ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ (ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም)
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ የአካዳሚክ ክፍሎች ለተውጣጡ መምህራን በአፈጻጸምና ግምገማ ላይ መሰረት ያደረገ የTOT ስልጠና (TOT Training on Performance-Based Assessment) በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከዛሬ በ11/02/17 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የአቅም ግንባታ ስልጠና በፔዳ ግቢ የስልጠና ማዕከል በሙያው በሰለጠኑ መምህራን በመሰጠት ላይ ነው፡፡
ስልጠናውን በንግግር ያስጀመሩት የዩኒቨርሲቲው የፈተና ማዕከል (Testing Center) ዳይሬክተር ዶ/ር ጥሩወርቅ ታምሩ ማዕከሉ የሚያከናውናቸው ተግባራት የዩኒቨርሲቲውን የፅንሰ ሃሳብም ሆነ የተግባር ትምህርቶችን የፈተና ጥራት የማሻሻል፣አገር አቀፍ፣የውጭና የቅጥር ፈተናዎች ጥራታቸውን ጠብቀው ማዘጋጀትና ማስፈተን እንዲሁም ዓለም አቀፍ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ፈተና (International English Language Tasting Center /IELTC/) እና የመሳሰሉ ፈተናዎችን መስጠት መሆኑን አስስረድተዋል፡፡
እንደ ዳይሬክተሯ ገለፃ የሶስቱ ቀን ስልጠና ዓላማ ተግባር ተኮር ለሆኑ ትምህርቶች የመመዘኛ መሳሪያዎችን ለማሻሻል ታልሞ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም ከስልጠናው መልስ ይህ ሰልጣኞች ከተለያዩ የተግባር ተኮር ምዘናዎች ጋር ተዋውቀው ምዘናዎችን በመስራት በኮሌጃቸው ላሉ መመህራን ስልጠናውን በመስጠት ተደራሽ እንደሚያደርጉት እና የተለያዩ መመዘኛዎችን አዘጋጅተው ለማሰልጠኛ ማኑዋሉ ተጨማሪ ግብዓት እንደሚሰጡ በንግግራቸው ጠቁመዋል፡፡
ለሰልጣኞች የተግባር ስልጠናውን የሚሰጡ መምህራን በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ካሉ ስድስት የአካዳሚክ ክፍሎች ማለትም ከባህሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣ ከኢትዮጲያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣ ከሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ፣ ከግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ፣ ከሳይንስ ኮሌጅ እና ከስፖርት አካዳሚ የተውጣጡ 32 አሰልጣኝ መምህራኖች መሆናቸውን ዶ/ር ጥሩወርቅ አክለው ገልፀዋል፡፡
ስልጠናውን ያዘጋጁት የዩኒቨርሲቲው የፈተና ማዕከል እና የስልጠና ዳይሬክቶሬት በጋራ ሲሆኑ ስልጠናው ከ11/02/17-13/02/17 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ የስራ ቀናት የሚሰጥ መሆኑ ታውቋል፡፡
#share #share
@Bahrdar_university