የብቃት ምዘና ፈተና ለወሰዳችሁ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
____
በMedicine, Nursing, Public Health, Medical Laboratory Science, Midwifery, Dental Medicine, Medical Radiology Technology, Environmental Health, Psychiatric Nursing, Pediatric & Child Health Nursing, Emergency & Critical Care Nursing, Surgical Nursing, Physiotherapy እና Human Nutrition ሙያዎች ተመርቃችሁ በሰኔ 19/2016 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር እና በጤና ሚኒስቴር በኩል የተሰጠውን የመውጫ እና ብቃት ምዘና ፈተና የወሰዳችሁ ተመዛኞች ከነሀሴ 01/2016 ዓ.ም ጀምሮ http://hple.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት ሙሉ ስም እና የፈተና መለያ ቁጥራችሁን (username) በማስገባት የፈተና ውጤታችሁን መመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተመዛኞች ውጤት ከተገለጸበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት በስልክ ቁጥር 0118275936 በመደወል ወይም በኢሜይል
[email protected] ላይ ሙሉ ስም፣ ዲፓርትመንት፣ የመለያ ቁጥር(username) እና የተማራችሁበትን የትምህርት ተቋም ስም በመሙላት ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ማሳሰቢያ፦
▪በትምህርት ሚኒስቴር የማለፊያ ነጥብ አሟልታችሁ ዲግሪ የያዛችሁና የጤና ሚኒስቴርን የማለፊያ ነጥብ አሟልታችሁ ያለፋችሁ ተመዛኞች ስም ዝርዝራችሁን ከ03/12/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለክልል የጤና ተቆጣጣሪ አካላት የሚላክ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
▪በትምህርት ሚኒስቴር የማለፊያ ነጥብ አሟልታችሁ ዲግሪ የያዛችሁ የአንስቴዥያ ተመዛኞች ይህን ተከትሎ በሚወጣ ማስታወቂያ የተግባር ምዘና(OSCE) ፈተና የምዝገባ መርሃ ግብር ስለሚወጣ በትዕግስት እንድትጠባበቁ እንዲሁም ለፈተናው ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን።