Wolayta sodo university @wsu19be Channel on Telegram

Wolayta sodo university

@wsu19be


Info about wolayta sodo university
Photos ,new music ,vine and different thing about the
Campus@@@@@@@@@@@@@@
For junior and senior students.@veva1

Wolayta Sodo University (English)

Are you a student at Wolayta Sodo University or simply interested in learning more about this prestigious institution? Look no further than the Telegram channel '@wsu19be'! This channel is dedicated to providing valuable information about Wolayta Sodo University, as well as sharing photos, new music, vines, and other exciting content related to the campus. Whether you're a junior or senior student, this channel has something for everyone. Stay updated on the latest events, activities, and news happening at Wolayta Sodo University by joining this engaging community. Connect with fellow students, share your experiences, and immerse yourself in the vibrant culture of this renowned university. Don't miss out on this opportunity to be part of the WSU19BE community - join today and get ready to explore Wolayta Sodo University like never before!

Wolayta sodo university

03 Jan, 07:28


በመርሃ ግበሩ ላይ በዩኒቨርሲቲው ተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ሰሎሞን ጉንታ እና ከማህበራዊ ሳይንስና ሥነ ሰብ ኮሌጅ የዲኑ ተወካይዋ መ/ርት ወይንሸት ሰሎሞን ኮሌጆቹ ተማሪዎችን ለመቀበል ሙሉ ዝግጅት እንዳጠናቀቁ ገልፀው ተማሪዎቹ ለማህበራዊ ሚድያ ትኩረት ሳያደርጉ ከመምህራን ጋር ላላቸው ቁርኝት ትኩረት በመስጠት ለመልካም ውጤት እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ የአካዳሚክ ጉዳዮች ዙሪያ አጠቃላይ ገለፃ የስፖርት ሳይንስ መምህር እና ተመራማሪ በሆኑ ረዳት ፕሮፌሰር ደብረወርቅ ተስፋዬ እንዲሁም በተማሪዎች አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ከተማሪዎች አገልግሎት ዲን በተወከሉ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡

የሪጅስትራር አገልግሎቶች በተመለከተ በሬጅስትራር ባለሙያ እና በዩኒቨርሲቲው ቆይታቸው ተማሪዎች ያላቸውን ዋና ዋና መብቶች እና ግዴታዎች (የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዲሲፒሊን መመሪያ) ላይ ያተኮረ ገለፃ በህግ መምህር እና ተመራማሪ መምህር ጨምር ወልዴ በኩል ግንዛቤ ተፈጥሮላቸዋል፡፡

የህይወት ክህሎት ስልጠና "Life Skill and Assertiveness" በሳይኮሎጂ መምህር እና ተመራማሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሚሊዮን ደሳለኝ እንዲሁም 'Stress and Study Skill' በዩኒቨርሲቲው የሳይኮሎጂ መምህርና ተመራማሪ ዶ/ር መብራቱ በለጠ ተሰጥቶ በቀረቡት ገለጻዎች
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን🙏🙏🙏🙏🙏
@wsu19be

Wolayta sodo university

03 Jan, 07:25


በ2017 የትምህርት ዘመን ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ አዲስ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች አጠቃላይ ገለፃ እና የህይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ፡፡

ተማሪዎቹ በዩኒቨርሲቲው የሚኖራቸው ቆይታ ጊዜን በአግባቡ በመጠቀም የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ እንዳለባቸው ተነገራቸው፡፡

************

በስልጠና መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተለለፉት የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር አክበር ጩፎ ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን በሚያስፈልጋቸው የትምህርት ሥራዎች ሁሉ ለማገዝ ብቁ መምህራን የተዘጋጁ መሆኑን ጠቁመው ተማሪዎቹም ከራሳቸው የሚጠበቀውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

የዘንድሮ የፈተና አሰጣጥ ሙሉ በሙሉ (100%) ከትምህርት ሚኒስቴር በሚወጣው ጥያቄ መሰረት እንደሚሆን የገለጹት ዶ/ር አክበር የማለፊያ ውጤት ለማምጣት ተማሪዎች፣ መምህራን እንዲሁም ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ጥራት ያለው ትምህርት እንዲሰጥና የተማሪዎች አገልግሎት አሰጣጥ የተሳለጠ እንዲሆን ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ አለባቸው ብለዋል፡፡

