የፍቅር ጋጋታ 💚❤️🌕 @yefikirgagata Channel on Telegram

የፍቅር ጋጋታ 💚❤️🌕

@yefikirgagata


ቴሌግራምን ለመታወቅ ሳይሆን ያወቅነውን ለማሳወቅ እንጠቀም፡፡ ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ ደግሞ ፍፁም በጎነት ነው፡፡

በምድር ላይ የምናደርጋቸው መልካም ነገሮች ሁሉ በሰማይ ላይ የዘላለም ደመወዝ ሆነው ይከፈሉናል፡፡ ሁሌም ቢሆን ከክፋት ይልቅ በጎ በጎውን ነገር እናስብ መልካምነት ለራስ ነው፡፡

ቻናላችንን Join ያድርጉ
https://t.me/YefikirGagata

የፍቅር ጋጋታ 💚❤️🌕 (Amharic)

የፍቅር ጋጋታ በፍቅር ሰማይና ምስራቅ ማህበረሰብ ማለትም እንዲሆን የሚወቁ ታሪኮችን የሚያገዙትን መልካም ኮንትንታንን እንወቅሳለን፡፡ በተለያዩ የማለዳ ምስራቅ እና ታፈናኝ ታሪኮች አራትን ሜሪዎችን እናሳይ መርሀዊ ዳርቶችን እንወቅሳለን፡፡ ከዚህ በኋላ ትእዛዝ እና ፍፁም መረጃዎችን በእንቅስቃሴ ወደቀረረ ከመሆኑ በፊት ያቀርባል፡፡ ቻናላችንን በማለት የውስጥ ገጽ ለመሄድ ያንብቡ የፍቅር ጋጋታ ቶሮንቴንት ለመቀነስ እና ለሌላቸው ተጨማሪ መለዋወጥ ለማስቻለል ይህንን ለማወቅ ፈጣን በብርት ሲለው ሶስት ከክፋት ያመለከታል፡፡

የፍቅር ጋጋታ 💚❤️🌕

19 Aug, 11:14


♻️ 100 ብር ዛሬም በድጋሚ ተቀብዬለሁ
Hule pay Bot Withdrawal Proof  Video ነው ሙሉውን አዩት 💯👆👆

አልረፈደም እናንተም መስራት ትችላላቹ ይሄንን Bot ተጠቅማቹ ፍጠኑ  🔥
              👇👇👇👇
                 https://t.me/hulepay_official_bot?start=r02243510900

የፍቅር ጋጋታ 💚❤️🌕

21 Nov, 13:24


✍️ የወጣቱ አስተሳሰብ ሲቀየር አኗኗሩ ለህይወት እና ለስኬት ያለው አመለካከት ሲቀየር በደረጃ የሆነን እድገት በሂደት በሆነ ለውጥ ያምናል ያኔ ....ከየትም አምጭው ዱቄቱን ፍጭው ሳይሆን መንገዱን የሚያውቅ ከስህተቱ የሚማር ትልቅ የሚያስብ በትንሽ ለመጀመር የማያፍር ትውልድ ይበዛል።
#ምርጥ_መጣጥፎች👇👇👇
https://t.me/YefikirGagata
https://t.me/YefikirGagata

የፍቅር ጋጋታ 💚❤️🌕

19 Mar, 15:57


ጎዶሎዋ ቀን

ምሽት ይመስለኛል እለቱ ቅዳሜ
እኔና አንቺን ይዛ ያዋየችን ጳግሜ።
የወርም ጎዶሎ ከጎዶሎም መካን
ፍሬ ያላፈራች የነጠፈች እርቃን።
የጊዜ ሰካራም ደንበርባራ በቅሎ
መጨበጥ አቅቷት የቆመች የኋሊት ቅርፅ አልባ አሎሎ።

ያ ናት ያቺ ማታ...........

