Addis Ababa City Administration Health Bureau

@aacahealthbureau


Addis Ababa City Administration Health Bureau

20 Sep, 02:24


📱 www.moh.gov.et

📱 @MoHEthiopia

📱 Ministry of Health,Ethiopia

📱 twitter.com/FMoHealth

📱 YouTube.com/FMoHealthEthiopia

Addis Ababa City Administration Health Bureau

14 Sep, 08:35


The owner of this channel has been inactive for the last 11 months. If they remain inactive for the next 7 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.

Addis Ababa City Administration Health Bureau

02 Sep, 13:11


The owner of this channel has been inactive for the last 11 months. If they remain inactive for the next 19 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.

Addis Ababa City Administration Health Bureau

24 Aug, 17:59


The owner of this channel has been inactive for the last 11 months. If they remain inactive for the next 28 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.

Addis Ababa City Administration Health Bureau

03 Jun, 16:33


ቆልማማ እግር በፈጣሪ ቁጣ ወይም በዘር የሚከሰት አይደለም!

#clubfootawareness


📱 www.moh.gov.et

📱 @MoHEthiopia

📱 Ministry of Health,Ethiopia

📱 twitter.com/FMoHealth

📱 YouTube.com/FMoHealthEthiopia

Addis Ababa City Administration Health Bureau

02 Jun, 10:23


በህፃናት ላይ በተፈጥሮ የሚከሰተው ቆልማማ እግር በወቅቱ ከታከመ መዳን እንደሚችል ያውቃሉ?
#clubfootawareness

📱 www.moh.gov.et

📱 @MoHEthiopia

📱 Ministry of Health,Ethiopia

📱 twitter.com/FMoHealth

📱 YouTube.com/FMoHealthEthiopia

Addis Ababa City Administration Health Bureau

25 May, 10:36


የኩላሊት ጠጠር (Nephrolithiasis) ምንድን ነው?

ብዙዎቻችን ውሀን የመጠጣት ባህላችን በጣም ዝቅ ያለ ነው። ይህ ልምድ ደሞ ብዙ መዘዝን ይዞብን መምጣቱ አይቀሬ ነው።

አንድ ወንድማችን "ኩላሊቴ በጠጠር ምክንያት ፈሳሽን ሙሉ ለሙሉ ማስወገድ አልቻለም እና ሀኪሞቹ አሁን መውጣት አይችልም ፣ ገና ነው የሚል መልስ ነው የሰጡኝ ፣ እና ለምንድን ነው" የሚል ጥያቄ አንስቶልኝ ነበር።

የኩላሊት ጠጠር በአብዛኛው ጊዜ 80% በውስጡ ካልሺየም ኦግዛሌት (calcium oxalete) የተቀሩት ደግሞ ከካልሺየም ፍስፌት (calcium phosphate) ፣ ዩሪክ አሲድ (uric acid) ፣ ሲስቲን (cystine) ሊሰሩ ይችላሉ።

የኩላሊት ጠጠር በአብዛኛው በአንድ ኩላሊት በኩል ይታያል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በሁለቱም ኩላሊት ሊኖር ይችላል።

ለኩላሊት ጠጠር የሚያጋልጡን ነገሮችስ?

ለኩላሊት ጠጠር የመጋለጥ እድላችን የሚወሰነው ሽንት በተሰራበት (composition) ለምሳሌ በካልሼየም ኦግዛሌት የተሰራ ጠጠር ከሆነ በሽንት ወስጥ የሚገኝ ከፍተኛ መጠን ካልሺየም እና ኦግዛሌት ሲኖር እንዲሁም ዝቅተኛ ካልሽየም እና ፖታሺየም መውሰድ እና ፈሳሽ ነገር ያላቸው ምግቦች አለማዘውተር እንዲሁም ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከስኳር የተሰሩ ጣፋጭ መጠጦች ተጋላጭነተን ይጨምረዋል ተብሎ ይታሰባል።

