ABIYOT KIRS SENIOR SECONDARY SCHOOL

@abiyotkirspreparatorysxyzabc


Together we can scale up the height of excellence .

ABIYOT KIRS SENIOR SECONDARY SCHOOL

21 Nov, 12:15


ቀን 11/3/2016
በ2015 አገረ አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለቴክኒክና ሙያ ውጤት ለመጣላችሁ ተማሪዎች በሙሉ ምድባችሁ ቂርቆስ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ስለሆነ ምዝገባ የጀመረ በመሆኑ በኮሌጁ በመገኘት እንድትመዘገቡ ያሳስባል።
ት/ቤቱ

ABIYOT KIRS SENIOR SECONDARY SCHOOL

18 Oct, 13:50


ቀን. 07/02/2016
በ 2015 ዓ .ም አገር አቀፍ ፈተና ለወሰዳችሁ ተማሪ ዎች በሙሉ የዩኒቨርሲቲ ምርጫ ቁጥሩ ከ44 ወደ 46 ሰለ ጨመረ ት/ቤት በመገኘት እንደገና እንድሞሉ ያሳስባል።
ት/ቤቱ

ABIYOT KIRS SENIOR SECONDARY SCHOOL

04 Oct, 08:19


ቀን 23/01/2016
በ 2015 ዓ.ም አገር አቀፍ ፈተና የወሰዳችሁ የአብዮት ቅርስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በሙሉ የዩኒቨርሲቲ ምርጫ ከዛሬ መስከረም 23/2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 25/2016 ደረስ በት/ቤቱ በመገኘት እንድትሞሉ በጥብቅ እያሳሰበ በወቅቱ ለማይሞላ ተማሪ ት/ቤቱ የማጠየቅ መሆኑን ያሳውቃል ።
ት/ቤቱ

ABIYOT KIRS SENIOR SECONDARY SCHOOL

13 Sep, 15:48


ቀን 02/01/2016
ለአብዮት ቅርስ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተማሪ ወላጆች በሙሉ ለመስከረም 5/2016 ተላልፎ የነበረው የስብሰባ ጥሪ ለእሁድ መስከረም 6/2016 ዓ.ም መዛወሩን ከይቅርታ ጋር እየገለፅን በተጠቀሰው ቀን ከጧቱ 2:30 ሰአት በት/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንደተገኘ እናሳስባለን ።
ት/ቤቱ

ABIYOT KIRS SENIOR SECONDARY SCHOOL

11 Sep, 07:00


ቀን 06/13/2015
ለአብዮት ቅርስ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተማሪ ወላጆች በሙሉ ቅዳሜ መስከረም 5/2016 ዓ.ም ስለ 2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አዲስ በወጣው የተማሪዎች ስነ ምግባር ህግና ደንብ እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ከወላጆች ጋር ውይይት ስለሚካሄድ ከጧቱ 2:30 ሰአት በት/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንደተገኙ ያሳስባል።ተማሪዎች ይህንን መልዕክት ለወላጆቻችሁ እንድታስተላልፋ እያሳሰብን በስብሰባው ለማ ይገኝ ወላጅ ልጁን ት/ቤቱ የማያስተምር መሆኑን የሳው ቃል።
ት/ቤት የሚከፈተውም መስከረም 7/2016 ዓ.ም ነው።

ABIYOT KIRS SENIOR SECONDARY SCHOOL

01 Sep, 09:33


ቀን 26/12/2015
ለአብዮት ቅርስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ነባር ተማሪ ዎች በሙሉ የ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ምዝገባ ቀኑ እያለቀ ስለሆነ በሚቀሩት ቀናት እንድትመዘገቡ እያሳሰብን በወቅቱ ለማይመዘገብ ተማሪ ባለው ክፍት ቦታ አዲስ ተማሪ የምንቀበልበት መሆኑን እናሳውቃለን።
ት/ቤቱ

ABIYOT KIRS SENIOR SECONDARY SCHOOL

29 Jul, 09:59


ማሳሰቢያ ለተፈታኝ ተማሪዎች

ጧት አንድ ሰአት ተብሎ የተገለጠው የመነሻ ሰአት ስለሆነ ቀድማችሁ እንድትደርሱ ያሳስባል።
ት/ቤቱ

ABIYOT KIRS SENIOR SECONDARY SCHOOL

28 Jul, 06:37


ቀን 21/11/2015
ለአብዮት ቅርስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
አገር አቀፍ ፈተና ለምትወስዱ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ጣቢያ የምትገቡት እሁድ ሐምሌ 23/2015 ዓ.ም ከጧቱ 1:00 ሰዓት መሆኑን እያሳወቅን በተጠቀሰው ቀንና ሰአት ተገኝቶ የማይጓዝ ተማሪ ካለ ት/ቤቱ የማይጠየቅ መሆኑን ያሳውቃል ።
ት/ቤቱ