እዮብ የረገማት ከቀናት ለይቶ
ከአምላክ ተቆጥቶ
ከራሱ ተጣልቶ
ልጁን ቤቱን አጥቶ
ንብረት ጤናዉ ጠፍቶ
ምሬትን የማያዉቅ አንደበቱ ከፍቶ
ትረገም ያላት ቀን ከቀናት ለይቶ።

አዎ ይግረምሽ ባይገርምሽ
እኔ ምጠላት ቀን ያቺ ናት አለምሽ።

ጨለማዬን መቅረዝ
ማጣቴን ለመዘዝ
ባዶነቴን ገልጠሽ
ዉስጤን አንጠፍጥፈሽ
ልቤን ወዲ.....ያ ጥለሽ
ጭልጭል ያለዉን ብርሀኔን ገፈሽ።

ደንገዝጋዛ ቤቴን
መፅናት የተሳነዉ ምርግ መሰረቴን

እያንገጫገጭሽዉ እያወዛወሽዉ
እያንከላወሽዉ እያንገዳገድሽዉ

ትርጉም ባጣ ስላቅ ሆዴን እያጮህሽዉ
ፍቅራችንን ናድሽዉ።
ህ...............
ባይደንቅም ይድነቅሽ

ጣዖቱ ግዑዝሽ አሳሳች ዉበትሽ
ሶምሶሙ አቋሜን እያንደረደረ
ደሊላ ልብሽ ላይ ሄዶ ተዘረረ።

ዳሩ ምን ያደርጋል
ድመት ብትመነኩስ
መሆኗ ልኩስኩስ አይቀርም ሆነና
አመለኛዉ ልብሽ ተነሳ እንደገና።

በጥርስሽ መሳቅሽ
በአይንሽ መግደልሽ
በአለንጋ ጣቶችሽ እኔን መዳበስሽ
በዘንፋላዉ ፀጉርሽ አይኔን መጋረድሽ
እሱም ነዉ ጥፋትሽ😳

ባትይም ልንገርሽ..........
አፍሽ ባያወጣም መዉደድሽን አፍርጦ
ይታየኝ ነበረ ፍቅርሽ ከአይኔ ፈጦ።

ባታምኚም አዉቃለሁ እሱ ነዉ ጦሰኛ
አንከላዉሶ አምጥቶ ያረገኝ ብቸኛ።

ተይኝ በቃ ተይኝ ከራሴ አታጣዪኝ
በለመደዉ እግርሽ ደርሰሽ አትከጅዪኝ።

ባታዉቂም ማወቄን ለኔ እንደማቶኚ
ጎዶሎ ቀኔ ነሽ በይ ከኔ ተሸኚ።

በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ


,,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••

https://t.me/YefikirGagata
━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━

የፍቅር ጋጋታ 💚❤️🌕

18 Mar, 16:26


👌ምርጥ ባህሪያማ ማንነት
------------------------------------------
◈ ጥቂት አዉራ፡፡ ስታወራ ቀስ ብትል መልካም ነዉ

◈ አንድ ቦታ ላይ ብዙ አትታይ፡፡ ስራህ ላይ አተኩር
ተግባቢና የተረጋጋ ሰዉ ሁን

◈ ማንም ትክክል ነህ እንዲልህ አትጠብቅ፡፡ ማንም ደጋፊህ እንዲሆን አትጎትጉት

◈ ስላለህ ነገር ደጋግመህ እየተናገርክ የመጎረር ስሜትን አስወግድ

◈ ምርጥ አዳማጭና መፍትሄ አምጪ ሁን

◈ አደርገዋለሁ ያልከዉን ነገር አድርገዉ

◈ በጣም ደስ ሲልህ ወይም በጣም ስታዝን ዉሳኔ አትወስን

◈ ሴቶችን በአስተሳሰባቸዉ መዝናቸዉ

◈ የግል ጉዳይህን ላገኘኸዉ ሰዉ አትናገር

◈ ሰዉ ስላንተ የፈለገዉን ቢያስብ ከማንነትህ ጋር አታገናኘዉ

◈ ሃላፊነት መዉሰድን አትፍራ

◈ ማንንም ለመጉዳት ብለህ ጉድጓድ ከመቆፈርም ይሁን ከማስቆፈር ራስህን አሽሽ

◈ የጎዱህንና ‘ምንም የለዉም!’ ብለዉ የራቁህን ሰዎች ስኬታማ በመሆን አሳያቸዉ

◈ ሃሳብህን ለማሳመን የሰዎችን ማንነት አትጉዳ፡፡ ትክክክል ብትሆን እንኳን ካመኑ ይመኑህ ካላመኑህ ጊዜዉ ያሳምናቸዋል!!

