Dernières publications de ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖 (@bookshelf13) sur Telegram

Publications du canal ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖
"ስለመጻሕፍት ከመጻሕፍት መንደር እንዘምራለን!"
18,903 abonnés
2,716 photos
24 vidéos
Dernière mise à jour 27.02.2025 06:07

Le dernier contenu partagé par ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖 sur Telegram


ውድ የፌስቡክ ወዳጆቼ እንኳን ደስ ያለን!!!

መቼም ቤጃይን የማያውቅ ፌስቡክ ተጠቃሚ አለ ማለት ይከብደኛል። ለፈጠራ ባለቤቱና ለስራ ጀማሪው በሚያሳየው የገንዘብና የሀሳብ ድጋፍ ሲያደርግ የምናውቀው ቤጃይ ዛሬም በቅርብ የወጣውን "ዓይነ ርግብ" የተሰኝውን አጫጭር ልብወለድ ታሪኮችን የያዘው መጽሐፌን 200 ኮፒ በመግዛት የፌስቡኩን ጀማ በስጦታ አንበሽብሺልኝ ብሎኛል።
ለቀና ሀሳቡና ለትብብሩ ከፍ ያለ ምስጋና እያቀረብኩ እንግዲህ "ዓይነ ርግብ" እንዲኖራችሁ የምትፈልጉ ሁሉ መገናኛ በሚገኝው
3M Mall - 3ኛ ፎቅ ላይ Phoenix Store (ኮምፒውተር መሸጫ ቤት)
( 251919875964 - በረከት ጋር)
ከነገ ጀምሮ ሄዳችሁ ነጻ ኮፒያችሁን መውሰድ ትችላላችሁ።
ብትችሉ ደግሞ መጽሐፉ እንደደረሳችሁ የሚያሳውቅ ማስታወሻ ፎቶ ከመጽሐፉ ጋር ተነስታችሁ በፌስቡክ ገጻችሁ እንድትለጥፉ በትህትና እጠይቃለሁ።

ሌላው ጥሩ ዜና ደግሞ ቤጃይ ይህን ሁለት መቶ ኮፒ ሰዎች ወስደው ከጨረሱ ለሌሎች 200 እድለኞች ስጦታ የሚሰጥ መሆኑን ነግሮኛል። ስለዚህ ይህንን ስጦታ ቶሎ ቶሎ በመውሰድና የንባብ ውጤታችሁን በማጋራት የንባብን ባህል አበረታቱ

ነመስቴ 🙏 ውድ Bejai Nerash Naiker

© Tigest Samuel (Art of Tigest)

ቀልዱ ቀልድ ነው። ግን በህይወትህ ስትኖር በትንሽ በትንሹም ቢሆን እንደ አርኪቴክቶች ዓይነት የቻልከውን ሁሉ ነገር የማወቅ ያልተቋረጠ ስብዕና መገንባት ይኖርብሃል እንደ ሰው ብዬ አምናለሁ!

ብዙ ጊዜ የሚገጥምህ ደፋር ሰው ታገኛለህ። አንድን የተለየ ነገር ነው ያጠናውና የሚያውቀው። ከዚያ ግን ስለሌላም ነገር በድፍረት ሲናገርና ሲደመድም ታገኘዋለህ። እንዴ? እሱ ያጠናው ስለሴቶች ጥቃት፣ የሚናገረው ስለ ኒውክሊየር ጥቃት፣ ይሄነገር ግን እንዴት እንዴት ነው?

Well, አንብቦ፣ ራሱን በራሱ አሳውቆ፣ አስተምሮ፣ አጥንቶ፣ መርምሮም ሆነ ተመራምሮ ከሆነ እሠየሁ! አለበለዚያ ግን የሚናገረው ሁሉ ከንቱ ነሲብ ብቻ ነው! በከንቱ ነሲብ ስንት የዓለም ነገር፣ ስንት የሀገር ነገር ጠፍቷል! ...

ግን ማንበብ የሚባል ነፍስ-አድን ነገር አለ! ማንበብ ከነሲበኛነትና ከጥራዝ ነጠቅነት ይጠብቅሃል! ካነበብብቻ ነው ይቅር ልልልህ የምችለው እንጂ ያልዋልክበትን ነገር ስትቀባጥር ብሰማህ ታዝቤህ አላባራም!🥺😊

የኛ ነገር ብዙ ጊዜ እንዲያ ይሆንብኛል! ማንበብን ባህላችን ስለማናደርግ፣ ራሳችንን የዕድሜልክ ተማሪ ለማድረግ ኑሮና ልማድ ስለሚይዘን፣ ብዙ ነገሮቻችንን ለነሲበኞች አስረክበን ያልተጨበጠ ነገር እንዳንጠለጠልን እናዘግማለን! እነዚህ ነገሮች ድምር ውጤታቸው በሀገርም፣ በዓለምም ደረጃ ያሻቅባል! ያው ነው! ይህን ስል አንድ የቅርብ የዓለም ነገር ትዝ አለኝ!

የአሜሪካውን የቀደመውን ፕሬዚደንት ጆ ባይደንን አንድ ጋዜጠኛ ጠየቀው። ለማንበብ ጊዜ አለህ ወይ? ካለህስ፣ ምን ዓይነት መፅሐፎችን ነው የምታነበው? ብሎ ጠየቀው።

ለንባብ የማውለው ጊዜ እጅግ ጠባብ ነው፣ ብዙ ጊዜ በአማካሪዎቼ ሃሳብ ለመመራት እገደዳለሁ፣ ግን ባለችኝ ጊዜ የግድ የማነባቸው መፅሐፍት አሉኝ፣ ለምሣሌ ፊዮና ስለ ቭላዲሚር ፑቲን የፃፈችውን መፅሐፍ!🤓🤔

ይሄን የባይደንን አስተያየት ሳነብ፣ ይበልጥ እገረማለሁ። ባለፈው ሌላ ጋዜጠኛ ሲጠይቀው ነበር፣ እውነት ግን እርስዎ ፑቲንን ፊትለፊት "ነፍስህን ሠይጣን የነጠቀህ ሰው ነህ!" ብለውታል? መረጃ ስለደረሰኝ ነው እርስዎ ያረጋግጡልኝ።

ባይደን ሳቀ። አይ አንተ እንዳልከው እንኳ ቃል በቃል አላልኩትም። ግን ይሄንኑ ለማለት ነው የፈለግኩት። አብረን እየሄድን እርሱ እያስጎበኘኝ እያለ፣ "የብዙ ሰዎችን ዓይን ተመልክቼ፣ የውስጣቸውን ሃሳብ ማወቅ እችላለሁ፣ ያንተን ዓይን ግን ሳየው ባዶ ነው፣ ነፍስህን ላገኛት አልቻልኩም!" አልኩት።

ጋዜጠኛው ሌላ ጥያቄ አስከተለ። እና ግን ይህን ሲሉት ፑቲን ምን መልስ ሰጠዎት? "Well, that's good! It means now we've perfectly understood each other!" ብሎኝ ወደቀጣዩ ጉብኝት ከፊት እየመራ ወሰደኝ!🤪😃

("የታየዎት ነገር ጥሩ ነው፣ አሁን በሚገባ ተግባብተናል/ተዋውቀናል መለት ነው፣ ወደሚቀጥለው ጉብኝታችን መሄድ እነችላለን?" - ቭላዲሚር ቭላዲሚሮቪች ፑቲን🤓😯🤔🤪😃)

የሠላዩን ዓይን ለመሠለል በመሞከር ሂደት የተገኘ ተሞክሮ!🤪😃 ግን ሌላ ጊዜ ራሺያ ዩክሬይንን ከወረረችጰበኋላ፣ ባይደን ጋዜጠኞች ሰብስበው ከዋይትሃውስ፣ ፑቲንን "ሠይጣናዊው ሰው" ሲሉ ጠርተውታል!

ከራሺያ አምባሳደር የዚያኑ ቀን የመጣላቸው አጭርና አስቸኳይ መልዕክት እንዲህ የሚል ነበር፦

"እንከባበር! የርዕሰብሔራችን ክብር እንዲጠበቅና፣ ከመዘላለፍ እንዲቆጠቡ፣ በተገቢው የአክብሮት ቃልም እንዲጠራ እንጠይቃለን! ዓለማቀፍ ዲፕሎማሲያዊ መርህን እየጣሳችሁ ነው፣ የሀገር መሪ ነው፣ በክብር አድሬስ አድርጉት፣ ታረሙ!"

(ብርቱ የማስጠንቀቂያ መልዕክት!🤓🤔😊🤪)!

ግን ባይደን ስለ ፑቲን መዓት አማካሪ እያላቸው፣ በአካል ዓይኑን አይተውት፣ አሊያም ይህን መፅሐፍ አንብበው ሲያበቁ፣ ለምን በዩክሬይን ጦርነቱ ሲፈነዳና በመቶ ሺህዎች የሰው ህይወት በጦርሜዳና በከተሞች ሲረግፍ፣ ከፑቲን ጋር አልነጋገርም ብለው በአቋማቸው ደረቁ? ...

ከሚያነብ ሰው፣ ሁሌ ተማሪ ከሆነ ሰብዕና፣ ስለ ፑቲን ከአማካሪዎቹ አልፎ በራሱ ለማወቅ ጊዜውን ከሰጠ ሰው፣ ሰውየውን በዓይኔ አያሳየኝ ብሎ ድርቅ ማለት የተሟላ ሰብዕና መገለጫ ይሆን? ያውም ወደ ኒውክሊየር ጦርነት የሚያመራ አስፈሪ ፍጥጫ ከዕለት ዕለት እየጨመረ በሚመጣበት በቀለጠ የጦርነት ሠማይ ሥር? ...

ወይስ ጆ ባይደን ከዚህ መፅሐፍ ስለ ፑቲን ሰብዕናና ስነልቦና ወይም ማንነት ምን ዓይነት ሴለሰውየው ጨርሶ መደምደሚያ የሚሆን ሃሳብ ቢያገኙ ነው?..

አላውቅም! ይሄንንና ሌሎችንም ነገሮች ጨምሬ ለማወቅ ስል ግን፣ ይህን መፅሐፍ የግድ ማንበብ እንዳለብኝ ተሰማኝ። እነሆ እጄ ከገባ ሁለተኛ ቀኑ! ቀኑን ለሠራዊት፣ ምሽቱን ለመፅሐፍት፣ ሌቱን ለአራዊት... ሰጥተን ተነስተናል!

ይሄን መፅሐፍ ማንበብ፣ ጆ ባይደንንም፣ ፑቲንንም ማንበብ እንደሚሆንልኝ አምናለሁ! በበኩሌ የጆ ባይደንን መፅሐፍ አንብቤያለሁ፣ ግን እስካሁን የጆ ባይደንን ነፍስ አላገኘኋትም!😃🤪 ምናልባት በዚህ መፅሐፍ በኩል አገኘው ይሆናል!😊🤓

ባለፈው የካረን ዳዊሻን ስለ ፑቲን ክሌፕቶክራሲ የተፃፈ አስገራሚ ሪሰርች የሚባል መፅሐፍ አንብቤያለሁ። ብዙ መረጃዎች ነበሩበት። ልክ አንድ የሥለላ መሥሪያ ቤት በሆነ ሰው ላይ ለዓመታት ያጠናቀረው የሚመስል ብዙ ውስጠ ምሠጢሮችን የሚያውጣጣ መፅሐፍ ነው።

ግን ... ብዙው ነገር የአንድ ወገን ስሞታ ብቻ ነው፣ እና ስም ማጥፋት፣ ሁሉንም የፑቲንን እንቅስቃሴ እኩይ የጋንጊስተሮች ጨዋታ አድርጎ ማቅረብ ነው! ሚዛናዊ አይደለም! ዓይን ገላጭ ግን ነው! ከነትዝብቴ ከድኜዋለሁ!

አሁን ግን ይሄኛውን መፅሐፍ ብዙዎች በገለልተኝነቱ ሲያደንቁት ተመልክቼያለሁ። ከሆነ፣ (ቢሆን ኖሮ) ግን፣ ፑቲንን አላናግርም ብለው እስከመጨረሻዋ የሥልጣን ሰከንዳቸው የደረቁት ባይደን፣ ይሄን መፅሐፍ አንብበው ሌሎችም እንዲያነቡት ይጠቁሙት ነበር ይሆን? -

አልመሠለኝም! አይመስልም! ግን እስቲ ጉዱን አያለሁ! ከሁለት ወር በኋላ ስንገናኝ ጠይቀኝ! አሁን ወደ ስነ-ፑቲን🤪🤓! የፐርሰናሊቲ ኮንሴፕትኮ ሆኗል! ፑቲንነት ራሱን የቻለ የሰብዕና መገለጫ እየሆነ ነው!

