✍ባለንበት ዘመን አንድን ሙስሊም ዛሬ ከቁርኣን ምን ያህል ቀርተካል? ምን ያህል አንብበካል? ብለህ ብትጠይቀው
ዛሬ አላነበብኩም ቢዚ ነበርኩ አልቻልኩም ይልሀል።
እሺ በዛሬዋ ቀንክ ዩቱዩብ፣ ቲክቶክ፣ፌስቡክ ምን ያህል ስክሮል አርገሀል? ምን ያህል ጊዜስ ቻት አርገሀል? ምን ያህል ጊዜስ ኮሜንት አንብበካል? ብለህ ብትጠይቅ ስፍር ቁጥር የለውም።
ነገር ግን የአላህን ከላም የአላህን ቁርኣን ለማንበብ ጊዜ የለክም/ሽም ብዙ ወንድምና እህቶችን ለመጨረሻ ጊዜ ቁርኣንን መች ነው ያነበብከው ብለን ብንጠይቃቸው? ጁምዓ ቀን ይላሉ ረመዷን ላይ ሚሉም አይጠፉም ይህ ለኛ ትልቅ አይብ ትልቅ ውርደት ነው።
ያ በሁሉ ነገሩ በረካ ያለበትን የአለማቱን ጌታ ከላም(ንግግር) ቁርኣንን ለማንበብ እንዴት ነው ጊዜ ያጣከው እንዴት⁉️
ተው ነገሩ እንዲህ ከሆነ ልንጠነቀቅ ይገባል ያ ደስታ፣ክብር፣እርካታ፣ሰላም ሚገኝበትን ቁርኣን አኩርፈን ነገ አላነበበኝም፣ አልሰራብኝም ብሎ ቢመሰክርብክስ ?
⚠️አላህ ሆይ ይህን የተከበረውን ቁርኣን የቂያማ ቀን ከሚመሰክርላቸው እንጂ ከሚመሰክርባቸው ባሮችህ መሀል አታድርገን አሚን ያረብ።