ወድሞቼ እህቶቼ ሼር አድርጉት👏

https://t.me/YefikirGagata

የፍቅር ጋጋታ 💚❤️🌕

15 Mar, 15:27


ለብቻዬ በቃኝ
ደስታ ቢኖር ትንሽ🙄🥰
ይጎላል ፍቅር......😩
ያለ አጋር እንዴት ይሆናል 😝😍🥰
በቃኝ ብዬዋለሁ🤨😙😚
ለብቻ ጉዙዬን _

ለብዬ በቃኝ ለብቻዬ(2)🙅🏻‍♀🙅🏻‍♀😍🦋

https://t.me/YefikirGagata

የፍቅር ጋጋታ 💚❤️🌕

15 Mar, 15:27


ከመቀመጥ በላይ
የመቆም ረፍቱ
ከመምጣት ይልቃል
የመሄድ ጥልቀቱ
መቅረት ለትዝታ
ለደግሞ መናፈቅ
በማጣት ተላወሶ
ማግኘትን መመኘት
መመኘት
መመኘት
መባከን
መብከንከን
የነበረን ሁሉ
የተኖረን ሁሉ
እንደነበር መርሳት
መቃጠል በምኞት
ባለማግኘት እሳት
.
ማግኘት በረዶ ነው
ቁርጡ ይታወቃል
ማጣትን የሚያህል
ፀሀይን ያጠልቃል
የህይወት ጥፍጥና
የመኖር ስሪቱ
ጠብቆ ጠብቆ
በምኞት መቅረቱ


...ሄለን ፋንታሁን


,,,,,,,,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••

https://t.me/YefikirGagata

የፍቅር ጋጋታ 💚❤️🌕

15 Mar, 15:26


ለምን ብዬ ልጠይቅሽ አልችልም .....እንኳን አንቺን ልጠይቅ የራሴም ልብ ለሚጠይቀኝ ጥያቄ መመለስ አልቻልኩም.........ሳስበው እያበድኩ ነው ወይ ደሞ እየዳንኩ.... መዳን ግን እንዲ አይመስለኝም ...አይምሮዬ ለሚጠይቀኝ ጥያቄ መልስ መመለስ ከብዶኛል... ልቤም አትስማው እያለ ይታገለኛል ..ማነው ትክክል አይምሮዬ ወይስ ልቤ .....አላውቅም 🤷‍♂️...ሁለቱም የኔው ናቸው ምንም ማረግ አልችልም በቃ ....
ግን እንዲህ መሆን ያስጠላል😔😔😫

https://t.me/YefikirGagata

የፍቅር ጋጋታ 💚❤️🌕

15 Mar, 15:25


ዓለማችን ላይ ብዙ እውቀት አለ፣ እና ግን ሁሉን ማወቅ አትችልም፣ ከምትችለውም ደግሞ ካልመረጥክ የሚተርፍህ ውዝግብና እብደት ነው።

ከዓላማህ ጋር የሚሔደውን መርጠህ ከቀጠልክ አንተ የዓላማህ ራስ ከመሆን ማንም ሊያስቆምህ አይችልም። ምክንያቱ የሚያበረታ ሀይል የሚሆንህን እውቀት ይዘሀል።

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
https://t.me/YefikirGagata
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝

የፍቅር ጋጋታ 💚❤️🌕

15 Mar, 15:25


ጎማ መቀየር እየቻልክ መኪናህን አትጣል!!

የመኪናህ ጎማ ተንፍሶ አላስኬድ ቢልህ ጎማውን ትቀይራለህ እንጂ መኪና አትጥለውም ፡፡ ወዳጄ አንድ እውነት ልመስክርልህ ፡፡ ያሰብከው ካልተሳካ ሀሳብህን ቀይር እንጂ ህይወትህን አታጥፋ ፡፡ ፍቅርህ መሀል ችግር ቢፈጠር ፍቅርህን ጠግን እንጂ ቤትህን ትተህ አትሒድ ፡፡ ህይወት ሁሌም ሙሉ አትሆንም ፡፡ የጎደለህን እየሞላህ ቀጥል ፡፡ በፍፁም አትሸነፍ አለምን እልህ የተጋባ ነው የሚጥላት ህይወት የስኬት ገበያ ናት በብልጠት ተገበያይ ፡፡
https://t.me/YefikirGagata

