🇪🇹 Ethio Students 1 - 12 University 🎓

@ethio_student_textbook_and_news


📚ከ 1_12 ክፍል የተማሪና የአስተማሪ መጽሀፍትን PDF ያገኛሉ አዳዲስ የትምህርት መረጃንም እንዲሁ እናጋራችሁሀለን።
YOU TUBE :- https://www.youtube.com/channel/UCZuIXbtTfzfV10GsiwFo1vQ?sub_confirmation=1
በዚህ ቻናል ላይ ያጣችሁት መጽሀፍ ካለ በ @Ethio_student_ASTYAYTE
በመቀላቀል አስተያየትና መጽሀፍት ማግኘት ይችላሉ።

🇪🇹 Ethio Students 1 - 12 University 🎓

21 Oct, 13:02


#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምደባ በቅርቡ እንደሚገለጽ አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ፤ " በ2016 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ምደባ በቅርቡ ይገለጸል " ብሏል።

ተማሪዎች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጥሪ አቅርቧል።

@ethio_student_textbook_and_news

🇪🇹 Ethio Students 1 - 12 University 🎓

21 Oct, 10:03


የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ።

የ2017 የቴክኒክና ሙያ የመደበኛ ስልጠና ዘመን መቁረጫ ነጥብ ዛሬ ይፋ ተደርጓል።

የመቁረጫ ነጥቡ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።
@ethio_student_textbook_and_news

🇪🇹 Ethio Students 1 - 12 University 🎓

16 Oct, 15:57


ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር እና በዩኒቨርሲቲው የተሰጠውን የሪሚዲያል ፈተና በተቋሙ የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን ከዛሬ ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ አሳውቋል፡፡

በ https://dku.edu.et/stud_result/index.php?con=2 ሊንክ በመጠቀምና በዩኒቨርሲቲው የተሰጣቹሁን Username በማስገባት ውጤታቹሁን ማየት የምትችሉ መሆኑን ዩኒቨርሲው ገልጿል፡፡

@ethio_student_textbook_and_news
@ethio_student_textbook_and_news

🇪🇹 Ethio Students 1 - 12 University 🎓

16 Oct, 10:06


በአዲስ አበባ የህዝብ ትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ጭማሪ ተደረገ

ዝቅተኛው 10 ብር ሲሆን ከፍተኛው 65 ብር ገብቷል።

4 ብር ከ50 ሳንቲም የነበረው 10 ብር፣ 8 ብር ከ50 ሳንቲም የነበረው 15 ብር፣ 13 ብር የነበረው 20 ብር፣ 17 ብር የነበረው 25 ብር፣ 30 ብር የነበረው 40 ብር ገብቷል።
@ethio_student_textbook_and_news
@ethio_student_textbook_and_news

🇪🇹 Ethio Students 1 - 12 University 🎓

15 Oct, 19:59


#ASTU #AASTU

በአማራ ክልል ሁለተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ላመጣችሁ ተማሪዎች

የመግቢያ ፈተናውን ለመውሰድ ከጥቅምት 05 እስከ 07 /2017 ዓ.ም ድረስ ብቻ ከታች በተቀመጠው ሊንክ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡

👇👇
http://stuoexam.astu.edu.et

@ethio_student_textbook_and_news
@ethio_student_textbook_and_news

🇪🇹 Ethio Students 1 - 12 University 🎓

15 Oct, 14:53


መስማት ለተሳናቸው የሬሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ

(ጥቅምት 5/2017 ዓ.ም) በ2016 ዓም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ወስደው በመንግስት ተቋማት የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ያመጡ መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች የማለፊያ ውጤትን ትምህርት ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሠረት፤

👉 የተፈጥሮና ማሕበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከስድስት መቶ  192

👉 የተፈጥሮ እና ማሕበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከስድስት መቶ 186

👉 በፕሪፓቶሪ ፕሮግራም የተፈጥሮ እና ማሕበራዊ ሳይንስ ወንድ ከሰባት መቶ 224

👉 በፕሪፓቶሪ ፕሮግራም የተፈጥሮና ማሕበራዊ ሳይንስ ሴት ከሰባት መቶ 217 እና በላይ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

@ethio_student_textbook_and_news
@ethio_student_textbook_and_news

🇪🇹 Ethio Students 1 - 12 University 🎓

10 Oct, 22:37


#ተራዝሟል

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በመደበኛ እና በሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች፣ የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ እንድትሞሉ መባሉ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ "አንዳንድ ትምህርት ቤቶች በሲስተም ችግር ምክንያት የተማሪዎቻቸውን የትምህርት መስክ እና የዩኒቨርሲቲ ምርጫ መሙላት በመቸገራቸው" የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫ መሙያ ጊዜው እስከ ረቡዕ ጥቅምት 6/2017 ዓ.ም ድረስ መራዘሙን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

@ethio_student_textbook_and_news

🇪🇹 Ethio Students 1 - 12 University 🎓

10 Oct, 11:21


#high_quality
የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የዩኒቨርስቲው ምርጫ ፎርም ከላይ በዝርዝር ተቀምጦላችሁዋል በዚህ መሰረት መዘጋጀት ትችላላችሁ😊👍
@ethio_student_textbook_and_news
@ethio_student_textbook_and_news