ዶ/ር አክበር አክለውም ተማሪዎቹ በዩኒቨርሲቲው በሚኖራቸው ቆይታ ሳይረበሹ ጊዜያቸውን በአግባቡ በመጠቀም የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ እንዳለባቸው ተናግረው በተማሪዎቹ አመርቂ ውጤት አስመዝግበው የተሳካ ጊዜን እንዲያሳልፉ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡

በዩኒቨርሰቲው የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ተማሪ ተስፋጽዮን መድኅን ዩኒቨርሲቲ ዕውቀት የሚጋራበት እና ተማሪዎች ራሳቸውንና ሕይወታቸውን በአግባቡ ለመምራት ክህሎት የሚያገኙበት ተቋም መሆኑን ጠቅሶ አዲስ ወደ ዩኒቨርሲቲው የተመደቡ ተማሪዎች በመልካም ድስፕሊን ታንፀው ጥሩ ዉጤት ለማስመዝገብ መስራት እንዳለባቸው መክሯቸዋል፡፡

Wolayta sodo university

29 Dec, 13:54


በ2017 የትምህርት ዘመን ከኢ. ፌ. ዴ. ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር አዲስ ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች በዛሬው ዕለት ወደ ዩኒቨርሲቲ እየገቡ ይገኛሉ።

******
****

20/04/2017 ዓ.ም

ተማሪዎች ወደ ግቢ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል እየተደረገላቸው ነው።

ተማሪዎቹ ነገም ሲገቡ ለመቀበል ሙሉ ዝግጅት አጠናቅቆ እየተጠባበቀ ይገኛለ።

የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ተማሪዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ እያለ በዩኒቨርሲቲው ያላቸው ቆይታ በመልካም ውጤት የታጀበ እንዲሆን ይመኛል።

#የዩኒቨርሲቲው #አስተዳደር
@wsu19be

Wolayta sodo university

21 Dec, 14:49


#ማ ሳሰቢያ 3

1.የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከA እስከ TESLIM EGALI MOHAMMED የሆናችሁ የተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Science) የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲውዋናውካምፓስ (ወላይታ ሶዶ)

2.የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከ A እስከ TESHOME ASALIF MEKONIN የሆናችሁ የማህበራዊ ሳይንስ (Social Science) የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ዋና ውካምፓስ (ወላይታ ሶዶ)

3.ስማችሁ ስማችሁ ከ (TEWABECH GUYITA KUSSE) ጀምሮ እስከ Z የሆናችሁ የተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Science) የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ዳውሮታርጫካምፓስ (ዳውሮ ታርጫ)

4.ስማችሁ ከTEWDIROS TEGEGEN SHANKA ጀምሮ እስከ Z የማህበራዊ ሳይንስ (Social Science) የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ (ዳውሮታርጫ) ሬጅስትራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በአካል ቀርባችሁ ከላይ በተጠቀሱት ቀናት እንድትመዘገቡ፣ ገለፃ እንድትከታተሉ እና ትምህርት እንድትጀምሩ እናሳስባለን፡፡

ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው አያስተናግድም፡፡

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@wsu19be

Wolayta sodo university

21 Dec, 14:48


#ማስታወቂያ
በ2017 የትምህርት ዘመን አዲስ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች በሙሉ፡-

በ2017 የትምህርት ዘመን ከኢ. ፌ. ዴ. ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር አዲስ ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች የ2017 የትምህርት ዘመን መግቢያ ቀን ታህሳስ 20 እና 21/2017 ዓ.ም መሆኑን እናስታዉቃለን፡፡

#ማሳሰቢያ 1

1.ምዝገባ (በአካል ቀርበው) ታህሳስ 21 እና 22 ቀን 2017 ዓ.ም
2.አጠቃላይ ገለፃ (orientation) ታህሳስ 23 ቀን 2017 ዓ.ም
3.ትምህርት የሚጀመረው ታህሳስ 24 ቀን 2017 ዓ.ም መሆኑን እንገልፃለን፡፡

