Dandii Boru School (DBS) ዳንዲ ቦሩ ት/ቤት

@dandiiboruofficial


Dandii Boru School Official Telegram Channel. የዳንዲ ቦሩ ት/ቤት ትክክለኛው የቴሌግራም

Dandii Boru School (DBS) ዳንዲ ቦሩ ት/ቤት

20 Jan, 23:57


Hi everyone,
We're thrilled to launch our school's first newsletter! Stay informed about upcoming events, school news, and student achievements. Your feedback is welcome.
Thanks for your support!

Dandii Boru School (DBS) ዳንዲ ቦሩ ት/ቤት

20 Jan, 20:28


🎉 Exciting News Alert! 🎉

Hey there, brilliant minds! We’re thrilled to announce that our online classes are back in action, and guess what? They’re absolutely FREE!

Don’t miss out on this golden opportunity to learn and grow. Click the link below to register and join our vibrant community of learners. Let’s make the most of this together!

Get ready to embark on an incredible journey of knowledge. See you in class! 🚀

https://docs.google.com/forms/d/1MIUjhREfTQWlCIlaL0zBdajc01rhRJs4ff2nKjWS9RI/viewform?pli=1&pli=1&edit_requested=true

Dandii Boru School (DBS) ዳንዲ ቦሩ ት/ቤት

20 Jan, 19:42


ቀን፡ 30/07/2016 ዓ.ም
ለውድ የዳንዲ ቦሩ ትምህርት ቤት ወላጆች/አሳዳጊዎች በሙሉ
በመጀመሪያ የከበረ ሰላምታችንን እያቀረብን የ2016 ዓ.ም የ3ኛ ወሰነ-ትምህርት /ኳርተር 3/ የትምህርት አገልግሎት ክፍያን በጊዜ በመፈፀም የወላጅነት ሃላፊነታችሁን የተወጣችሁትን ከልብ እያመሰገንን እስካሁን ያልከፈላችሁ ወላጆች ከሚያዚያ 5 ቀን 2016 ዓ.ም በኃላ ከቅጣት ጋር ለማስከፈል የምንገደድ መሆናችንን አጥብቀን እናሳውቃለን፡፡
ለልጆቻችን ውጤታማነት በጋራ እንትጋ
የትምህርት ቤቱ አስተዳደር

Dandii Boru School (DBS) ዳንዲ ቦሩ ት/ቤት

20 Jan, 17:21


ታህሳስ 22 ቀን 2016 ዓ.ም

ዉድ ወላጆች/አሳዳጊዎች
ጉዳዩ፡-የመጀመሪያ ወሰነ-ትምህርት የተማሪዎች እረፍት ጊዜ (inter- quarter break) ላይ የተደረገ ለዉጥን ማሳወቅ፤

በመጀመሪያ ወሰነ ትምህርት የተማሪዎች የእረፍት ጊዜ ላይ ስለተደረገዉ መጠነኛ ለዉት ይቅርታ እየጠየቅን፤ ከጥር 1—3 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በሚሰጠዉ የ6ኛ፤8ኛ እና 12ኛ ክፍሎች ሞዴል ፈተና ምክንያት የመጀመሪያ ወሰነ ትምህርት የተማሪዎች የእረፍት ጊዜ ከታህሳስ 29 እስከ ጥር 3 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ መሆኑን በአክብሮት እየገለጽን በዚሁ የእረፍት ጊዜ ዉስጥ ከጥር 1 ቀን 2016 --ጥር 3 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ለ6ኛ ፤8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሞዴል ፈተና የሚሰጥ መሆኑን ከወዲሁ እናሳዉቃለን፡፡

ማስታወሻ፡-
** ከታህሳስ 22-26 ቀን 2016 ዓ.ም ሙሉ ሳምንት መደበኛ ትምህርት የሚካሄድ መሆኑን እንገልፃለን፤
** የሞዴል ፈተና ፕሮግራም በየትምህርት ክፍሉ ወደፊት ይገለፃል፤
** ትምህርት ቤት ሰኞ ጥር 6 ቀን 2016 ዓ.ም ይከፈታል፡፡

የት/ቤቱ አስተዳደር

Dandii Boru School (DBS) ዳንዲ ቦሩ ት/ቤት

20 Jan, 17:21


1st January, 2024
Subject: Inter-quarter break amendment

Dear Parents/Guardians,
According to the Education Office schedule, the grade 6,8 and 12 students` Model Examination will be conducted from January 10—12/2024. This has forced our school to amend the inter-quarter break.

Therefore, we kindly inform you that the inter-quarter break will be from January 8/2024 to January 12/2024. Also, the grade 6,8 & 12 students will have the Education Office Model Exam from January 10/2024 to January 12/2024.
Note:-
There will be regular class from January 1—5,2024
* * The Model Exam specific notice will be announced by the divisions
The school will resume on Monday 15th, 2024.

The School Administration.

