Youth focus @youthfocus Channel on Telegram

Youth focus

@youthfocus


This channal .s created for the benefit of this generation (teenage and youth) to grow in the knowledge of God and to live our life for God and also to help those who are called to focus on their calling. Join us

Samikebe19@gmail

Youth focus (English)

Are you a young person looking to deepen your knowledge of God and live a life aligned with your faith? Look no further than the 'Youth focus' Telegram channel! Created specifically for the benefit of the younger generation, this channel - with the username @youthfocus - is dedicated to helping teenagers and youth grow in their understanding of God and His teachings. Whether you are seeking guidance on how to live a more fulfilling life for God or looking to explore your calling and purpose, this channel is the place for you.nnWith a community of like-minded individuals, 'Youth focus' provides a supportive and encouraging environment for young people to connect, learn, and grow together. Through regular updates, inspirational messages, and shared experiences, members of the channel have the opportunity to engage with each other and be a part of a community striving to live a life of faith and purpose.nnIf you are ready to embark on a journey of spiritual growth and self-discovery, join us on the 'Youth focus' Telegram channel today. Let's support each other as we navigate the challenges of youth and fulfill our calling in life. For more information, you can reach out to us at [email protected]'t miss out on this opportunity to connect with like-minded individuals and deepen your relationship with God. Join 'Youth focus' and start your journey towards a life of faith and purpose today!

Youth focus

22 Nov, 04:39


የ11ኛ ክፍል ተማሪ ናት በምንችለው እናግዛት ካስገባችሁ በሗላ ስክሪን ሾት ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን ጌታ ይባርካችሁ

Youth focus

21 Nov, 11:28


Channel photo removed

Youth focus

17 Nov, 17:27


የዛሬዋን ጨረቃ እዮአትማ🌔

Youth focus

17 Nov, 14:51


"...ምን ማድረግ እንዳለብን አናውቅም አይኖቻችን ግን በአንተ ላይ ናቸው።..."

Youth focus

13 Nov, 08:26


ድብርትን መርጫለሁ!

ድሮ ድሮ ድብርት ሲገጥመን የነበሩን አማራጮቻችን ፊልም (እንደዛሬው left influence ሳይደረግ በፊት ማለቴ ነው) እሱንም ለማየት ወይ መከራያት ወይ ዲሽ መግዛትን ይጠይቃል አልያም ከጓደኞች ጋር ፑል፣ፒኤስ፣ ኳስ ማንበብም አንዱ ከድብርት መውጫ መገዳችን ነበሩ የዛሬን አያርገው እና!

ዛሬ ዛሬ ዛሬ ግን ነገር ሁሉ በእጅ ሆነና እንኳንስ ደብሮን ሊደብረን እንደሆነ ሲመስለን ራሳችንን አቀርቅረን ታፕ ታፕ ማድረጉን እንያያዘዋለን ዘማኑም ሶሻል ሚዲያውም ሰው አቅሉን እንዲስት በእጁ ላይ ካለው መሳሪያ ውጪ መኖር እንደማይችል ለማሳመን ከዛም ውስጥ እንዳይወጣ መጥፎ እና ክፋ አጀንዳዎቻቸውን ባሸበረቀ፣ በተብለጨለጨ ሽፋን ያቀርቡልናል እኛም እየሳቅን፣ ወይ ጉድ ፣ አይዘመን፣ ወይ ትውልድ እያልን ሳንጠነቀቅ እነዛን ኮንተንቶች አእምሯችንን መመገብ ተያይዘነዋል

አሁን ላይ ባገኘነው አጋጣሚ ሁላ ከስልካችን ጋር ሕጋዊ ጋብቻ ያደረግን ያህል በእጆቻችን አጥብቀን ይዘን አብዝተን ጊዜያችንን ከነዚህ መገልገያ እቃዎች ጋር በማጥፋት ጥብቅ የሆነ ወዳጅነት መፍጠርን ቀጥለናል

አንዳች አዚም በላያችን እንደተደረገ ቢገባንም ነገሩ ሱስ ነውና መላቀቅ ዳገት የመውጣት ያህል አዳጋች ሆኖብናል። በዚህ ሁሉ ባርነት ውስጥ ከመያዝ ድብርትን ብንመርጥስ ያኔ መሬት ላይ ሆነን ማሰብ ለሕይወታችን የእውነት ጠቃሚ የሆኑትን ነገሮች ማድረግ እንጀምራለን።

እኔ ድብርትን መርጫለሁ!