#ማሳሰቢያ 2

ሁሉም ተማሪዎች ሲመጡ፡-
1.የ8ኛ ክፍል ሰርተፍኬት (ዋናው እና ኮፒው)
2.ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕትና የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ኦርጂናልና የማይመለስ ሁለት ኮፒ
3.አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ በመያዝ መምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡

#ማ ሳሰቢያ 3

1.የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከA እስከ TESLIM EGALI MOHAMMED የሆናችሁ የተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Science) የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲውዋናውካምፓስ (ወላይታ ሶዶ)

2.የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከ A TESHOME ASALIF MEKONIN የሆናችሁ የማህበራዊ ሳይንስ (Social Science) የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ዋና ውካምፓስ (ወላይታ ሶዶ)

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
Share
@wsu19be

Wolayta sodo university

16 Dec, 14:44


#ወጣቱን_አገልጋይ_እናድነው...
(እባኮ ሼር ያድርጉልን)
ይህ የምታዩት ወንድም ልደቱ ተዘራ ይባላል የወላይታ ዮንቨርስቲ ተማሪና የፌሎሽፑ አገልጋይ ሲሆን ባደረበት ድንገተኛ የልብ ህመም ወደ አዲስ አበባ ሪፈር ተብሎ በኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል ይገኛል። ሆኖም ይህ ወንድም ቀዶ ጥገናውን ለማድረግ ወደ 2,000,000 (ሁለት ሚሊዮን) ብር ተጠይቋል። ወንድማችን ይሄንን ገንዘብ ለመክፈል የሚያስችል አቅም ስለሌለው እንድናግዘው በጌታ ስም አደራ እንላለን።
አካውንት 1000340306965 lidetu tezera dako
እንዲሁም ወንድማችንን በዚህ ቁጥር ማግኘት ትችላላችሁ +251973522180
@wsu19be

Wolayta sodo university

16 Dec, 14:30


ተስፈኛው ወንድማችን አገልጋይ ልደቱ ተዘራ ድንገት ባጋጠመው በልብ ህመም ምክንያት ለህክምና ብዙ ብር ስለተጠየቀ እባካችሁን ይሄን ተስፈኛውን ወጣት የአቅማችን ያህል በማድረግ እናትርፈው!!!🙏🙏

ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር የብድራል በጎነቱም መልሶ ይከፍላል።
ምሳሌ 19:17
የአቅማችውን ኢንድትረዱት በጌታ ፍቅር
እንለምናለን።🙏🙏🙏
1000340306965-LIDETU TEZERA DAKO
@wsu19be

Wolayta sodo university

06 Dec, 18:24


19ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ክብረ በዓል ታዳሚዎች አቀባበል በዩኒቨርሲቲው…

********************

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 29/2017 ዓ.ም 19ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን "ሃገራዊ መግባባት ለህብረብሄራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአርባ ምንጭ ከተማ የሚከበረውን ለመታደም ከተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች ወደ አርባ ምንጭ የሚጓዙ ታዳሚዎች በመቀበል አስተናግዷል፡፡

ተዳሚዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ደማቅ አቀባበል አድርገዋል፡፡

ከ1300 በላይ እንግዶችን የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እንኳን አደረሳችሁ፣ እንኳን በደህና መጣችሁ በማለት ልዩና ደማቅ የሆነ አቀባበል ያደረገ ሲሆን ታዳሚዎች በተደረገው ደማቅ አቀባበል ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

ዕውቀትን በተግባር!

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
@wsu19be

Wolayta sodo university

08 Nov, 17:55


#ማስታወቂያ

በ2017 ዓ.ም ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ የ1ኛ ዓመት (FRESHMAN) ተማሪዎችሙሉ

በ2017 የትምህርት ዘመን ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አድስ የተመደባችሁ የ1ኛ ዓመት (FRESHMAN) እንድሁም በ2016 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ (REMEDIAL) ፕሮግራም ተከታትላችሁ ማለፊያ ዉጤት 50% እና ከዛ በላይ ያመጣችሁ ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚካሄደዉ ህዳር 09 – 10/2017 ዓ.ም ስለሆነ በተጠቀሰዉ ቀን ብቻ በአካል በመቅረብ እንድትመዘገቡ እናሳዉቃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ፤ 👇👇👇👇👇👇👇
@wsu19be