የፍቅር ጋጋታ 💚❤️🌕

22 Feb, 16:40


የፍቅር ጋጋታ 💚❤️🌕 pinned Deleted message

የፍቅር ጋጋታ 💚❤️🌕

14 Feb, 16:14


📚📚🗞🗞 ለምርጥ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ። 👇👇👇https://t.me/YefikirGagata
https://t.me/YefikirGagata

የፍቅር ጋጋታ 💚❤️🌕

14 Feb, 16:00


📚📚🗞🗞 ለምርጥ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ። 👇👇👇https://t.me/YefikirGagata
https://t.me/YefikirGagata

የፍቅር ጋጋታ 💚❤️🌕

14 Feb, 15:59


ወጣቱ የአንድን አርሶ አደር ቆንጆ ልጃገረድ ማግባት ፈልጓል ፡፡ እናም ወደ አባቷ ቀርቦ ፍቃዳቸው ይሆን ዘንድ ጥያቄውን አቀረበ ፡፡ አባት ልጁን ከእግር ጥፍሩ እስከ እራስ ፀጉሩ እየተመለከቱት አንድ ተግባር ሰጡት ፡፡ “ናስኪ ልጄ! ሂድና እዛ እመስኩ መሐል ቁምና እነዚህን ሦስት ኮርማዎች ተራበተራ እለቃቸዋለሁ ፡፡

ከሦስቱ ኮርማ ያንደኛውን ኮርማ ጅራት የያዝክ እንደሁ ልጄን እድርልሃለሁ ፡፡ ታገባታለህ” አሉት ፡፡ ወጣቱ በታዘዘው መሰረት ከግጦሹ ሜዳ ሁኖ መጠባበቅ ጀመረ ፡፡ የኮርማዎቹ በረት እንደተከፈተ ትልቅ ኮርማ ከዚህ በፊት አይቶት የማያውቅ ሻኛ የተሸከመ ኮርማ ሲመጣ ተመለከተው ፡፡ ወጣቱ “ይሄስ ይለፈኝ የቀጣዩን ኮርማ እይዘዋለሁ” ብሎ ወሰነና አስተላለፈው ፡፡ ሁለተኛው ሲመጣ የሚያየውን ማመን አልቻለም ፡፡

🔑ከመጀመሪያው በላቀ ግዙፍ ሆነበት ፡፡ “የሚቀጥለው ኮርማ (ሦስተኛው ማለቱ ነው ፡፡) የፈለገውን ይሁን እሱን እይዘዋለሁ” በማለት ይሄኛውን ወደ ጥግ በመሸሽ አሳለፈው ፡፡ ለሦስተኛ ጊዜ የኮርማዎች በር ሲከፈት ወጣቱ ፈገግ አለ ፡፡ ከበረቱ የወጣው ኮርማ ደከም ያለ ነበር ፡፡ ወጣቱ የኮርማውን ጅራት ለመያዝ እንዲያመቸው አቋቋሙኝ አስተካክሎ ጠበቀው ፡፡ ኮርማው እሱጋ ሲደርስ ዘሎ ወጣበት ነገር ግን የኮርማውን ጅራት መያዝ አልቻለም ፡፡ ምክንያቱም ኮርማው ጅራተ ቆራጣ ስለነበር ሙሉ ጅራት አልነበረውምና ፡፡ ሕይወት በመልካም አጋጣሚዎች (Opportunities) የተሞላች ናት ፡፡

አንዳንዱን መልካም አጋጣሚ ለመጠቀም ቀላል ነው ፡፡ ሌላኛው ደግሞ አስቸጋሪ ነው ፡፡ ነገር ግን የተሻለ ይገኛል በማለት እጅ የገባን መልካም እድል ማሳለፍ የማይመጣን እንደመጠበቅ ይቆጠራል ፡፡ ምክንያቱም ያመለጠ መልካም አጋጣሚ መልሶ እራሱ አይመጣም ፡፡ ይህ ማለት ግን ሌላ መልካም አጋጣሚ የለም ማለት አይደለም ፡፡ የከፋ ወይም የተሻለ ይኖራል ፤ ይመጣልም ፡፡ እራሱ የበፊቱ ግን አይመጣም ፡፡