ABIYOT KIRS SENIOR SECONDARY SCHOOL

21 Jul, 05:48


ቀን 14/11/2015
ለአብዮት ቅርስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
አገር አቀፍ ፈተና ለምትወስዱ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በሙሉ ወደ መፈተኛ ጣቢያ መግቢያ ቀን ሰኞ ሐምሌ 17/2015 ዓ.ም ከጧቱ 1:00 ሰአት መሆኑን እያሳወቅን በተጠቀሰው ሰአት ተገኝቶ የማይጓዝ ተማሪ ካለ ት/ቤቱ የማይጠየቅ መሆኑን በጥብቅ ያሳውቃል።
ት/ቤት

ABIYOT KIRS SENIOR SECONDARY SCHOOL

20 Jul, 04:17


ቀን 13/11/2015
አገር አቀፍ ፈተና ለምትወስዱ የማሀበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በሙሉ ወደ መፈተኛ ጣቢያ መግቢያ ቀን ሐምሌ 17/2015 ዓ.ም መሆኑ የተረጋገጠ ስለሆነ በተሰጠው ኦረንቴሽን መሰረት እንድትዘጋጁ እያሳሰበ መነሻ ቦታ ት/ቤት ግቢ ሲሆን ሰአት በሚቀጥለው ቀን ይገለጻል ።
ት/ቤቱ

ABIYOT KIRS SENIOR SECONDARY SCHOOL

16 Jul, 17:43


ቀን 09/11/2015
ለአብዮት ቅርስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለ12ኛ ከፍል ተማሪዎች በሙሉ ሰኞ ሐምሌ10/2015 ከጧቱ 12:30ሰአት በት/ቤቱ ግቢ የችግኝ ተከላ መረሐ ግብር ስላለ በሰአቱ ተገኝታችሁ እንድትሳተፋ ያሳስባል።
ት/ቤቱ

ABIYOT KIRS SENIOR SECONDARY SCHOOL

13 Jul, 15:24


ቀን 06/11/2015
አገር አቀፍ ፈተና ለምትወስዱ የ12ኛ ከፍል ተማሪዎች በሙሉ ወደ ፈተና ጣቢያ ለመጓዝም ሆነ በፈተና ወቅት መንግሥት የሰጠውን ዩኒፎርም ለብሶ መገኘት ግዴታ መሆኑን አውቃችሁ ከወዲሁ አዘጋጁ።
-የአይን መነጽር የምትጠቀሙ ሐኪም ያዘዘበትን ወረቀት አዘጋጅታችሁ እንድትይዙ በጥብቅ እናሳስባለን።
-አድሚሽን ካረድ፣የት/ቤት ወይም የቀበሌ መታወቂያ መያዝ ግዴታ ነውና
-በሶና ጭኮ መያዝ የተከለከለ ነው ።
በአጠቃላይ በተሰጠው ኦረንቴሽን መሰረት እንድትዘጋጁ ከወዲሁ እያሳሰብን ወደ ፈተና ጣቢያ መግቢያ ሶሻል ሳይንስ ሐምሌ17 የተፈጥሮ ሳይንስ ሐምሌ 23ሲሆን ለውጥ ካለ እናሳውቃለን።

ABIYOT KIRS SENIOR SECONDARY SCHOOL

11 Jul, 12:17


ቀን 04/11/2015
አገር አቀፍ ፈተና ለምትወስዱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ ሐሙስ ሐምሌ 6/2015ዓ.ምከጧቱ 2:30 ሰአት በክፍለ ከተማ ደረጃ ስለ ፈተና አሰጣጥ ኦረንቴሽን ስለሚሰጥ በት/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንደተገኙ እያሳሰበ በማይገኝ ተፈታኝ ለሚ ፈጠረው ችግር ት/ቤቱ ሐላፊነቱን የማይወስድ መሆኑን
ያሳውቃል ።

ABIYOT KIRS SENIOR SECONDARY SCHOOL

26 Jun, 10:20


ቀን 19/10/2015
በ2015 ዓ.ም አገር አቀፍ ፈተና ለምትወስዱ የአብዮት ቅርስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪ ዎች በሙሉ ማክሰኞ ሰኔ 20/2015ዓ.ም ኦረንቴሽ ፣የስም ስህተት ማስተካከያ፣አድሚሽን ካርድ የሚሰጥ በመሆኑ ከረፋዱ 5:00 ሰአት በት/ቤቱ የመሰብሰብያ አዳራሽ እንደተገኙ እያሳሰበ የማይገኝ ተማሪ ካለ ለሚፈጠረው ችግር ት/ቤቱ የማይጠየቅ መሆኑን ያሳውቃል ።
ት/ቤቱ