(በነገራችን ላይ እዚህ ከመጣሁ ያወቅኩት፣ አንድ የሚወደድ የብዙ ነገሮች ቅልቅል (እና ከፍ ያለ ካሎሪም ያለው) አንድ ምግብ አለ፣ በተለይ ህንዶቹ፣ አረቦቹ፣ እና ከኪዩቤክ የመጡት... ይሥሩት አቦ!🤩🥰 ጣት ያስቆረጥማል! ፑቲን (Poutine) ነው ስሙ የምግቡ!)

መልካም ፑቲን !🤪🤩

ፈጣሪ ኢትዮጵያችንን ይባርክ!

እናንብብ! እናንብብ! እናንብብ! እንቀጽል! እንቅራ!...

(እና እናቅራራ🤪፣ እንፃፍም! እንጂ!😊 ስለ ፑቲኖች!🤩🙏🏿)

አመስግኜ አበቃሁ!

መልካም ጾም!

ሰናይ ቀን!🙏🏿❤️

© Assaf Hailu

ስለ ፑቲን . . . እናንብብ!
______

(ካነበብክ በኋላ ፊቱን አያሳየኝ የምትል ከሆነስ?
ማንበብ ግን እውን ሙሉ ሰው ያደርጋል? ወይስ...?)

ይህን ስፈልገው የነበረ በቭላዲሚር ፑቲን ማንነት፣ ታሪክ፣ ውስጠ ሰብዕና፣ ዓለማዊ እይታ፣ ስነልቦናዊ ውቅር፣ የህይወት ጉዞና ተሞክሮዎች፣ እና የሚንቀሳቀስበትን አጠቃላይ ሎጂክና የመጨረሻ ምኞት በሁለት በራሺያ ሲቪልና ሚሊቴሪ ጉዳይ ላይ አሉ በተባሉ ሪሰርቸሮች የተፃፈ መፅሐፍ አገኘሁ።

በጠቅላላው ከነማጣቀሻውና ድህረ ማስታወሻዎቹ በ530 ምናምን ገፆች ጥቅጥቅ ተደርጎ በጥቃቅን ፎንቶች የተፃፈ የዳጎሰ መፅሐፍ ነው። በኖርማል ፎንት ቢፃፍ ከ1ሺ ገፅ የሚተናነስ አይደለም፣ ትናንት ሀ ብዬ ጀመርኩት። ...

ካለብኝ የጊዜ ሽሚያ ጋር ሳስበው... መፅሐፉን ልቅም አድርጎ እንደ ጥናት ለማንበብ በርከት ያሉ ቀናትን ሳይጠይቅ አይቀርም፣ ምናልባትም አንድ ወር ከዚያም ከፍ ያለ ጊዜ ይፈጅብኝ ይሆናል።

ግን በብዙ የተደነቁ ሪቪወሮችና የፖሊሲ ሪሰርቸሮች በዓይን ገላጭነቱና ከፍ ሲልም በፑቲን ላይ የተፃፈ ምሉዕ የምርምር ሥራ እሲደነቅ የቆየ ድርሳን እንደመሆኑ፣ በራስ እይታ ይዘቶቹን ለማጤንና የግራቀኙን እውነታ በነፃ ሚዛን ለማጣራት የፈለገውን ጊዜ ቢፈጅ አንጠርጥሬ ሳላነብ አልተወውም! ውዝፍ ዕዳዬ ነው! ግዴታዬ ነው!

ማንበብ፣ ማንበብ፣ ማንበብ! አሁንም ማንበብ፣ ሁሉንም ማንበብ! የግራውንም የቀኙንም ማንበብ! የራስህን ትንሽዬ ግንዛቤና አቋም ትንሽ በትንሽ መገንባት፣ ግድ ነው! ተማሪ ነህ? አንብብ! አስተማሪ ነህ? አንብብ! የፖሊሲ አናሊስት ነህ? አንብብ! የፖለቲካ ተንታኝ ነህ? አንብብ! ...

ፑቲን የሰውልጅ አንድ የሰብዕና ዓይነት ሆኗል፣ ፑቲንነት እንደ ፐርሰናሊቲ እየተጠና ነው! እና በዚህ አጋጣሚ ምን የሚል ሃሳብ ደጋግሞ መጣብኝ? እንቀጽል፣ እናንብብ፣ እንቅራ... የሚል!

ዕድሜ ለንባብ፣ ዕድሜ ለመፅሐፍ፣ እድሜ በዓለም ሁሉ በሚተቻቸውና በሚያብጠለጥላቸው ስንት ዐዋቂ ፊት መፅሐፋቸውን ደጉሰው አንካችሁ ለሚሉን የዘመናችን ልሂቃን! ቤትህ ቁጭ ብለህ፣ ሁሉን ማንበብ መታደል ነው! ማተሚያን የፈለሰፈው ጉተንበርግ የተባረከ ይሁን! እንለዋለን መቼም!

ማንበብ ግዴታ አይደለም! ግን ዓለምን በትክክል እንደሆነችው መረዳት ትፈልጋለህ? አንብብ! ሀገሬስ ከእነዚህ ነገሮች መሐል የት ላይ ነች? ምንስ የሚጠቅምና የሚጎዳ ነገር ይገጥማታል? ምንድነው አዋጪው? የነገሮች አዝማሚያ ምንን ያመላክታል? ...

እነዚህን አንኳር ነገሮች ከሚዲያ ቅንጫቢዎችና ሌሎች ከሚተነትኑልህ አልፈህ ለራስህ በራስህ መነፅር ለመገንዘብ ትፈልጋለህ? አንብብ! አንብብ! አንብቢ! ሁላችንም ፊደል የቆጠርን ሁሉ እናንብብ!

ሁሌ ራሴን የምቀጥረው እንደ ዕድሜልክ ተማሪ ነው። በሆነ ወቅት ላይ ዓይኖቼ ቢጠፉ እንኳ ማንበብ እንዳይቸግረኝ፣ በጣቶቼ ዳስሼ ለማንበብና በመርፌ ለመፃፍ እንድችል ብሬይልን (ዓይነስውራን የሚጠቀሙበትን ፊደላት) ሳጠና ነበር። ..

ዕድሜዬ ለሁሉ አልበቃ ብሎኝ እንጂ በብዙ ቋንቋዎች የተፃፉትን ሁሉ ማንበብ እንድችል ብዙ ቋንቋ የመማሪያ ጊዜውና ዕድሉ ቢኖረኝ ምንኛ በወደድኩ!

ማንኛውም ፊደል የቆጠረ ሰው የግድ ማንበብ አለበት! አለዚያ ፊደል መቁጠሩ ጥቅም አልባ ነው! ሳታነብ የምትይዘው አቋም ሁሉ አቦሰጥ ነው። አንብበህም የግዴታ የተፃፈውን እንድትከተል የሚያስገድድህ የለም! ማንበብ ግን ዓለምህን በዳበሳና በሌሎች ዓይን እየተመራህ ለመገንዘብ ከመሞከር ያድንሃል! ምን ጠቅሞህ ነው?

ምንም አይጠቅምህም ይሆናል! Awareness ብቻውን በቂ ነው! ቢያንስ ስለሁሉም ነገሮች ባይሆን፣ ስለሚመስጡህ ነገሮችና፣ የሚመስጡህን ነገሮችም መርጠህ ማንበብ ግድ ነው!

አንድ የማደንቃት አክስቴና ባሏ አሉ። ከልጅነት እስከ ዕውቀት ዕድሜዬ ሳውቃቸው፣ ባልና ሚስት ከሥራ ደክመው መጥተው፣ ራት ወይ ምሳ ቤት ውስጥ ተበልቶ፣ ከእንቅልፍ እኩል ሁለቱም በየፊናቸው ወደየጥናት ክፍላቸው፣ ወደየጓዳቸው ገብተው የሚመስጣቸውንና የሚመለከታቸውን ያነባሉ!

ሶስት ወልደው ለኮሌጅ ያበቁ፣ ብዙ የህይወት ጫና ያለባቸው ናቸው፣ ግን ተማሪነታቸውን አላቆሙም። እጅግ ይገርሙኝና ያስቀኑኝ ነበር። እሷ ሃኪም እሱ የሣተላይት ኢንጂነር ነው! ለእኔ ከቤተሰብ ኃላፊነት ጎንለጎን ዕድሜልክ ማንበብና አዕምሮን ማሳደግ እንደሚቻል ትልቅ አርዓያ ሆነውኛል።

ሌሎችም ብዙ አርዓያ አድርጌ የምወስዳቸው የቅርቤ ሰዎች አሉ። የራሴን አባት ጨምሮ!

በበኩሌ በህይወት ዘመኔ የምፈልገውን መርጬ ራሴን በራሴ ያስተማርኩ ሰው ነኝ። ማንም አስተማሪ ወደምፈልገውና ወደሚያስፈልገኝ ርዕስና ዕውቀት ይጠቁመኛል እንጂ አንደ ግሉኮስ ጭንቅላቴ ላይ ሰክቶ ሀ አና ሁ ብሎ እንዲመግበኝ ራሴን በተቀባይነት ብቻ አመቻችቼው አላውቅም!

ፊደል መቁጠር ከቻልክ ሌላው ሰው ወዳየውና ወደሚመስለው፣ ወዳወቀውና ወደተገነዘበው ነገርና አቅጣጫ ይጠቁምሃል እንጂ አንተን ቁጭ ብሎ እንደ ቄስ ትምህርት ቤት ቀለም ሲያስቆጥርህ አይኖርም! ማንም ሰው ላንተ ሊሰጥህ የሚችለው ነገር በነገሩ ኢንተረስት እንዲያድርብህ ማድረግ ብቻ ነው! የተቀረው ያንተ ፍላጎትና የራስህ ምርጫ ይሆናል!

ብዙዎቻችን በተለይ እኛ ሀገር መማርን የሆነ ቦታ ላይ የሚቆም አድርገን ስናስበው አገኛለሁ። ይገርመኛል በጣም። በአንድ ሙያ ውስጥ ብቻ ሺህ ዓይነት ዕውቀቶች አሉ። አንዱን ስትጨርስ ሌላ ይጠብቅሃል። አንዱ ራሱ ባለበት አይቆምም። ሁሌ ያድጋል፣ ይሰፋል፣ ይቀጫል፣ በየዕለቱ የሚጨመርና የሚቀነስ አለው።

ፊደል የቆጠረ ሰው ርዕሰጉዳዩ እጅግ ቴክኒካል ሆኖበት መሠረታዊ ግንዛቤውን ለመጨበጥም ካልከለከለው በስተቀር፣ ስለሁሉም ነገር የተወሰነ ግንዛቤ ሊኖረው የግድ ነው!

አንድ የባዮሎጂ ፕሮፌሰር ሆኖ ግን ህግንም፣ ህክምናንም፣ ጆርናሊዝምንም፣ ፖለቲካንም፣ ቲዎሎጂንም፣ እና ሌሎች ብዙ ነገሮችን ሲያጠና የኖረ የሚያስቀና አጎት አለኝ። ተገርሜ አላባራም! እንዲህ ዓይነት ሰዎች ረሃቤን ይቀሰቅሱብኛል!

ቋንቋ የተፈጠረው፣ ፊደል የተቀረፀውና ዋና አገልግሎቱም ያንዱን ሃሳብና ዕውቀት፣ ተሞክሮ ለሌላው በቀላሉ ለማስተላለፍ ይመስለኛል! ሁሉን የቻልከውን አንብበህ፣ ቀስመህ፣ በሁሉም አቅጣጫ የተሳልክ፣ የሠላህ፣ የበሰልክ ሰው እንድታደርገው ነው ራስህን!

እንዲህ ስል ሲቪል ኢንጂነሮች፣ አርኪቴክቶች ጓደኞቻቸውን የሚተርቡበቀልድ ትዝ አለኝ። An architect is a guy who wants to know everything that he ends up in knowing nothing about anything!😃🤓🤪

አርኪቴክት ሁሉንም ነገር ለማወቅ የሚፈልግ ፍጡር ነው! የሆስፒታልን ንድፍ ለመሥራት የሆስፒታሎችን ሥራና አገልግሎት፣ የመሣሪያዎቹን ዓይነትና መጠን፣ ግነኙነት፣ የሚንቀሳቀሱበትን ቦታና እያንዳንዳቸው የሆስፒታሉ ክፍሎች የሚሰጡትን ዓላማና አገልግሎት ጠንቅቆ ማወቅ ይኖርበታል። ...