አንዴ ካመለጠ መልሶ እንደማይገኝ ሲናገሩ መልካም አጋጣሚ ቁንጮ ነው ይሉታል ፡፡ ቁንጮ ልጆች በአብዛኛው በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ፊት ለፊት ላይ ቁጢጥ አድርገው የሚተውት የፀጉር አቆራረጥ ነው ፡፡ መልካም አጋጣሚም እንደመጣ ፊት ለፊት ካልይዙት ዘወር ካለ መላጣ ስለሆነ መያዝ አይቻልም ፡፡ ስለሆነም ሁሌም ከፊትህ የመጣን መልካም አጋጣሚ ይዋል ይድር ሳትል ተጠቀምበት ነው መልዕክቱ ፡፡

ምንጭ፡ NEVER MISS FIRST OPPORTUNITY !!

የፍቅር ጋጋታ 💚❤️🌕

14 Feb, 15:59


ሁሉም ባንተ ይብቃ!

አንዳንዴ የጭካኔን ጥግ መግለፅ እንደሚሳነን ሁሉ የበጎነትን፣ የመልካምነትን ጥግ መግለፅ ፣ ማመን ይከብደናል ። አለማችን አያሌ ውብ ፣ ደግ ፣ እጅጉን መልካም የሚባሉ ብሎም የመኖር ትርጉምና ህልማቸው ለሰው መኖር ፣ መልካም ሆኖ መገኘት የሆነላቸው ሰዎችን አሳይታናለች ።

አዎ! ጀግናዬ..! ያንተም መልካምነት ይሄን ያክል ጥግ ባይደርስም በመጠኑ መሆን ይችላል፣ በልክ መደረግ ይችላል ።
አዎ! አንተ ባለፍክበት ችግር ማንም አይለፍ ፤
አንተ ያየሀውን ስቃይ ማንም አይይ ፤
አንተ በተጎዳህበት ማንም አይጎዳ ፤
አዎ! ሁሉም ባንተ ይብቃ ፤
አንተ ባማረርከው ማንም አያማርር ፤

ዛሬ የተሻለ ነገር መፍጠር ጀምር ፣ ትውልዱን ታደገው ፣ መልካም ፍሬን ዝራ ፣ ለነገ ጥላ የሚሆን ዛፍ ትከል ፤ ችግር ላይ ሌላ ችግር አትጨምር ፤ መልካሙን የምታይ ፣ በጎውን የምታደርግ ፤ የእራስ ድንበር ያለህ ሰው ሁን ።

አዎ! ጀግናዬ..! ችግሩን እያየህ ዝም ካልክ ችግሩ አንተ ነህ ። ቀላል ገለፃ ነው ። ዛሬ ብትተወው ነገም እንደሚከተልህ ታውቀዋልህ ፣ አንተ ስትሸሸው እርሱ ይከተልሃል ፣ አንተ ብትገፋው እርሱ ባለው ሀይል ይጣበቅብሃል ። ይሔንን ክፋቱን እያየህ እንዴት ጥለሀው ትሸሻለህ ?
እንዴትስ ለሌላ ሰው አሳልፈህ ትሰጠዋለህ ?

አዎ! ባንተ የመጣውን በእራስህ ተወጣ ፤ ተጋፈጠው ፤ ምክንያቶችህን አቆያቸው ። ዛሬ የሸሸሀው ቀላል ፈተና ነገ አስር እጥፍ ይሆንብሃል ፤ ካንተም አልፎ በዙሪያህ ያሉትን እስከ መጉዳት ይደርሳል ።

አዎ! የገጠሙህን ችግሮች ሁሉ በተቻለህ መንገድ እየቀረፍክ እለፍ ፤ ያጋጠመህን ውጣውረድ አስተካክል ፤ ያልተመቸህን መንገድ ከመቀየር እንዲመች ማድረጉ ላይ አተኩር ፣ አንተ ብትቸገርበትም ሌሎች በምቾት እንዲጓዙበት አድርግ ። ትናንት ፣ ዛሬ ፣ ነገ ህይወት ያቀበለችህን አልገመትክም ፣ የምታቀብልህን አታውቀውም ፣ ስትዘጋጅ ግን ምላሾችህን ታውቃለህ ። ታሪክ ሆኖ አለፏል የምትለው ፣ የምትተርከው ፣ በኩራት የምታወራው የአሸናፊነት ፣ የጀብደኝነት ታሪክ ይኖርሃል ።

