Tirita 97.6 FM Radio (@tiritaradio)の最新投稿

Tirita 97.6 FM Radio のテレグラム投稿

Tirita 97.6 FM Radio
ትርታ 97.6 ኤፍ ኤም ''ከልብዎ የቀረበ''

ትርታ ሚዲያ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያለ የንግድ መዝናኛ፣ ዜና እና ቢዝነስ ጭብጥ ያለው ሚዲያ ነው።
1,271 人の購読者
955 枚の写真
7 本の動画
最終更新日 09.03.2025 15:19

類似チャンネル

FIDEL POST NEWS
18,229 人の購読者

Tirita 97.6 FM Radio によってTelegramで共有された最新のコンテンツ

Tirita 97.6 FM Radio

08 Nov, 13:04

274

ፍራንኮ ቫሉታ ተሰርዟል!
***
የገንዘብ ሚኒስቴር የፍራንኮ ቫሉታ ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ተፈቅደው የነበሩ ምርቶች ፍቃድ መሰረዙን አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ውሳኔውን ያሳለፈው መንግሥት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ተከትሎ የዋጋ ግሽበት እንዳይከሰት በሚል እንደነበር አስታውሶ፤ "አሁን ላይ ዋነኛውን ምእራፍ የታለፈ በመሆኑ ፍቃዱን አንስቻለሁ" ብሏል በመግለጫው።

ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ተፈቅደው የነበሩ የምግብና የፋብሪካ ግብአት የሚውሉ የውጭ ምርቶች መሆናቸውም ተገልጿል።

የፍራንኮ ቫሉታ ፍቃዱን ከጥቅምት 29/2017 ዓም ጀምሮ ተግባራዊ የማይደረግ መሆኑን ለጉምሩክ ኮሚሽን አባሪ አድርጎ በላከው ደብዳቤ ላይ ገልጿል።

የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በተመለከተ በኢትዮጵያ ያሉ ንግድ ባንኮች በቂ የሚባል የውጭ ምንዛሪ በበቂ ሁኔታ እየቀየረ ስለሆነም ከእንግዲህ በኃላ ፍራንኮቫሉታ የሚባል ነገር እንደማይኖርም አሳውቋል።

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

08 Nov, 12:13

262

10ኛዉ የአፍሪካ ሶርሲንግ እና የፋሽን ሳምንት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ::

የአፍሪካ ሶርሲንግ እና የፋሽን ሳምንት ከዛሬ ጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በስካይላይት ሆቴል የሚካሄድ ሲኾን፣ የፋሽን ጨርቃጨርቅ እና ቆዳ ኢንደስትሪዎችን በአንድ ጣራ ስር ያሰባሰበ ነዉ ተብሏል::

በዝግጅቱም ከ30 ሀገራት የተወጣጡ ከ250 በላይ የዘርፉ ባለሙያዎች ምርትና አገልግሎታቸዉን ያስተዋውቃሉ።

ከ60 በላይ ሀገሮች የሚመጡ ከ7 ሺ በላይ የንግድ ዘርፍ ባለሙያዎች ተቋማትና ግለሰቦች እንደሚገኙበት ተገልጿል።

(ትባረክ ኢሳያስ)

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

07 Nov, 11:23

229

"ፊናፍ" የተሰኘ የኦሮምኛ ፊልም ከዛሬ ጀምሮ በቴሌ ቲቪ መታየት ይጀምራል::

ኤግልላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ፣ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ቴሌ ቲቪ የተሰኘ የኦላይን ሲኒማ መተግበሪያን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። በዚህም
<<ፊናፍ>> የተሰኘ የኦሮምኛ ፊልም በቴሌ ቲቪ አማካኝነት በዛሬዉ ዕለት መታየት እንደሚጀምር የኤግልላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ በሱፈቃድ ጌታቸው ገልፀዋል::

በእጅ ስልክ በመታገዝ በ ቴሌ ቲቪ ፊልሞችን ለመመልከትም በሀገር ዉስጥ በቴሌ ብር እንዲሁም በዉጭ ሀገር በማስተር ካርድ በቪዛ እና በአሜሪካን ኤክስፕረስ የክፍያ አማራጮች መጠቀም እንደሚቻልም አብራርተዋል።

የድራማ ዘዉግ እና የአንድ ሰዓት ከ45 ደቂቃ ቆይታ ያለዉ <<ፊናፍ>> ፊልም በእንግሊዘኛም ትርጉም የተሰራለት መሆኑ፣ ቋንቋዉን ለማይረዱ  መናገርም ሆነ መስማት ለማይችሉ በአማራጭነት መቅረቡን የፊልሙ ፀሀፊ እና አዘጋጅ ቢቂላ አስፍዉ ተናግረዋል::

ፊናፍን ጨምሮ 8 ሀገርኛ ፊልሞችን በቴሌ ቲቪ የኦላይን ሲኒማ መተግበሪያ ለዕይታ መቅረባቸዉም ተገልጿል።

(ትባረክ ኢሳያስ)

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

06 Nov, 12:47

243

ግሎባል አልያንስ 4.6 ሚልዮን ብር ለአፋርና ለአማራ ልማት ማህበሮች ድጋፍ አደረገ!