ሌሎች አጋላጭ ምክንያቶች ለምሳሌ አንድ ሰው ከዚህ በፊት የኩላሊት ጠጠር ከነበረበት ድጋሚ የመመለስ እድል ሊኖረው ይችላል። ከዚህ በተጨማሪ በዘር (በቤተሰብ) ወስጥ ጠጠር ያለበት ካለ ፣ በተደጋጋሚ የላይኛው የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ተጠቂ መሆን ፣ መድሀኒቶች ለምሳሌ Idinavir, Acyclovir, Sulfadiazine፣ መድሀኒቶችን ከሚገባው መጠን በላይ መውሰድ፣ ከመጠን በላይ ውፍረት፣ ከመጠን በላይ በፕሮቲን እና Vitamin C የበለፀጉ ምግቦች መመገብ ፣ ከከመጠን በላይ የሰውነት እንቅስቃሴ ለምሳሌ የማራቶን ሯጮች ፣ ደም ግፊት ፣ ስኳር ፣ ሪህ ችግር ያለባቸው ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ።

ምልክቶቹስ?
- በአብዛኛው ከ20-60 ደቂቃ ሄድ መጣ የሚል ህመም በጎናችን አካባቢ ሊሰማን ይችላል። ህመሙ በጣም ሀይለኛ ውጋት ፣ ቁርጠት ስለሆነ ህመምተኛው የመንቆራጠጥ ነገር ሊያሳይ ይችላል።

አንዳንዴም ህመሙ እስከ ሽንት ፌኛ አካባቢ ሊደርስ ይችላል። ይህም አንደ ጠጠሩ ያለበት ቦታ ይወሰናል። ከዚህ በተጨማሪ የሽንት ቀለም ወደቀይነት (ደም) መቀላቀል ፣ ማቅለሽለሽ ፣ ማስመለስ ፣ ሽንት ማጥ ፣ ሽንት ማጣደፍ ሊኖር ይችላል።

ምርምራዎቹስ?
- ከላይ የጠቀስኳቸውን ምልክቶች በምናይበት ግዜ ቶሎ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ተገቢውን ምርመራ ማድረግ ይጠበቅብናል። የጤና ባለሙያውም እንደ አስፈላጊነቱ የተለያዩ ምርመራዎችን ለምሳሌ የሽንት ምርመራ ፣ የሆድ አልትራሳውንድ ፣ የሆድ x ray ፣ የሆድ ሲቲ ስካን ፣ ሊያዝልን ይችላል

ነፍሰ ጡር እናት ላይ ምርመራዎችን ስናዝ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅብናል። ምክንያቱም ከx-ray ፣ እና ሲቲ ስካን የሚወጣው ጨረር በተለይ ፅንሱን ሊጎዳው ስለሚችል ነው። ስለዚህ በዚህ ጊዜ አልትራሳውንድ ተመራጭ ይሆናል።

የሚያመጣውስ ችግር?
-የኩላሊት ጠጠር ካልታከመ ለኢንፌክሽን ፣ ደጋሚ ተመልሶ የመምጣት ችግር (recurrence) ፣ የሽንት ቱቦ መዘጋት ፣ ኩላሊትን ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጪ እስከማድረስ ሊደርስ ይችላል።

ህክምናውስ?
- አመጋገባችንን ማስተካከል
- ጠጠሩን ያመጣብን ችግር ከታወቀ ማከም
- የህመም ስሜት ላላቸው ታካሚዎች እንደ አስፈላጊነቱ የህመም ማስታገሻ ሊሰጥ ይችላል።

- ማንኛውም የኩላሊት ጠጠር በቀዶ ጥገና ይወጣል ማለት አይደለም። ይህም የሚወሰነው እነደ ጠጠሩ መጠን ሲሆን የጠጠሩ መጠን እስከ 10 ሚሊ ሜትር ከሆነ በሽንት እንዲወጣ ነው የሚመከረው። በዚህ ጊዜ ታካሚው ዉሀ በብዛት እንዲጠጣ ይመከራል መጠናቸው ከ10 ሚሊሜትር በላይ ከሆነ የመውጣት እድላቸው ጠባብ ስለሆነ ሌሎች አማራጮችን መጠቀም ሊጠበቅን ይችላል። ለምሳሌ በድምፅ እና በጨረር በመታገዝ ጠጠሩ እንዲሰባበር በማድረግ ከዛም ውሀ በመጠጠት በሽንት እንዲወጣ ይደረጋል አንዳንድ ጊዜም በቀዶ ጥገና መውጣት ሊያስፈልግ ይችላል።

