ETV ዜና 57(🇪🇹) @wwetvzena1 Channel on Telegram

ETV ዜና 57(🇪🇹)

@wwetvzena1


https://t.me/wwetvzena1
ይህ ETV ZENA 57 (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።👇👇👇👇👇
https://t.me/ETVSPORTGole
https://t.me/ETVzenaSPORT
https://t.me/etvzenaAfaanOromoo

ETV ዜና 57 (Amharic)

ኢቲቪ ዜና 57 (ተስፋ) በፋብሪካዊ ዕቃዎች እና ጥይት ላይ አንድ የኢትዮጵያ ቤተሰብ ትግራይ ስትል ነው። በዚህ ቤተሰብ በሰውነቱና ህዝብ፣ ሀገር፣ ሚዛናዊ ስነምግል ላይ የተተካችበሉን የአመለካከት አዳዲስ አዝናኝ ይከታተሉ። በብሔራዊ የሚባሉ አዳዲስ ከጥላቻ አመለካከትን በግልፅ እንዲለያዩ ያዳብናሉ። አመለካከት ያለው እትምህርት ያከማቻሉ፣ በየቅርብ ስለኢትዮጵያውያን ከጥላቻ አመለካከት እንዲጋለጥ በተጨማሪ ጊዜ በአሰፋን ያስተላልፋሉ።

ETV ዜና 57(🇪🇹)

28 Aug, 18:17


https://t.me/etvzenaAfaanOromoo

ETV ዜና 57(🇪🇹)

28 Aug, 18:11


#ATTENTION🚨

ከ6 ሽህ በላይ ወገኖቻችን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል።

በስልጤ ዞን ባሉ 2 ወረዳዎችና 8 ቀበሌዎች ከአንድ ሺህ በላይ አባዉራ ቤትና ማሳዉ በውሀ መዋጡን ተከትሎ ከአካባቢዉ መነሳታቸው ተሰምቷል።

እስካሁን ባለዉ መረጃ ከ6 ሺህ በላይ ሰዎች ድጋፍ እንደሚሹ የዞኑ የአደጋ ስጋት ኃላፊ ወሲላ አሰፋ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ጎርፉ የፈጠረዉን ሀይቅ በዚህ ወቅት ማፋሰስ አሰቸጋሪ መሆኑን ያነለከቱት ኃላፊዋ " የሁለቱን ወረዳ ነዋሪዎች በክልሉና በዞኑ ድጋፍና ትብብር አውጥተን በትምህርት ቤቶችና በአርሶ አደሩ የስልጠና መዕከላት አስፍረን ስላልበቃን ትርፍ ቤት ያለዉ ሁሉ ትርፍ ቤቱን በመስጠት በጊዜያዊነት ለማስጠለል ተሞክሯል " ብለዋል።

" የመሬቱ አቀማመጥና የጎርፉ ብዛት የፈጠረዉ የዉሀ መጠን ከፍተኛ በመሆኑ ዝናቡ እስኪቆም ዘላቂ መፍትሄ መስጠት አንችልም ፤ ይሁንና አንዳንድ ቦታ ላይ ቋሚ ሰብሎች እንዳይጎዱና ቤቶች እንዳይበሰብሱ አንዳንድ ስራዎች እየሰራን ነው " ሲሉ አክለዋል።

አሁን ላይ ለተጎጂዎች እየቀረበ ያለው የምግብ እና አልባሳት ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ የዞኑ አደጋ ስጋት ምክር ቤት ተቋቁሞ ድጋፍ የሚሰበሰብበት መንገድ መመቻቹትን አመልክተዋል።

የስልጤ ዞን የጎርድ ድጋፍ ማሰባሰቢያ አካዉንት 1000647585535 (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) መሆኑ ተገልጿል።
https://t.me/wwetvzena1

ETV ዜና 57(🇪🇹)

28 Aug, 18:08


#Oromia : በኦሮሚያ ክልል ተፈርዶባቸው እስር ላይ የነበሩ 3,611 ታራሚዎች በይቅርታ ከእስር እንዲፈቱ መወሰኑን የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አሳውቋል።