ትያትርቤትን ለመንደፍ ስለትያትርቤት አሠራር ማወቅ አለበት! የእሣትአደጋ መሥሪያቤትን መንደፍና የጦር ካምፕን መንደፍ፣ ወይም የአየርመንገድን ንድፍ መሥራት ሁሉምና እያንዳንዱ ነገር ራሱን የቻለ የተለየ ዕውቀት ይጠይቃል! በዚህ የተነሳ አርኪቴክቶች ዕድሜያቸዌን የሚጨርሱት ስለያንዳንዱ ነገር በማጥናት ነውና፣ ስለአንድ ነገር ብቻ ስፔሻላይዝ ለማድረግ ይቸገራሉ! እና መሃንዲሶች ጓደኞቻቸው ያሾፉባቸዋል! A jack of all pots but no trades እያሉ!😃🤪

Brother የአዕምሮ ሰላም ትሻለህ? ማን ይጠላል?!

ልብ በል።

① [What you resist, persists]

ስማኝ እነ Daniel Wegner ልቡናን ሲያጠኑ የሰው ልጅ አንጎል ጅላጅል መሆኑን አሳይተውናል። እንዴት?

እስቲ ቀጣዩን ሙከራ አብረኸኝ ሞክር — [በዋቃ ይሁንብህ!]።

ሙከራው: — " ለአፍታ እስቲ ስለ አፄ ምኒሊክ አታስብ!"።
:
:
እንደው ሳትዋሽ! ይሄን ሙከራ ስትጀምር መጀመሪያ ያሰብከው ነገር ምንድን ነው?

አትዋሽ። ምኒሊክ!

በቃ እንዲያ ነው። ልትጨቁነው፣ ልታፍነው የምትታገለው ልቡናዊ/አዕምሯዊ ሀሳብ በሞላ ይበዛል፤ ይባዛል። አታስቆመውም። ተፈጥሮ! አጀብ አደል?! (Ironic Process Theory) እንለዋለን።

② ጦሱ

ሀሳብን ከከንሺየስ ክፍልህ ሆን ብሎ ዘወር ማድረግ/መካድ ወይ ማመቅ በጣም በጣም ብዙ ኤነርጂ ይፈልጋል። ስፐርምህ ውስጥ ያለውን ካለሪ 8 እጥፍ ሊጠይቅህ ይችላል።
አስበኸዋል?
እየቀበርክ ያለኸው ሀሳብ ቀላል አይደለማ!

"የምትጠላው ሰው ፤ መላውን የጥቁር ታሪክ የቀየረ ነው! "

እናም ይሄ experience ረፍት ይነሳሀል። [ያቅነዘንዝሀል እንዲሉ —እመው]። ደባሪ ሙድ ይሰጥሀል። በዚህ ምክኒያት "ፊርስ" ትሆናለህ። በቁጣህ ጠሀይዋ ትጠልቃለች። ትሳደባለህ፣ ትራገማለህ። ያው መከረኛው "ጎጥህ" ውስጥ ገብተህ ትጠለላለህ።

እሱም ምቾት አይሰጥህም። ለምን መሰለህ?

እውነትን በመካድና ፣ ሆን ብለህ እንደካድከው በማወቅህ መሀል የሚፈጠር Cognitive inconsistencies አደገኛ ስለሆነ ነው። ጠጠር ላይ እንደመተኛት ያህል።

እና ይሄን መሰል ጉዳይ ሀይ ካላልከው it will keep fucking your brain out! ከዛስ?

ታብዳለህ።

③ አዕምሯዊ ሰላም ትሻለህ?
ውስጥህ ያለን ሀሳብ፣ ሀቅ ወይም ሌላ ለማዳፈን አትታገል።

ይገባኛል!
እረዳሀለሁ።
ወደዚህ ምድር እንድትመጣ— የእናትህን እንቁላል ያገኘው ወሳኙ የአባትህ ሴል ውስጥ አባትህ ያዳበረውና በደንብ ያከማቸው ጥላቻ coded ሆኗል፤ እንጂ ከተማ አድገን ተመሳሳይ ሻይና፣ ባቅላቫ በልተን እንዲህ ልንራራቅ አንችልም።

እና ሰላምህ እንዲመለስ፤
ከዚህ በኃላ እንድታነብ አልገፋፋህም። ጥላው። ምንሊክን ጥላው። የታባቱንስ።

ብቻ ዋናው ነገር የአዕምሮ ሰላምህ ነው!
ዋናው ነገር ጤናማ መስተጋብራችን ነው።

ዋናው ነገር ይሄ መስተጋብር abuse ሳይደረግ ያቆየውን፤

ሌላው ወገን ለ identity ቀውሱ 50 dollar እየከፈለ ነጭ ሳይኪያትሪስት ጋር ሄዶ ለደቂቃ ለፍልፎ መልስ ሳያገኝ እየወጣ ፤
ሌላው ወገን " ብላክ ላይቭስ ማተር " እያለ እስከዛሬ ሲጮህ፤

"ምን ሆነው ነው?" በሚል ከጥቁርም ከነጭም ራስህን ነጥለህ እንደ ልዕለሰብ እንድትቆጥረው የረዳህን ፤

ይሄን damn ምኒሊክ የተባለ አፄ! ይሄን ጥቁር ሰው! ይሄን ጨፍጫፊ! ይሄን ጨፍላቂ ወዘተርፈ you name him, you tell him off!

አትውደደው። ለዓለመ ዓለም አትውደደው።

ብቻ የሰራውን ፤ የሰራልህን፤ የሰራልንን በውስጥህ ተቀበል። አትካደው። የሰራውን መካድህ ነው የሚያሰቃይህ። በምትጠላው ሰው ግዙፍ ታሪክ መከናወኑ ነው የሚያሳምምህ።

"አልወደውም ነገር ግን That motherf*r was a real deal in history" ብትል ከዚያ ቀን አንስቶ ከገዛ ታሪክህ ትታረቃለህ።

ትፈወሳለህ።
ኧረ አልጋህን ይዘህ ሁላ ነው ምትሄደው!
----

© Surafel Ayele

የምትመራበት በትረ―ስልጣኑን ለሰሜን አሜሪካ አስረከበች። ሆሊውድ የአለም የጥበብ ማእከልና መለኪያ ሆነ። ከገዛ ፈሳችን ቀድሞ ሆሊውድ ያስነጠሰው ይደርሰናል። መፅሀፍት ወደ ፊልም ይቀየራሉ፤ በቴሌቪዥን ይታያሉ፤ በሬዲዮ ይተረካሉ። ነገሮች መልቲሚድያ ሆኑ። ብሮድዌይ የአለም የቲያትር ማእከል ሆነ። የአሜሪካ የመካላከያ የኢኮኖሚ የፖለቲካ የበላይነት ሁሉ እጁን ይዞ የሚመራው ፊታውራሪ ሆሊውድ ነው። አሜሪካ ውስጥ ትልቅ ቀውስ ሲፈጠር የሆሊውድ ፕሮዲዩሰሮች ኋይትሃውስ ይጋበዛሉ። መመሪያ ይቀበላሉ። ቢሊዮን ዶላር ይመድባሉ። በማር የተለወሰ ፖሊሲያቸውን በፊልም ያሽጋሉ። እኛም ሲኒማ ቤት ደጃፍ እንሰለፋለን። በገዛ ገንዘባችን መዝናኛ ገዝተን እራሳችንን እንሸጣለን። በአራት ሜትር አቡጀዲ ያየነውን ትእይንት የመጨረሻ እውነት አድርገን እንቀበላለን። አሜሪካንን ሊያናውጣት ያሰፈሰፈው ወጀብ ከሽፎ ወደ በለጠ ከፍታ ትስፈነጠራለች። ፊልሞች የመጨረሻው የእውቀት ምንጭ ሆኑ።

21ኛው ክፍለዘመን ከገባ እነሆ 20 አመት ሞላው። አሁንም ጥበብ ሰዎች ጋር የሚደርስበት መንገድ መልኩን ቀየረ። ሰዎች በኪሳቸው የሚያስቀምጡት በእጃቸው የሚይዙት ትንንሽ ሃይለኛ መሳሪያዎች ተፈለሰፉ። እንደ በፊቱ ጥበብን ለመቋደስ ቦታን ግዜን መጠበቅ ቀረ። ሰዎች በማንኛውም ሁኔታ የሚፈልጉትን መረጃ፣ እውቀት የሚያገኙበት ሁኔታ ተፈጠረ። ነገር ግን የዘመኑ ቴክኖሎጂ የዘመኑን ተግዳሮት ፈጠረ። ጥበብ በብዛት ስትተኮስ በጥራት ተዘረረች። ጥልቀት አጣች። በየቦታው መገኘቷ አረከሳት። በብልጭልጭ ተጀቡና እውነተኛ ውበቷን አጣች። ለሃያ እና ሃያ አንደኛው ክፍለዘመን የአውሮፓ መልስ እግርኳስ ነበር። በስነፅሁፍ ያጡትን ከፍታ በሌላ ጥበብ ለመመለስ ኳተኑ። ይሁን እንጂ ተከታይ እንጂ ቀዳሚ መሆን አልቻሉም። እግርኳስ ጥልቀት ያለው ጥበብ አይደለም።

የትም የአለም ጫፍ ሂዱ። ስልጣኔ ባበበበት ሁሉ የጥበብ ችግኝ አለ። ጥበብ ስልጣኔን ይወልዳል ። ስልጣኔ መልሶ የበለጠ ጥበብን ያበረክታል። ሁለቱ አይነጣጠሉም። ታላቅ የስነጽሑፍ ስራ ያልፈጠረው ያልኮተኮተው ያላጀበው ስልጣኔ ኖሮ አያውቅም።

ይሄንን ሁሉ ይዘን ወደ ኢትዮጵያ እንምጣ። በተለምዶ ኢትዮጵያ የ3000 አመት ታሪክ ባለቤት የአክሱም ስልጣኔ መስራች የሚለው ሃሳብ ከሁሉም ገንኖ ይሰማል። አንዳንዶች የኢትዮጵያን የጽሑፍ ታሪክ እስከ 5,500 አመት ያደርሱታል። ሄኖክ ኢትዮጵያዊ ነው፤ የኖህ ቅድመ አያት ነው፤ የአዳምና ሄዋን ገነት ግዮን ወንዝ አጠገብ ኢትዮጵያ መሐል ነው ይላሉ። ይህንን ሁሉ መረጃ ተከትላችሁ ብትነጉዱ አሁንም ምንጩ ጥበብ ነው። ኢትዮጵያ የሶስት ሺህ አመት ቱባ ታሪክ ባለቤት የሚለው ተረክ የመጣው ከሌላ ከምንም ሳይሆን የጥንት አባቶቻችን "ክብረ―ነገሥት" ፣ "ፍትሐ―ነገሥት" እና "አውደ―ነገሥት"ን ፅፈው ስላስቀመጡልን ነው። ወደ 5,500 አመት የተለጠጠው ደግሞ በመፅሀፈ ሄኖክ ምክንያት ነው። ኢትዮጵያ በዚህ ረዥም ታሪኳ ሌሎች ብዙ ስልጣኔዎችን አስተናግዳለች። ታድያ ሁሉም ስልጣኔዎች የጥበብ ምልክት ትተው አልፈዋል―የአክሱም ሃውልት፣ የላሊበላ ቤተክርስቲያን፣ የፋሲል ግንብ እና ሌሎችም ብዙ።

(ምስሉ፣ ጣሊያናዊው ራፋኤል በአስራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን የሳለው "The School of Athens " የተሰኘ ዝነኛ ስእል ነው። ስእሉ በጥንታዊ ግሪክ የነበረውን የዘመኑን የፍልስፍና መንፈስ ጠቅሎ ይዞ የሚያሳይ የራፋኤል ታላቁ ስራ ነው።

በስእሉ መሐል ላይ የሚታዩት አበይት የግሪክ ፈላስፋዎች ፣ እንዲሁም የስእሉ ማእከላዊ አትኩሮቶች፣ በግራ ፕሌቶ( አፍላጦን) እና በቀኝ ተማሪው አሪስቶትል (አሪስጣጣሊስ) ናቸው። ሁለቱም በግዜው ዘመናዊ የሚባሉ መፅሀፍትን በግራ እጃቸው ይዘዋል። ወደ ሀሳባዊነት / idealistic ፍልስፍና የሚያዘነብለው አፍላጦን እጁን ወደ ላይ ጠቁሞ ይታያል። በተፃራሪ በተግባር የተፈተነ/empiricism ፍልስፍና የሚማርከው ወጣቱ አሪስጣጣሊስ ፣ እጁን ወደ ምድር ጠቁሞ ይታያል።

