በዚች ምድር ሳለሁ እስትንፋስ ነሸ ለኔ፣
ሁሉን የማይብሽ ብርሃኔም ነሸ ለአይኔ።
አዎን እወደሻለሁ ከሁሉም አብልጬ፣
አንድ አንቺን ዘላለም በደስታ መርጬ።
እኔ ያንቺ ሆኛለሁ ገና ያኔ ሳገኝሽ፣
የልቤን አውጥቼ መውደዴን ሰነግርሽ።
እያደር ቀን ሲሄድ ፍቅሬ መጠን አጣ፣
ላንቺ ያለኝ መውደድ ይፋ ሆኖጣ።
ሰው ይበልጥ ሲቀርብሸ እኔ አፈራለሁ፣
ድንገት እንዳትርቂኝ ሁሌ እጨነቃለሁ።
እኔንጀ የኔ አለሜ የማጣሸ መሰለኝ፣
አጠገቤ ሆነሸ ሩቅ የሆንሸ ተሰማኝ።
ልቤ ምነው ፈራ ከወትሮው ተለየ፣
አይኔም ዕንባ ቀሮት እየሳሳሸ አየ።
በተለየ ፀባይ ውስጤ ቅር፣ የሚለው፣
ምከንያቱን ካወቅሽ ንገሪኝ ምንድነው ።