እና ኦ! ጠይምነቷ: የቀሚሷ በጨዋታ መሃል ከኋላ ፊኒር አባባልና ከዛም ስር ሰርቄ የማያቸው(ዘራፍ ዓይነ ሌባው) ጠይም ወዛም ጭኖቿ………አላፈቀርኳትም ግን በዓይኔ በብሌኑ ገባች፡፡ ጠይም ጦር፡፡" ገጽ 8
"መኝታቤቴ ውስጥ ነው ብዙ ጊዜ የምቀመጠው:: መኝታቤቴ ማድቤቱ አጠገብ ነው:: ማድቤቱ መንገድ ዳር ነው:: መንገድ ዳር ሆነህ ብታፏጭልኝ እሰማለሁ»
ሒድ እንግዲህ! አለ ተገራሚ፡፡ በልቤ በዚህ ዘመን የዚህ ዓይነት ነገር ይደረጋል? አልኩ «ሦስቴ አፏጭልኝ» አለች
ይታያችሁ ከመሽኮርመምና ገመድ ከመዝለል ሌላ ምንም አታውቅም ያልኳት ልጅ ስለፉጨት ጠቃሚነት አንድ ነጥብ ብጉራም ዕውቀቴ ላይ ጨመረችልኝ፡፡ ጠንቅቄ የማውቀው ፉጨት የጎል ኪፐራችንን ነው.... አቀብለኝና እኔ ልለጋው' ሲለኝ:: ከዚያ ሆኖልን የተገናኘን ቀን...
እኔ ኋላ ኋላ፣ እሷ ፊት ፊት። እዛ እዛ የሚያይ መስዬ እዛች ሚኒ ቀሚስ ስር የማላውቀውን ሁለመናዋን እየጎመጀሁ፡፡ ከአፏ ላይም ለሆነ ማታ የሚሆነኝ ቅዠት ልለቃቅም፡፡" ገጽ 11
"የፋሲካ ትርጉም ፍፁም የመብላት ነው:: ከተክሎች እስከ እንስሳት የሚበሉበት ነው። አንዳንዴ እንደ እኔ ዓይነት ሞላጫ ወይም የመሰለው፣ እንደ ኮረሪማ ዐይነት የዋሕ ወይም የመሰለች የፌሽታ ሜኗቸው ላይ ልጃገረድ መሳምና መሳሳም የመሳሰለ ቢጨምሩበትስ?" ገጽ 15
***እዚህ ታሪክ ላይ ኮረሪማ ኤፍሬም ሲያፏጭላት ለምን አልወጣችም? ለምን ስምምነታቸውን አላከበረችም ብዬ ሳሰላስል ነበር። ነገር ግን በሌሎች ትርክቶች ውስጥ ብዙ ጊዜ ኮረሪማን የምናገኛት የሆነ የወፍ ደዌ ይዟት ታማሚ ሆና ነው። ስለዚህ ታማ ይሆን ያኔ ያልወጣችው? አላውቅም። በመጨረሻው ትርክት ውስጥ ግን ኤፍሬም የተሳካለት ይመስላል። ምክኒያቱም ነጻነት የተባለችው ገፀ ባሕሪ ኤፍሬም እነ ኮረሪማ ቤት እንደ አየር ሲገባና ሲወጣ አይቼዋለሁ ትላለች። I guess በዚህ ትርክት ውስጥ the happy ending happened። እንዲህ ነው አዳም ትርክቶቹን ያስተሳሰራቸው።
***በጣም ከወደድኩት ትርክት ከእቴ ሜቴ ሎሚ ሽታ ደሞ የመሰጡኝ አንቀፆች እነዚህ ነበሩ።
