መርሀ ግብሩ የባንኩ የ82 አመታት ጉዞ ላይ የደንበኞች አስተዋፅኦ የማይተካ በመሆኑ: ይበልጥ ደንበኛ ተኮር የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት ቃል የሚገባበት መሆኑ ተገልጿል።
ከአራት አመት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀው እና ለተከታታይ አራት ሳምንታት በሚቆየው የደንበኞች አገልግሎት ወር ለአንድ ሳምንት የሚቆይ አውደ ርዕይ የተከፈተ ሲሆን፡ በቀጣይም ተከታታይ ውይይቶች፡ የ የደም ልገሳ እንዲሁም የማስ ስፖርት ዝግጅቶች ይካሄዳሉ።
ባንኩ 81 ከመቶ የሚሆኑ ደንበኞቹ የዲጂታል ቴክኖሎጂ እንዲጠቀሙ ማስቻሉ በመርሀ ግብሩ ላይ ተጠቅሷል።
በዛሬው እለት በዋና መስሪያ ቤቱ የተካሄደው ይህ መርሀ ግብር ''የላቀ አገልግሎት ደስተኛ ደንበኛ'' በሚል መሪ ቃል በሁሉም ቅርንጫፎች ከታህሳስ 24 እስከ ጥር 25 ቀን 2017 ዓ.ም በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል።
በመክፈቻ መርሀ ግብሩ ላይም የገንዘብ ሚኒስቴር አህመድ ሽዴ ፣ የባንኩ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እና ሰራተኞች ተገኝተዋል።
(በንጉሱ በሪሁን)
#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