Dandii Boru School (DBS) ዳንዲ ቦሩ ት/ቤት

20 Jan, 17:08


🥇🥇Congratulation to all DBS community..!🏆🏆
Dear winners, we are proud of you!!!

እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ!👏👏

በቀን 12/04/2016ዓ.ም
በቂ/ክ/ከተማ በወረዳ 02 ት/ፅ/ቤት በነፃነት ጉድኝት ማእከል  አዘጋጅነት የ2016ዓ.ም የ1ኛ መንፈቀ ዓመት የ8ኛ ክፍል የጥያቄ እና መልስ ውድድር  ተካሄደ።
በውድድሩ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 ት/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው ለገሰ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ  ውድድሩን አስጀምረዋል።
ውድድሩ በ5 የመንግስት እና በ7 የግል በአጠቃላይ በ12 የት/ተቋማት ከፍተኛ ፉክክር በነበረበት ሁኔታ ተጠናቋል።
የማጠቃለያ ንግግር በጠመንጃ ያዥ ሱፐርቫይዘር አስተባባሪ ወ/ሮ ውባለም ደበበ ተደርጓል

፨በውድድሩ  አሸናፊ ተማሪዎች በአማርኛ ስርዓተ ት/ት

1ኛ ተማሪ ረድኤት እሸቱ ከዳንዲቦሩ ት/ቤት
2ኛ ተማሪ አሜን ሰይፈ ገብርኤል ከፊውቸር ታለንት ት/ቤት
3ኛ ተማሪ አብጌል ክበበ ከኒው ግራንድ ት/ቤት ሲሆኑ

  የመፅሀፍ ፥ ሰርተፍኬት እና የዋንጫ ሽልማት ለተማሪዎች እንዲሁም ለት/ት ተቋማት የተበረከተ ሲሆን ። በአጠቃላይ ውድድሩ እንዲሳካ አስተዋፅኦ ለነበራቸው የወረዳ02 ዋና ስራ አስፈጻሚ ፣ ፐ/ሰ/የሰው ኃብት ልማት ጽ/ቤት፣ ወጣቶች እና ስፖርት ጽ/ቤት ላደረጋችሁት ድጋፍ በጉድኝቱ ማዕከል እና በተማሪዎች ስም ምስጋና እናቀርባለን!

Guyyaa 12/04/2016 wal dorgommii gaaffiifi deebii barattoota kutaa 8ffaa Qopheessummaa wiirtuu Natsaannat Birihaaniin qopha'e irratti wiirtuu Falagaa Yoordaanoosii  sadarkaa1ffaa bahuun geeba argataniiru

Dandii Boru School (DBS) ዳንዲ ቦሩ ት/ቤት

20 Jan, 16:44


TO ALL DANDII BORU SCHOOL PARENTS AND STUDENTS

WE WOULD LIKE TO INFORM YOU THAT STUDENTS ARE NOT ALLOWED TO ENTER THE SCHOOL AFTER 8:20AM IN THE MORNING.

Dandii Boru School (DBS) ዳንዲ ቦሩ ት/ቤት

20 Jan, 16:36


1st December, 2023

Dear parents or Guardian

We regret to inform you that the First Quarter report card, which was scheduled to be issued on Saturday 2nd December, 2023, has been delayed due to a minor technical problem in the database system. We apologize for any inconvenience this may have caused.

We would like to inform you that the report card will now be issued on the coming Saturday, 9th December 2023. We appreciate your patience and understanding in this matter.

Sincerely,
The School Administration

Dandii Boru School (DBS) ዳንዲ ቦሩ ት/ቤት

20 Jan, 16:36


ህዳር 21 ቀን 2015 ዓ.ም

የማክበር ሠላምታችንን እያቀረብን፤

በት/ቤቱ ዓመታዊ ዕቅድ መሠረት ቅዳሜ ህዳር 22 ቀን 2016 ዓ.ም ይሰጥ የነበረዉ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ሪፖርት ካርድ ባጋጠመን መጠነኛ የመረጃ ቋት ችግር ሊደርስልን ባለመቻሉ ይቅርታ እየጠየቅን፤ ሪፖርት ካርዱ! በሚቀጥለዉ ቅዳሜ ህዳር 29 ቀን 2016 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን ከወዲሁ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
የት/ቤቱ አስተዳደር

Dandii Boru School (DBS) ዳንዲ ቦሩ ት/ቤት

20 Jan, 15:31


https://forms.gle/x5gMcbVkYTzUVmTQ9

Dandii Boru School (DBS) ዳንዲ ቦሩ ት/ቤት

20 Jan, 15:05


መስከረም 15 ቀን 2016 ዓ.ም
ለዳንዲ ቦሩ ትምህርት ቤት ወላጆች/አሳዳጊዎች በሙሉ
በመጀመሪያ በያላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛ እያልን የሚከተሉትን መልዕክቶች ለማስተላለፍ እንወዳለን፡፡
1. መስከረም 16 አእና 17 በበዓላት ምክንያት ትምህርት የማይኖር መሆኑን እንዲታውቁ፣
2. ዓርብ መስከረም 18 ቀን 2016 ዓ.ም ትምህርት ሙሉ ቀን እንደሚኖር፣
3. ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ማንኛውም ተማሪ ያለ ዩኒፎርም እና ባልተስተካከለ ፀጉር ግቢ መግባት የማይቻል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

