A+ Online Tutors Ethiopia @aplusonlinetutorsethiopia Channel on Telegram

A+ Online Tutors Ethiopia

@aplusonlinetutorsethiopia


A+ Online Tutors Ethiopia (English)

Are you in Ethiopia and looking for top-notch online tutoring services? Look no further than A+ Online Tutors Ethiopia! This Telegram channel is dedicated to providing high-quality tutoring services to students of all ages and levels in Ethiopia. Our team of experienced tutors is committed to helping students excel in their academics and reach their full potential. From math and science to language arts and history, we offer a wide range of subjects to meet the diverse needs of our students. Whether you need help with homework, exam preparation, or just want to sharpen your skills, A+ Online Tutors Ethiopia is here to support you every step of the way. Join our channel today to access live tutoring sessions, study materials, practice exercises, and more. Invest in your education and unlock a world of opportunities with A+ Online Tutors Ethiopia!

A+ Online Tutors Ethiopia

01 Feb, 11:23


Dear A+ Family,

Please join us in celebrating this milestone.

We are honored to be selected for the Mastercard Foundation's Cohort II EdTech Fellowship! This incredible opportunity will allow us to grow, learn, and make an even greater impact. We are particularly excited about the chance to shape the future of education in Ethiopia.

A+ Online Tutors Ethiopia

20 Jan, 11:11


መልካም የጥምቀት በዓል ይሁንላችሁ!!!

A+ Online Tutors Ethiopia

13 Jan, 16:05


ለሚወዷቸው ልጆች የሚሆን ውድ ስጦታ ያበርክቱ!!

With Big Discount!!

Happy Holidays!!

A+ Online Tutors Ethiopia

06 Jan, 07:49


Merry Christmass 🌟🌟🌟

A+ Online Tutors Ethiopia

06 Jan, 07:48


#NationalExam : የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ እንደሚጠናቀቅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ምዝገባቸውን ያላጠናቀቁ ተማሪዎች ከቀነ ገደቡ አስቀድመው እንዲያጠናቅቁ አገልግሎቱ አሳስቧል።

የፈተና ይዘትን በተመለከተ የሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ፈተና በአጠቃላይ ከ9-12ኛ ክፍሎች እንዲሁም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከ7-8ኛ ክፍሎች እንደሚሸፍን ተገልጿል።

ተማሪዎች በተማሩበት የክፍል ደረጀ የተማሪ መጽሐፍን መሠረት አድርገው እንዲዘጋጁ ተብሏል።

በሌላ በኩል ፥ ዘንድሮ በመደበኛው እና በግል 750,000 ተማሪዎች ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ይመዘገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ  ከአገልግሎቱ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

እስካለፈው ሳምንት ባለው ዳታ ወደ 500 ሺህ  ተማሪዎች ተመዝግበል።

በመደበኛው ፕሮግራም 600 ሺህ ተማሪዎች ለመመዝገብ እቅድ የተያዘ ሲሆን እስካሁን ባለው 82 በመቶ የሚሆኑ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ አከናውነዋል ፤ በግል የሚፈተኑ 150 ሺህ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ ይጠበቃል።

ኢንተርኔት ማይሰራበት ቦታ ተማሪዎች በወረቀት ከተመዘገቡ በኋላ ኢንተርኔት የሚሠራበት አካባቢ በመሔድ መረጃቸውን ወደ ኦንላይን እየተጫነ ነው።

A+ Online Tutors Ethiopia

28 Dec, 08:23


ለሳይንስ ወዳጆች በሙሉ!!

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የሳይንስ ማእከል “የኑክሊየር ኃይል ጥቅሞችና አስፈላጊነት” በሚል ርእስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፊዚክስ ትምህርት ክፍል የኑክሊየር ኃይል ሳይንቲስት በዶ/ር ጥላሁን ተስፋዬ አቅራቢነት ሳይንሳዊ ገለጻ ያካሂዳል።

መርሐግብሩ ቅዳሜ፣ ታህሣስ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 - 10፡00 ሰዓት በአካዳሚው ዋና ጽ/ቤት ስለሚካሄድ በአካል ተገኝተው እንዲሳተፉ በአክብሮት ተጋብዘዋል።
አድራሻ:- ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አካባቢ ወይም በንግድ ባንክ ጉለሌ ቅርንጫፍ በኩል ገባ ብሎ።
ጉግል ካርታ፡- https://maps.app.goo.gl/yb1LFT7PDTwLUP217