ግሎባል አሉያንስ የገንዘብ ድጋፉን ያደረገው በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ከፍተኛ ውድመት የደረሰባቸውን ትምህርት ቤቶችን  መልሶ ለማቋቋምና ግንባታዎችን ለማካሄድ ይረዳ ዘንድ እንደሆነ ዛሬ በነበረው የርክክብ ፕሮግራም ላይ ተጠቅሷል።

በእርዳታ የተገኘውን 4.6 ሚልየን ብር ሁለቱ ማህበሮች እኩል ተካፍለዋል። የማህበራቱ ተወካዮችም ድጋፌን በአካል ተገኝተው ተረክበዋል። ለግሎባል አሊያንስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ግሎባል አልያንስ በአጠቃላይ ላለፉት ስድስት አመታት በመላው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላጋጠሙ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ አደጋዎችን ተከትሎ ከ300 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉ ተጠቁሟል።

(ራህማ መሐመድ)

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

06 Nov, 10:40

221

ዶናልድ ትራምፕ የ2024 የአሜሪካን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫን ማሸነፋቸውን ሲ ኤን ኤን በይፋ ዘግቧል!

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

05 Nov, 17:30

213

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የብሪክስ ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎች ማህበር መስራች አባል ሆነ
**
አዲስ አበ
ባ ዩኒቨርሲቲ ሩሲያ፣ ህንድና ብራዚልን ጨምሮ ከብሪክስ ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመሆን በጣምራ የብሪክስ ሀገሮች ዩኒቨርሲቲዎች ማኅበርን በመመስረት የመጀመሪያው የምስራቅ አፍሪካ ሀገር ዩኒቨርስቲ መሆኑን አስታውቋል። 

አራቱ የብሪክስ ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎች የመሰረቱት ማህበር በትምህርት በዲፕሎማሲ በጥናትና ምርምር እንዲሁም በፈጠራ ስራ በጋራ መሰራት የሚያስችላቸው መሆኑ ተመላክቷል።

ዩኒቨርስቲው በአዲሱ የራስ-ገዝ ስትራቴጂክ እቅድ መሰረት አጋርነትና ዓለማቀፋዊነትን በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

05 Nov, 15:03

240

በእሳት አደጋ የእናትና ልጅ ህይወት አልፏል።
***
በዛሬው እለት በፉሪ ክፍለ-ከተማ በመስሪያና መሸጫ ሼድ ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ  የአንድ  እናት ከስድስት ወር ልጃቸው  ጋር ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል። ስድስት የንግድ ሱቆችም ተቃጥለዋል ተብሏል።

ከንግድ ሱቆቹ መካከል በአንደኛዉ ነዳጅ በፕላስቲክ ጠርሙስ በችርቻሮ የሚሸጥበት ሱቅ በመሆኑ ለሽያጭ የተዘጋጀዉ ነዳጅ ለቃጠሎ መከሰትና  መባባስ ጉዳት ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ከአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከስድስት ወር ልጇ ጋር ህይወቷ ያለፈችዉ እናት በእሳት አደጋዉ ከተቃጠሉት የንግድ ሱቆች ዉስጥ በአንደኛዉ ሱቅ የንግድ ስራ ላይ የነበረች መሆኗም ተጠቅሷል።

ነዳጅ መከማቸትም ሆነ መሸጥ ያለበት በተፈቀደለትና የአደጋ ደህንነት መስፈርትን ባሟሉ የነዳጅ መሸጫ ጣቢያዎች ዉስጥ ብቻ ነው ያለው ኮሚሽኑ፣ በተለያዩ የንግድ ሱቆች ዉስጥ ነዳጅ ማከማቸትም ሆነ መሸጥ መሰል አደጋዎችን የሚያስከትል በመሆኑ የንግድ ፈቃድ የሚሰጡ አካላትም ተገቢዉን ቁጥጥር ማድረግ ይኖርባቸዋል ብሏል።

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

05 Nov, 04:13

143

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን አውሮፕላን ተረከበ።
***
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን ኤር ባስ A350-1000 አውሮፕላን ተረከበ፡፡

በርክክብ ሥነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የቦርድ ሰብሳቢ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው፣ የአየር መንገዱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር አሌክሲ ለሚክ፣ የኤር ባስ ኩባንያ ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የላቀ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ቴክኖሎጂ የተገጠመለት አውሮፕላኑ በአየር መንገዱ ምድረ ቀደምት (Ethiopia land of origins) የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው A350-1000 አውሮፕላን 400 መቀመጫዎች አሉት፡፡

አየር መንገዱ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2035 በዓመት 67 ሚሊዮን መንገደኞችን በማጓጓዝ 25 ቢሊዮን ዶላር ዓመታዊ ገቢ ለማግኘት እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅትም ባሉት 147 አውሮፕላኖች 139 ዓለም አቀፍ እና 22 የሀገር ውስጥ የበረራ መዳረሻዎችን እየሸፈነ ይገኛል፡፡

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

03 Nov, 16:16

192

ታምራት ቶላ የኒው ዮርክ ማራቶን በአራተኛነት አጠናቋል!

ውድድሩን ለኔዘርላንድስ የሚሮጠው ትውልደ ሶማሌያዊው አብዲ ነገዬ በ2:07:39 ሲያሸንፍ፣ ኬንያውያኑ ኢቫንስ ቼቤት እና አልበርት ኮሪር ሁለተኛና ሶስተኛ ሆነው ገብተዋል!

የአምናው አሸናፊ ታምራት ቶላ ርቀቱን 2:08:12 ነው ያጠናቀቀው።

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ
Tirita 97.6 FM Radio

03 Nov, 16:03

179

የኬንያ አትሌቶች በሴቶች የኒው ዮርክ ማራቶንን ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል!

ውድድሩን ሼይላ ቼፕኪሩይ በ2:24:35 በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ፣ ሄለን ኦቢሪ በ2:24:49 እና ቪቪያን ቺርዮት በ2:25:21 ሁለተኛና ሶስተኛ ሆነው ገብተዋል።

ኢትዮጵያዊቷ ሰንበሬ ተፈሪ በ 2:27:14 ሰባተኛ ደረጃን አግኝታለች።

#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