መልካም በዓል ይሁንላችሁ
የትምህርት ቤቱ አስተዳደር

Dandii Boru School (DBS) ዳንዲ ቦሩ ት/ቤት

20 Jan, 13:34


https://t.me/dbssummeronline2023

Dandii Boru School (DBS) ዳንዲ ቦሩ ት/ቤት

20 Jan, 12:44


15/10/2015
ለዳንዲ ቦሩ ትምህርት ቤት ወላጅ/አሳዳጊዎች

ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ት/ቢሮ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተናን አስመልክቶ በተላከልን ደብዳቤ መሠረት ለ8ኛ ክፍል ከሰኔ 26-27/2015 ዓ.ም ፈተና የሚሰጥ ሲሆን ለ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ደግሞ ከሰኔ 28-30/2015 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል፡፡

•ከአርብ ሰኔ 16 ቀን 2015ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሀሙስ ሰኔ 22 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ተማሪዎች ቤት የሚቆዩ ይሆናል፡፡

•አርብ ሰኔ 23 ቀን 2015 ዓ.ም ተማሪዎች በት/ቤት የሚገኙ ሲሆን እስከ 5፡30 ድረስ ይቆያሉ፡፡ በዕለቱ በት/ቤት ደረጃ ፈተናውን አስመልክቶ ገለጻ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

•አርብ ሰኔ 16 ቀን  የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ትምህርታቸውን መጨረሳቸውን በማስመልከት ከት/ቤቱ አዳራሽ ከ3፡00- 5፡00 የሚቆይ ፕሮግራም ይኖራቸዋል፡፡ ፕሮግራሙን መሳተፍ አስገዳጅ አይደለም ፈቃደኛ ከሆኑ ልጅዎች መላክ ይችላሉ፡፡

•ከፈተና በሚወጡበት ወቅት ት/ቤቱ ለተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ሊያቀርብ ይችላል፡፡

•ፈተናውን አስመልክቶ የሚኖሩ ተጨማሪ መረጃዎች ሲኖሩ በቴሌግራም ቻናል ላይ የምናሳውቅ ስለሆነ እንዲከታተሉ ይሁን፡፡

መካከለኛ ደረጃ ት/ክፍል

Dandii Boru School (DBS) ዳንዲ ቦሩ ት/ቤት

20 Jan, 10:18


መጋቢት 4 ቀን 2015 ዓ.ም

ለተማሪ ወላጅ/አሳዳጊ

የማክበር ሠላምታችንን እያቀረብን፤ በት/ቤቱ ዓመታዊ እቅድ መሠረት ቅዳሜ መጋቢት 9 ቀን 2015 ዓ.ም (Saturday Afternoon 18th March, 2023) በ1ኛ ወሰነ ትምህርት የተማሪዎች ዉጤት ዙሪያ እና የ2016ዓ.ም የት/ቤት አገልግሎት ማስተካከያ ክፍያን አስመልክቶ የት/ቤቱ አስተዳደር ከወላጆች/ከአሳዳጊዎች ጋር ሁለተኛ ስብሰባ ስለሚያካሄድ ልክ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በት/ቤቱ አዳራሽ እንድትገኙና በመማር ማስተማር ዙሪያ ያላችሁን ገንቢ አስተያየት እንድትሰጡን በአክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

የት/ርት ጥራትን ለመሻሻል የጋራ ጥረታችንን እናጠናክር!
የት/ቤቱ አስተዳደር

Dandii Boru School (DBS) ዳንዲ ቦሩ ት/ቤት

20 Jan, 10:09


ቀን፡ 28/06/2015 ዓ.ም

ጉዳዩ የሚመለከታችሁ ውድ የዳንዲ ቦሩ ትምህርት ቤት ወላጆችና አሳዳጊዎች

በመጀመሪያ የከበረ ሰላምታችንን እያቀረብንላችሁ የ3ኛው ሩብ ዓመት የትምህርት ቤት ክፍያ ጊዜው እያለፈ መሆኑን እና የክፍያ መዘግየት በመማር ማስተማር ሂደቱ
ላይም የራሱ የሆነ ተፅዕኖ እንዳያሳድርም ጭምር በመገንዘብ ያለባችሁን ክፍያ በጊዜ እንድታጠናቅቁ በትህትና እየጠየቅን ክፍያችሁን አስቀድማችሁ የፈፀማችትንም
በዚሁ አጋጣሚ ልናመሰግን እንወዳለን፡፡

የትምህርት ቤቱ አስተዳደር