በተጨማሪም እውነት እና እውቀትን የሚያጠና የፍልስፍና ዘርፍ/metaphysics ተከታዮች በአፍላጦን በኩል ሲሆኑ ቁስ አካልን የሚያጠኑ / physics ደግሞ በአሪስጣጣሊስ በኩል ተሰብስበዋል።

በስእሉ ላይ ከተካተቱት ሌሎች ፈላስፋዎች እና ሌሎችም አብይ የታሪክ ፣ የስነ ጥበብ እና የሳይንስ ሰብእናዎች መሐል ሶቅራጥስ ፣ ዲዎጋን ፣ ኤፒኩረስ፣ ፓይታጎረስ ፣ ኢኩሊድ፣ አርኪሜደስ ፣ አናክሲማንደር ፣ ዜኖ፣ ፕሊቲነስ፣ ሚኬልአንጀሎ፣ ሊዎናርዶ ዳ ቪንቺ ፣ ትልቁ እስክንድር ፣ እንዲሁም ሰአሊው እራሱ ራፋኤል ይገኙበታል።)

© Te Di

እነሆ እስራኤላውያን በመላው አለም ተበተኑ። የሮማውያን ኢምፓየር እና ስልጣኔ ቀስ በቀስ ፈራረሰ። አውሮፓ ከግሪክ የስልጣኔ ማማ ወረደች። መካከለኛው ዘመን ደረስን። ለ400 እና 500 አመት በጨለማ ዳከረች። የቲያትር ቤት ደጃፎች ተዘጉ። አውሮፓውያን በቁስም በመንፈስም ደኸዩ። በመካከለኛው ዘመን የነበረው ብቸኛ የስልጣኔ ጭላንጭል የአረቦች ነው። ነብዩ መሃመድ መፅሀፍ ቅዱስን በራሱ ህዝብ ልክ ሰፍቶ ቅዱስ ቁራንን ፃፈ። የግሪካውያን ጥበብ ወደ አረብኛ ተተረጎመ። በፓይታጎረስ ደረጃ የሚጠሩ የአረብ ሂሳብ ሊቆች ተፈጠሩ። ፊርዳውሲ ሩሚን ካያምን የመሳሰሉ የፔርሺያ ታላላቅ ገጣሚዎች ብቅ ብቅ አሉ። አል ጋዛሊን የመሰለ ፈላስፋ አቪሴናን የመሰለ የህክምና የፍልስፍና እና ሌሎችም የእውቀት መስኮች ሊቅ አቆጠቆጡ ።

በ14ኛው ክፍለዘመን አውሮፓ ድንገት ካንቀላፋችበት ረዥም እንቅልፍ ባነነች። ለ300 አመታት የዘለቀ ተሃድሶ ስታደርግ ፊታውራሪዎቹ ሊዎናርዶ ዳቬንቺ ፣ ሜኬልአንጀሎ እና ሌሎችም ነበሩ። ይህንን ተከትሎ በአውሮፓ የባህል የፖለቲካ የኢኮኖሚ መነቃቃት ተፈጠረ። ከ18ተኛው ክፍለዘመን በኋላ የኢንዱስትሪ አብዮት መቀስቀስ እያንደረደረ ወደ ዘመናዊው አለም ያመጣናል።

ከተሃድሶ ዘመን ተጠቃሽ የስነጽሑፍ ስራዎች መሐል የጣልያናዊው ኤፒክ ገጣሚ ዳንቴ አሊግሄሪ "The Divine Comedy" የሌላኛው ጣልያናዊ የፖለቲካ ፈላስፋ ኒኮሎ ማኪያቬሊ "The Prince" የስፔናዊው ሰርቫንቴስ "ዶን ኪኾቴ" ይገኙበታል። ዮሃንስ ጉተንበርግ የሕትመት ማሽኑን ከፈለሰፈ በኋላ ዘመናዊ ስልጣኔ እየተቀጣጠለ መጣ። መፅሀፍት በብዙዎች እጅ መገኘት ጀመረ። ሳይንስ እና ጥበብ ተስፋፋ። እውቀት የጥቂቶች ጉዳይ ብቻ መሆኑ አበቃ። ወፍራም የለውጥ አየር አሰገመገመ።

እንግሊዝ ነን። አስራስድስተኛው ክፍለዘመን። ንግስቷ ኤልሳቤጥ ናት። ኤልሳቤጥ የሰው ባልን ትታ አገሯን ያገባች የሃገር ፍቅሯ በልቧ ላይ የሚንቦገቦግባት ንግስት ናት። ግዜዋንም ፍቅሯንም ህይወቷንም ለሃገሯ ሰጥታለች። በሷ ዘመን ዊሊያም ሼክስፒር ተወለደ። ሼክስፒር በ52 አመት እድሜው 38 ተውኔቶችን ፃፈ―እያንዳንዳቸው ማስተርፒስ ናቸው። ግማሹ ትራጄዲ ሌሎቹ ኮሜዲ የተቀሩት ደግሞ ታሪካዊ ናቸው። ሼክስፒር ተውኔት በቃኝ ሳይል 154 ሶኔቶች ጽፏል። ሶኔት የግጥም አይነት ናቸው። ታድያ ሼክስፒር የ16ተኛው ክፍለዘመን ብቻ ጠቢብ አይደለም፤ የዘለአለም ነው። የእንግሊዝ ብቻ አይደለም፤ የአለም ነው። ብዙዎቻችን ማክቤዝን ሃምሌትን ሳናነብ ሼክስፒርን በስም ብቻ እናውቀዋለን። አለም ከሱ በፊትም ሆነ በኋላ የሱን ያህል ጥበበኛ አላየችም―ምናልባት ሊዎናርዶ ዳቬንቺን። (ንጉስ ሰለሞን ሌላ አይነት ጥበበኛ ነው) የሼክስፒር ተውኔቶች ለ500 አመታት ቋንቋን ማህበራዊ እሳቤን ስነልቦናን ዘመናዊ ፖለቲካ ላይ ተፅእኖ ፈጥረዋል። ሼክስፒር ብቻውን የጥበብ ቅፅር ነው። እነሆ ከግማሽ ሚሌኒየም(ሺህ―አመት) በፊት የለኮሰው የጥበብ ውጋጋን እስከአሁን ይንቦገቦጋል። እንግሊዝ ለብዙ አመታት አለምን በሥልጣኔ በፖለቲካ በጦር ሃይል መራች። የዛች ሚጢጢ ሃገር ወፍራም ጡንቻዎች ጠቢቦቿ ናቸው። ህዝቦቿን በብርቱ የቀረፁት ገጣሚዎች ፣ ፀሐፊ ተውኔቶች ፣ የልብወለድ ደራሲዎች ናቸው። ከሼክስፒር ቀጥሎ ጆን ሚልተን የእንግሊዝ ትልቁ ገጣሚ ነው። የሼክስፒር ሃገር ልጆች ብርቱ ገጣሚ ናቸው―ቻውሰር፣ ስፔንሰር፣ ቴኒሰን፣ ኮልሪጅ፣ ሼሊ፣ ባይረን፣ ብሌክ፣ ዎርድስዎርዝ። የተውኔት ደራሲዎችም አሉ―ሚድልተን፣ ቤን ጆንሰን፣ ማርሎው። ከእንግሊዝ ፈቀቅ ስንል በመላው አውሮፓ በተለይ ፈረንሳይ ጀርመን ታላላቅ ፀሐፊ ተውኔቶች ነበሩ።

ቪክቶሪያ ዘመን ላይ ስንደርስ የተውኔት እና ግጥም ተወዳጅነት እና ጉልበት ቀንሷል። ዘመኑ የልብወለድ ነው። ታላቁ የልብወለድ ደራሲ ደግሞ ቻርልስ ዲክንስ። ዘመኑ አስራዘጠነኛው ክፍለ ዘመን። የኢንዱስትሪ አብዮት በመፈንዳቱ እልፍ ፋብሪካዎች ተከፍተዋል። ዲክንስ ራሱ በልጅነቱ የፋብሪካ ሰራተኛ ነበር። ይህንኑ ገጠመኙን በ"Hard Times" ልብወለድ መፅሀፍ አድርጎታል። በዘመኑ መፅሀፍት የሚወጡት በአንድ ቅፅ ተጠርዘው አይደሉም። በየሳምንቱ በሚወጡት ጋዜጦች እንጂ። አንድ ጋዜጣ ማለት አንድ ምእራፍ ነው። የሚቀጥለውን ምእራፍ ለማንበብ ሌላ አንድ ሳምንት መጠበቅ ግድ ነው። የልብወለዶች ተወዳጅነት የጋዜጣ ሽያጩን አደራው።( እዚህ እኛ ሃገር አዲስ አድማስ ይህንን ቅርፅ ሞክሮታል። አራት አብነቶችን አስታውሳለሁ። እነዚህ መፅሀፍት በአንድ ተጠርዘው ከመውጣታቸው በፊት በየሳምንቱ ቅዳሜ አዲስ አድማስ ላይ አንብበናቸዋል―የኦዶኒስ "የአና ማስታወሻ" ትርጉም፣ የራሱ የነብይ መኮንን "የኛ ሰው በአሜሪካ"፣ "የፍሬሿ ማስታወሻ(የፀሀፊዋ ስም ሄርሜላ መሰለኝ)፣ የአብርሃም ረታ አለሙ "አልን አስባልን ተባለ") ይቺ በየሳምንቱ እየከፋፈሉ ልብወለድን መዘርዘር መለኛ ሳይሆን አይቀርም። አንባቢዎች ያነበቡትን ለማመንዠክ አንድ ሙሉ ሳምንት አላቸው። የሚቀጥለውን ክፍል የሚጠብቁት በጉጉት ነው። ደረስኩ ሲልም የሚነበበው በከፍተኛ ሃይል ነው። መጽሐፉን ማንበብ እንዲያው የመጨረስ ጉዳይ ሳይሆን የስሜት ጉዳይ ይሆናል። እንደገና እንግሊዝ ነን። በቪክቶሪያ ዘመን የፈሉትን የልብወለድ ደራሲዎች ለመዘርዘር እዚህ ጋር ቦታ አይበቃም። እንግሊዝ በዚህ ሁሉ የጥበብ አጀብ በአለም ላይ ብርቱ ሃይል ሆነች። የዜጎቿ ንቃተህሊና ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደረሰ። እንግሊዝነት የነቄነት የአዋቂነት የብልጥነት የገዛ ጥቅም አስጠባቂነት አለም አቀፍ መለያ ሆነ። ሶስት አራተኛው አለም የእንግሊዝ ግዛት ሆነ። ታድያ ይህ እንግሊዛውያን ጥሩ አልሞ ተኳሾች ስለሆኑ ብቻ አይደለም―ከኋላ ያለው የጥበብ፣ የእውቀት፣ የንቃት ደጀን ነው። ይህንን የሚቀርፁት ደግሞ ደራሲዎች፣ ፈላስፋዎች፣ ገጣሚዎች፣ አሳቢዎች ናቸው።

ሃያኛው ክፍለዘመን ላይ ደረስን። የአለም ሁኔታዎች ተቀያይረዋል። ሃያኛው ክፍለዘመን የከፍታም የዝቅታም ዘመን ነው። ሳይንስ ከፍተኛ እምርታ ያሳየበት ዘመን ነው። ሁለት የአለም ጦርነቶች በማድረግ የሰው ልጅ መንፈስ የዘቀጠበት ዘመን ነው። አልበርት አንስታይን ፊዚክስን ሪቮሊዩሽናይዝ ያደረገበት ዘመን ነው። ሂትለር ስድስት ሚሊየን አይሁዳውያንን የፈጀበት ዘመን ነው። ካርል ማርክስ በታላቅ ፍልስፍናው አለምን በሁለት ታላላቅ ጎራ የከፈለበት ዘመን ነው። ስታሊን የማርክስን ፍልስፍና በተሳሳተ መንገድ ተረድቶ 50 ሚሊየን ራሽያውያንን እንደ እባብ የጨፈጨፈበት እንደ ውሻ የቀጠቀጠበት ዘመን ነው። ፍሩይድ ስነልቦናዊ እሳቤን የሕይወት ማጠንጠኛ አድርጎ ማእከላዊ መሰረታዊ ጥያቄ የጠየቀበት ዘመን ነው። ማኦ―ሴ―ቱንግ(ማኦዜዱንግ) 78 ሚሊየን ቻይናውያንን ወደ ሞት የሸኘበት ዘመን ነው። በአጠቃላይ ቻርልስ ዲክንስ በ"የሁለት ከተሞች ወግ" ውስጥ እንዳለው "ዘመኑ ተቃራኒ ሁኔታዎች የነገሱበት ዘመን ነበር" ሰዎች በቀኝ በኩል አስደናቂ ስልጣኔ ይገነባሉ። በግራ በኩል ተሰምቶ የማይታወቅ ለአይንና ለጆሮ የሚቀፍ ተወዳዳሪ የሌለው የጭካኔ እልቂት ይፈፅማሉ። የሰዎች መንፈስ በሁለት አፅናፎች በከፍታ እና ዝቅታ በልእልና እና ድድብና መካከል እንደ ሸማኔ ድር የሚመላለስ ድውር ነው። ጥበብ አሁንም አለምን መምራት አላቋረጠችም። መልኳን ቀየረች እንጂ። ሳይንሳዊ ስልጣኔው ብዙ ነገሮችን ሪቮሊዩሽናይዝ አደረገ። ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ ተፈለሰፈ። ሲኒማ ተፈጠረ። ሰዎች ጥበብን የሚያስተላልፉበትና የሚቀበሉበት መንገድ ሙሉ ለሙሉ ተቀየረ። እንግሊዝ አለምን በስውርም ሆነ በገሃድ

Art is the source of all civilization!