Wolayta sodo university

04 Oct, 08:13


በዩኒቨርሲቲው ሁለተኛ ቀኑን የያዘው ሁለተኛና ከዚያ ዓመት በላይ ነባር መደበኛ ተማሪዎች አቀባበል ቀጥሎ ውሏል፡፡

ከመስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በዩኒቨርሲቲው የ2017 ዓ.ም በተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚመጡ ነባር መደበኛ ተማሪዎች አቀባበል እየተደረገላቸው ቆይቷል፡፡

በዛሬው ዕለትም በዩኒቨርሲቲው ሁለተኛ ቀኑን የያዘው ሁለተኛና ከዚያ ዓመት በላይ ነባር መደበኛ ተማሪዎች አቀባበል ቀጥሎ የዋለ ሲሆን መደበኛ ትምህርት የመጀመሪያ ቀን (DOCO, Day One Class One) መስከረም 22 ቀን 2017 ዓ.ም መሆኑን ከሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያመላክታለ፡፡

በዕለቱ (DOCO) ሁሉም ተማሪዎች ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በተመደቡበት የመማሪያ ክፍል እንዲገኙ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ከወዲሁ ያሳስባል፡፡

የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ተማሪዎችን በድጋሚ እንኳን ደህና መጣችሁ እያለ ቀጣዩ የትምህርት ጊዜ የተሳካና በመልካም ውጤት የታጀበ እንዲሆን ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲሰፍን በትኩረት ይሰራልም ብሏል፡፡

ዕወትን በተግባር!

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
@wsu19be

Wolayta sodo university

20 Sep, 03:50


#ማስታወቂያ!!

ለወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ነባር መደበኛና ተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም ተማሪዎች በሙሉ
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለሁለተኛና ከዚያ በላይ መደበኛና ተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም ተማሪዎች ዲጂታል መታወቂያ ስለተዘጋጀ ማንም ተማሪ ማንነቱን የሚገልጽ 4*4 የሆነ ሁለቱንም ጆሮዎች የሚያሳይ ጉርድ ፎቶ በEstudent ስስተም እስከ እሁድ (12/01/2017 ዓ/ም) ድረስ እንዲያስገባ በጥብቅ እናስታዉቃለን፡፡

የዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት!!
@wsu19be

Wolayta sodo university

16 Sep, 15:38


#ማስታወቂያ!!

#ጉዳዩ፦ የ2ኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ ያሉ የመደበኛ ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም 1ኛ ሴሚስቴር ምዝገባ ጊዜ መራዘሙን ስለማሳወቅ!!

የምዝገባ ጊዜ (ከመስከረም 20-21/2017 ዓ.ም) መሆኑን እናሳውቃለን።
ለበለጠ መረጃ ከታች ያለውን ልጥፍ ይመልከቱ👇
@wsu19be

Wolayta sodo university

11 Sep, 11:11


@wsu19be

Wolayta sodo university

07 Sep, 14:33


የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ የአሜሪካ የረትገር ዩኒቨርሲቲ-ካምደን ቻንስለር በዶክተር አንቶኒዮ ዲ. ቲሊስ የተመራ የልዑካን ቡድን ተቀብለው በጽ/ ቤታቸው አነጋገሩ፡፡

ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ቻንስለሩንና የልዑካን ቡድናቸውን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ስለ አገራችን ዘመናዊ ትምህርትና የከፍተኛ ትምህርት ታሪክና መስፋፋት ዙሪያ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡
የረትገር ዩኒቨርሲቲ ከትምህርት ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በቴክኖሎጂና በሌሎችም የትብብር መስኮች በጋራ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው መክረዋል፡፡

ዶክተር አንቶኒዮ ዲ. ቲሊስ በበኩላቸው የረትገር ዩኒቨርሲቲ-ካምደን ከማላዊ፣ ኬኒያ ፣ ናይጄሪያና ከሌሎችም የአፍሪካ ዩኒቨርስቲዎች ጋር በትብብር እንደሚሰራ ጠቅሰው ከትምህርት ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች ጋር በተለያዩ መስኮቸ በትብብርና በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

#MoE

➬ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይጎብኙ/ይቀላቀሉ!
👇👇👇
@wsu19be

Wolayta sodo university

04 Sep, 14:24


#NGAT

የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) በተመለከተ አጭር ማብራሪያ!!

