ECWC BASIC LABOUR UNION @yesneh Channel on Telegram

ECWC BASIC LABOUR UNION

@yesneh


Basic Labour Union

ECWC BASIC LABOUR UNION (English)

Are you a worker looking to have your voice heard? Look no further than the ECWC Basic Labour Union Telegram channel, managed by user @yesneh. This channel is dedicated to advocating for the rights and well-being of workers from all industries. Whether you are facing unfair working conditions, seeking better pay, or simply want to connect with like-minded individuals, this channel is the perfect place for you. The ECWC Basic Labour Union provides a platform for workers to discuss their concerns, share resources, and support one another in the fight for a fair and just workplace. Join us today and be a part of a strong, united community of workers who are committed to creating positive change in the labor force. Together, we can make a difference and ensure that every worker is treated with the respect and dignity they deserve.

ECWC BASIC LABOUR UNION

26 Dec, 13:34


ለኮርፖሬሽኑ ሴት ሠራተኞች የሥነ-ተዋልዶ ጤና ስልጠና ተሰጠ
-----------
በኢትዮጵያ ኮንስተራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) ቃሊቲ ግቢ ለሚገኙ ሴት ሠራተኞች የአንድ ቀን የሥነ-ተዋልዶ ጤና ስልጠና ተሰጠ፡፡
ስልጠናውን የሰጡት በኮርፖሬሽኑ ክሊኒክ ጠቅላላ ሀኪም ዶ/ር ሁሴን ዑመር፣ ስልጠናው ሴቶች በሥነ-ተዋልዶ ጤና ላይ አዎንታዊ አመለካከት እንዲኖራቸውና በማንኛውም ጊዜ በራሳቸው ላይ ያልተለመዱ ምልክቶችና የጤና ችግሮች ሲከሰቱ ምርመራ፣ ህክምናና ክትትል እንዲያደርጉ ያስችላል ብለዋል፡፡
ስልጠናው ቀጣይነት እንደሚኖረው የተናገሩት በኮርፖሬሽኑ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ፋጠማ ጀማል ስልጠናው አካላዊና ሥነ-ልቦናዊ ጤናቸው የተጠበቀ አምራች ሴት አመራሮችንና ሠራተኞችን ለመፍጠር ያለመ ነው ብለዋል፡፡

ECWC BASIC LABOUR UNION

26 Dec, 13:34


ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በጋራ ለመስራት ተስማሙ
************************

ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በግንባታ ግብዓት አቅርቦት እና በሌሎች መስኮች በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

ስምምነቱን የኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ብሩ ወልዴ እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው ተፈራርመውታል፡፡

የሆልዲንጉ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ብሩ ወልዴ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ግዙፍ የኮንስትራክሽን ተቋም እንደመሆኑ የትብብር ስምምነቱ ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ ለኮርፖሬሽኑ የግንባታ ግብዓትን በተለይም የናሽናል እና የለሚ ሲሚንቶ ምርቶችን በበቂ ሆኔታ የሚያቀርብለት ይሆናል ብለዋል፡፡

ኢ.ኮ.ሥ.ኮ በምህንድስና ዘርፍ፣ በፕሮጀክት ማኔጅመንት እና በኮንስትራክሽን ማኑፋክቸሪንግ ጠቃሚ ልምድ ያለው ተቋም ነው ያሉት አቶ ብሩ ፤ ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ ከትብብሩ ከፍተኛ ተጠቃሚ እንደሚሆን ሙሉ እምነት አለኝ ብለዋል፡፡

ኢንጂነር ዮናስ አያሌው በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ ከዚህ በፊትም ሆልዲንጉ የሚያመርተውን ናሽናል ሲሚንቶ ይጠቀም እንደነበር ገልጸው በቅርቡ በሃገሪቱ ግዙፍ የሆነውን የለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካን ገንብቶ ወደ ሥራ ማስገባቱ የኮንክሪት መንገዶችን በሲሚንቶ ለመስራት የሚያጋጥምን የሲሚንቶ ችግር በእጅጉ እንደሚያቃልለው ጠቁመዋል፡፡

ECWC BASIC LABOUR UNION

26 Dec, 08:23


አስቸኳይ‼️

ECWC BASIC LABOUR UNION

25 Dec, 18:51


የቦርድ አባላት የኮርፖሬሽኑን የሥራ እንቅስቃሴ ጎበኙ
-------------------
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የስራ አመራር ቦርድ አባላት ቃሊቲ የሚገኘውን የኮርፖሬሽኑን ኢንደስትሪ መንደር ጎበኙ፡፡
የኮርፖሬሽኑ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ኢ/ር አይሻ መሀመድ እና ሌሎች የቦርድ አባላት የኮንስትራክሽን ግብዓት ማምረቻን፣ የተተከሉና እየተተከሉ የሚገኙ የግብዓት ማምረቻ ኢንዱስትሪዎችን፣ ዲጅታል የፕሮጀክት ማኔጀመንት ሥርዓቱንና አጠቃላይ የሥራ እቅስቃሴዎችን ጎብኝተዋል፡፡
ጉብኝቱም የኮርፖሬሽኑን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ በመረዳት አስፈላፈጊ ድጋፎችን ለማከናወን ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ECWC BASIC LABOUR UNION

15 Nov, 09:51


Updated!