ከጥንት እንጀምር። ግሪክ ነን። የማወራችሁ የኢኮኖሚ ቀውስ ክፉኛ ስለደቆሳቸው የሃያ አንደኛው ክፍለዘመን ግሪካውያን አይደለም። የአለም ባንክ ወይም የአውሮፓ ህብረት ያበደራቸውን በመቶ ቢሊየን የሚቆጠር ዶላር መመለስ ስላቃታቸው ዘመነኞቹ አቴናውያን አይደለም። የለት ጉርሳቻውን መሸፈን አቅቷቸው ለት ተለት ለፉድ ስታምፕ ስለሚሰለፉት ግራ የተጋቡ ደቡብ አውሮፓውያን አይደለም።

የማወራው ከክርስቶስ ልደት በፊት ስለነበሩት የስልጣኔ አውራዎች ጥንታዊ ስፓርታውያን አቴናውያን ግሪካውያን ነው። መፅሀፉ "ፊተኞች ኋለኞች ፣ ኋለኞች ፊተኞች ይሆናሉ" ያለው ተፈፀመ። እነዛ የፍልስፍና ጀማሪዎች እነዛ የኤፒክ ስነግጥም ጠበብቶች እነዛ የቲያትር ቀንዲሎች የሚቀጥለው ምግባቸው ከየት ዱብ እንደሚል የማያውቁ ምስኪኖች ሆኑ።

የዘመናችንን ግሪካውያን ዳግም እንርሳቸው፣ የጥንቱ ዜዉስ ይድረስላቸው። እኛ ከሄሮዱቱስ ፣ ሶቅራጥስ ፣ ሶፎክለስ ፣ ሆሜር ፣ አሪስጣጣሊስ፣ ሂፖክራተስ፣ ፓይታጎረስ፣ አርኪሜድስ ጋር ነን። በታሪክ ውስጥ የስነጽሑፍ ፍልስፍና ቲያትር የመጨረሻ ከፍታ ይኼው ዘመን ነበር። ስልጣኔውን አምጦ የወለደው ጥበቡ ነው። ፈላስፋዎች በአደባባይ ተገኝተው ይከራከራሉ። ታዳሚያን በትያትር አዳራሽ ታላላቅ ተውኔቶችን ይኮመኩማሉ። ተማሪዎች የሆሜርን ባለ 28,000 መስመር ግጥም ኢሊያድ እና ኦዲሴይን በቃላቸው ይወጣሉ። ዜጎች በየእለቱ በአደባባይ እየተገኙ በዲሞክራሲያዊ መብታቸው ዲሞክራሲያዊ ህይወት ይመራሉ። በየአራት አመቱ ደግሞ የኦሎምፒክ ስፖርትን እያዘጋጁ ይታደማሉ። ግሪካውያን ብዙ ሰጥተውናል―ዲሞክራሲን፣ የኦሎምፒክ ስፖርትን፣ ፍልስፍናን፣ ዘመናዊ ህክምናን፣ አልኬሚን(ለዘመናዊ ኬሚስትሪ መሰረት ነው)፣ ፊዚክስን(በተለይ አሪስጣጣሊስ) ፣ ሎጂክን(ሳይንሳዊ አመክንዮን) እስከዛሬ ድረስ የሚሰራ የነጠረ ከዘመን ዘመን የሚዘረዘር ጥበብን ሁሉ ቸረውናል። ነገር ግን ሁሉም ጥሩ ነገሮች ሁሉ መጨረሻ አላቸው። በትሮይ ጦርነት ትሮይ ተደመሰሰች። የግሪካውያን ስልጣኔ መጨረሻ ሆነ። ወደ ሮማውያን እንሻገር።

ሮማውያን ጦረኞች ናቸው። ከግሪካውያን የወረሱት እልፍ ነው። ሆሜር የግሪክ ትልቁ ገጣሚ ሲሆን ሮማዊው ቨርጂል ይህንኑ ኤፒክ ስነግጥም ዘዬ ተከትሎ "ኢሊያድ"ን የሚገዳደር ውብ ስንኝ "ኤኒድ"ን ፃፈ። ሌሎች ገጣሚዎችም አሉ እነ ኦቪድ። ነገር ግን ሮማውያን ሮማውያን እንጂ ሙሉ ለሙሉ የግሪካውያን ቅጂዎች አይደሉም። ሮማውያን የራሳቸውን አዲስ ዘዬ ፈጠሩ። ሮማውያን ተዋጊዎች ናቸው፤ የጦር ስልት አዋቂዎች ናቸው፤ ተስፋፊዎች ናቸው። አለም ታላቁን የእንግሊዝ ኢምፓየር አይቷል፤ ቤዛንታይንን አይቷል፣ መቄዶንያዊውን ትልቁ እስክንድርን አይቷል፣ ካርቴጂያዊው ሃኒባልን አይቷል፣ ፈረንሳዊውን ናፖሊዎን ቦናፓርትን አይቷል። እንደ ሮማውያን የተዋጣለት ጦረኛ ግን አላየም። አንድ አባባል "በእንግሊዝ ምድር ፀሐይ አይጠልቅም" ይላል። "በሮማውያን ምድር ግን ጦር አይጠልቅም" ሮማውያን ሁሌ እንደተዋጉ ነው፤ ደም እንዳፈሰሱ ነው፤ ግዛት እንዳስፋፉ ነው፤ ባሪያ እንደማረኩ ነው። ጦረኝነት ደማቸው ውስጥ ያለ ተፈጥሯቸው ነው። ይህ ታዲያ ከመሬት አልበቀለም፤ ዝም ብሎ አልመጣም። ጦረኝነት ዲሲፕሊን ይፈልጋል። እንከተለው። ሮማውያን ስልጡን ፖለቲከኞች ናቸው። ታላላቅ ኦራተሮች አሏቸው። ሮም ሪፐብሊክ ናት። ሪፐብሊኩን የሚመሩ ብዙ ሴናተሮች አሉ። ጁሊየስ ቄሳር መጥቶ ሪፐብሊኩን ወደ ኢምፓየር ቀየረው። ኤምፔሬሮቹ በዚህ በኩል ሃገር ይመራሉ፤ እልፍ ብለው ግዛት ያስፋፋሉ፤ ደሞ ወደ እልፍኛቸው ተነጥለው ይፈላሰፋሉ። እሳት የላሰ ንግግር ያደርጋሉ። ውስብስብ ስብእና አላቸው። በአካልም በመንፈስም የተሞረዱ ናቸው። ሁሉንም እሴቶቻቸውን ተከትለን ብንነጉድ ከምንጩ እንደርሳለን። ልክ እንደ ቅድመ አያቶቻቸው ግሪካውያን ሮማውያንም በጥበብ ድንጋይ ላይ የተመሰረቱ ረዥም ቅጥር ናቸው። ሮማውያኑ ሴኔካ ፣ ማርከስ ኦሬሊየስ ፣ ሁለቱም ፕሊኒ ፣ ሲሴሮ የፍልስፍናም የፖለቲካም ፣ የሳይንስም የጥበብም ሰዎች ነበሩ። መልቲዲሲፕሊናዊ ስብእናዎች በመሆናቸው ሮምን ታላቅ እና የማትነቃነቅ ኢምፓየር አድርገው ለመመስረት አስችሏቸዋል። በሁለት በኩል የተሳሉ ቢላዎች በመሆናቸው ጠንካራ የፖለቲካ አመራር፣ የተሳካ የጦር ሜዳ ገድል፣ የደረጀ መንፈሳዊ ልእልና ነበራቸው።

ወደ መካከለኛው ምስራቅ እንሻገር። ባቢሎን፣ ሱሜር፣ ሜሶፖቶሚያ፣ ግብፅ፣ እስራኤላውያንን እናገኛለን። ግብፅ ከሮማም ከግሪክም የቀደመች ጥንታዊ የጥቁር አፍሪካውያን ስልጣኔ ናት። ሜሶፖቶሚያ የመጀመሪያውን በታሪክ የተገኘ ስነጽሑፍ የጊልጋሜሽ ኤፒክ(Epic of Gilgamesh) ደራሲዎች ናቸው። ኤፒክ ስነግጥም ሜሶፖታሚያውያን ፈጠሩት ካልን ግሪካውያን በሆሜር የፍፅምና ደረጃ ላይ ሰቅለውታል። ኤፒክ ስነግጥም ለማታውቁት ልብወለድ ባልነበረበት በዚያ የጥንት ዘመን ረዥም ታሪኮችን በግጥም መልክ የሚቀርብበት የስነጽሑፍ ዘውግ ነው። በጣም ቀለል አድርገን ካየነው ልብወለድ በግጥም ልንለው እንችላለን። እንደ ልብወለድ ሴራ ገፀባህሪያት አሉት ግን ከልብወለድ በጣም የሚለይ የረቀቀ የስነጽሑፍ ጥበብ ነው።

ጥቁር ግብጻውያን ለፈርኦኖቻቸው መቀበሪያ ፒራሚዶችን የገነቡ፣ በፓፒረስ ቅጠል ስነፅሁፍን የከተቡ፣ በአስማት ጥበባቸው የታወቁ የራሳቸውን ልዩ ስልጣኔ የፈጠሩ ህዝቦች ነበሩ። ስለ ግብፅ ፈርኦኖች ዘወትር የሚደንቀኝ ጉዳይ አለ። መቃብሮቻቸው ፒራሚድ ከሆነ መኖሪያ ቤተመንግስታቸው እንዴት የላቀ ነበርን?! በእርግጥ ግን ፈርኦኖች ከሞት በኋላ ስላለው ህይወት የበለጠ አትኩሮት የሚሰጡ ፒራሚዶቻቸው ቤተመንግስታቸውን አንበሳ ዶሮን ወደታች እንደ ጫጩት እንደሚገረምም ያሉ ነበሩ። ቴክኒካሊ የግብፅ ፒራሚዶችን የገነቡት እስራኤላውያን ናቸው። መፅሀፍ ቅዱስ የእስራኤላውያን የአእምሮ ጭማቂ ውጤት ነው። የእስራኤላውያን የመንፈስ ልእልና ከስነፅሁፋዊ መፅሀፍ ቅዱስ ይመነጫል። ሰለሞን ትልቁን የኢየሩሳሌም ቤተመንግሥት የገነባው በድንጋይ እና በወርቅ አይደለም―በአምስቱ የሙሴ የህግ መፅሀፍት እንጂ። የሙሴ መፅሀፍት ምህንድስናውን፣ ህክምናውን፣ ኮከብ ቆጠራውን፣ ህግጋቱን ጠቅልለው የያዙ ህዝቦችን በአካልም ሆነ በመንፈስ የመቅረፅ እምቅ አቅም የነበራቸው እና የቀረፁ ጠብሰቅ ያሉ ሰነዶች ነበሩ። የብሉይ ኪዳን ጥበብ እስራኤላውያን በመላው አለም እስከሚበተኑበት ድረስ ትልቅ ህዝብ አድርጓቸዋል። ዳግም ከ70 አመት በፊት እንደ ሃገር ሲመሰረቱ የተአምራዊ ጥንካሬያቸው መፍለቂያ ነበር። በእርግጥ አሁን የግሪክን እና የሮማውያንን አማልክት የሚያመልክ ከመሃከላችን አንድም የለም። የእስራኤላውያን አምላክ ግን ከመቼውም ግዜ በላይ ቢሊየን ተከታዮች አሉት። ይህ የሚያሳየው የእስራኤላውያንን ጂኒየስነት እና ድንቅ የፈጠራ ችሎታ ነው―የፈጠሩት አምላክ የበለጠ ተአማኒ ስነፅሁፋቸውም solid ነው። መፅሀፍ ቅዱስ ሌላ ምንም ሳይሆን የእስራኤላውያን የታሪክ መፅሀፍ ነው―ግማሽ እውን ግማሽ ቅዠት ነው።