A+ Online Tutors Ethiopia

16 Dec, 09:53


ውድ ወላጆች፥

ልጆቻችሁ የኦንላይን ቱቶርያሉ በሚከታተሉበት ወቅት ወረቀትና እስክርቢቶ ወይም እርሳስ ማዘጋጀታቸውን ሁልጊዜ ማረጋገጥ አለብን።

እዚህ ቪድዮ ላይ እንደምታዩት ጥያቄዎችን በሚሰራበት ጊዜ ልጆች አብረው መስራት አለባቸው።

A+ Online Tutors Ethiopia

10 Dec, 09:25


ሰላም ውድ ቤተሰቦቻችን፣

ምዝገባ በምታከናውኑበት ጊዜ ክፍያዎቻችሁ በሚከተሉት የባንክ አካውንቶች ብቻ እንድታደርጉ እንገልፃለን።

To: A Plus Online Tutors PLC

1. Awash Bank 01304732978600

2. Zemen Bank 1212210726681015

3. Commercial Bank of Ethiopia 1000486134082

4. Abay Bank 1752119323553015

5. Telebir Short Code 520258

ከከፈሉ በኋላ የከፈሉበትን ማስረጃ (Deposit Slip ወይም Screenshot) በቴሌግራም 0960601718/0000 ይላኩልን። በ አጭር ግዜ ውስጥ ኢሜይልና ፓስዎርድ ይላክሎታል።

ስለመረጣችሁን እናመሰግናለን🙏

A+

A+ Online Tutors Ethiopia

06 Dec, 10:43


Do you know that you can access your tutorials on a mobile app?

For Google Play Store
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.thinkific.android&pcampaignid=web_share

For Apple App Store
https://apps.apple.com/us/app/thinkific/id1557573471

Once you’ve downloaded the app, simply search for ‘A+ Online Tutors’ and sign in with your access code to instantly access your enrolled subjects and communities.

A+ Online Tutors Ethiopia

24 Nov, 08:40


ለሚወዷቸው ልጆች የሚሆን ውድ ስጦታ ያበርክቱ!!
ከ 5ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የሚሆን የሒሳብ (Mathematics) ትምህርት ቱቶርያል እጅግ በጣም ዘመናዊና አነቃቂ በሆነ መልኩ አዘጋጅተናል። ልጆችዎ ለሒሳብ ትምህርት ሲያስመዘግቡ በተጨማሪም የGeneral Science ወይም የአካባቢ ሳይንስ ትምህርት ቱቶርያል በነፃ ይበረከትላቸዋል።
ትምህርቶቹ በኦንላይን ወይም በገፅ ለገፅ ወይም በሁለቱም አማራጮች ተዘጋጅተዋል። ልጆችዎን ለማስመዝገብ በስልክ ቁጥሮች
09-60-60-00-00 ወይም 09-60-60-17-18 ይደውሉ።
የኦንላይን ትምህርቶቹ ልጆችዎ በየትኛውም ቦታና ሰአት ሆነው መከታተል የሚችሏቸው ናቸው።
ልጆች በሒሳብ የትምህርት ዓይነት ከፍተኛ አቅም ከገነቡ ሌሎች የትምህርት ዓይነቶችን በቀላሉ የመረዳት ችሎታ ይኖራቸዋል። በተጨማሪም የማስታወስ፣ የማሰላሰል እንዲሁም ችግርን የመፍታት አቅማቸው እንዲጎለብት ይረዳቸዋል።
Telegram: @APlusOnlineTutorsEthiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@aplus_onlinetutors?_t=8nukx8tOlzJ...
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/aplus-online-tutors/
Facebook: A+ Online Tutors
Website: www.aplusonlinetutors.com
#onlinelearning #education #tutorial #afterschoolprogram #Ethiopia #school #educational #mathematics #science

A+ Online Tutors Ethiopia

10 Nov, 04:51


በስራ ጫና ምክንያት ለልጆቻቸው ጊዜ መስጠት ላልቻሉ ወላጆች የሚሆን ጠቃሚ ምክር።

A+ Online Tutors Ethiopia

22 Oct, 10:55


ውድ ወላጆች፣

በዚህ ሰሚስተር ልጆችዎ ‘Most Active Online Student’ በመሆን ከተሸላሚዎች መሃል እንዲሆኑ እነዚህን በማድረግ ከአምና የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል።

1ኛ/ በሳምንት ቢያንስ ከ 4 ጊዜ በላይ ኦንላይን በመግባት መከታተል
2ኛ/ በቱቶርያል ቪድዮ ውስጥ ባለው “Discussion” በመጠቀም ያልገባቸውን መጠየቅ
3ኛ/ በቱቶርያሉ ውስጥ ያሉ ጥያቄዎችን መሞከር
4ኛ/ የጥያቄ ማብራርያዎችን መከታተል
5ኛ/ “Community” ውስጥ በመግባት ከሌሎች ተማሪዎች እና ከ A+ Admin ጋር ስለትምህርቱ መወያየት

A+ Online Tutors Ethiopia

22 Sep, 17:36


The most active online students - የክረምት ቱቶርያል

Congratulations!!! 💫💫💫

A+ Online Tutors Ethiopia

21 Sep, 14:49


የ 2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተጀምሯል።
እንኳን አደረሳችሁ!!