🇪🇹 Ethio Students 1 - 12 University 🎓

10 Oct, 11:03


የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የዩኒቨርስቲው ምርጫ ፎርም ከላይ በዝርዝር ተቀምጦላችሁዋል በዚህ መሰረት መዘጋጀት ትችላላችሁ😊👍
@ethio_student_textbook_and_news
@ethio_student_textbook_and_news

🇪🇹 Ethio Students 1 - 12 University 🎓

09 Oct, 05:22


የሪሜድያል ማለፊያ ነጥብ ያመጣችሁ የዩኒቨርሲቲ ምርጫ በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ ሰዎች ምርጫችሁን ማስገባት ትችላላችሁ😊👍
እንዲሁም ያለፋችሁ ተማሪዎች
‼️የሚቆየው እስከ መስከረም 30 ብቻ ነው
@ethio_student_textbook_and_news

🇪🇹 Ethio Students 1 - 12 University 🎓

09 Oct, 05:17


#MoE

👉በ2017 የትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial Program) ለመከታተል የመቁረጫ ነጥብ ተወስኗል።

👉በዚህም በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና የወሰዱና እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 31% ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የሪሚዲያል ፕሮግራም መከታተል ይችላሉ ተብሏል።

👉በመንግስት ተቋማት ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ የሪሚዲያል ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥብ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

👉በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ መሙላት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

👉በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎች ማመልከቻቸውን በ https://student.ethernet.edu.et በኩል ብቻ እንዲልኩ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
Via tkv
@ethio_student_textbook_and_news
@ethio_student_textbook_and_news

🇪🇹 Ethio Students 1 - 12 University 🎓

08 Oct, 17:29


#MoE #Placement

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ መሙላት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎች ማመልከቻቸውን በ https://student.ethernet.edu.et በኩል ብቻ እንዲልኩ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
Via tkv
@ethio_student_textbook_and_news
@ethio_student_textbook_and_news

🇪🇹 Ethio Students 1 - 12 University 🎓

06 Oct, 18:32


#Update

" እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ የለም፤ ሞገዱ በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ ነው ፤ አዋሽ አካባቢ ነው የተከሰተው በሬክተር ስኬል 4.9 ነው " - ዶክተር ኤልያስ ሌዊ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶክተር ኤልያስ ሌዊ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

" እስካሁን ባለው መረጃ እዚህ የመሬት መንቀጥቀጡ እዚህ አዲስ አባባ የተከሰተ ሳይሆን አዋሽ አካባቢ የተከሰተ ነው።

ግን በመሬት ውስጥ አልፎ እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ ልዩ ልዩ ቦታዎች ተሰምቷል።

ይሄን ግልጽ ማድረግ እንፈልጋለን እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ አይደለም። ግን በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ እዚህ ያሉ ህንጻዎችን አንቀጥቅጧል።

በሪክተር ስኬል 4.9 ነው ያገኘነው። ይሄም ከፈንታሌ የሚባል ተራራ አለ ወደ መተሃራ አካባቢ ነው የተከሰተው። እስካሁን ያለው መረጃ ይሄ ነው።

ሰውም ይረጋጋ እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ሳይሆን ከሩቅ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ሞገዱ በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ በተለይ እዚህ ሰሜን እና ሰሜን ምስራቅ ያሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በጣም ተረብሸዋል። ልክ ነው ከዛም ሊሰማ ይችላል።

በሬክተር ስኬል 4.9 ነው ይሄ ነው ያለው መረጃ።

ተጨማሪ መረጃ እንዳገኘን በግልጽ እንነግራለን። " ብለዋል።
#tkv
@ethio_student_textbook_and_news
@ethio_student_textbook_and_news

🇪🇹 Ethio Students 1 - 12 University 🎓

06 Oct, 18:25


#Breaking_News‼️

በተለያዩ አካባቢዎች የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱ ሸገር ፕረስ ከተለያዩ ምንጮቿ መስማት ችላለች።

ነገሩ የተፈጠረው ከደቂቃዎች በፊት ከምሽቱ 2 ሰዓት በኋላ
አዲስአበባ ብዙ አከባቢ #ቢሾፍቱ #አዳማ ከሚሴ  እንዲሁም አፋር ክልል #አዋሽ7 ጭምር ነው በተመሳሳይ ሰአት ርዕደመሬቱ የተከሰተው።
የካ አባዶ ሰሚት
ቦሌ ቡልቡላ ቤተል
አሸዋ ሜዳ
መገናኛ ሾላ
ካሳንቺስ
ጀሞ ሚካኤል
ቱሉ ድምቱ
ሶማሌ ክልል ሲቲ አፍደምተከስቷል
cmc
ጋርመንት ሳሪስ አቦ
አዲሱ ገበያም እንደዛዉ
እና ዱከም
በአያት ኮንዶምኒየም -ጣፎ
ተክለሃይማኖት ኮንዶሚኒየም
ኮተቤ 02
አዳማ
6ኪሎ
ጀሞ
በሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋሮቢት ከተማ
ደብረብርሃን
ደሴ ባንቧ ውሃ
ሳላይሽ
ምንጃር አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ነው የተሰማው።
#shegerpress
#ethiodigitallibrery
@ethio_student_textbook_and_news
@ethio_student_textbook_and_news