የህክምና አማራጮቹ የሚወሰኑት በባለሙያው ስለሆነ ከባለሙያ የሚሰጡንን ምክሮች ማክበር ተገቢ ነው።

NB. ንፁህ ውሀ በብዛት መጠጣት ተነገሮ ከማያልቁት ጥቅሞች አንዱ በሰውነታችን ውስጥ ያሉ አላስፈላጊ ቆሻሻዎችን ባሉበት ተቀምጠው ጉዳት እንዳያስከትሉ እና ለማስወገድ እጅግ ጠቃሚ ስለሆነ ውሀ የመጠጣት ልምዳችንን ብናዳብር መልካም ነው።

ለወዳጅዎ ያጋሩ
ጤና ይብዛሎ!
ዶ/ር ኤርሚያስ ማሞ

@AACAHealthBureau
@MoHEthiopia

Addis Ababa City Administration Health Bureau

25 May, 10:36


የኩላሊት ጠጠር (Nephrolithiasis) ምንድን ነው?

Addis Ababa City Administration Health Bureau

25 May, 10:34


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የአጥንት ቀዶ ህክምና እና የመገጣጠሚያ ቅየራ ከፍተኛ ቀዶ ህክምና በይፋ አገልግሎት መሰጠት ጀመረ ።

የአጥንት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት እና የመገጣጠሚያ ቅየራ እንዲሁም የአርትሮስኮፒ ህክምና ሠብ ስፔሻሊስት ሃኪም በሆኑት ዶ/ር ሰኢድ መሐመድ የሚመራው የሙሉ ዳሌ እና ጉልበት መገጣጠሚያዎች ቅየራ ከፍተኛ ቀዶ ህክምና በተቋማችን የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በይፋ አገልግሎት መሰጠት ጀምሯል ።

ይህ አገልግሎት በሃገራችን የፕራይቬት ዊንግ ህክምና ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሠጥ ሲሆን ፣ በርካታ የችግሩ ሰለባ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ይጠቀሙበታል ተብሏል።

ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጁ በሚሰጠው ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለመሆን ኘራይቬት ዊንግ ከፍቶ በተመጣጣኝ ዋጋ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ ለማቅረብ በሰፊው እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

@AACAHealthBureau
@MoHEthiopia

Addis Ababa City Administration Health Bureau

04 May, 12:54


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የትንሳዔ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

በዓሉ የሰላም የጤና እና የመተሳሰብ እንዲሆን እየተመኘን በበሉ ወቅት ለጤናዎ ይበልጥ ጥንቃቄ በማድረግ በተለይም ቅባቶችን በብዛት ከመመገብ እና ምግብን በደንብ ሳያበስሉ በመመገብ የጤና እክል እንዳይገጥመን ፣ ቅባቶችን መጥኖ በመመገብ እንዲሁም ምግብን በደንብ አብስሎ በመመገብ ጤናዎን እንዲጠብቁ እያሳሰብን ለሚገጥማችሁ ማንኛውም የጤና እክል ጤና ተቋማቶቻችን እንደሁልጊዜው እናንተን ለማገልገል 24 ሰዓት አገልግሎት ላይ መሆናቸውን ለመግለጽ እንወዳለን መልካም የትንሳዔ በዓል ይሁን!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ !!

@AACAHealthBureau
@MoHEthiopia

Addis Ababa City Administration Health Bureau

04 May, 02:20


በአዲስ አበባ ከተማ በዘንድሮዉ ዓመት የሚከበረዉን የትንሳኤ በአል አስመልክቶ ህብረተሰቡ በየቤቱ በእርድ መልክ የሚጠቀመዉን እና በየአካባቢዉ የቁም እንስሳትን ቅርጫ በማረድ የሚከፋፈለዉን ተከልክሏል በሚል በማህበራዊ ሚዲያዉ ሀሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ ይገኛል።

