merkatotube

@merkatotube


Important Ethiopian and international news.

If you have tips/ጥቆማ @merkatotube_bot

We are open 24/7

merkatotube

11 Dec, 19:25


ይህ ተደጋጋሚ ክስተት የዜጎች በሕይወት የመኖር፣ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ የመሥራት፣ የአካል እና የንብረት ደኅንነታቸው፣ የሃይማኖት እና የእምነት ነፃነት ስጋት ላይ ከመጣሉ በሻገር “የዜጎችን ሁለንተናዊ ደኅንነትን የመጠበቅ እና የማስጠበቅ ግዴታ ያለባቸውን አካላት በሙሉ በምድርም ሆነ በሰማይ ተጠያቂ የሚያደርግ ጉዳይ ነው” ብሏል።

@merkatotube @merkatotube_bot

merkatotube

11 Dec, 19:00


ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን የሚመሩት ኃይል የፈጥኖ ደራሽ ኃይልን ካለፈው ዓመት ታኅሣሥ ጀምሮ ሲፋለም ቆይቷል። ጂቡቲ በተደረገው ጉባኤ አብዱልፈታህ አልቡርሃን ተገኝተዋል። የኢጋድ መሪዎች ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን ከሚመሩት ጄኔራል ሐምዳን ደጋሎ ጋር በስልክ መነጋገራቸውም ተመላክቷል።

@merkatotube @merkatotube_bot

merkatotube

11 Dec, 18:25


አምባሳደር ተሾመ፤ ከአማራ ክልል የሚነሳው የአካባቢ ይገባኛል ጥያቄ እና የኤርትራ ሠራዊት በድንበር አካባቢ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ በትግራይ ክልል እና በፌደራል መንግሥት መካከል ያለውን መተማመን “ሊሸራርፍ” እንደሚችልም ገልጸዋል።

@merkatotube @merkatotube_bot

merkatotube

11 Dec, 18:00


ስማቸውን እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ሌላ የአጣዬ ከተማ ነዋሪ ሕይወታቸውን ያጡት “ሁለት ጠና ያሉ ሴት የባጃጁ ተሳፋሪዎች” መሆናቸውን ገልጸዋል። ሦስተኛው የከተማዋ ነዋሪ በበኩሉ “ቁጥራቸውን ይሄን ያህል ማለት አይቻልም። አሁንም በከተማዋ ውስጥ የተኩስ ልውውጡ ስላልቆመ እንኳን ቁጥሩን ለማወቅ ይቅር እና እነማን እንደሞቱም ለመለየት አዳጋች ነው” ሲል የሟቾቹን ቁጥር በአሃዝ ለማስቀመጥ አንደሚያስቸግር ተናግሯል።

@merkatotube @merkatotube_bot

merkatotube

11 Dec, 17:25


አቶ ታዬ ደንደአ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሥልጣናቸው የተሰናበቱት በአገሪቱ ያለው ጦርነት እንዲቆም ጥሪ በማቅረባቸው እንጂ ሌላ ምክንያት እንደሌለ ለቢቢሲ ተናገሩ።

@merkatotube @merkatotube_bot

merkatotube

11 Dec, 16:25


የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ የሆኑት አቶ ታዬ ደንደአ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ደብዳቤ ከሥልጣን መነሳታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ እንደደረሳቸው አስታወቁ።

@merkatotube @merkatotube_bot

merkatotube

11 Dec, 14:50


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በአገልግጋዮች፣ በምእመናን እና በአብያተ ክርስቲያንት ላይ እየተፈጸመ ያለው ድርጊት በምድርም በሰማይም የሚያሰጠይቅ ነው አለ።

@merkatotube @merkatotube_bot

merkatotube

11 Dec, 14:25


በአማራ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ አጣዬ ከተማ ከትላንት እሁድ ረፋድ ጀምሮ በመከላከያ ሠራዊት እና በታጣዊዎች መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ የሰዎች ሕይወት ማለፉን ነዋሪዎች ተናገሩ።

@merkatotube @merkatotube_bot

merkatotube

11 Dec, 13:50


በአማራ ክልል ከመንግሥት ጋር ውጊያ ላይ ያለው የፋኖ ኃይል በአንድ ዕዝ ሥር አለመሆኑ መንግሥት ከኃይሉ ጋር ለሚደረግ “ንግግርም ሆነ ድርድር” አመቺ እንዳልሆነ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ተናገሩ።

@merkatotube @merkatotube_bot

merkatotube

11 Dec, 13:25


የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ የሆነው የአል-ቃሳም ብርጌድ ቃል አቀባይ በእስራኤል-ጋዛ ጦርነት ጎልተው ከወጡት መካከል አንዱ ነው። “አቡ ኡቤይዳ” በመባል የሚታወቀው ግለሰብ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የቡድኑን መልዕክት በበይነ መረብ ሲያሰራጭ ደጋግሞ ይታያል።


@merkatotube @merkatotube_bot

merkatotube

11 Dec, 12:50


ስለ ታንዛኒያ ምክንትል ፕሬዝዳንት ፊሊፕ ምፓንጎ የጤና ሁኔታ ሐሰተኛ መረጃ በማሰራጨት የተጠረጠሩ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ላይ በአገሪቱ መሪዎች ምርመራ እየተደረገ እንደሆነ ተገለጸ።

@merkatotube @merkatotube_bot

merkatotube

11 Dec, 12:25


በገጠራማዋ ቻይና የነበረውን የኤድስ ወረርሽኝ ያጋለጡት እና ለግዞት የተዳረጉት ቻይናዊቷ ዶክተር ጋኦ ያኦጄ በ95 ዓመታቸው አረፉ።
ከአውሮፓውያኑ 2009 ጀምሮ ለስደት የተዳረጉት ዶክተር ጋኦ በኒውዮርክ ህይወታቸው ማለፉን ጓደኛቸው አስታውቀዋል።


@merkatotube @merkatotube_bot

merkatotube

11 Dec, 11:25


በስፔን ላ ሊጋ ግራናዳ ከአትሌቲክ ቢልባዎ የሚያደርጉት ጨዋታ የአንድ ተመልካች ሕይወት በማለፉ ምክንያት ተቋርጧል።
በኑዌቮ ሎስ ካርሜኔስ ስታድየም የነበረው የላ ሊጋ ጨዋታ ሰኞ ዕለት ከተቋረጠበት እንደሚቀጥል ተሰምቷል።


@merkatotube @merkatotube_bot

merkatotube

11 Dec, 10:25


ለሁለት ዓመት የዘለቀውን ደም አፋሳሽ ጦርነት ማክተሙን ተከትሎ አርሶ አደሮች ወደ እርሻቸው ቢመለሱም በድርቅ ምክንያት ለከፋ የምግብ እጥረት ተዳርገዋል።
እርጅና እና መከራ የተፈራረቀባቸው አርሶ አደር ገብረመድኅን ገብረማርያምን ቢቢሲ ያገኛቸው በደጃፋቸው ከተቀመጠ ያልተወቃ ትንሽ የባቄላ ክምር ፊት ተቀምጠው ሲቆዝሙ ነው።
በአካባቢያቸው ያጋጠመውም ድርቅ ምን ያህል የከፋ እንደሆነም ሲናገሩ በሐዘን ነው።


@merkatotube @merkatotube_bot

merkatotube

11 Dec, 09:25


በቁጥር 200 የሚሆኑና ከዩኬ ጎን ተሰልፈው ታሊባንን ሲፋለሙ የነበሩ የአፍጋኒስታን ልዩ ኃይል ወታደሮች ‘ዩኬ ክህደት ፈጸመችብን’ ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ።

@merkatotube @merkatotube_bot

merkatotube

11 Dec, 08:25


በሱዳን እየተፋለሙ ያሉት ኃይሎች የተኩስ አቁም ስምምነቱን እንደሚያከብሩ መስማማታቸውን ኢጋድ ገለጸ።
የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (IGAD) እሑድ እንዳስታወቀው እዚህ ስምምነት ላይ የተደረሰው በጂቡቲ በተደረገ የአባላት አገራት ስብሰባ ነው።