247ቱ ሴቶች ናቸው።

የሞት ቅጣት ያለባቸው የህግ ታራሚዎች፤

ተደጋጋሚ ወንጀል የፈጸሙ

➡️ ሀሰተኛ ማስረጃ በማዘጋጀትና በማሰራጨት የተጠየቁ የህግ ታራሚዎችን ይቅርታው አያካትትም ተብሏል።

የይቅርታው መስፈርት ፦
° በማረሚያ ቤት ቆይታቸው የታረሙ
° ከተጎጂ ቤተሰብ ጋር የታረቁ
° የገንዘብ መቀጮ የከፈሉና ይቅርታ እንዲደረግላቸው የጠየቁ ናቸው ሲል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስረድቷል።
https://t.me/wwetvzena1

ETV ዜና 57(🇪🇹)

28 Aug, 18:06


https://t.me/etvzenaAfaanOromoo

ETV ዜና 57(🇪🇹)

28 Aug, 18:05


https://t.me/ETVSPORTGole

ETV ዜና 57(🇪🇹)

28 Aug, 18:05


https://t.me/wwetvzena1

ETV ዜና 57(🇪🇹)

28 Aug, 18:05


https://t.me/ETVzenaSPORT

ETV ዜና 57(🇪🇹)

27 Aug, 05:05


" የ11 ወንዶች እና 2 ሴቶች አስክሬን ነው የተገኘው " - አይ ኦ ኤም

" ፍልሰተኞችን የጫነ ጀልባ በየመን የባህር ዳርቻ መስጠሙን ተከትሎ በርካታ ሰዎች መሞተዋል ፤ አልያም ጠፍተዋል " ሲል የተመድ የፍልሰተኞች ድርጅት አሳውቋል።

አደጋው የበርካቶችን ህይወት ከቀጠፉና በተደጋጋሚ ከደረሱ የጀልባ መስጠም አደጋዎች የቅርብ ጊዜው ነው።

በታይዝ ግዛት ጀልባው ለአደጋ በተዳረገበት ወቅት 25 #ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን እና ሁለት የመናዊ መረከብ ዘዋሪዎችን ጭኖ እንደነበረ ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ተቋም (አይ ኦ ኤም) ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

እስካሁን ድረስ የ11ወንዶች እና 2 ሴቶች አስክሬን የኤደን ባህረሰላጤ እና ቀይ ባህርን በሚያገናኘው በባበል ኤል መንደብ መተላለፊያ ባህር ዳርቻ መገኘቱን እና ሁለቱን የመናዊያን ጨምሮ 14 ሰዎች የገቡበት እንዳልታወቀ ተገልጿል።

ፍልሰተኞች ከጂቡቲ የተነሱ እንደነበሩ አይ ኦ ኤም አስታውቋል ።

እንደ ተቋሙ መረጃ ከሆነ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በየመን የሚደርሱት ስደተኞች በሦስት እጥፍ አድጓል።

በ2021 27,000 ገደማ የነበረው የፍልሰተኞች ቁጥር ባለፈው አመት ከ97,200 በላይ ደርሷል።

በአሁኑ ወቅት 380,000 የሚጠጉ ስደተኞች ግጭት ባየለባት ሀገር ውስጥ ይገኛሉ።

የመን ለመድረስ ፣ፍልሰተኞቹ ቀይ ባህርን ወይም በኤደን ባህረ ሰላጤ ለማቋረጥ በህገወጥ አዘዋዋሪዎች አማካይነት አደገኛ በሆኑና በተጨናነቁ ጀልባዎች ይወሰዳሉ።

ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ ቢያንስ 2,082 ስደተኞች የገቡበት አልታወቀም ከእነዚህ መካከል 693 ያህሉ ሰጥመው ቀርተዋል።

በሰኔ ወር ቢያንስ 49 ስደተኞች በየመን ደቡባዊ የባህር ዳርቻ ጀልባቸው በመስጠሙ ሞተዋል።

140 ሰዎች ደግሞ የገቡበት እንዳልታወቀ ድርጅቱ አስታውሷል።

ተጨማሪ 62 ስደተኞች ባለፈው ሚያዝያ ወር የመን ለመድረስ ሲሞክሩ በጅቡቲ የባህር ዳርቻ ላይ በተከሰቱት ሁለት የጀልባ መገልበጥ አደጋዎች ህይወታቸው አልፏል። #IOM #VOA

ETV ዜና 57(🇪🇹)

26 Aug, 18:18


#ትግራይ

ባለፈው ሳምንት በትግራይ 2 ወረዳዎች የነበረውን ሃይለኛ ዝናብን ተከትሎ በተፈጠረው ከባድ ጎርፍ የ3 ሰው ህይወት ጠፍቷል።

በክልሉ ምስራቃዊ  ዞን ጉሎመኸዳ ወረዳ አዲስ ተስፋ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ደንጎሎ መንደር ነሃሴ 16/2016 ዓ.ም ሌሊት የዘነበው ከባድ ዝናብ ቤት አፈርሶ የአንድ ሰው ህወይት አሳጥቷል።

እሁድ ነሃሴ 19/2016 ዓ.ም በደቡባዊ ምስራቅ ዞን ሕንጣሎ ወጀራት ወረዳ ዓዲ ቐይሕ ከተማ ከባድ ዝናብ ያስከተለው ሃይለኛ ጎርፍ የ2 ህፃናትን ህይወት ቀጥፏል።

በደቡባዊ ዞን የሰለዋ ወረዳ ስምረት ቀበሌ ገበሬ ማህበር  ያጋጠመው የመሬት መደርመስ አደጋ በርካቶች አፈናቅሏል።

ተፈናቃዮቹ የመጠለያ ፣ የምግብና ሌሎች መሰረታዊ ነገሮች እገዛ ባለማገኝታቸው ምክንያት ለከፍተኛ ችግር ተዳርገዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ፥ የተከዘ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድብ ሙላትን ለመቀነስ አልሞ የተለቀቀ ውሃ ከተፋሰሱ በታች በሚገኙ አከባቢዎች ጉዳት አድርሷል።

በሰሜናዊ ምዕራብ ዞን የታሕታይ አድያቦ ወረዳ እንዳስታወቀው ውሃው በሰፋፊ የአርሶ አደሮች መሬት የበቀለውን እህል በማጥለቅለቅ ከጥቅም ውጭ አድርጓል።

#ትግራይ

ETV ዜና 57(🇪🇹)

20 Apr, 18:52


#እንድታውቁት #AddisAbaba

ነገ መንገድ ይዘጋል።

ነገ ሚያዚያ 13 ቀን 2016 ዓ/ም በአዲስ አበባ መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገ ሩጫ ይካሄዳል።

ሩጫው የ2016 " የኢትዮጵያ ታምርት " የጎዳና ላይ የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ነው።

የአዲስ አበባን ዋና ዋና መንገዶችን የሚያካልል እንደሆነም ታውቋል።

መነሻው መስቀል አደባባይ ከዛም በለገሃር ፣ ሜክሲኮ አደባባይ ፣ ቡልጋሪያ ማዞሪያ ፣ ቄራ ፣ ጎተራ ማሳለጫ ፣ አጎና ሲኒማ ፣ ጥላሁን አደባባይ አድርጎ መዳረሻውን መስቀል አደባባይ ያደርጋል።

ይህን ተከትሎ ሩጫው ተጀምሮ እስኪያልቅ የሚዘጉ መንገዶች እንዳሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

በዚህ መሰረት ፦

- ከመገናኛ ወደ መስቀል የሚወስደው መንገድ ኡራኤል አደባባይ
- ⁠ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል
- ከመስቀል ፍላዎር አደባባይ ወደ አጎና መስቀለኛ
- ከጎርጎሪዎስ አደባባይ ወደ ጎተራ
- ከጎተራ ሼል ወደ ጎተራ
- ከማሞ ማቋረጫ ወደ ጎተራ
- ከጎፋ ገብርኤል ወደ ጎፋ ማዞሪያ
- ከአልማዝዬ ሜዳ ወደ ቄራ በረት
- ከመካኒሳ አቦ አደባባይ ወደ ሳር ቤት አደባባይ
- ከካርል አደባባይ ወደ ሳር ቤት አደባባይ
- ከልደታ ፀበል ወደ ኤዩ መብራት
- ከቡልጋሪያ ማዞሪያ ወደኤዩ መብራት
- ከኦርቢስ መታጠፊያ/ጮራጋዝ/ መስቀለኛ ወደ ሲጋራ ፋብርካ
- ከጠማማ ፎቅ ወደ ጥይት ፋብርካ
- ከላንድ ማርክ ሆስፒታል ወደ ገነት መብራት
- ከከፍተኛ ፍ/ቤት /ባልቻ ሆስፒታል/ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
- ከአረቄ ፋብርካ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
- ከሠንጋ ተራ 40/60 መስቀለኛ ወደ ሠንጋ ተራ መብራት
- ከበድሉ ህንፃ ወደ ቴሌ ባር
- ከብሔራዊ ቲያትር መብራት ወደ ለገሃር መብራት
- ከሀራምቤ መብራት ወደ ሳንጆሴፍ መብራት
- ⁠ከብ/ቤተመንግስት ወደ መስቀል አደባባይ
- ⁠ከኢንተርኮንትኔታል ሆቴል ወደ ባምቢስ የሚወስዱ መንገዶች ከማለዳው 11:00 ሰዓት ጀምሮ ሩጫው እስኪጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