ECWC BASIC LABOUR UNION

05 Nov, 14:07


አስቸኳይ‼️ ለሁሉም ዘርፍ ሰራተኛ ማህበር አመራሮችና ሰራተኞች በሙሉ
የስም ዝርዝራቸው ከዚህ በታች ለተጠቀሱ ሰራተኞች መረጃው እንዲደርሳቸውና ከተጠቀሰው ቀን በፊት ሪፖርት እንዲያደርጉ ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ እንድታደርጉላቸው ስንጠይቅ ለትብብራችሁ ከወዲሁ በማመስገን ነው።🙏

ECWC BASIC LABOUR UNION

02 Nov, 09:36


ቀን፡ 23/02/2017
በስፖርት ውድድር ለመሳተፍ ለተመዘገባችሁ ሠራተኞች
በ2017 ዓ.ም የኢሠማኮ የበጋ ወራት የስፖርት ውድድር ላይ ኮርፖሬሽኑን ወክላችሁ በእግር ኳስ፣ በመረብ ኳስ፣ በቴብል ቴንስ፣ በሩጫ እንዲሁም በከረንቡላ የስፖርት አይነቶች በሥራ ኃላፊያችሁ ፈቃድ አግኝታችሁ በቀን 22/02/2017 ለምልመላ ሳትመጡ ለቀራችሁ እንዲሁም በአሰልጣኞቻችሁ ተመርጣችሁ ለማጣሪያ የተመረጣችሁ ተጫዋቾች ማክሰኞ ጥቅምት 26/02/2017 ዓ.ም በኮርፖሬሽኑ የጂም አዳራሽ በድጋሚ ምርጫ ስለሚደረግ በእለቱ እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡

ከሠላምታ ጋር

ECWC BASIC LABOUR UNION

26 Oct, 10:01


Subject: Postponement of 3rd Round Future Project Managers Entrance Exam

Dear Lead and Senior Engineers,

I hope this message finds you well. Please be informed that the 3rd round of the Future Project Managers Entrance Exam has been postponed. We will communicate the new exam date as soon as it is confirmed.

We apologize for any inconvenience this may cause.

Best regards,
Argaw Asha (PhD)
ECC-CPDi

ECWC BASIC LABOUR UNION

17 Oct, 07:54


Updated!

ECWC BASIC LABOUR UNION

08 Oct, 07:13


E3ኛ ዙY ስልጠና ተመዝጋቢዎች

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ለተሰማራችሁ ባለሞያዎች፤ ሰራተኞች፤ ተማሪዎች እንዲሁም የትምህርት ተቋማት በሙሉ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ቃሊቲ የሚገኘው ፕሮጀክት ዴቨሎፕመንትና ማኔጅመንት ማዕከል (PROJECT DEVELOPMENT AND MANAGEMENT CENTER) ስር በተቋቋመው ማዕከላዊ ምህንድስና ላቦራቶሪ (Engineering Central Laboratory) ውስጥ በአፈር (Soil test)፤ በኮንስትራክሽን ማቴሪያል (Construction material test)፣ በኮንክሪት (Concrete test) እንዲሁም በአስፓልት (Asphalt test), አዲስ ባስገባነው ዘመናዊ አስፋልት ሚክስ ዲዛይን ሱፐር ፔቭ ጃይራቶሪ ኮምፓክተርን ያካተተ በተለያዩ የኮንስትራክሽን ግብአቶች ላይ ለ3ተኛጊዜ የላቦራቶሪ ቴስት በአጭር (short term training) እና በረጅም ጊዜ (Long term training)
ከ ህዳር 01-2017 ጀምሮ 3ተኛ ዙር ስልጠና ስለምንጀምር ተመዝግባቹ በመጠባበቅ ላይ ያላቹ ከተባለው ቀን ጀምሮ ስልጠናውን ስለምናካሂድ ራሳችሁን እንድታዘጋጁ እናሳውቃለን ፡፡

ለበለጠ መረጃ ፡-
• በአካል መምጣት ለምትፈልጉ ቃሊቲ ማሰልጠኛን አለፍ ብሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ግብአት ማምረቻ ግቢ ውስጥ የሚገኘው PDMC-ECL ቢሮ ቁጥር 03 ወይም በስልክ ቁጥር 0923-620135/ 0923-520333 ወይም +251116675473 ዘወትር በስራ ቀናቶች በመደወል መመዝገብና ወረፋ ማስያዝ ትችላላችሁ፡፡

ECWC BASIC LABOUR UNION

01 Oct, 14:06


For your info and participation‼️

ECWC BASIC LABOUR UNION

22 Sep, 19:04


እንኳን ለወላይታ የዘመን መለወጫ "ጊፋታ" በዓል አደረሳችሁ!

ዮ ዮ ጊፋታ!