መልካም ቀን
ሳሙኤል ከበደ

Youth focus

09 Nov, 14:58


Hi guys subscribe to our YouTube channel we are preparing new content that will be aired in the coming months
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://youtube.com/@youthfocuspodcast3339

Youth focus

09 Nov, 13:56


ለካ ሰው እንደዚህ ውድ ነው! ቆይቶ የሚገባን ነገር ሰውን ማግኘት እንዴት ከባድ እንደሆነ ነው።
ሰው በሞላበት፤ ሰውን ፍለጋ
በ"ወዳጅ" ተከበን፣ወዳጅን ፍለጋ
ፍለጋው አያበቃም ሰው እስኪገኝ

ሳሙኤል ከበደ

Youth focus

08 Nov, 18:00


are you ready?

Youth focus

08 Nov, 12:34


እያነበባችሁ ነው?😊

በኢትሮንስ መተግበሪያ ለአንባቢያን ቀርቧል በ80 ብር ብቻ መተግበሪያውን ከ app store እና play store በማውረድ መጽሐፋን ያግኙ ከታች ያለውን ሊክ በመጠቀም ማውረድ ይቻላል

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.aquila.ethrons

መተግበሪያውን አውርደው መጽሐፋን ያግኙ


ከኢትዮጲያ ውጭ ለምትገኙ አማራጮች አሉ ፍላጎት ካላችሁ ኮሜንት ላይ ጻፋልን እናቀርባለን

                    ሳሙኤል ከበደ

Youth focus

07 Nov, 17:53


የታመነ ነው

በሕይወታችን ለሚሆኑት ነገሮች ሁሉ መልስ የለንም። ብዙ ለምኖችን በየእለት ኑሯችን እናስተናግዳለን፤ ልባችንን አስደንግጦ እንደ እንጨት ድርቅ አርጎ የሚያስቀሩን ብዙ ነገሮች እንዳሉ ነዋሪ ምስክር ነው ግና ብዙ ነገር እየሆነ ማዕበሉ እየተናወጠ፣ ወጀቡም እያጓራ ልባችን ላይ ግን አንድ ድምጽ አለ " እርሱ እኮ ታማኝ ነው፣ እርሱ እኮ እውነተኛ ናው፣ ያለውን ያደርጋል ያለውን ይፈጽማል የሚል እርግጠኝነት በዛ ሁሉ ነገር ውስጥ እያለፍንም ግን ልባችን ይመሰክራል እንዲህም ይለናል
"አባቶቻችን ተማመኑበት ደግሞም አላፈሩም"

ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 10:23
የተስፋውን ቃል የሰጠን ታማኝ ስለ ሆነ አሁን አምነን የምንመሰክረውን ተስፋ ሳናወላውል አጥብቀን እንያዝ።
ሳሙኤል ከበደ

Youth focus

30 Oct, 16:57


የመነመነ

በ21ኛ ክፍለ ዘመን ነዋሪ ዘንድ መንምኖ እጅግ ዘመናዊ የሆነው፣ መንኩሶ በከተማ ሚኖረው መንፈሳዊ ህይወት፤ ተመናምኖ መጥፊያ ላይ የደረሰ ይመስላል ፈልቶ እንደቀዘቀዘ ሻይ ለብታ ውስጥ ገብተናል ምንም አይመስለንም ሁሉም ኖርማል ነው ፈታ በል፣ በሗላ ይደርሳል፣አታካብድ፣ምንችግር አለው? ብቻ ብዙ የዘነጋነው ለብታ ውጦን ከልባችን እየወጣ ያለው እንዳያድግ አንቆ እንደያዘው በእሾኹ መካከል እንደተዘራው ዘር ሆኗል መንፈሳዊ ሕይወታችን

የመነመነው እንዳይቀነጭር፣ በአጭሩ እንዳይቀጭ መፍትሄ ፍለጋ ላይ የተሰማሩ እረኞቻችን ፍለጋው አታካች ሆኖባቸዋል፣ ምክንያቱም ዘመናዊነት ስሩን ሰዶ እንደሚያድግ አረም መልካሙን ዘር እንዳያፈራ እየከለለለው ስለሆነ ማደግ አልቻለም እና እጅ አጣጥፈን እንቀመጥ በፍጹም እስቲ እንንቃ ወጥመድ የሆኑብንን እናስወግድ ዛሬ መንገድ ለማስተካከል ካልተነሳን ሳናውቀው እያሳሳቀ እያዝናና ከገደል ሊከተን እየታገለ ይኸው አለ።
እምቢ ማለትን ሕይወታችንን በጣታችንን ወደላይ እና ወደታች እያልን ብቻ ላለመኖር መወሰን አለብን

ሳሙኤል ከበደ

Youth focus

27 Oct, 14:45


ለራሴ አሳልፈህ አትስጠኝ

እንካ ሕይወቴን እኔ አልፈልገውም! እኔ ጋ ከሆነ አመሳቅለዋለው፣ እመርዘዋለሁ፣ አቆሽሸዋለሁ፣ ያወኩ መስሎኝ ራሴን ቅርቃር ውስጥ እከተዋለሁ ስለዚህ ይህች ጸሎቴን ስማኝ ለራሴ አሳልፈህ አትስጠኝ።

ሳሙኤል ከበደ

Youth focus

24 Oct, 09:12


ስልጠናው የሚጀምረው ቀጣይ ሳምንት አርብ ይሆናል

Youth focus

24 Oct, 02:18


"The proper understanding of everything in life begins with God"

John piper  "desiring God" book

@youthfocus

Youth focus

23 Oct, 17:23


ሰላም የ online leadership ስልጠና በነፃ ቀረበላችሁ መማር ምትፈልጉ

ዕድሜ:- 16-25 ብቻ

ፍላጎት ያለው በየሳምንቱ ትምህርቱ ስለሚኖር ተከታትሎ መማር ይጠይቃል

አርብ ማታ 3:00 ላይ የሚደረግ ይሆናል።

ከስር ባለው ሊንክ ተመዝገቡ

ምዝገባው ዛሬ ማታ ጥቅምት 14/2017  ይጠናቀቃል።

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdP-ifbKoqdoHxN9eWAmzpukth-wnCWB0IMKIhzqMUG0lDwIg/viewform?usp=sf_link

Youth focus

21 Oct, 09:35


ቦልት

ኑሯችን ከአጭር እርቀት ሩጫ የተለየ አይመስለኝም አጭር ርቀት ሩጫ ፋጥነትን የተመረኮዘ የስፓርት አይነት ነው ስለዚህም ገና ከጀማሬው ተፈትልኮ ወጥቶ ፍጻሜው ድረስ በፍጥነት መጓዝን ይጠይቃል።

ገና ጎህ ከመቅደዱ የሚጀመረው የኛ የኑሮ ሽኩቻ ቀኑን ሙሉ ሲጧጧፍ ውሎ ላደለው አመሻሽ ላይ ሲያበቃ ለማረፍ ከጎጆው በታች ይከትማል ለተቀረው ደሞ እስከ እኩለ ለሊት አልያም እስከ ንጋት ይቀጥላል

ስራን በትጋት መስራት እጅግ የሚበረታታ ልምምድ ነው ነገር ግን ማብቂያ የሌለው በአካል በጎጆአችን ተሰይመን በአልጋችን ላይ እየተገላበጥን ልብ እና አእምሯችን ግን አሁንም ትተነው የመጣነውን ስራ እየሰራ ያድራል። mind absent body present እንዲሉ

ዛሬ የእጅ ቦምቦቻችን(ዘመናዊ ስልኮቻችን) ሌላ የእረፍት እና ጥሞና ነጣቂ ለምድ የለበሱ ተኩላዎቻችን ናቸው። ኑሮን ለማሸነፍ የምናደርገው ትግል ሳያንስ በቃኝን የማያውቀው አይን እና ጆሮዋቻችን ልክ እንደ ልጅ እያታለሉ 'ይጠቅማችሁአል"፣"ይበጃችሗል" እያሉ ሚረባውንም ማይረባውንም እንድንመገብ የሚያቀርቡልን "የይዘት ፈጣሪዎቻችን" ተጨምረው ብዙ እንዲያበረክት የተፈጠረው ሰው በጣቶቹ ወደ ላይ እና ወደ ታች ደግሞ መታ መታ እያደረገ ቀና ብሎ ሕይወቱን እንዳይገፋ ከአንገቱ ሰብሮ አስቀርቶታል።

ታዲያ በዚህ አይነት የሩጫ እና ስውር ጦርነት ውስጥ ለምንኖር ፍጡራን ዝምታን ማግኘት ማይታሰብ ከሆነ እንዴት ትኩረት ሳይሰረቅ አላማችንን የሕይወት ጥሪያችንን፣ በጥሞና ሊሰራ የሚገባውን ስራ እንፈጽም?

መፍትሄው እንዲህ ቀላል አይደለም ምክንያቱም ነገሩ ስር የሰደደ አረም በመሆኑ ከጫጫታው ራቅ ማለት፣ ራሳችንን "የዲጅታል ጾም ማስተማር" እንደ መፍትሄ ልንወስዳቸው ብንችልም በመጀመሪያ ግን ቁርጥ የሆነ ውሳኔን መውሰድ ይጀምራል ለሰው ልጅ በየቀኑ ጥቂት ዝምታ ብዙ ውለታ ይውልለታል።የተነጠቀውን የትኩረት በረከት መልሶ ይሰጠዋል

ሳሙኤል ከበደ

Youth focus

19 Oct, 03:15


🙏አንድ ደቂቃችሁን ብቻ🙏

በኢትሮንስ መተግበሪያ ለአንባቢያን ቀርቧል ዋጋው ኪስን የሚጎዳ አደለም 80 ብር ብቻ ነው መተግበሪያውን ከ app store እና play store በማውረድ መጽሐፋን ያገኙታል በቴሌብር ወይም cbe birr መግዛት ትችላላችሁ።

ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መተግበሪያውን ማውረድ ይቻላል

ብትችሉ አገልግሎቱን ለመደገፍ ይህን ማስታወቂያ ለብዙዎች አጋሩልኝ ተባረኩ!

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.aquila.ethrons

መተግበሪያውን አውርደው መጽሐፋን ያግኙ


ከኢትዮጲያ ውጭ ለምትገኙ አማራጮች አሉ ፍላጎት ካላችሁ ኮሜንት ላይ ጻፋልን እናቀርባለን

                    ሳሙኤል ከበደ

Youth focus

18 Oct, 14:38


Cover:-Kingdom sound

Song :-Lily tilahun

@Youthfocus

Youth focus

17 Oct, 20:54


አካሄድን......... ከ እግዚአብሔር ጋር

መጽሐፍ ቅዱስ ምድር ከተፈጠረችበት ወቅት አንስቶ እስከዛሬ ድረስ መልክ፣ ጾታ፣ እድሜ፣ ቁመት እና ቀለም ይለያይ፤ የምንኖርበት ስፍራ፣ባህል እና ቋንቋ ለየቅል ይሁን እንጂ የሰው ልጆችን በሁለት ከፍለን መመልከት እንደምንችል ያስተምረናል የሚከፍላቸውም በምድር ጉዟቸን በምንመርጠው ምርጫዎቻችን በመመርኮዝ ነው፤ ይህ ምርጫ በብርሃን እና ጨለማ፤ በእውነት እና ሃሰት መካከል የሚደረግ ሲሆን  ምንም አይነት አወዛጋቢነት እንዳይኖረው ከፍጥረታችን እውነት እና ሃሰትን መልካሙን እና ክፉን የምንለይበት ማመዛዘኛ በውስጣችን አስቀምጧል.

በአንድነት ውስጥ ያለን ሃይል ተጠቅሞ ሰማይ የሚደርስ ህንጻ ለመገንባት እርምጃ መውሰድ፣ እስከዛሬ የቆሙ፣ በዘመናት መካከል በተካሄዱ ጦርነቶች እና ሽምቅ ውጊያዎች ምክንያት የወደሙ፣ ከአፈር በታች የተቀበሩ ከፍርስራሽ ክምር ስር የሚገኙ፣ በቁፋሮ ለዘመናችን ጠቢባን ተጨማሪ ግርምትን ሊፈጥሩ ከዘመናት አኩኩሉ በኋላ ብቅ ብቅ ያሉ አስደናቂ ስራዎቻቸው እንዲሁም የሂሳብ፣ የኪነ-ህንጻ፣ የስነ-ጽሁፍ ጠበብተኛነታቸው በ21ኛው ክፍለ ዘመን የምንገኝ እኛ እስከዛሬ ከሃገር ሃገር እየተዘዋወርን የእጅ ስራዎቻቸውን ለማየት ረብጣ ገንዘቦችን የምንገብር ያላቸውን ችሎታ እና ግባአት ተጠቅመው ከልብ በትጋት ስለሰሩ ከእነርሱም ዘመን አልፎ ለልጅ ልጅ ልጅ.....ልጆቻቸው የኢኮኖሚ እድገት ዋልታ የሆኑላቸው እነዛ ጠቢባን እውነት እና ሃሰትን መለየት ጠፍቶአቸው ነው ብንል መቼም ትርፉ ትዝብት ነው

በእርግጥ የሚያወዛግቡ ብዙ ምርጫዎች ስለመኖራቸው ሃገር ያወቀው ጸሃይ የሞቀው እውነት ቢሆንም እውነት እና ሃሰት መልካሙን እና ክፉውን መለየት ግን ፈጽሞ አወዛጋቢ አይደለም እውነት እውነት ነውና ፤ ወተትን ከቡና ፤ ነጭን ከጥቁር የመለየት ያህል ግልጽ ነው

የሰው ልጆች ግን ከጥንት ጀምሮ ይህን ሚዛን መጠበቅ አቅቶን ብዙ ስንንገዳገድ ኖረናል መለስ ብለን ታሪክን የኋሊት ስንመለከት "...የሰው ዐመፅ በምድር ላይ የበዛና የልቡም ሐሳብ ዘወትር ወደ ክፋት ብቻ ያዘነበለ መሆኑን ተመለከተ..."ዘፍ 6 ፡5 ልባችን ወደ ዐመፅ እና ክፋት እንደሚፈጥን አምላክ በብዙ ሃዘን ሲናገር እንመለከታለን

አለማችንን ስንመለከትም ዛሬ የዜና አውታሮቻችን፣ የቲክ ቶኩ ሰፈር ሽኩቻ ፣የፌስ ቡኩ ሃሜት እና ስድብ፣ ዲጂታል መኖሪያ መንደራችንን (ስልክ) ያጨናነቀው እውነታ መሆኑን እናውቃለን በዚህም ጥድፊያ እና ውድድር በበዛበት የፍልሚያ ሜዳ ለእውነት ቆሞ መወገን፣ አቅልን ገዝቶ ሚዛንን መጠበቅ እጅግ አዳጋች ነው በእርግጥ ለሁሉም በየዘመናቱ የየራሳቸው ተግዳሮቶች ነበሩባቸው እንዴት በቅድስና፣እግዚአብሔርን በመፍራት፣ እርሱንም በመታመን መኖር ይቻላል የሚያስብሉ ሁኔታዎች ውስጥ ኖረዋል እየኖርንም ነው ዋናው ጥያቄ ግን ያለንበት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን አካሄዳችን ግን ከማን ጋር ነው?

"እሱ ሲሞት ይመጣል" (ማቱሳላ ማለት ትርጓሜው "እሱ ሲሞት ይመጣል" ) ብሎ የጥፋት ውሃን መምጣትን የተነበየ የዘመኑን ክፋት እና አመጽን ርቆ አካሄድን ጠብቆ 365 ዓመታትን የኖረው ሄኖክ "... አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረገ እግዚአብሔር ስለወስደውም አልተገኘም..." ዘፍ 5:23 ስፐርጅን ሲናገር "..አይደለም 365 ዓመታት ለተወሰኑ ስአታት አብረውን ያሉ ሰዎችን ሰልችተን ለመቀየር ሌላ ሰው እንፈልጋለን..." ይህ ሰው ግን ያንን ያህል አመታት 3 ክፍለ ዘመናት አካሄዱን ጠብቆ ለእርሱ ተለይቶ ኖሯል

የምድር ላይ ክፋት እጅግ በመብዛቱ ምርር ያለው አባት ላሜህ ልጁን "እግዚአብሔር በረገማት ምድር ከልፋታችንና ከጉልበታችን ድካም ያሳርፈናል ሲል ኖኅ ብሎ ጠራው"ዘፍ 5:29 ይህ ሰው ክፋት እጅግ በናኘበት፣ ቅድስና በረከስበት ዘመን ውስጥ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ያደረገ በዚህም

"እግዚአብሔርም የሰው ክፉት በምድር ላይ እንደ በዛ፥ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደ ሆነ አየ። እግዚአብሔርም ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፥ በልቡም አዘነ።
እግዚአብሔርም። የፈጠርሁትን ሰው ከምድር ላይ አጠፋለሁ፥ ከሰው እስከ እንስሳ እስከ ተንቀሳቃሽም እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ፤ ስለ ፈጠርኋቸው ተጸጽቼአለሁና አለ።
ኖኅ ግን በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን አገኘ።
....ኖኅም በትውልዱ ጻድቅ ፍጹምም ሰው ነበረ፤ ኖኅ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረገ።" ዘፍ 6:5-9
የተባለለት በአምላክም ዘንድ ሞገስን ያገኘ፣ ለጽድቅ የጨከነ ለእውነት የቆመ ሰው ነው አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ያደረገ

በእድሜው ማምሻ ብርሃንን በቤቱ፣ ድንቅ የሆነ ተአምራትም የተደረገለት አብርሐም ከአባቱ ቤት መውጣት፣ ከወንድሙ ልጅ መለየት፣ በዙሪያው ከከበቡት አሕዛብ ተጠብቆ እየኖሩ አካሄድን ከእግዚአብሔር ጋር ማድረግ ከባድ ውሳኔ ነው ነገር ግን አብርሃም በዘመኑ ሁሉ ማንም አልተገዳደረውም አካሄዱን ከአምላኩ ጋር ስላደረገ እርሱም እንደተናገረው ጋሻ ሆኖለታል

ስለሌሎች አባቶቻችን ስለ ዮሴፍ፣ ሙሴ፣እያሱ፣ ሳሙኤል፣ ዳዊት፣ ጳውሎስ፣ ጢሞቴዎስ ባወራ ጊዜ አይበቃኝም እንጂ ሁሉም አካሄዳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር ያደረጉ የእምነት አባቶቻችን ናቸው ታዲያ እኛ ምን ላይ ነው ያለነው? አካሄዳችንስ ከማ ጋር ነው? በዘመን ተሸነፍን? ወይስ ከከበባ በላይ መራመድችለናል? ሰው እኛን ሲያዩ ኢየሱስን ያያሉ ወይስ ጭልፊቱ ከዶሮዎች ጋር ተመሳስሎ እንደኖረው ተመሳስለን እየኖርን ነው?

መልሶቻችን ተመሳስሎ ኑሮ ከሆነ ዛሬ መንቃት ያሻናል ይህች ጥጽሁፍ ከእንቅልፍ የምንነሳበት አንቂ ደውል ናት ከለብታ ሕይወት ከድንዛዜ ሰፈር የምንኮበልልበት አካሄዳችንንም የምናስተካክልበት

"እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥
እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።"ዕብ 12:1

ሳሙኤል ከበደ

@youthfocus
@youthfocus
@youthfocus

Youth focus

16 Oct, 15:25


I still bless you 😍

By mavric

@youthfocus