1. የመፈተኛ ተቋም እና የመፈተኛ schedule በ portal በኩል የምታገኙ ሲሆን ዝርዝር መረጃውን የምናሳውቃችሁ ይሆናል።

2. ማንኛውም ተፈታኝ በ portal በኩል የተላከለትን Pass Card ሳይዝ ወደ ፈተና ጣቢያ መግባት የማይችል መሆኑን እያሳሰብን Pass Card የሚገኘው በያንዳንዳችሁ Poral Dashboard ላይ ብቻ ነው። የፖርታል አድራሻ ngat.ethernet.edu.et ነው።

#ማሳሰቢያ

Pass Card ላይ ያሉ መረጃዎች እደሚከተለው ይቀርባል👇

a. የተፈታኝ ሙሉ መረጃ
b. የሚፈተኑበት ተቋም እና ካምፓስ አድራሻ
c. የሚፈተኑበት የትምህርት ዘርፍ
d. የሚፈተኑበት Session እና የፈተና ሰዓት እንዲሁም
e. የተፈታኝ ፎቶ ሲሆኑ ሁሉም ተፈታኝ Pass Card Print አድርጎ መምጣት ይጠበቅባቸዋል።

3. ፈተናው ሊሰጥ የታቀደው ነሐሴ 30 እና ጳጉሜን 1/2026 ሲሆን ለውጦች ካሉ በዚህ በኩል መረጃዎችን ይከታተሉ።

#ትምህርት_ሚኒስቴር

➬ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇
@ wsu@19be

Wolayta sodo university

28 Aug, 18:59


የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር እና የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በትምህርት ተቋማት ስፖርት ልማት ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡
======================
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የመግባቢያ ስምምነቱን በተፈራረሙበት ወቅት ስፖርት አእምሮአዊና አካላዊ ብቃት የተላበሱ ዜጎችን ለማፍራት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም የትምህርት ሚኒስቴር ብቃት ያላቸው ዜጎችን የማፍራት ተግባር የትምህርት ዘርፉ ሪፎርም አካል አድርጎ እየሰራ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ በዚህም መሠረት በቀጣዩ የትምህርት ዘመን የትምህርት ቤቶች ስፖርት ውድድርን ለማካሄድ እና መርሃ ግብሩን አጠናክሮ ለማስቀጠል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የባህልና ስፖርት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ በበኩላቸው በሁሉም ዘርፍ አሸናፊ አገር ለመፍጠር ብቁና ንቁ ዜጎች ማፍራት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው በማህበረሰብ አቀፍ እና በባህላዊ ስፖርቶች ላይ የትምህርት ማህበረሰቡን በማሳተፍ በጋራ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ ተቋማት በዕለቱ የተፈረረሙት የመግባቢያ ሰነድ መሰረት በቀጣይ በየደረጃው ባሉ ቴክኒካል ባለሙያዎች በየጊዜው እየታቀደ እና እየዳበረ ለተሻለ ስኬት እንደሚውል ጠቁመዋል፡፡

የትብብር ስምምንቱ ዓላማ በሁለቱ ተቋማት መካከል ወጥ እና ተከታታይነት ያለው ቅንጅታዊ አሰራርን በመፍጠር የትምህርት ቤት ስፖርት ልማትን በማስፋፋት የስፖርት ትምህርት ጥራትን ለማሻሻል መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ሰፖርታዊ ልማትን ባህል ያደረገ በመማር ውጤቱ የተሻለ የሆነ ንቁና ሁለንተናዊ ሰብዕናው የተሟላ ተተኪ ትውልድ ለማፍራት ምቹ ሁኔታን መፍጠር የስምምነት ሰነዱ ሌለው ዓላማ መሆኑን ተመላክቷል፡፡
===////====
@wsu19be

Wolayta sodo university

28 Aug, 17:51


#ማስታወቂያ

የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ተጨማሪ የምዝገባ ጊዜ እና የፈተና ቀንን ስለማሳወቅ

