***
እናት ባንክ የአለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓለን በማስመልከት የ200ሺህ ብር ወጪ በማድረግ የንፅህና መጠበቂያና ተያያዥ የንፅህና መጠበቂያዎችን በአዲስ አበባ ቂርቆስ ከፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት ለምስራቅ ጎህ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚማሩ 400 ሴት ተማሪዎች ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፉን የእናት ባንክ የሥራ ሃላፊዎችና የባንኩ የብራንድ አምባሳደር አርቲስት ሐረገወይን አሰፋ ለቂርቆስ ከፍለከተማ የወረዳ ስምንት የሥራ ኃላፊች፣ የትምህርቤቱ ርዕስ መምህራን፣ መምህራንና ተማሪዎች በተገኙበት በዛሬው እለት አስረክበዋል፡፡
በወቅቱም የእናት ባንክ የስራ ሃላፊዎች ባስተላለፉት መልክት ፣ ባንኩ የሴቶችን ኢካኖሚያዊ አቅም ከማጎልበትና ለሁሉም ማህበረሰብ የተሟላ የባንክ አገልግሎት ከመስጠት ጎን ለጎን ማህበራዊ ሃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
በዚህም ለሴቶች የቢዝነስ አሰራር ሥልጠና በመስጠት ፣የብድር ዋስትና ማቅረብ የማይችሉ ሴቶች ብድር የሚያገኙበት አሰራር በመዘርጋት ሀሳባቸውን እውን እንዲያደርጉ በማመቻቸትና የሥራ ዕድል በመፍጠር የበኩሉን እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
እናት ባንክ ሴቶችን በማብቃት ተጠቃሚ ለማድረግ ከሚሰሩ አካላት ጋር በትብብር መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
#ትርታ 97.6 FM #ከልብዎ_የቀረበ