እንደተለመደው በመስከረም ወር ለሁሉም ተማሪዎች ቱቶርያል በነጻ እንሰጣለን።
በስልክ ቁጥሮቻችን 0960601718 ወይም 0960600000 በመደወል የመስከረም ወር ነጻ ቱቶርያል ተጠቃሚ ይሁኑ።

#መልካም_የትምህርት_ዘመን!!!

A+ Online Tutors Ethiopia

21 Sep, 04:35


Let Your Children Learn Anywhere, Anytime!

A+ Online Tutors Ethiopia

07 Sep, 16:33


New Year, New Beginnings, New Approach!!!

A+ Online Tutors Ethiopia

17 Aug, 09:27


ክረምቱ ተጋምሷል፤

ትምህርት የሚጀመርበት ጊዜ እየተቃረበ ነው። በአዲስ ዓመት አዲስ እና ጠቃሚ አስተሳሰብ ማምጣቱ አስፈላጊ ነው ብለን እናምናለን። ከዚህም በመነሳት በአንድ ጉዳይ ላይ ሃሳብ ማጋራትና ድምጽ ማሰባሰብ ፈለግን።
እሱም ምንድነው፣ በትምህርት ሰዓት ሴት ልጆቻችን ወርሃዊ አበባ ላይ በሚሆኑበት ጊዜ የሞዴስ አለመኖር፣ የመግዛት ዓቅም አለመኖር፣ በግልጽ ለማውራት ማፈር፣ ትምህርት ቤት ውስጥ ሞዴስ ካለበት ክፍል ለመቀበል መሸማቀቅ የመሳሰሉ ችግሮች በመኖራቸው በትምህርታቸውና በራስ መተማመን ደረጃቸው ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ ቀላል የሚባል አይደለም።

ከዚህም በመነሳት የሚቀጥለው ዓረፍተነገር ለማጋራት ፈለግን።
ድምጽ ስጡበት፣

A+ Online Tutors Ethiopia

17 Aug, 05:57


እኩለ ክረምቱን በማስመልከት የተዘጋጀ አስደሳች ዜና ለወላጆች ... በ 600 ብር ብቻ!!!
ወላጆች የክረምቱን መጋመስ በማሰብ ለልጆቻችን ዩኒፎርምና የትምህርት ቁሳቁስ የማሟላት ስራ ላይ እንተጋለን። እዚህ ላይ ግን አንድ መጠየቅ ያለበት ጉዳይ አለ። ምን ያህሎቻችን ከትምህርት ቁሳቁስ አልፈን ስለ ልጆቻችን የትምህርት ዝግጅትና መልካም አጀማመር እናስባለን?
የልጆቻችን የትምህርት አጀማመር ቀለል ያለና ውጤታማ መሆን ዓመቱን በሙሉ በስኬት ለመጨረስ የራሱ የሆነ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ያውቃሉ?
የትምህርት ጊዜ መቃረቡን በማስመልከት ከ5ኛ ክፍል እስከ 8ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የ 50% ቅናሽ አድርገናል።
ለሚወዷቸው ልጆችዎ የሒሳብ ትምህርት የኦንላይን ቱቶርያል በ600 ብር ብቻ!!!
በተጨማሪም ልጆችዎ የGeneral Science ወይም የEnvironmental Science ትምህርት ቱቶርያል በነጻ ያገኛሉ።
ቱቶርያሉ እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስ የሚቆይ በመሆኑ ልጆችዎ የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በስኬት ጀምረው በስኬት እንዲያጠናቅቁ ያለው አስተዋጽኦ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው።
ይፍጠኑ!!!

