ማስታወቂያ
-----
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በሪሜዲያል ፕሮግራም በኤክስቴንሽን መርሃ-ግብር ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለሪሜዲያል ትምህርት መግቢያ ውጤት ያላችሁ ተማሪዎች በሙሉ የምዝገባ ጊዜ ከጥቅምት 01 - 15 /2017 ዓ.ም ድረስ ስለሆነ ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ባሉት ቀናት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የትምህርቱ አጠቃላይ ክፍያ፡-
1. ለተፈጥሮ ሳይንስ የመመዝገቢያ ክፍያን ጨምሮ 2,350 ብር
2. ለማኅበራዊ ሳይንስ የመመዝገቢያ ክፍያን ጨምሮ 1,950 ብር
አመልካቾች በዩኒቨርሲቲው የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000258464428 አጠቃላይ ክፍያ በመክፈል ዋናውን የባንክ ደረሰኝ ከ 2 ፎቶ ኮፒ ጋር በመያዝ ሬጅስትራር ጽ/ቤት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የተከታታይና ርቀት ትምህርት ዳይሬክቶሬት