በ2017 የትምህርት ዘመን የድህረምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ያላቸሁ እና በተለያዩ ምክንያቶች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ ያመለጣችሁ አመልካቾች እስከ ነሐሴ 26/2016 ዓ.ም ድረሰ በ https://ngat.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑንን እየገለጽን በየተመደባችሁበት የፈተና ማዕከላት እና የመፈተኛ ፕሮግራም መሰረት ከ ነሐሴ 30 እስከ ጳጉሜን 1/2016 ዓ.ም ድረስ ፈተናው የሚሰጥ መሆኑን እንገልጻለን።

#ማሳሰቢያ
በፈተና ወቅት የተሰጣችሁን User Name and Password፣ እና ማንነታችሁን የሚገልጽ መታዋቂያ ይዛችሁ መቅረብ ይጠበቃባችኋል።

© የኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር
@wsu19be

Wolayta sodo university

31 Jul, 16:36


#ማስታወቂያ!!

የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የምዝገባ ጊዜን ስለማሳወቅ።

ትምህርት ሚኒስቴር በ2017 የትምህርት ዘመን የድህረምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ላላቸው አመልካቾች የሚሰጠው የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ የሚካሄደው ከሐምሌ 24 - ነሐሴ 05/2016 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ የመመዝገቢያው ቅጽ ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በሟሟላት በ https://NGAT.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
@wsu19be

Wolayta sodo university

31 Jul, 05:11


#MoE

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚያስመርቋቸው ተማሪዎች የሚሰጡት ዲግሪ የህትመት ሥራ በመንግሥት ሊከናወን ነው፡፡

የዲግሪ ህትመት ሥራው በሀገር ውስጥ እነደሚከናወንና አሰራሩም ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ትናንት ባዘጋጀው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዳግም ምዝገባ የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡

"ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዲግሪ በማሳተም ለተማሪዎቻቸው መስጠት አይችሉም" ያሉት ሚኒስትሩ፤ ዲግሪ የሚታተመው በትምህርት ሚኒስቴር በኩል እንደሚሆንና ለዚህም ተቋማቱ ክፍያ ለሚኒስቴሩ እንደሚፈፅሙ ገልፀዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎቹን ዲግሪ የሚያትመው ተቋማቱ በሚልኩት መረጃ እና የተማሪዎቹ የሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ውጤትን መሰረት በማድረግ እንደሚሆንም ጠቁመዋል፡፡

አሰራሩ ተግባራዊ ሲደረግ በሀገሪቱ የሚታየውን የሐሰተኛ ዲግሪ ህትመት ለማስቆም እንደሚያስችል ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡

መንግሥት የ Security Printing ሥራ በሀገር ውስጥ በ2017 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ እንደሚጀምር ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

Wolayta sodo university

25 Jul, 10:28


@wsu19be

Wolayta sodo university

16 Jan, 21:18


@wsu19be

Wolayta sodo university

29 Sep, 17:37


#ማስታወቂያ!!

ለወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ሠራተኞች በሙሉ።

ጉዳዩ፦አዲሱ የሰው ሀይል አደረጃጀት መወቅር በድልድል አፈጻጸም መመሪያ መሠረት የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ምርጫን ይመለከታል፡፡

አዲሱ የፌዲራል መንግስት መወቅራዊ አደረጃጀት ለውጥ ምክንያት በድልድል አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 859/2014 ክፍል አራት አንቀጽ 29 መሠረት የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አባላት በቁጥር ዐ2 ከሠራተኞች የሚመረጥ ስለሆነ በቀን 21/01/2016 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ሁሉም ሠራተኞች በዋናው ካምፓስ በመመረቂያ አደራሽ በተጠቀሰው ቀን በሰዓት በመገኘት ከሰራተኞች በቁጥር ዐ2 የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ እንድትመርጡ እናሳውቃለን።

#ማሳሰቢያ፦ በመድረኩ የድልድል ኮሚቴው የእስከ አሁን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትና ቀጣይ የስራ አቅጣጫ ቀርቦ ውይይት ስለሚደረግ በዕለቱ ሁሉም የአስተዳደር ሰራተኛ በተጠቀሰው ሰዓት እንዲገኝ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር በጥብቅ ያሳስባል።

ከሰው ሀብት አስተዳደር ልማት ዳይሬክቶሬት

መስከረም 18/2016 ዓ/ም
@wsu19be