በምእራቡ የፍልስፍና አለም እጅግ የሚያስደንቁኝ ሶስት ፈላስፋዎች አሉ—ሶቅራጥስ፣ ፕሌቶ እና ኒቼ። ሶቅራጥስ አስደናቂነቱ የፍልስፍናን ማእከላዊ ርእስ የሰውን ልጅ በማድረጉ ነው። ከሶቅራጥስ በፊት የነበሩ ፈላስፎች የፍልስፍናቸውን ርእስ ከሰው ልጅ ንቃተህሊና ውጪ የሆነ ነገር ማለትም ቁስ ላይ አድርገውት ኖረዋል። እነዚህን ፈላስፎች በአንድ ጠቅልለን Pre-Socratic Philosophers/ቅድመ-ሶቅራጥስ ፈላስፋዎች የምንላቸው ያለ ምክንያት አይደለም። ታለስ፣ አናክሲሜንደር፣ አናክሳጎረስ ወዘተ ያሉ ፈላስፋዎች ህልውና የተሰራው ከአየር፣ ከአፈር፣ ከውሃ፣ ከእሳት ወይም ምንነቱ ከማይታወቅ ነገር ether እንደሆነ ሲፈላሰፉ ኖረዋል። ሶቅራጥስ ግን ይህንን ሁሉ ሽሮ የፍልስፍና ማእከላዊ ርእስ ሰው ነው፤ የምንፈላሰፈውም ስለሰው ነው ብሎ መሰረታዊ የፍልስፍና እሳቤ ለውጥ ወለደ። ከሶቅራጥስ በኋላ የመጡት ፈላስፎች ሁሉ የፈሰሱት ሶቅራጥስ በቀደደው ቦይ ነው። ከሶቅራጥስ ወዲህ ያሉት ሁሉም ፈላስፋዎች የፍልስፍናቸውን ርእስ በትክክለኛው ቦታ ሰው ላይ አድርገዋል።

ሶቅራጥስ ፍልስፍናን ለሁለት ከፈለ—ቅድመ ሶቅራጥስ እና ድህረ ሶቅራጥስ አስብሎ። የእየሱስ ክርስቶስ መወለድ ዘመንን እንደከፈለ የሶቅራጥስ ደግሞ የፍልስፍና እሳቤን እንዲሁ ለሁለት ከፈለ። Socrates was a turning point. And, no one ever looked back since. እውነተኛ የፍልስፍና መሰረት የጣለው ሶቅራጥስ ነበር። ከሶቅራጥስ በኋላ የመጡት ሁሉም ፈላስፎች የፍልስፍና ቤታቸውን የሶቅራጥስ ሰዋዊ መሰረት ላይ አድርገዋል። ይህ ታላቅ መሰረታዊ የፍልስፍና መሰረቱ ሶቅራጥስን የፈላስፋዎች ሁሉ አውራ ያደርገዋል።

ደግሞ በዚህ ላይ የሶቅራጥሳዊ ዘዴ ወይም ዳያሌክቲካዊ ዘዴ ጨምሩበት። ይህ ሳይንሳዊ ዘዴ አሁን ድረስ የሚሰራ፣ የነጠረ ሳይንሳዊ እውነት ላይ ለመድረስ ፍቱንነቱ የተመሰከረለት ዘዴ ነው። በዚህ ዘዴ አንድ አሳቢ እውነት ነው ብሎ የተቀበለው ጽንሰሃሳብ ይኖረዋል። ታዲያ ሶቅራጥስ ይህንን እሳቤ የሚገዳደሩ ብልህ ጥያቄዎችን በመጠየቅ አሳቢው እሳቤውን በጥሞና እንዲመረምርና ወደ ትክክለኛው የእውነት ጎዳና እንዲያመራ ይረዳዋል።

ሶቅራጥስን ይበልጥ አስደናቂ ፈላስፋ የሚያደርገው ይህንን ሁሉ ጥበብ ይዞ "እኔ የማውቀው አለማወቄን ነው" ማለቱ ነው። በንግግሩ ውስጥ ያሉት ሁለት ሃሳቦች እርስበእርስ የሚጻረሩ በመሆናቸው ሶቅራጥሳዊ ቅራኔ የሚል አንድምታንም ወልደዋል። ሶቅራጥስ ያውቃል? ወይስ አያውቅም? ይህ የህይወትን ማእከላዊ እንቆቅልሽ የሚገልጽ እውነተኛ መደምደሚያ ነው። በህይወት ውስጥ ሁሌም ተቃራኒዎች አብረው ነው የሚኖሩት—ትልቅና ትንሽ፣ ላይና ታች፣ ወንድና ሴት፣ ማወቅና አለማወቅ ወዘተ። ማወቅ ካለማወቅ፣ አለማወቅ ከማወቅ ተነጥሎ ሊኖር አይችልም። ሶቅራጥስ እኩል አዋቂነቱንም አላዋቂነቱንም በአንድ አረፍተነገር በጥበብ የገለጸ ታላቅ ፈላስፋ ነው። የአቴና ጠቢቦች ሁሉ በአንድ ድምጽ በመላው አቴና እንደ ሶቅራጥስ ያለ ብልህ፣ ጠቢብ የለም ይላሉ። ምክንያታቸው ቀላል ነው። ሌሎቹ ጠቢባን ነን ባዮች አውቃለሁ ብለው ሲኮፈሱ ሶቅራጥስ ብቻ አላዋቂነቱን በማወቁ ተወዳዳሪ የሌለው ጠቢብ አድርጎታል።

ሁለተኛው ታላቅ ፈላስፋ የሶቅራጥስ ተማሪ ፕሌቶ ወይም በአማርኛ ስሙ አፍላጦን ነው። በነገራችን ላይ ፕሌቶ የግሪክ ስሙ አሪስቶክልስ ነው። ፕሌቶ ቅጽል ስሙ ነው—ትርጉሙም ባለ ሰፊ-ትከሻ ማለት ነው። ፕሌቶ ፍልስፍናውም እንደ አካሉ ባለ ሰፊ ትከሻ ነበር። ታዲያ ፕሌቶ የሶቅራጥስ ተማሪ ብቻ ሳይሆን እሳቤዎቹን የጻፈለት ደቀመዝሙሩ ጭምር ነው። ሶቅራጥስ በመላው ህይወቱ አንድም መጽሐፍ አልጻፈም። ሶቅራጥስ ብዙውን ግዜውን የሚያጠፋው በማሰብ ወይም ከሌሎች ጋር ዳያሌክቲካዊ ውይይት በማድረግ "እውነትን" በማዋለድ ነው። ተማሪው ፕሌቶ የሶቅራጥስን ንግግሮች ከስርከስሩ እየተከታተለ በአብዛኛዎቹ መጽሐፎቹ ውስጥ የውይይቶቹ ዋና ገጸባህሪ እያደረገው ዘለአለማዊ አድርጎታል። በፕሌቶ Symposium, The Republic, Apology, Phaedo ወዘተ የሶቅራጥስን ጥልቅ ሃሳቦች እናነባለን። የፕሌቶ መጻሕፍት ፍልስፍናዊ ውይይቶች ሲሆኑ ሁሌም ከተወያያቹ አንዱ ገጸባህሪ ሶቅራጥስ ነው። በነገራችን ላይ ፕሌቶ ሂሳብ ለፍልስፍና እጅግ ጠቃሚና መሰረታዊ እንደሆነ ስለሚረዳ ሂሳብ የሚከብዳቸውን ተማሪዎቹን ያባርር ነበር።

ታዲያ ፕሌቶ አንድ ጎበዝ የሶቅራጥስ ደቀመዝሙር ብቻ አልነበረም። ራሱም ታላቅ ፈላስፋ ነው። አልፍሬድ ኖርዝ ኋይትሄድ የተባለው የ20ኛው ክፍለዘመን ፈላስፋ ፕሌቶን ሲያደንቀው እንዲህ ይላል፦ "ፍልሰፍና ሁሉ በፕሌቶ መጻህፍት ግርጌ ስር የተሰጠ ማስታወሻ/ footnote ነው። የሌሎቹ የሁሉም ፈላስፎች እሳቤ ፕሌቶን በማብራራት ላይ የተመሰረተ ነው። ፕሌቶ ምን አይነት ፍልስፍናዊ ሃሳብ ቢያረቅ ነው በፍልስፍናው አለም ይህንን የሚያክል ግዙፍ ቦታ የተሰጠው?! አብረን እንይ።

ፕሌቶ የዋሻው ምሳሌ ብሎ የገለጸው ተምሳሌት አለ። በዚህ ምሳሌ በአንድ ዋሻ ውስጥ ታስረው የሚገኙ እስረኞች አሉ። እስረኞቹ የታሰሩት ከጀርባቸው ምን እንደሚካሄድ ማየት በማይችሉበት ሁኔታ ነው። እስረኞቹ ማየት የሚችሉት ከፊታቸው ያለውን ግድግዳ ብቻ ነው። ከእስረኞች ጀርባ የሚነድ፣ የሚንቀለቀል እሳት አለ። እስረኞቹ ማየት የሚችሉት ይህ እሳት ከፊትለፊታቸው ያለው ግድግዳ ላይ የሚጥለውን ጥላ ብቻ ነው። እስረኞቹ ከዚህ ዋሻ ወጥተው ስለማያውቁ ለነሱ በአለም ላይ የነጠረ፣ ፍጹም እውነት ይህ ብቻ ነው። ከነሱ መካከል አንዱ ከዋሻው ወጥቶ "እውነተኛውን" አለም ተመልክቶ ቢነግራቸው እንደ እብድ ነው የሚቆጥሩት።

ይህ የዋሻ ተምሳሌት በጣም ኃይለኛ ነው። አያችሁ ሁላችንም አለም የምትባል ትልቅ ዋሻ ውስጥ ነው የምንኖረው። ነፍሳችን በስጋ እስርቤት ተጠፍንጋ ታስራለች። በዚህ አለም ውስጥ የምናየው፣ የምንሰማው፣ በአጠቃላይ በስሜት ህዋሶቻችን የምንረዳው እውነት አይደለም—ጥላ ነው። ከዚህ የስጋ እስርቤት ወጥተው እውነታን በፍጹም ቅርጿ የተመለከቱ ጥቂት ሰዎች አሉ—ሶቅራጥስ፣ ክርስቶስ፣ መሀመድ፣ ቡድሃ፣ ክሪሽና ወዘተ። ፍጹም እውነቱን ሲነግሩን አናምናቸውም። ከዋሻው ወጥተን ስለማናውቅ የሚነግሩን ተአምር ከኛ የመረዳት አቅም በላይ ስለሆነ ለማመን ይከብደናል።

ለመሆኑ ከዚህ እስርቤት እንዴት እንወጣለን። ለኔ መልሱ ብዙ ውስብስብ አይደለም። መልስ ፍለጋ ወደ ምስራቅ አማትራለሁ። መጀመሪያ የፕሌቶን ዋሻ በስነልቦናዊ መነጽር እንፈክረው። አእምሯችን ንቅና ኢንቅ ክፍሎች አሉት። የነቃው የአእምሮ ክፍላችን ሚጢጢ ነው። አብዛኛው ንቃታችን በጨለማ የተወረረ ነው። ለዚያ ነው የምናየው የተጥበረበረ፣ ያልጠራ ምስል የሆነው። አእምሯችንን እንዴት እናጠራዋለን? እይታችንን እንዴት እናስተካክለዋለን? እንዴት እንነቃለን? አእምሯችን 90% ተኝቷል። የፕሌቶ ዋሻ ውስጥ የተገኘነው አእምሯችን ስላልነቃ ነው። ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ነን። በሁለት እግራችን ቆመን መራመዳችን፣ መናገራችን፣ መስማታችን እንዳይሸውዳችሁ። በዚህ ሰፊ የህልውና አለም ውስጥ የሚካሄደውን እያስተዋልን አይደለም። ከፊትለፊታችን ያሉ ብዙ የማናያቸው ነገሮች አሉ፤ በዙሪያችን ያሉ የማንሰማቸው ብዙ ድምጾች አሉ። እይታችን፣ ግንዛቤያችን በጣም ውሱን ነው። እነ ሶቅራጥስ ከዚህ ውስንነት እንዴት ተፈወሱ? እንደነገርኳችሁ መልሱ ያለው ወደ ምስራቅ በኩል ነው። በነገራችን ላይ ካስተዋላችሁ የምእራብ ፍልስፍና ብዙ ጥያቄዎች አሉት። ምእራባዊ ፍልስፍና