አዎ! ለእራስህ መልካም ሁን ፤ ለመልካምነትም ምክንያት አትፈልግ ሰውነትህ ይበቃሃል ።

📚📚🗞🗞 ለምርጥ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ። 👇👇👇https://t.me/YefikirGagata
https://t.me/YefikirGagata

የፍቅር ጋጋታ 💚❤️🌕

14 Feb, 15:59


ምንጊዜም ልንረሳው የማይገባው ቁምነገር ቢኖር ሁሌም ቢሆን የውስጣችንን ሁኔታ የምናውቀው እኛው ራሳችን ነን ፡፡ ሰው ከላይ አይቶ ይፈርዳል ፡፡ ጥሩም ሆነ መጥፎ መወራቱ እንደው አይቀርም ፡፡ በሰው አፍ ልክ የእኛም አመለካከትና ለራሳችን ያለን ግምት የሚቀያየር ከሆነ የእኛን ቅን መንገድ እየሳትን ፣ አለን ያልነውን ጥሩ ማንነታችንን እያፈረስን ነው ፡፡ ይህም በይሉኝታ ውስጥ ታስረን ራሳችንን ወደ ማጣት ይመራናል ፡፡ ስለዚህ ለራሳችን መቆም እንዲቻለን እውነታን ይዞ መጓዝና ራስን ማወቅ ፍቱን መፍትሄ ነው ፡፡

👉የውስጥን እውነታ ይዞ ህይወትን ሚዛናዊ ማድረግ መንገዳችን የተቃና እንዲሆን አስተዋጽኦ አለው ፡፡ ዋናው ነገር በትክክለኛ የህይወት መንገድ ላይ መሆናችንን ማረጋገጥ ፣ ከየት እንደተነሳን አለመርሳትና መድረሻችንን ማወቅ ነው ፡፡

📚📚🗞🗞 ለምርጥ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ። 👇👇👇https://t.me/YefikirGagata
https://t.me/YefikirGagata

የፍቅር ጋጋታ 💚❤️🌕

14 Feb, 15:59


የህይወት ምልከታ

በአንድ ቀዝቃዛና ብርዳማ የክረምት ወቅት ሙቀት ለጋሽ ልብሶችን ደራርቦ በመልበስ በመንገድ ላይ የሚሄድ ሰው
#ሙላህ ነስሩዲን አንዲት ሸሚዝ ብቻ ለብሶ ሲሄድ ተመልክቶ በሁኔታው ስለተደነቀ እንዲህ ሲል ጠየቀው ፦

<<ሙላህ! እኔ ይሄን ሁሉ ልብስ ደራርቤ ለብሼ እንኳን ብርዱን አልቻልኩም ፡፡ አንተ ግን በዚህች ሸሚዝ ብቻ ጎዳናው ላይ ስትሄድ ትንሽ እንኳን የመብረድ ስሜት አይታይብህም ? >> ሲል ጠየቀው

ናስሩዲንም ፦ <<አየህ! አንተ ብዙ ልብሶች አሉህ ። እናም ብርድን የመቋቋም ብቃትህ ተወስዷል ። እኔ ደግሞ ከዚህች ሸሚዝ ሌላ የምለብሰው የለኝምና የብርድ ስሜት ቅንጦት ሆኖ ከውስጤ ጠፍቷል >> በማለት መንገዱን ቀጠለ ።