ልጆችዎን ለማስመዝገብ በስልክ ቁጥሮች
09-60-60-00-00 ወይም 09-60-60-17-18 ይደውሉ።
የገጽ ለገጽ ቱቶርያል ለምትፈልጉ ወላጆችም ብቃት ያላቸው ቱቶሮች አዘጋጅተናል። ይደውሉልን!
በተጨማሪም ከትምህርት ቤቶች ጋር በልዩ ሁኔታ ለመስራት የተዘጋጀን መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።

TikTok: https://www.tiktok.com/@aplus_onlinetutors?_t=8nukx8tOlzJ...
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/aplus-online-tutors/
Facebook: A+ Online Tutors
Website: www.aplusonlinetutors.com

A+ Online Tutors Ethiopia

10 Aug, 09:03


በማራቶን ውድድር ላይ " ተጠባባቂ ነህ " ተብሎ የተያዘውና ለውድድሩ የተመረጠ ሌላ አትሌት መጎዳቱን ተከትሎ ሀገሩን ወክሎ የተሳተፈው ጀግናው አትሌት ታምራት ቶላ ለሀገሩ ኢትዮጵያ ወርቅ ማምጣት ብቻ ሳይሆን በሚደንቅ ብቃት የኦሎምፒክ ሪከርድም ጭምር ነው የሰበረው። 🕺💫💫💃

A+ Online Tutors Ethiopia

27 Jul, 19:35


ሰላም ውድ የA+ ቤተሰቦች፣

የኛን የኦንላይን ቱቶርያል በተመለከተ የእናንተ አስተያየት ማወቅ ስለፈለግን እባካችሁ ከስር ያለውን መጠይቅ ይምሉልን።
እናመሰግናለን 🙏🙏🙏

A+ Online Tutors Ethiopia

26 Jul, 19:18


በስራ ጫና ምክንያት ለልጆቻቸው ጊዜ መስጠት ላልቻሉ ወላጆች የሚሆን ጠቃሚ ምክር።

A+ Online Tutors Ethiopia

23 Jul, 14:57


የA+ ቱቶርያሎች ተማሪዎች በሚገባቸው ቋንቋ እና መንገድ የተዘጋጁ በመሆናቸው ብዙዎች ይመርጡናል።

የ5ኛ ክፍል ሒሳብ ትምህርት አሰጣጥሒደት ይመልከቱ።

A+ Online Tutors Ethiopia

22 Jul, 19:25


ሰላም ወላጆች፣

በእያንዳንዱ ትምህርት መሃል ምሳሌዎችና ጥያቄዎች የሚሰራ በመሆኑ ወላጆች ልጆቻቹሁ የኦንላይን ቱቶርያል በሚከታተሉበት ወቅት ምንጊዜም እስክርቢቶና ወረቀት መያዛቸውን ማረጋገጥ ይኖርባቹኋል።

ለምሳሌ ይሄንን የ 8ኛ ክፍል የሒሳብ ትምህርት ተመልከቱ።
ይህንን ትምህርት በሚሰጥበት ወቅት ተማሪዎች ከቱቶራቸው ጋር አብረው በጋራ መስራት አለባቸው።

A+ Online Tutors Ethiopia

21 Jul, 12:12


ተማሪዎች የሚሰጣችውን ቱቶርያል ከተከታተሉ በኋላ ፈተና (Quiz) ይሰጣቸዋል። ፈተናውን ከሞከሩ በኋላ ደሞ በቱቶራቸው የፈተናው ማብራርያ ይሰጣቸዋል።

ከወላጆች ምን ይጠበቃል?
ተማሪዎች የፈተናውን ማብራርያ ከተከታተሉ በኋላ ጥያቄውን ደግመው እንዲሰሩ ማበረታታት ከወላጆች የሚጠበቅ ነው። ይህንን በማድረጋቸው ልጆቻችን ጥያቄዎችን የመስራትና የማሰላሰል አቅማቸው ብእጅጉ እንዲያድግ ይረዳቸዋል።

ለምሳሌ የ 7ኛ ክፍል የፈተናው ማብራርያ እዚሁ ቪድዮ መከታተል ይቻላል ...

A+ Online Tutors Ethiopia

21 Jul, 08:19


እንደ ልጆቻችን እንደዚህ የመማር ዕድሉ ቢኖረን ኖሮ ብላችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁ?
የት በደረስን!! 😊

A+ Online Tutors Ethiopia

20 Jul, 11:01


በአዲስ አበባ ከተማ የ2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

የ2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና የማለፊያ ነጥብ 50 ሲሆን ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ደግሞ 45 እንደሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

በከተማዋ በሚገኙ የመንግሥት እና የግል ትምህርት ቤቶች በቀን እና በማታ መርሐግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው፥ በ2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 85,046 ተማሪዎች መካከል 80,198 ተማሪዎች ወይም 94.3 በመቶዎቹ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣታቸው ተገልጿል፡፡

የተማሪ ወላጆች ተማሪዎች ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን የመለያ ቁጥር እና ስም በማስገባት ውጤት መመልከት ይችላሉ። ወይም ከስር የተቀመጠውን የቴሌግራም ቦት ይጠቀሙ:👍️

ውጤት ለማየት፦ https://aa6.ministry.et/#/result

በቴሌግራም ቦት፦ @emacs_ministry_result_qmt_bot