በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ሜታ ወረዳ ቁልቢ 01 ቀበሌ ሐምሌ 19 ቀን 2017 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ለሚከበረው የቁልቢ ገብርኤል ንግስ በዓል አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የድሬዳዋ ፖሊስ አስታወቀ።እንደ ድሬዳዋ ከተማ በምስራቅ አጎራባች ሀይሎች መውጫ እና መግቢያ ቦታዎች ላይ አስፈላጊው ስራዎች እየተከናወነ መሆኑ ተገልጿል።
በዓሉ ከመከበሩ በፊት የድሬዳዋ ፖሊስ በትራፊክ መስተንግዶ እና በወንጀል መከላከል ስራ ላይ የበዓል አከባበሩ ፍፁም ሰላማዊ እና ከትራፊክ አደጋ የፀዳ ለማድረግ እንግዶች በመቀበል ላይ ነን ሲሉ የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የሚዲያ እና ገጽታ ግንባታ ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ዳግም ተፈራ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።
በዓሉን ለማክበር ለሚመጡ እንግዶች በከተማው ውስጥ ያሉ ፖሊስ ጣቢያዎች፣የትራፊክ ክፍሎች ስልክ ቁጥር የያዘ በራሪ ወረቀቶች እና ስቲከሮች በመበተን ህብረተሰቡ ማንኛውም ዓይነት ጥቆማ መስጠት ሲፈልግ ለፖሊስ ጥቆማ መስጠት እንዲችል መመቻቸቱ ተገልጿል።በተጨማሪም ምዕመናኑ በበዓሉ ወቅት የኪስ ቦርሳቸውን ፣ ሞባይል ስልካቸውን እና ሌሎች ንብረታቸውን እንዳይሰረቁ እና እንዳይጥሉ በጥንቃቄ እንዲይዙ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
ከዚህ ባለፈ ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያዎች ፣ ዓቃቤ ህግ እና ጊዜያዊ ፍርድ ቤት የተቋቋመ ሲሆን ተጠርጣሪ ወንጀለኞች ሲያዙ የምዕመናን መጉላላት እንዳይኖር የምርመራ መዝገብ ተጣርቶ በጊዜያዊ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ በማድረግ አፋጣኝ የፍርድ ሂደቱን መሠረት ውሳኔ ይሰጣል ተብሏል።
ወንጀል ፈፃሚዎችን ወይም ለመፈፀም የተዘጋጁ ተጠርጣሪዎች ሲያጋጥሙ ምዕመናኑ በአቅራቢያቸው ለሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ጥቆማ መስጠት እንዳለባቸው እና በአጭር የስልክ መስመር 620 በመደወል ማሳወቅ ይችላል ሲሉ ኢንስፔክተር ዳግም ተፈራ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
በሳምራዊት ስዩም
Join: @yegnatikuret