የተመሰረተው ብዙ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ነው። ምስራቃዊ ፍልስፍና ደግሞ ብዙ መልሶች አሉት። ልዩነቱ ከየት እንደመጣ ግልጽ ነው። የምእራባዊ ፍልስፍና ማእከሉ አእምሮ ወይም ሃሳብ ነው። አእምሮ ደግሞ የጥያቄዎች ፋብሪካ ነው። አእምሮ አንድ ጥያቄ ተጠይቆ መልሱ ሲመለስለት ከመልሱ ውስጥ 10 አዳዲስ ጥያቄዎች ይወልዳል። የማያልቅ አዙሪት ነው። ጥያቄው ጥያቄ እየወለደ እንዲሁ ለዘለአለም ይቀጥላል። የምስራቅ ፍልስፍና ማእከሉ ልብ፣ ስሜት፣ መንፈስ ነው። ፍልስፍናውም አለምን እንዳለች በመቀበል እንጂ በሃሳብ ለመረዳት አይሞክርም። የምስራቅ ፍልስፍና የመልሶች ሃብታም ነው። ፍልስፍናው ሁሉ እርጋታ፣ ተመስጦ፣ አርምሞ፣ ጥልቅ ማሰላሰል ዙሪያ ነው የሚሽከረከረው።

እንግዲህ ምእራባዊ ፍልስፍና መሰረታዊ ጥያቄ ጠይቋል። የምናየው አለም ሃሰት ነው፣ ኢሉዥን ነው፣ ግድግዳ ላይ ያለ የጥላዎች ግርግር ነው። አሁን በጣም አስፈላጊው ጉዳይ እውነተኛውን አለም እንዴት ማጣጣም እንችላለን? ከስጋ እስርቤት እንዴት ነጻ እንወጣለን? የምስራቅ ፍልስፍና ወፍራም መልስ አለው—ሜዲቴሽን። ለመሆኑ ሜዲቴሽን ምንድነው? እንዴት እንዲህ ያለ ግዙፍ አስፈላጊነት ኖረው?

ሜዲቴሽን በጣም ጥልቅ፣ መሰረታዊ፣ ሁላችንም የሰዎች ልጆች ልንለማመደው የሚገባ የማይተካ ልምምድ ነው። ከላይ እንደተጠቀሰው አእምሯችን 90% የተቆጣጠሩት የሌሎች ባእድ ሃሳቦች ናቸው። ይህንን ግዙፍ ኢንቅ የአእምሮ ክፍል አንቆጣጠረውም፤ እሱ ግን ይቆጣጠረናል። የተሳሳተ፣ ከእውነታ ያፈነገጠ፣ ያልሆነ መረጃ ይሰጠናል። ስሜታችን፣ እይታችን፣ መረዳታችን በእንከን የተሞላ ነው። ሜዲቴሽን ይህንን የደፈረሰ ኩሬ የምናጠራበት መንገድ ነው። አእምሯችን የደፈረሰ ኩሬ ነው። ኩሬው፣ እውነታው ጥርት ብሎ የማይታየን ስለደፈረሰ ነው። ኢንቅ አእምሯችን ውስጥ ያሉ ባእድ ሃሳቦች ናቸው ኩሬያችንን ያደፈረሱት፤ ከእውነታው የነጠሉን፤ የተሳሳተ እይታ እንዲኖረን ያደረጉት። አንድ ኩሬ ሲደፈርስ ከነካካነው ይበልጥ እየደፈረሰ ነው የሚሄደው። የረጋ ኩሬ፣ ጥልል ያለ ንጹህ ውሃ የምናገኘው ደፍርሶ የነበረው ኩሬ ለራሱ በራሱ እንዲጠራ ስንተወው ነው። በቃ! ሜዲቴሽን በቀላሉ ሲገለጽ ይሄ ነው። በሃሳብ የደፈረሰው አእምሯችንን ከሃሳብ ግርግር ማሳረፍ፣ ለራሱ ዝምታ መተው። ታዲያ ይህንን ለማድረግ ብዙ መንገዶች አሉ። አካሄዳቸው የሚለያይ ነገር ግን የመጨረሻ ግባቸው ሁሉም አንድ የሆነ እልፍ ዘዴዎች። እስከአሁን በተለያዩ ማስተሮች የጎለበቱ በሺ የሚቆጠሩ የሜዲቴሽን ዘዴዎች ወይም ቴክኒኮች አሉ። አንድ ሁለቱን እንመልከት።

ሜዲቴሽን ላይ በጣም መሰረታዊ ከሆኑ ጉዳይ አንዱ የትንፋሽ ስርአት ነው። መተንፈስ በየቅጽበቱ የምናደርገው ግን የማናስተውለው ቋሚ ተግባራችን ነው በህይወት እስካለን። አእምሯችን ትንፋሻችንን ያለ እኛ conscious ተሳትፎ ይቆጣጠራል። ታዲያ አእምሮን ከሃሳብ ግርግር ለማሳረፍ ከሚረዱ ዘዴዎች ዋነኛው አትኩሮታችንን አተነፋፈሳችን ላይ ማድረግ ነው። የሜዲቴሽን የመጨረሻ ግብ ሃሳብ-አልባ የንቃት አለም መፍጠር ነው። አእምሯችንን ትንፋሻችን ላይ እንዲያተኩር ስናደርገው ቀስበቀስ አእምሮ ሙሉለሙሉ ከማሰብ እየተላቀቀ፣ ኩሬው ከሃሳብ ድፍርስነቱ እየተፈወሰ፣ ህልውናን በፍጹም ባህሪው እናየዋለን። ኦሾ ስለ ሜዲቴሽን ቴክኒኮች ብቻ የሚገልጽ አንድ ሙሉ መጽሐፍ ጽፏል። በመጽሀፉ ስለ 112 የሜዲቴሽን ዘዴዎች አብራርቷል።

ሌላ ጠቃሚ የሜዲቴሽን ዘዴ አእምሮ በአንድ ሃሳብ ላይ ብቻ እንዲያተኩር ማድረግ ነው። በአእምሮ ውስጥ በየቅጽበቱ በሺ የሚቆጠሩ ሃሳቦች ያልፋሉ። ሜዲቴሽን ሃሳብ-አልባ ንቃት የመፍጠሪያ ዘዴ ነው። ይህም ማለት በአእምሮ ውስጥ ምንም ሃሳብ እንዳይኖር ማድረግ ወይም በአእምሮ ውስጥ ያሉ የሃሳቦች ብዛት ዜሮ እንዲሆን ማድረግ ነው። ሜዲቴሽን ኮንሰንትሬሽን አይደለም። ኮንሰንትሬሽን በአእምሯችን ውስጥ ካሉ በሺ የሚቆጠሩ ሃሳቦች አንዱ ላይ ብቻ ማተኮር ነው። በሜዲቴሽን ግዜ ግን በአእምሯችን አንድ ሃሳብ እንኳን አይኖርም—ከሃሳብ ነጻ የሆነ ሁኔታ ነው። ሜዲቴሽን የ0 ሃሳብ ሁኔታ፣ ኮንሰንትሬሽን ደግሞ የ1 ሃሳብ ሁኔታ ነው። በአእምሮ ሳይንስ ሁለቱ እጅግ በጣም የተለያዩ ሁኔታዎች ናቸው። ኮንሰንትሬሽንን ሁላችንም በየቀኑ እንለማመደዋለን። ትኩረታችንን አሰባስበን ሬዲዮ ስናዳምጥ፣ ቲቪ ስናይ፣ ጋዜጣ ስናነብ፣ ከሰው ጋር ስናወራ አእምሯችን ውስጥ ከሚመላለሱ በሺ ከሚቆጠሩ ሃሳቦች አንዱ ላይ ብቻ እናተኩራለን። ኮንሰንትሬሽን ለሜዲቴሽን ቅርብ ነው። ግን ኮንሰንትሬሽን ሜዲቴሽን አይደለም። 0 እና 1 እኩል አይደሉም። ነገር ግን ከ1000 ይልቅ 1 ለ0 የቀረበ ነው። አንደኛው የሜዲቴሽን ቴክኒክ በዚህ ሃሳብ ላይ የተመሰረተ ነው። አእምሯችንን ወደ 0 ሃሳብ ሁኔታ ለማምጣት መጀመሪያ ወደ 1 ሃሳብ ብቻ ማስጠጋት። አንድ ሃሳብ ብቻ መርጠን ስናተኩርበት ኮንሰንትሬት እያደረግን ነው። ኮንሰንትሬሽን ሜዲቴሽን አይደለም ነገርግን ኮንሰንትሬሽን ወደ ሜዲቴሽን ሊያድግ ይችላል። የሜዲቴሽን ጠበብቶች ከደረሱበት እውነታዎች አንዱ ጠቃሚ ቴክኒክ ነው። ተግባራዊነቱ የተረጋገጠ ጠቃሚ ዘዴ ነው።

ሜዲቴሽንን በድምጽ፣ በሽታ፣ በአተነፋፈስ ዘዴ፣ በእይታ ወዘተ መለማመድ ይቻላል። መንገዱ ቢለያይም መድረሻው አንድ ነው። ማንም ሰው ቢሆን ለግሉ የሚስማማውን አዲስ የሜዲቴሽን ዘዴ ሊፈጥር ይችላል። ሰፊ አለም ነው። ሁላችንም ተራራ ወጪዎች ነን። መድረሻችን ንቃት ወይም የተራራው ጫፍ ነው። ታዲያ ተራራውን ለመወጣት ብዙ መንገዶች አሉ—ትክክል ወይም ስህተት መንገድ የለም። ተራራው ጫፍ ላይ የደረሱ፣ የነቁ ሰዎችን ጉዞ ታሪክና የመንገድ አቅጣጫ መስማት ግን ብልህነት ነው። የአንዱ መንገድ ለሌሎች ሊሰራም ላይሰራም ይችላል። ነገር ግን ክርስቶስና ቡድሃ ስለ ልምምዳቸው ሲያወጉ ጆሮን ከፍቶ፣ አትኩሮትን አሰባስቦ መስማት ተገቢ ነው።

በነገራችን ላይ ወደ ፕሌቶ እንመለስና ይህ የዋሻ ተምሳሌት ለምን በጣም መሰረታዊ እንደሆነ እንይ። ከፕሌቶ ወዲህ የተነሱ ፈላስፋዎች ሁሉ ሲያደርጉ የኖሩት ዋሻ ውስጥ እንዳለን ተቀብለው ከዋሻው ውጪ ያለው እውነተኛ አለም ምን እንደሚመስል ለራሳቸው በገባቸው ልክ ለመግለጽ መሞከር ነው። እነዚህ ሁሉ ሙከራዎች በሺ የሚቆጠሩ የተለያዩ እሳቤዎች ወልደዋል—አይዲያሊዝም፣ ማቴሪያሊዝም፣ ኢምፕሪሲዝም፣ አግኖስቲሲዝም፣ አቴይዝም፣ ኤግዚስተንሺያሊዝም፣ አብዘርዲዝም፣ ማርክሲዝም፣ ስኬፕቲሲዝም፣ ሶሊፕሲዝም ወዘተ። ሁሉም ከኢሉዥኑ ጀርባ የተደበቀውን እውነተኛ አለም መፈለግ ላይ ነው ትኩረታቸው።

ካርል ማርክስ እንዲህ ይላል፦ ፈላስፋዎች አለምን የምንረዳበት የተለያየ ሞዴል ፈጥረዋል። ቁምነገሩ ሞዴሉን መለወጥ ነው።

አሁንም ሞዴሉን ለመለወጥ የምናንኳኳው የሜዲቴሽንን በር ነው። ሜዲቴሽን ነው የሞዴሎቹ ቁልፍ። ሞዴሉን ለመለወጥ በመጀመሪያ ሞዴሉን መረዳት ያሻል። ሞዴሉን የምንረዳው ደግሞ በሜዲቴሽን ነው። የምናየው አለም፣ የምንሰማው ድምጽ፣ የተቀመጥንበት ወንበር፣ የለበስነው ልብስ፣ የቀመስነው መጠጥ፣ የምናሸተው ሽታ፣ በአጠቃላይ ሁሉም ሃሰት ነው። መጽሐፍ ቅዱስም ይላል፦ ይህ አለም ሃሰት ነው። በጣም መሰረታዊ፣ ጠቃሚ እውነት ነው። ማርክስ እንዳለው ቁምነገሩ አለም ሃሰት የመሆኑን እውነት መረዳት ብቻ ሳይሆን እውነተኛውን ፍጹም አለም ከነሙሉ ግርማሞገሱ ማየት ነው። አለም ሃሰት የመሆኑ እውነታ ሌላ የተጻራሪዎች አብሮነት ምሳሌ ነው። ሃሰትም እውነትም አብረው ነው የሚኖሩት። አንዱ ከሌላኛው አይነጣጠሉም። አሁን በአእምሯችን በኩል