@merkatotube @merkatotube_bot

merkatotube

11 Dec, 07:25


እስራኤል በጋዛ ላይ አጠናክራ የቀጠለችው የማያባራ የቦምብ ጥቃት የተኩስ አቁም ስምምነት ዕድሉን እያጠበበው ነው ሲሉ የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር ተናገሩ።
ሼክ መሀመድ ቢን አብዱልራህማን አል ታኒ በዶሃ ጉባኤ ላይ እንደተናገሩት ኳታር ሁለቱ ወገኖች የተኩስ አቁም እንዲያደርጉ ግፊት ማድረጓን ትቀጥላለች።


@merkatotube @merkatotube_bot

merkatotube

11 Dec, 06:25


በሱዳኗ መዲና ካርቱም በእርዳታ መኪኖች ላይ ‘‘ሆን ተብሎ በተፈጸመ ጥቃት’ ሁለት ሰዎች መገደላቸውን አለም አቀፉ ቀይ መስቀል አስታወቀ።
በዚህ ጥቃት ከሟቾቹም በተጨማሪ ሰባት ሰዎችም መቁሰላቸው ተነግሯል።


@merkatotube @merkatotube_bot

merkatotube

11 Dec, 05:25


በኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ ለሕጻናት እና ለታዳጊዎች የሚሆኑ መጽሐፍትን የሚቀርቡ ቤተ መጽሐፍትን በገጠሩ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በከተሞች ማግኘት አዳጋች ነው። ከዚህ አንጻር ሕጻናት የማንበብ ልማዳቸውን ለማዳበር ያለባቸውን ችግር የተገነዘበችው መምህርት ኤልሳቤጥ፣ በእራሷ ጥረት በአንድ የገጠር መንደር ውስጥ ለሕጻንት የሚሆን ቤተ መጽሐፍትን ከፍታለች።

@merkatotube @merkatotube_bot

merkatotube

11 Dec, 03:25


‘የጠፉ መጽሐፍት አዳኙ’ ኤልያስ ሜክሲኮን እስከ ወዲያኛው ይሰናበታት ይሆን?

ኤልያስ ገብረማሪያም ንባብ በሚያዘወትሩ አዲስ አበቤዎች ዘንድ የሚታወቅ ስም ነው። ዋቢ ሸበሌ ሆቴልን አለፍ እንዳሉ ነጠላ ጫማ የተጫማ ባለ‘ድሬድ’ ፀጉር ጎልማሳ ከተመለከቱ እሱ ኤልያስ ነው።

“ሜክሲኮ አምደ መጻሕፍት” ሲል የሰየማት እና ባለ አስራ አንድ ወለሉን ሸበሌ ሆቴልን ሽቅብ የምትመለከተው የመጽሐፍት መደብሩ ላለፉት አስር ዓመታት ከሜክሲኮ መልኮች አንዷ ነበረች።

ኤልያስ ጋር ተፈልጎ የማይገኝ የድሮ መጽሐፍ አለመኖሩን ቢቢሲ ያነጋገራቸው ደንበኞቹ ይገልጻሉ። ከአገርኛ የሥነ ጽሑፍ ሥራችዎች እስከ ብሉይ (classical) የሩሲያ ልቦለዶች ድረስ ከኤሊያስ መደርደሪያ ላይ አይታጡም። ከዘመን አይሽሬዎቹ የኩራዝ አሳታሚ ውጤቶች እስከ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ የአካዳሚ መጽሐፍትም ይገኛሉ።

የማስታወቂያ ሰሌዳ ተጎራብታ የምትገኘው መደብር የመጽሐፍ መሸጫ ብቻ አልነበረችም። “ሜክሲኮ አምደ መጽሐፍት” ከዘመድ ወዳጅ ጋር መገናኛ፣ አዳዲስ ሰው መተዋወቂያም ጭምር ነበረች።

@merkatotube @merkatotube_bot