Cecilia School Alamura Branch @cecsch1 Channel on Telegram

Cecilia School Alamura Branch

@cecsch1


Cecilia School Alamura Branch

Cecilia School Alamura Branch (English)

Welcome to Cecilia School Alamura Branch! Are you looking for a quality education for your child in Alamura? Look no further, as Cecilia School Alamura Branch is here to provide your child with the best learning experience possible. Founded with a mission to nurture young minds and empower them to reach their full potential, Cecilia School Alamura Branch is dedicated to ensuring that every student receives a well-rounded education. From academics to extracurricular activities, our school offers a comprehensive curriculum that focuses on holistic development. Our experienced and passionate teachers are committed to providing a supportive and engaging learning environment for all students. At Cecilia School Alamura Branch, we believe in fostering creativity, critical thinking, and a love for learning in every student. Join our Telegram channel @cecsch1 to stay updated on school events, academic achievements, and important announcements. Be part of the Cecilia School Alamura Branch community and give your child the gift of quality education. Enroll your child today and watch them thrive at Cecilia School Alamura Branch!

Cecilia School Alamura Branch

21 Nov, 07:59


ቀን 12-03-2017 ዓ.ም


ለት/ቤታችን ተማሪዎች እና ወላጆች
የፈተና ፕሮግራምን ስለማሳወቅ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ቀደም ብለን የ1ኛው መንፈቀ ዓመት አጋማሽ ፈተና፦

👉ከአፀደ ህፃናት ጀምሮ እስከ 10ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የፊታችን ሰኞ ህዳር 16/2017 ዓም

👉 ለ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች የመጀመሪያው ዙር ሞዴል ፈተና ደግሞ ህዳር 19/2017 ዓም እንደሚጀመር በገለፅነው መሠረት በየክፍል ደረጃው ያለውን ዝርዝር የፈተና ፕሮግራም ከዚህ በታች ስለለጠፍን ለዝግጅት መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
👇👇

Cecilia School Alamura Branch

20 Nov, 16:36


ቀን 11/03/2017ዓ.ም


ለመላው የት/ቤታችን ወላጆች
።።።።።።።።።።።።።።

👉 ነገ ህዳር 12/2017 ዓም
ከጤና ጣቢያ የሚመጡ ባለሙያዎች ዕድሜያቸው ከ9-14 ለሆኑ ሴት ተማሪዎች የማህፀን በር ካንሰር ክትባት ይሰጣል።
ስለሆነም፦
በወላጅ የተፈቀደላቸው ልጆችን ብቻ ስለምናስከትብ ልጆቻችሁ ክትባቱን እንዲወስዱ የምትፈልጉ ወላጆች መፍቀዳችሁን በልጆቻችሁ በኩል ታሳውቁን/ትልኩልን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን ።


።።።ት/ቤቱ።።።።

Cecilia School Alamura Branch

13 Nov, 19:24


ቀን 05/03/2017ዓ.ም


አስታውሱ
""""""""""""
👉ለመላው የት/ቤታችን ተማሪዎች
።።።።።።።።።።።።።።።።።

የ2017 ዓ.ም የ1ኛው መንፈቀ - ዓመት አጋማሽ ፈተና የሚሰጠው፦
ከህዳር 16 - 20/2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ መሆኑን እያሳወቅን አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ታደርጉ ዘንድ በአፅንኦት እንመክራለን።

የተከበራችሁ የተማሪ ወላጆችም ልጆቻችሁን ለፈተና በማዘጋጀት የድርሻችሁን እንደምትወጡ አንጠራጠርም !!


።።።ት/ቤቱ።።።

Cecilia School Alamura Branch

12 Nov, 20:00


።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ይህን ትውልድ አስችለነዋል❗️

" በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ "
እንዲሉ

ከተማሪዎቻችን ጋር ከታች ጀምሮ ለተከታታይ ዓመታት እያደረግናቸው የመጣናቸው የመድረክ ውይይቶች በየጊዜው የሚታዩ ተቋማዊ ክፍተቶቻችንን ለማረም ከማስቻላቸውም በላይ ልጆቻችን ሀሳባቸውን፦

👉ያለፍርሃት በትህትና ፣
👉በስማ በለው ሣይሆን በተጨባጭ ምክንያት/ማስረጃ
👉 በጥራትና በነፃነት የመግለፅ አቅማቸው እና
👉በራስ የመተማመን ስሜታቸው በእጅጉ መጎልበቱን አረጋግጦልናል ።


👇👇