"ረዳቷ ነሽ' ስለተባልኩ ለድምፅዋና ለግልምጫዋ እንድቀርብ ከእሷ ብዙ እርቄ ተቀምጬ አላውቅም (በማላውቀው ምክንያት አንዳንዴ ስጠጋት ብትነጫነጭም) ሁልጊዜ ስርስሯን ነው የምሄደው! ስርስሯን። የታዘዝኩትም እንደዚያ እንድራመድ ነው። እንደ እንቅፋት። ወይ ምን ልበል እንደ ውሻ። ተከናንበን ስንጓዝ ግራና ቀኝ ተመልካች የሚያስበ ልጅና እናት እንደሆንን አድርጎ ነው:: ሎሚሽታ በጣም ረዥም ሴት ናት። ደልደልም ያለች ናት። እኔ ትራፊዋ እመስላለሁ:: እሷ ከሰማይ ብትወረወር እና ብትሰባበር ደቃቃዋ ተፈናጣሪት እዛ ቦይ ወድቃ የምትገኝው እኔ ነኝ። ማሪያምን። መጀመሪያ ጨዋ መስላኝ ነበር አጃቢ ስትፈልግ:: በኋላ በኋላ ሳይ ለካስ ባሏ ያልበቃት የውሸት ዓይኖቿን የደፋች ቅሪ ናት፡፡ ያገባች ጋለሞታ።" ገጽ 42
"ባለቤቴ ጠበቃ ስለሆነ ነገር ሲጥልና ሲያነሳ ጠዋት ከቤት የወጣ የሚመለሰው ሲመሽ ነው፡፡ እሱን ራት አብልቼ፤ አልጋ ላይ አስተኝቼ፣ ከእኔም ነገር ጉዳይ ካለው እሷን አደራርጎ፣ ስለፍትሐ ብሄርና ስለወንጀለኛ መቅጫ እያሰበ ወይም እያለመ ይተኛል፡፡ ጎኑ ተጋድሜ ገና ሳገባው አደርገው እንደነበረ ሁሉ ሆዱን እዳብስለታለሁ፣ ችፍ ያለ ቅንድቡን በአመልካች ጣቴ እካክክለታለሁ፣ በጀልጃላ ውስጥ ሱሪው ስር እጄን አስገብቼ ፀጉር የፈሰሰበት ጭኑን እነካካዋለሁ:: ከደስታ ይልቅ ውስጤ የሚሰማኝ አነጣጥሬ ያለመውደዴ ቁጭት ነው:: ታዲያ ወደ ውጭ እሱ እንዳይሰማኝ አድርጌ እተነፍሳለሁ፤ አተነፋፈሴን ከሰማኝም የፍቅር ስራው ያረካኝ ለመምሰል በወዛም ፀጉር የተሸፈነ ፊቱን አፌን ከፍቼ እስምለታለሁ፡፡" ገፅ 87
"ታዲያ ለቅሶ ቤት እንዳየኝ (እኔም እንድታይ ፊት ለፊቱ ሄጄ ተጎለትኩ) ትክ ብሎ አፉን ከፍቶ ሲያጠናኝ ቆየና ሰላምታ ሰጠኝ………ከአምስት ዓመት በፊት:: ቤቴ በአሮጌ ፔጆው ሸኘኝ፡፡ ለስድስት ወር አብረን ወጣንና ለመጋባት ወሰንን:: አያችሁ ሰው ጣዕሙ እንደ ከረሜላ የሚያልቅ አልመሰለኝም:: ሁለት ዓመታት መጠጥኩት። በትልቅ አፌ አስገብቼ አንገላታሁት፡ ትልቅ ክንዴ ላይ አስቀምጬ እኔ ልጅት ወንድነቱን ተፈታተንኩት:: በከፊል ሽክላ በከፊል ጭቃ በሆነች ቤቱ ከዳር እዳር ዘለልኩባት፡፡ አንድ ጠዋት ስነቃ ብዙ ያለፍኳቸው፣ ያልኖርኳቸው መልካም ነገሮች እንዳሉ ሊያሳየኝ ነው መሰለኝ እግዜር አስናቀን አምጥቶ ፊቴ ገተረው:: ገበያ መሃል ጣልያን እድሞ ፒያሳ አሳዶ የተከተለኝ ዕለት ዞር ብዬ ሳየው ጥቁር ረዥም ፊቱ (አንዳንዱ ያልገባው 'ሞጋጋ' የሚለው)፣ ሰማይ የነካ የመሰለው ሎጋ ቁመናው አብረከረከኝ:: የአለባበሱ ጥራት፣ ትላልቅ ዓይኖቹ ውስጥ የሚንቦገቦገው የፈላ ስሜት መረጋጋቴን አበለሻሽው፡፡" ገፅ 189