#AddisAbabaPolice #እንድታውቁት

ETV ዜና 57(🇪🇹)

20 Apr, 18:18


የአማራ ክልል ለ1 ሺህ 460 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ‼️

የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ሀላፊ አቶ ብርሃኑ ጎሽም ይቅርታውን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሠጥተዋል።

በመግለጫቸውም፤ የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ሚያዝያ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው 6ኛ መደበኛ ስብሰባ በክልሉ የይቅርታ አሠጣጥ መመሪያዎች መሠረት በበጀት አመቱ ሁለተኛ ዙር በማረሚያ ቤት ለሚገኙ ታራሚዎች ይቅርታ መደረጉን አንስተዋል።

በይቅርታው በማረሚያ ቤት ቆይታቸው በመታረምና በመታነፅ አርአያነት ያሳዩ፣ ከተበዳይ ወገኖች ጋር እርቅ የፈፀሙ፣ አስፈላጊውን ካሳ የከፈሉ እና ለማህበረሠቡ የወንጀልን አስከፊነት እንደሚያስተምሩ የታመነባቸው 1 ሺህ 431 ወንድ እንዲሁም 29 ሴት ታራሚዎች ይቅርታ እንደተደረገላቸው ገልፀዋል። 

በተጨማሪም መስተዳድር ምክር ቤቱ የተሠጣቸውን ይቅርታ ባለመጠበቅ ሌላ ወንጀል ፈፅመው በቻግኒ ማረሚያ ቤት የሚገኙ አምስት ግለሠቦችን ይቅርታ መሰረዙንም ኃላፊው ጠቁመዋል።

የህግ የበላይነት የሁለንተናዊ ለውጥ እና ለዘላቂ ሠላም መሠረት ነው ያሉት ኃላፊው፤ በክልሉ በሚታየው የፀጥታ ችግርና በሌሎችም አጋጣሚዎች ከማረሚያ ቤት የወጡ  ፍርደኞች እና ጉዳያቸው በሂደት ላይ የነበሩ ታራሚዎች ተመልሠው በህግ እንደሚዳኙም ገልፀዋል።

ETV ዜና 57(🇪🇹)

17 Nov, 16:35


https://t.me/etvzenaAfaanOromoo

ETV ዜና 57(🇪🇹)

17 Nov, 16:25


በጋዛ ግንኙነት ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ምግብና ሌሎች ድጋፎችን ማድረስ እንዳልተቻለ ተነገረ‼️

ድርጅቶቹ የሚሠጡትን አገልግሎት በዛሬው ዕለት ሙሉ በሙሉ ማቋረጣቸውን ተከትሎ ንጹሐን ሊራቡ እንደሚችሉ ማስጠንቀቃቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
የበይነ-መረብ እና የሥልክ አገልግሎት የተቋረጠው ወደ ጋዛ ይደርስ የነበረው ነዳጅ መቆሙን ተከትሎ ነው፡፡

አሁን ላይ የግንኙነት መሥመሮች መቋረጣቸውን ተከትሎ 2 ነጥብ 3 ሚሊየን የሚደርሰው በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ የሚኖረው የጋዛ ሕዝብ ለመገናኘት መቸገሩ ነው የተገለጸው፡፡

በሌላ በኩል የእስራዔል ጦር በሰሜናዊው የጋዛ ክፍል እያካሄደ ያለውን ጥቃት ወደ ደቡብም ማስፋት እንደሚፈልግ ምልክት አሳይቷል፡፡