ለዚህ ነው እውነት ለሁላችንም አንድ መስላ ብትታየንም እንደ ሕይወት ምልከታችንና እምነታች ትርጉሟ የተለያየ ሆኗል ።
#ከጲላጦስ

የፍቅር ጋጋታ 💚❤️🌕

14 Feb, 15:59


#_ያንተ_ቦታ_ከፍታው_ነው

ዋናው
#መውደቅህ አይደለም ወድቀህ #መነሳትህ ነው ። #ማጎንበስህ አይደለም መልሰህ #ቀና ማለትህ ነው ። #ማዘንህ አይደለም እንደገና #መሳቅህ ነው ። ወዳጄ አትርሳ #የዋንጫ ቡድንም አንዳንዴ #ይሸነፋል#ለጊዜው ነው እንጂ ያንተ ቦታ #ከፍታው ነው ። መልካም ውሎን ተመኘሁላችሁ
═══════❁✿❁ ═══════
📚📚🗞🗞 ለምርጥ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ። 👇👇👇
https://t.me/YefikirGagata
https://t.me/YefikirGagata

የፍቅር ጋጋታ 💚❤️🌕

14 Feb, 15:59


ማንኛውም ነገር እንደማይቻል የሚነግርህ ያልተሳካላቸው ሰዎች መሆናቸውን አስታውስ ። እንዲህ ያሉ ሰዎች አስተያየት መርዝ ነው ። ስለዚህ አስተሳሰባቸው ትንሽ ከሆነና የአንተን ትልቅ ሀሳብ ለማቀጨጭ ከሚቃጡ ሰዎች እራስህን አርቅ ። ሰዎችን ማመስገን ልመድ ፦ ሰዎች ላደረጉልህ ነገር ምስጋና ማድረግን ህግህ አድርገው ። ማንኛውም ሰው ቢሆን የተጠቀምክበት መስሎ እንዳይሰማው ተጠንቀቅ ።

ምስጋናህን በልባዊ ፈገግታ አጅበው። ፈገግታ ለሌሎች ያለህን መልካም አመለካከት ይገልፃል። " አንተ ባትኖር ምን ልንሰራ እንችል እንደነበር ግን ይገባኛል " የሚል ሙገሳንም ተጠቀም ። ይህ የበለጠ እንዲሰሩ ያበረታታቸዋል ።

Dr.David schwartz the magic of thinking big (በትልቁ የማሰብ ሀይል - ሱራፌል ግርማ)

📚📚🗞🗞 ለምርጥ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ። 👇👇👇https://t.me/YefikirGagata
https://t.me/YefikirGagata

የፍቅር ጋጋታ 💚❤️🌕

14 Feb, 15:59


"ማንበብ ሙሉ ሰው አያደርግም" ያነበብነውን ተግባር ላይ ህይወታችን ላይ ስናመጣው ስንተገብረው ነው ሙሉ የሚያደርገን ።

የፍቅር ጋጋታ 💚❤️🌕

14 Feb, 15:59


ነገ ሌላ ቀን ነው

ለጠላቶችክ ደስታ ብለክ ሳይሆን መሸነፍክ ለሚያስከፋቸው ሰዎች ብለክ ጠንካራ ሁን

ዛሬ ውስጥህ ሰላም አጥቶ መኖር አስጠልቶካል ? ተስፋ እንዳትቆርጥ ነገ ሌላ ቀን ነው ።

ዛሬ ሰዎች ከሰው ክብር ዝቅ አርገውክ በሚጠሉክ ሰዎች ተከበሀል ? የሚወዱክ ይመጣሉ ፤ ነገ ሌላ ቀን ነው ።

ዛሬ ስንት የደከምክበት ቢዝነስ ብልሽትሽቱ ወጥቷል ? ቀና በልና አማራጮችን ተመልከት ፤ ነገ ሌላ ቀን ነው ።

ዛሬ በትዕምርትህ የተዘጋጀከውንና የደከምክበትን ያህል ውጤት አላመጣህም ? ትምርት በቃኝ እንዳትል ፤ ነገ ሌላ ቀን ነው ።

የተሸነፍከው የወደክ ፣ የተሰበርክ ቀን አይደለም ። የተሸነፍከው በወደክበት ለመቅረት አምነክ የተቀመጥክና ዳግም መሞከር ያቆምክ ዕለት ነው ።

በል ተነስ የእኔ አንበሳ ፤ ይቺ ምድር ለተሸናፊ ቦታ የላትምና "ለችግሮችህ በሙሉ ትልቅ ችግር ሁንባቸው ።"

═══════❁✿❁ ═══════
📚📚🗞🗞 ለምርጥ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ። 👇👇👇https://t.me/YefikirGagata
https://t.me/YefikirGagata