"ሳቅሁባት:: ሁሉ አገርሽም እኔም ቁንጅናችንን ልጅነታችንን በትክክል ያልተጠቀምንበት ጅሎች ነን:: እኔ ብዙ ፍቅር ሳላገኝበት ራሴን ስቆጥብ፤ እሷ ደ'ሞ ላገኘችው ወዲያና ወዲህ ስትወረውረው፡ እኔ የማያስፈልግ ውድ ነገር ራሴን አድርጌ ስቆጥር፣ እሷ እንደ ርካሽ ነገር ለአላፊ አግዳሚ ሰጥታው:: ለእሷ የመዝናናት ነጻነት የሰጣት ለእኔስ ያልሰጠኝ ማነው?" ገጽ 93
"'ሴት ነኝ አየሽ:: በትምህርት ነፃ አልወጣም:: እዚህች አገር በትምህርት ነፃ አይወጣም: በትምህርት ብቻ ነፃ የወጣ የለም፡፡ ሕይወት አሁን ነው:: በልጅነት ነው ጨዋታ:: ሴት ሆነሽ ሁለት ነገር፤ ዋና ዋና ነገር ያስፈልግሻል፡፡ ቢቻል ሦስት:: ወሲብ መስጠት፣ ቁንጅና፣ ትምህርት፡፡ በአጭሩ ሸርሙጣ፣ ቆንጆና ምሁር መሆን፡፡ አለበለዚያ የትም አትደርሺም፡፡ ሽርሜነትን ጀማምረሽ አቁመሽዋል፣ ምሁር አይደለሽም፣ ቁንጅናሽ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ይጠፋል፡፡ ይጎልሻል፡፡ አንዱን ብቻ ከሆንሽ ይጎልሻል። ወንዶች ወይም ገዢዎችሽ እንድትሆኚ የሚፈልጉትን መሆን አለብሽ፡፡ ሴት ለማን ተሰራች? ለወንድ፡፡ ቆንጆ... ሽርሙጣ……..ምሁር። ሦስቱን በአንዴ አጠቃለሽ መያዝ፡፡ እንደ እኔ መኪና መንዳት ትፈልጊያለሽ? ነጠላ ተከናንበሽ ከሠፈር ሉዘሮች ጋር ስትዳሪ ልታረጂ ነው? ነቃ በይ፡፡ ቆንጆ ነሽ። ሽርሙጣ ነሽ፡፡ በቀላሉ ካናሳ ፖለቲከኛ ጋር አገናኝሻለሁ……..ከፈለግሽ፡፡ ይኼ ሁሉ የምታየው ብዙው የማይረባ ሰው ነው:: ይሉኝታ አይያዝሽ፡፡ ኢትዮጵያ ሺት ነገር ሆናለች። ትዳር ይፈርሳል በየቦታው………እንደ እኔ አይነቶች 'አፍርሱ' የተባልነውን እናፈርሳለን፡፡ ሻል ያለ ፈልጊ 'ጎጆ መውጣት' ምናምን ሲሉ ቃሉ ራሱ አያስቅም? እ? ሂሂሂ 'ቪላ መውጣት' 'መኪና መውጣት' አይሉትም እንዴ?… ሂሂሂሂ…………የምትኖሪው አንድ ጊዜ ነው……..አስናቀ ምንድነው? የሆነ ባርያ ነገር (አውጥታዋለች እኮ) ወንድ ላሳይሽ? ያለው? የሚያበሉ የሚያጠጡ፣ የሚተኙ፣ የሚያለብሱ:: ማሳደር የሚችሉ:: መኪናቸውን የሚያውሱ፡፡ ሳይቆጥቡ የሚያሰክሩ:: ከፈረንጅ እስከ ተቃጠለ አበሻ አሳይሻለሁ:: የእኔን ልብስ ተዋሺና አንድ ቀን እንውጣ ትምህርት ቤት ደርሶ አለማያ ከመሄዴ በፊት…….አያይዤሽ.....»
'በይ እግዜር ይርዳሽ እቴ' አልኳት በልቤ፡፡ እግዜር የማይረዳው ዓይነት ሰው የለ)" ገፅ 97