በመሆኑም ከዚህ ጋር በተያያዘ ምንም አይነት ክልከላ ያልተደረገ ሲሆን በየአካባቢዉ በህገ ወጥ መንገድ እርድ በመፈፀም ለሆቴሎች እና ለስጋ ቤቶች በማከፋፈል ተግባር ላይ የሚገኙ አካላት የቁም እንስሳቱ ጤንነት ባልተረጋገ ጠበት ሁኔታ የከተማዉን ነዋሪ ጤንነት ላይ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል።

የከተማችን ነዋሪ በአላትን ሽፋን በማድረግ ጤንነቱ ያልተረጋገጠ እንስሳት አርዶ ማከፋፈል በጤና ላይ የሚያደርሰዉን ጉዳት ግምት ዉስጥ በማስገባት በህገወጥ እርድ የሚሰማሩ አካላት በሚደረገዉ ቁጥጥር ተባባሪ እንዲሆን መልክታችንን እናስተላልፋለን።

@AACAHealthBureau
@MoHEthiopia

Addis Ababa City Administration Health Bureau

03 May, 11:02


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ስቅለቱ በሰላም አደረሳችሁ!
#መልካም_በዓል!

@MoHEthiopia

Addis Ababa City Administration Health Bureau

28 Jun, 03:22


ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1444ኛው የዒድ አል አድሃ በዓል አደረሳችሁ!
#eiduladha

@MoHEthiopia

Addis Ababa City Administration Health Bureau

21 Jun, 19:40


ዛሬ ባስጀምርነው የቀዳማይ ልጅነት ንቅናቄ ሳምንት "አ.አ. ሕጻናትን ለማሳደግ ምርጥ የአፍሪካ ከተማ ለማድረግ" የሚል ራዕይ የሰንቀንበት እና ለወላጆቸ እንዲሁም ለህጻናት ሁለንተናዊ የተቀናጀ አገልግሎት መስጠትን ያለመ ፕሮግራም ነው።

ከዚህ ዓመት ጀምረን በሚቀጠሉት 3 ዓመታት

❖ የወላጆች የምክር እና ሁለንተናዊ አገልግሎት ድጋፍ ስርአት መዘርጋት፣
❖ 1000 የህጻናት መዋያዎችን ማልማት፣
❖ 12000 የህጻናት መጫዎቻ ስፍራዎችን መገንባት፣
❖ 1095 የቅድም አንደኛ ደረጃ ትምሀርት ቤቶቻችንን ትራንስፎርም ማድረግ፣
❖ 101 የጤና ጣቢያዎችን ለቀዳማይ ልጅነት ልማት አገልግሎት ምቹ ማድረግ
❖ 5ዐዐዐ ለወላጆችና አሳዳጊዎች የምክር አገልግሎት የሚሰጡ ሰራተኞችን አሰልጥኖ ማሰማራት እና
❖ የሀገራችንን ብሎም የአፍሪካን የቀዳማይ ልጅነት ስራዎች በምርምር እና ስርጸት የሚደግፍ የልህቀት ማእከል መገንባትን የምናከናውን ይሆናል።
በዚህም መሰረት፤
ዛሬ ባስጀምርነው የቀዳማይ ልጅነት ንቅናቄ ሳምንት በሕጻናት እንክብካቤና አስተዳደግ ዙሪያ ያሰለጠናቸውን 2500 ባልሙያዎች መርቀን ወደ ስራ አስገብተናል። በዚህ አጋጣሚ በርካታ የከተማችን ወጣት ሴቶች የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል።
በተጨማሪም በክበበ ፀሐይ ያስገነባውን የሕፃናት ክሊኒክ እና በልደታ ክ/ከተማ የተገነባውን የሕፃናት ማቆያ ማዕከል መርቀን ሥራ አስጀምረናል።
ይህ ፕሮግራም የተሳካ እንዲሆን የከተማችንና የፌዴራል መስሪያ ቤቶች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በተለይም ቢግ ዊን ፊላንትሮፒስ እና በርናርድ ቫን ሊር የተባሉ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ከፍተኛ የቴክኒክ እና የፋይናንስ ድጋፍ አድርገውልናል። ሁሉንም በራሴ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም እጅጉን እያመሰገንኩ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ።

@AACAHealthBureau
@MoHEthiopia