዜው ብታሳውቁ መልካም ነው። ኮሚቴ ነን በማለት እናስመልሳለን በሚል ምክንያት ድጋሜ ባለሙያውን እንዳትበዘበዙ እናሳስባለን። ጤና ባለሙያዎች ሁሉንም ነገር በማጣራት ገንዘባችሁን ያላግባብ እንዳታወጡ ክትትል እንድታደርጉ እናሳስባለ።

Ethiopian Health Professionals Association

26 Apr, 06:33


በትላንትናዉ እለት ሃገሪቱ ላለፉት ሰላሳ አመታት ስትከተለዉ የነበረዉን የጤና ፓሊሲ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ መሸሻሉን መንግስት አሳዉቋል።
1) ለመሆኑ ተሸሻለ የተባለዉ የጤና ፓሊሲ ምን ምን ምን ላይ ትኩረት ያደረገ ነዉ
2) በተሸሻለዉ የጤና ፓሊሲ ባለሙያዎች በቂ ትኩረትና እና ቦታ ተሰጧቸዉ ይሆን
3) ፓሊሲዉ ሲረቅ በሙያዉ በቂ እዉቀትና ግንዛቤ ያላቸዉ አካላት /ጤና ባለሙያዎች/ በበቂ ሁኔታ ተሳትፈዉበታል ዉይስ ለይስሙላ እና ለሚዲያ ፍጆታ ብቻ ነዉ።

"ጤና ሚኒስቴር ስለ ተሸሻለዉ የጤና ፓሊሲ "
ላለፉት 30 ዓመታት ሲያገለግል የቆየው የጤና ፖሊሲ በሽታዎችን መከላከል ላይ መሰረት ያደረገ ሲሆን፣ የጤና ስርዓታችን ወቅቱን የሚመጥን፤ የጤና ችግሮች እና ባህሪያቸው ጋር የተናበበ፣ ለመንስኤዎቹ ተገቢውን ምላሽ የሚሰጥ የጤና ስርአት መገንባት አስፈላጊ በመሆኑ፡ የተሻሻለው የጤና ፖሊሲ ዛሬ ሚያዚያ 17/2016 ዓ ም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ጸድቋል።

አዲሱና የተሻሻለው የጤና ፖሊሲ በሽታዎችን መከላከልና እና ጤናን ማበልጸግ አልፎም የፈውስ ህክምናን እና የቴሪሼሪ የህክምና አገልግሎቶችን ማጎልበትን፤  ጥራቱን የጠበቀ እና ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ የሆነ፤ የተጠናከረ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎችንና መሰል ክስተቶችን የሚቋቋምና ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ፤ በዲጂታል የታገዘ የጤና አገልግሎት መስጠት የሚችል፤ የግል ዘርፉ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ጋር የላቀ ትብብር ያለው፤ የጤና ፋይናንሲንግ ማጎልበት፤ የጤና መረጃ፣ ጥናትና ምርምር እና የእውቀት አሰተዳደርን፤ የማህበረሰቡን ባለቤትነት እና ራስን መቻል መርህ ያለው እና ሃገር በቀል ምርታማነትን ማጎልበት የመድሀኒትና የህክምና መሳሪያ አቅርቦትና አጠቃቀም አስተማማኝ ማድ

Ethiopian Health Professionals Association

24 Apr, 10:24


ዶክተር ኤልሳቤጥ ተሾመ በደብረ ማርቆስ ሆስፒታል የቆዳ ልዩ ሐኪም (specialist) በመኾን ወገኗን ስታገለግል ነበር።
በ14/8/2016 ዓ/ም በአሰቃቂ ሁኔታ በጥይት ተመታ ሂወቷ አልፏል ልብ የሚሰብር መራር ሃዘን!!!
እግዚአብሔር ነፍስሽን በደጋጎቹ ዕቅፍ ያኑርልን!
ለቤተሰቦቿ እና ለስራ ባልደረቦቿ መፅናናትን እንመኛለን!!
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭

Ethiopian Health Professionals Association

20 Mar, 06:57


https://youtu.be/Bg6OVzySg10?si=MGcjm8MNK5DLoYLc

የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኀበር ፕሬዚዳንት ዮናታን ዳኛዉ ከ አሻም ቲቪ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ!