- የጥላቻ ንግግሮች ያለ ሃይ ባይ ሲሰራጩ የህግ አካላት በዝምታ መመልከት የተለመደ በመሆኑ ህግ በተግባር እንዳይተረጎም ድርጊቱም እንዲስፋፋ አድርጓልና መንግስት ህግን የማስከበር አቅሙና ቁርጠኝኝነቱ ምን ያህል ነዉ?
-ዜጎች እየሞቱ እተፈናቀሉ እና እስር ላይ ይገኛሉ የፍርድ ሂደቱም እየተጓተተ ነው?
- የኢኮኖሚ ዕድገት የተዘረዘሩ ችግሮች ባሉበት እና የፓርቲው አባላት እርስ በእርሳቸው በማይተማመኑበት ሁኔታ እንዴት ሊሳካ ይችላል ? እነዚህን ለማረም ምን አይነት መፍትሄስ አስበዋል?
-ሀገር እና መንግስቶን እንዴት ሊታደጉ አስበዋል?
-በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ያለዉን የጥታ ችግር በንግግር /ድርድር ለመፍታት ለምን አልተቻለም?
-የ12ኛ ክፍል ፈተናውን ያላላፉ ተማሪዎች እጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል?
-የትምህርት ጥራቱን አስጠብቀን የተማሪዎችን ውጤታማነት ለማሳደግ እንደ መንግስት ምን ታስቧል? ከማንስ ምን ይጠበቃል?
-መንግስት በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ያሉ ግጭቶችን ለመቅረፍ በሰላም እንዲቋጭ ምን እየሰራ ነዉ?
-አለመግባባቶች ወደ ግጭት ከመግባታቸዉ በፊት ከባለፈዉ በተሻለ ምን ለመስራር አቅዷል?
[ዳጉ ጆርናል]Y