አጮልቀን የምናየው አለም ሚጢጢ ነው። ሁላችንም ጉድጓድ ውሰጥ እንዳለን እንቁራሪት ነን። እንቁራሪቱ በትንሹ ቀዳዳ አሻግሮ የሚያየው ሚጢጢ ሰማይ መላው አለም እንደሆነ አምኖ ተቀምጧል። መላው አለም ግን ከዚህች ሚጢጢ ሰማይ እጅግ የገዘፈ፣ የረቀቀ ነው። አእምሯችን ሚጢጢዋ ቀዳዳ ናት። የምናየው ሁሉ በዚህች ሚጢጢ ቀዳዳ፣ በአእምሮ የተቃኘ ነው። ከዚህች ትንሽ ጉድጓድ መውጣት አለብን። አእምሯችንን አውልቀን መጣል አለብን። እይታችን አእምሮ በሚባል መጋረጃ ተሸብቧል። መጋረጃውን ማውለቅ አለብን። ሜዲቴሽን እንግዲህ የአይናችንን መጋረጃ አውልቀን የምንጥልበት ዘዴ ነው፤ ከጉድጓዱ ውስጥ የምንወጣበት መንገድ ነው። መንፈሳዊ ንቃትን የምናጣጥምበት ስልት ነው።

አንድ ፈላስፋ እንዲህ ብሎ ነበር፦እኛ መንፈሳዊ ልምምዶች ያሉን ሰዎች ሳንሆን፣ ሰዋዊ ልምምዶች ያሉን የመንፈስ ፍጥረቶች ነን። መልእክቱ ግልጽ ነው። እኛ መንፈስ ነን። ወደ ምድር የመጣነው ለአጭር እንግድነት ነው። ስጋችን፣ አእምሯችን፣ ኢጓችን፣ ስብእናችን ሁሉ ግዜያዊ ነው። መንፈሳችን የኛ አይደለም። እኛ መንፈሳችንን ነን። የረሳነው ትልቅ እውነት ነው። ሜዲቴሽን ይህን ትልቅ እውነት የምናስታውስበት ዘዴ ነው። እኛ እኮ ለአጭር ጉብኝት የመጣን መንፈሳዊ ቱሪስቶች መሆናችንን ረስተናል። ለእንግድነት የሄድንበት ቤት ውስጥ ቋሚ መኖሪያ ቀልሰናል። ነገር ግን ሞት እስከሚቀሰቅሰን ሳንጠብቅ ቀድመን መንቃት ይገባናል። ይኸው ነው ሜዲቴሽን። መሰረታዊ እኛነታችንን የምናገኝበት ቁልፍ ነው።

ብዙውን ግዜ በምናየው፣ በምንሰማው በአጠቃላይ በግኡዙ አለም እንወሰዳለን። ህልውና ግኡዝ አይደለም፤ ህልውና ረቂቅ ነው። እውነተኛ ተፈጥሯችን ረቂቅ መንፈስነት ነው። ግን ይህ ትልቅ እውነት ተጋርዶብናል። የወረረንን ግዙፍ ብዥታ ለማጥራት፣ ከራሳችን ጋር ለመገናኘት፣ አይናችንን የጋረደውን ሰንኮፍ ለመንቀል አሁንም፣ መቼም መከተል ያለብን ሜዲቴሽንን ነው። ሜዲቴሽን አማራጭ መንገድ አይደለም። ብቸኛው ትክክለኛ መንገድ ነው። ምናልባት ይህንን እውነት የሰው ልጅ እስከሚደርስበት በመቶ፣ በሺህ የሚቆጠሩ አመታት ሊወስድ ይችላል። The sooner we realize this the better. ምእራባውያን ቁሳዊ ስልጣኔ ገንብተው መንፈሳቸው ባዶውን እንደሆነ፣ እንዳልሰለጠነ ተረድተው ፊታቸውን ወደ ምስራቅ አዙረዋል። የትምህርት ስርአታቸው ውስጥ ሜዲቴሽን እና ማይንድፉልነስን እያካተቱ ነው። ከትንሿ፣ ጠባብ ጉድጓድ ለመውጣት እየታተሩ ነው። ግዙፉን ረቂቁን አለም ለማየት መንፈሳቸውን እያሰለጠኑ ነው። ለእኛም የተለየ መንገድ የለም። መንፈሱን ማሰልጠን የማያስፈልገው ከመካከላችን አንድም የለም።

እስኪ ደግሞ በሳይንሳዊ ዘዴ ይሄንን መንፈሳዊ ንቃት ለምን ማምጣት እንደማይቻል እንይ። የሳይንስ ትልቁ መሳሪያ ሃሳብ ነው። ሳይንስ ሁሉንም ነገር ለመረዳት የሚሞክረው በሃሳብ መነጽር ነው። ቅድም እንዳየነው ደግሞ ሃሳብ ሚጢጢ ጉድጓድ ነው። ህልውና በአይነት በመጠንም ከሃሳብ የረቀቀና የገዘፈ ነው። በዚህ ሴናሪዮ ሃሳብ ራሱ የችግሩ አካል ነው። ችግር የሆነ ነገር ደግሞ መፍትሔ ሆኖ አያውቅም። መፍትሔው ችግሩን ማስወገድ ነው። ለዚህ ነው ለመሰረታዊ ችግራችን ከሳይንስ መንደር መፍትሔ ልናገኝ የማንችለው። አእምሮ፣ ሳይንስ፣ ሃሳብ ውሱን ዶሜይን አለው። ሃሳብ የሚሰራው ለቁስአካሎች ነው። የፊዚክስ፣ የኬሚስትሪ፣ የባዮሎጂ ህጎች የሚሰሩት ቁስአካሎች ላይ ነው። እዚህ ሳይንስ ይግባኝ የማይባል ሁላችንም የምንቀበለው ዳኛ ነው። ወደ ረቂቁ ስንመጣ ነው ሳይንስ ደካማና ሊረዳን የማይችል የሚሆነው። መንፈሳዊ ርቀትን በሃሳብ ልቀት ልንተነትን አንችልም። እዚህ ሳይንስ ጉልበት የለውም። ሳይንስን ቁሳዊው አለምን ለመረዳትና ለማሻሻል እየተጠቀምን ለመንፈሳችን ፊታችንን ወደ ሜዲቴሽን ማዞር አለብን። ከጉድጓዱ ውስጥ ለመውጣት ዝግጁ ስንሆን፣ ሜዲቴሽን ምን ያህል አስፈላጊ መሆኑን ለማወቅ ሁለቴ አናስብም። ሜዲቴሽን ውስጥ ከጠባቧ ጉድጓድ የምንወጣበት ረቂቅ መሰላል አለ።

አሁን አንድ በጣም ትልቅ መሰረታዊ ችግር አለ። ሁላችንም ጠባብ ጉድጓድ ውስጥ እንደሆንን አናውቅም። የፕሌቶ ዋሻ ተምሳሌትነቱ አልተገለጸልንም። ፕሌቶ የሚደነቀው ቢያንስ የሁላችንንም መሰረታዊ ችግር አጥርቶ ማየትና ማሳየት ችሏል። ጠባቧ ጉድጓድ መላው አለም መሆኑን አምኖ የተቀበለ ከጉድጓዱ ውስጥ ለመውጣት ያለውን አስፈላጊነት አይገነዘብም። ያለንበትን ጠባብ ጉድጓድ በትክክል መረዳት ስንችል መሰላሉን ሜዲቴሽንን ለመሻት ከቅጽበት ያነሰ ግዜ ነው የምንፈልገው። የፕሌቶ ዋሻ እስረኛ መሆናችንን ስንገነዘብ ሜዲቴሽን ተፈጥሯዊ መልሱ እንደሆነ ወዲያውኑ ይከሰትልናል።

በነገራችን ላይ ፕሌቶ ፍጹም አልነበረም። አንድ ቀን ተማሪዎቹ በተሰበሰቡበት ፕሌቶ እንዲህ አለ፦ ሰው ማለት ክንፍ የሌለው በሁለት እግሩ የሚሄድ ፍጥረት ነው። በማግስቱ ሌላው ታላቅ ፈላስፋ ዲዎጋን ክንፎቹ ሙልጭ ብለው የተሸለተ ዶሮ ይዞ መጥቶ፦ ተመልከቱ! ይህ የፕሌቶ ሰው ነው ብሎ ተሳልቆበታል።

ከፕሌቶ ጋር የሚገናኝ እስከአሁን የምንጠቀምበት ጽንሰሃሳብ platonic friendship/ ፕላቶናዊ ወዳጅነት ነው። ይህ ወዳጅነት የጾታ ፍቅር ተቃራኒ ነው። ፕላቶኒክ ወዳጆች የጾታ ፍቅር ዝንባሌ የላቸውም፤ ወዳጅነታቸውም ተራ አይደለም። ይልቁንም ከወሲባዊ ዝንባሌ ነጻ የሆነ ነፍስ ድረስ የጠለቀ ወዳጅነት ነው። ይህ ወዳጅነት ለምን በፕሌቶ ስም እንደተሰየመ ስመራመር የደረስኩበት መደምደሚያ ፕሌቶ ከመምህሩ ሶቅራጥስና ከተማሪው አሪስቶትል ጋር ይህ አይነት ፕላቶኒክ ወዳጅነት ስለነበረው ነው።

ሌላው ከፕሌቶ ጋር ተያይዞ መነሳት ያለበት አይዲያሊስት ዝንባሌው ነው። ፕሌቶ ተፈጥሮው በረቂቅ ነገሮች ይማረካል። በዚህም ከተማሪው አሪስቶትል ጋር ተቃራኒ ነው። አሪስቶትል ኢምፕሪሲስት ነበር። ፕሌቶ በአዲያሊዝም ዝንባሌው እየተመራ ፕላቶኒዝምን አርቅቋል።

ፕሌቶ በዋሻው ተምሳሌት ያስረዳው ሃሳብ theory of forms ይባላል። በጥልቀት እንየው፦ እንደ ፕሌቶ ከሆነ ለምሳሌ በአለም ላይ ክብ ነገሮችን ልናገኝ እንችላለን—ክብ እንጀራ፣ ክብ አለም፣ ክብ ኳስ ወዘተ። ክብነትን ራሱን ግን ልናገኘው አንችልም። ክብነት ሃሳባዊ ነገር ነው። በዚህ አለም አይገኝም። በዚህ አለም የምናገኘው ለክብነት የተጠጉ ነገሮችን ነው። ስለዚህ ክብነት የፎርም ምሳሌ ነው።

እንዲሁ በሌላ ምሳሌ በዚህ አለም ውብ ሴት፣ ውብ መኪና፣ ውብ መልከአምድር ልናገኝ እንችላለን። ውበትን ራሱን ግን አናገኘውም። ስለዚህ ውበት ፎርም ነው። በዚህ የተነሳ ሁለት እውነታዎች አሉ። የቁሶች አለምና የፎርሞች አለም። የቁሶች አለም ይህ አለም ሲሆን የፎርሞች አለም ረቂቁ አለም ነው። ፕሌቶ ጨምሮ አንድን ነገር እውነተኛ ተፈጥሮ ልንረዳ የምንችለው በፎርሞች አለም ነው ይላል። ያ ነው ረቂቁ የመንፈስ አለም ክብነትን፣ ውበትን ወዘተ የያዘ።

ከላይ በተሰጡት ሁለት ምሳሌዎች ውስጥ ክብነትና ውበት ፎርም ናቸው። ፎርሞች እድሜያቸው ምን ያህል ነው? ውብ ሴት ወይም ውብ መኪና እድሜው ውሱን ነው። ክብ ኳስ ወይም ክብ እንጀራም ዘመኑ የተቆጠረ ነው። ክብነትና ውበት ራሳቸው ግን እድሜ የላቸውም። ዘለአለማዊ ናቸው። ይህም የረቂቅ ነገሮች ባህሪ ነው።

ሁለተኛው የፎርሞች ባህሪ የማይለወጡ ወይም ቋሚ መሆናቸው ነው። ለምሳሌ ቆንጆ ሴት ልትለወጥ፣ ውበቷ ሊረግፍ ይችላል። ክብ ኳስ ክብነቱን ሊያጣ ይችላል። ውበትና ክብነት ራሳቸው ግን የማይለወጡ ናቸው።