🦅 የሥነ — ግጥም ዘመነኛ መልኮች| overview
ባለንበት ዘመን ሥነ — ግጥም እያበበ ነው ወይስ እየሞተ?
🎈 Full Version | እሱባለው አበራ ንጉሤ
⨳ ሥነ — ግጥም ምንድነው?
የሰው ልጅ ከሥጋዊ ሥሪቱ በተጨማሪ መንፈሳዊ የኾነ ፍጡር ነው። ከሌሎች እንስሳት የሚለየውም በእዚሁ የመንፈሳዊ ሥሪት፣ አሳብና ስሜቱ ጭምር ነው። ስለዚህም የሰው ልጅ ፍላጎት በመብላት፣ በመጠጣት፣ በመዳራት ከሚገኙ ሥጋዊ እርካታዎች ይረቅቃል። ይህ ረቂቅ መሻት ደግሞ እርሱ ካለፈ በኋላ ለሚመጣው ቀጣይ ትውልድ ራስን በመግለጽና የኖረበትን የዘመን መንፈስ በመመርመር ለመተረክ በመትጋት ይገለጻል። ቃላት ተፈጥረው ለአፍአዊ ትርክት፣ ፊደላት ደግሞ ተፈጥረው ለሕትመትና ንድፍ ግልጋሎት ሲውሉ ይህንን የሰው ልጅ ነባር ፍላጎት ለሟሟላት ነበር። “ከሰው መርጦ ለሹመት፤ ከእንጨት መርጦ ለታቦት” እንደሚባለው ከቃላትም ደግሞ መርጠው ለሥነ-ግጥም ያውላሉ። ሥነ — ግጥም በአጭሩ የኖርንበትን የዘመን መንፈስ ለመግለጽ ያጨናቸው፣ ረቂቅ ስሜት የሚያጋቡ፣ ትርጉምና ውበትን አስተባብረው የያዙ የንዑድ ቃላት ስብስብ ነው ማለት ይቻላል።
⨳ ሥነ — ግጥም ለምን ይጻፋል?
አሜሪካዊው ገጣሚና ኀያሲ ዳና ጊኦያ ሥነ- ግጥም ከጥንታዊ የሰው ልጅ ኑባሬ፣ ዕድገትና ውስጣዊ ጉዞ ጋር ተያያዥነት ያለው የጥበብ ዘርፍ መሆኑን ያነሣል። ሥነ — ግጥም ሕልውናውም ከቅድመ ታሪክ (pre-history) ጊዜ አንሥቶ የነበረ ነው። የሰው ልጆች ታሪካቸውንና ጥበባቸውን በጽሑፍ መሰነድ ከመጀመራቸው በፊት የነበረ ኪነት እንደመሆኑ መጠን ሥነ ግጥም ለሰው ልጆች የህልውና ጉዳይ ነበር ማለትም ይቻላል። ነገሮችን ባሉበት ወይም በተከሰቱበት ሐተታዊ ኹኔታ እንደ ወረደ ለማስታወስ መሞከር ከባድ ፈተና ነው። የማስታወስ ክሂሎት እጅግ ተለዋዋጭና የማያስተማምን ነው። ስለዚህም ሰዎች ታሪካቸው፣ ባሕላቸው፣ እምነታቸው፣ ፍልስፍናቸው፣ ግላዊ ተመስጥዖና ኀሠሣቸው እንዳይጠፋና እንዳይረሳ ወደ ሥነ — ግጥምነት ያረቁታል፣ ያሻግሩታል። ሕይወታቸው በቃላዊ ሥነ ግጥም እየተነበነበ፣ እየተመደረከ መታወስ ይጠበቅበታል።
🦅
ጥንታውያኑ ሥነ — ግጥምን እንደ «Memory technology» ተገልግለውበታል። አሜሪካዊው ገጣሚ ሮበርት ፍሮስት «Poetry is a way of remembering what it would impoverish us to forget» ወይም «ሥነ ግጥም እንድንረሳ የሚያደርገንን የምናስታውስበት መንገድ ነው» በማለት ይናገራል። ስለዚህም ሥነ — ግጥም ለሰው ልጆች ከትውስታ ዝንጋኤ ጋር ትግል የሚገጥሙበት፣ ራሳቸውን ለመግለጽ የሚጣጣሩበት፣ ጀብዱን የሚተርኩበት፣ አማልክቱን የሚያመልኩበት፣ መንፈሳቸውን የሚያድሱበት መንፈሳዊ ጸጋና መሣሪያቸው ነው። የሆሜር Iliad፣ Odyssey፣ የህንዶችን Mahabharata፣ የዳንቴን Divine Comedy፣ የጆን ሚልቶን Paradise Lost መሰል ጥንታዊ የገድል (Epic) ሥነ — ግጥም ድርሳናትን፣ እንዲሁም ከብሉያት ቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ትንቢተ ዕዝራ፣ ትንቢተ ሕዝቅኤል፣ መዝሙረ ዳዊት፣ መጽሐፈ መክብብ፣ መጽሐፈ ኢዮብ ያሉትን በአብነት ማቅረብ እንችላለን።
🦅
ባሕልን ከዝንጋኤ ከመከላከል ባለፈ ሥነ-ግጥም የቃላትን ኃይል ለማጠንከርና ጉልበት ለመስጠት ይውላል። ገብረክርስቶስ ደስታ በመንገድ ስጡኝ ሰፊ ያላለቀ መግቢያው “አብዛኛውን ጊዜ ቃላት በግጥም ተቀርጸው በሚገቡበት ጊዜ ከትርጉማቸው በላይ አልፈው ተርፈው ይሄዳሉ” ይላል። ግጥም ከዝርው ይልቅ ለሰው ስሜትና ውስጣዊ ጆሮ ቅርብ ነው። በፕሮፖጋንዳ ያልዘመተው በሽለላና ቀረርቶ ይነሣል፤ በምክር ያልተገሰጸው በጥበባዊ ሥራ “እሺ” ይላል። እንዲሁም ግጥም ሀገራዊ ብልሽቶችን ለመታገል፤ ማኅበራዊ መበስበሶችን ለማረቅና የእኩልነትና የፍትሕ ድምፆችን ለማስተጋባት ጥቅም ላይ ውሏል።
🦅
በዓለም ላይ የነበሩ ትላልቅ አብዮቶችና ንቅናቄዎችን ከፊት ሆነው የመሩት ጠመንጃ ካነገቱ ተዋጊዎች ባልተናነሰ መልኩ ገጣሚያን ነበሩ። የጥቁሮችን የሰብዓዊ መብት መገፈፍ ወይም “Civil right movement” እንደ Maya Angelou, Nikki Giovanni, Margaret Walker, June Jordan ያሉ እንዲሁም፣ በተለያዩ የዓለም ጥግጋቶች የሕዳጣንን መበደል ይፋ አውጥተው ድምፅ የሆኑት ገጣሚያን ናቸው። ከእዚህም ባለፈ ብዙኅን ተስፋ ባጡበት፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ አስተዳደሮች በተንኮታኮቱበት ወቅት ተስፋ እንዳለ በመንገር፣ ገብተው የወጡበትን ጨለማ በማመላከት ተስፋ የሰጡ፣ ኑሮን ያስቀጠሉ፣ የሕይወትን ሽታ ያሳዩ ባለቅኔዎች ናቸው።
🦅
በእኛም ሀገር “አዝማሪው ምን አለ?” ይባል ነበር። ነገሥታቱ የሕዝቡን ትርታ በአዝማሪዎች በኩል ያደምጡ እንደነበር ታሪክ ያስረዳል። በ1960ዎቹ የአብዮቱ ትውልድ የተማሪዎች እንቅስቃሴ ውስጥም በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴና በመኳንንቱ ፊት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በድፍረት ይቀርቡ የነበሩ የኮሌጅ ቀን ሥነ — ግጥሞች የትግል እንቅስቃሴው አንድ መልክ ናቸው። ከዚያ ባሻገር በተለያዩ የደስታ፣ የችግርና የመከራ ጊዜያት በቃል የተሰናኙ ጥንታዊ ግጥሞችን ለትውስታ ብንከልስ ሥነ — ግጥም የህልውና ወይም የ«Necessity» ጉዳይ እንደሆነ እንረዳለን።
🦅
ባለመሰንቆ የገዘገዘው፣ ባለበገና የደረደረው፣ አባ ውዴዎች በአራራይ ያንጎራጎሩት ሥነ — ግጥም ልባች ድረስ ዘልቆ መንፈሳችንን ያነቃቃዋል። ያስተክዘናል፣ ያሳስበናል። ዘመን ያሳልፋሉ እንጂ፣ ጊዜ አያልፍባቸውም። የባለቀረርቶና የሸላይ የስንኝ ጉልበትና ዘራፋቸው በሰላም ሀገር ያዘምታል። ፍርሃትን አባርሮ ወኔን ያስታጥቃል። በአጠቃላይ የ “Dead poet society” ገጸ ባሕርይ የሆነው “John Keating” እንደሚለው “We read and write poetry because we are members of the human race” ግጥም የምንጽፈው የሰው ልጅ በመሆናችንና ከዚህ ተላላፊ እዳ ነጻ ልንሆን ባለመቻላችን ነው።
⨳ ዘመነኛ የሥነ — ግጥም ተግዳሮቶች
ባለቅኔ በዕውቀቱ ስዩም በኗሪ አልባ ጎጆዎች መክፈቻው «ግጥም የህያው ስሜቶች ምስክርነት እንደሆነ እናምናለን፤ ምናባዊ መገለጥ እንደሆነ እናምናለን፤ ለአባቶቻችን የአብዮትን ሰይፍ የሚስል ሞረድ፣ ለእኛ ፍለጋ /ኀሰሳ/ መሆኑን እናምናለን፤ ያልተንዛዛ ለቅሶ፣ ያልቆረፈደ ተረብ፣ ያልተዝረከረከ ፍልስፍና መሆኑን እናምናለን» ሲል ያውጃል። ከዚህ አንጻር ተነሥተን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየተገጠሙ በማኅበራዊ ሚዲያ ሰሌዳና በመጻሕፍት ሰፍረው ያነበብናቸው፣ የሰማናቸውና የተመለከትናቸው አብዛኛዎቹ ሥነ — ግጥሞች ከውስጣዊ መቃተት የመነጩ፣ መረሳት ስለሌለባቸው የተጻፉ፣ በጊዜ የማይደበዝዙ፣ ውበትና እውነትነታቸው እያደር እየገዘፈ የሚሄዱ ግጥሞች ናቸው ወይ? የሚለውን ጥያቄ የመመለስ የቤት ሥራ ይጠበቅብናል። ኀያሲ አብደላ እዝራ ለኤፍሬም ስዩም ኑ ግድግዳ እናፍርስ ለተሰኘ መጽሐፉ ባሰፈረው ድኀረ ቃል ላይ «ግጥም ስሜትን ለማፍካት፣ በሆነ ጉዳይ ለመብሰክሰክ፣ በውበት ለመደመም፣ ቢቀር ቢቀር በቋንቋው ንዝረት ለማገገም ይነበባል። አንብበነው እውስጣችን የሚፈነዳ፣ ለንዴት አሳልፎ የሚሰጠን፣ ለባይተዋር ነፍስ ሆነ ለሌላው ጉዳይ እንድንቆረቆር፣ ከህሊናችን እሚላወሰው በጣም ጥቂት ነው» በማለት ያጸናል።