TlKVAH-UNIVERSITY @tikvahuniversity1 Channel on Telegram

TlKVAH-UNIVERSITY

@tikvahuniversity1


TlKVAH-UNIVERSITY (English)

Welcome to TlKVAH-UNIVERSITY, your one-stop destination for all things related to personal growth, self-improvement, and motivation. This Telegram channel, with the username @tikvahuniversity1, is dedicated to providing valuable resources, insightful tips, and inspiring content to help you become the best version of yourself. Whether you're looking to enhance your productivity, develop new skills, or simply boost your motivation, TlKVAH-UNIVERSITY is here to support you every step of the way. Who is it for? TlKVAH-UNIVERSITY is for anyone who is committed to personal growth and self-improvement. It is for individuals who are looking to make positive changes in their lives and achieve their full potential. What is it? TlKVAH-UNIVERSITY is a virtual hub of knowledge, inspiration, and encouragement. From daily affirmations to practical advice on goal setting, time management, and mindfulness, this channel offers a wealth of resources to help you on your journey to self-discovery and success. Join TlKVAH-UNIVERSITY today and embark on a transformative learning experience that will empower you to thrive in all aspects of your life.

TlKVAH-UNIVERSITY

01 Jul, 14:16


The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 11 months. If it remains inactive in the next 8 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.

TlKVAH-UNIVERSITY

22 Jun, 12:15


The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 11 months. If it remains inactive in the next 18 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.

TlKVAH-UNIVERSITY

03 Jul, 08:20


#ጥቆማ

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዓመታዊ ሀገር ዐቀፍ የምርምር ጉባኤውን ዛሬ ማካሄድ ይጀምራል።

የምርምር ጉባኤው "ሳይንስ፣ ፈጠራ እና ሀገር በቀል ዕውቀትን ማጎልበት ለዘላቂ ልማት" በሚል ጭብጥ ላይ ይመክራል።

ጉባኤው ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት ይካሄዳል።

@tikvahuniversity @TikvahUniversityybot

TlKVAH-UNIVERSITY

03 Jul, 08:20


ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዓመታዊ ሀገር ዐቀፍ የምርምር ጉባኤውን ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል።

ጉባኤው "ሳይንስ፣ ፈጠራ እና ሀገር በቀል ዕውቀት ለዘላቂ ልማት" በሚል ጭብጥ ላይ ይመክራል።

በመድረኩ የጠ/ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሂሩት ወ/ማሪያም (ፕ/ር)፣ የሳይንስና ከፍተኛ ት/ት ሚኒስቴር ዲኤታ አፈወርቅ ካሡ (ፕ/ር)፣ የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጴጥሮስ ወ/ጊዮርግስ (ዶ/ር) እና የዩኒቨርሲቲ ምሁራን በመሳተፍ ላይ ናቸው።

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት በርካታ ተግባራት ማከናወን መቻሉን ተቋሙን በጎበኙባቸው አጋጣሚዎች መመልከታቸውን የጠ/ሚ/ሩ አማካሪዋ ተናግረዋል።

ዶ/ር ጴጥሮስ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ለጥናት እና ችግር ፈቺ የምርምር ስራዎች ከመማር ማስተማር ዘርፉ ያልተናነሰ ትኩረት መስጠቱን ገልፀዋል።

ጉባኤው ነገም ይቀጥላል። #ዋልታቴቪ #ደሬቴኤ

@tikvahuniversity @TikvahUniversityybot

TlKVAH-UNIVERSITY

03 Jul, 08:20


ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አዲስ ገቢ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ሐምሌ 05 እና 06/2013 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

በማህበራዊ ሳይንስ መስክ የተመደቡና ስማቸው ከ'L' እስከ 'T' ፊደል የሚጀምር ተማሪዎች እንዲሁም በተፈጥሮ ሳይንስ መስክ የተመደቡና ስማቸው ከ'N' እስከ 'Z' ፊደል የሚጀምር ተማሪዎች የምዝገባ ቦታ በቡሬ ከተማ በሚገኘው ቡሬ ካምፓስ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ከተገለፁት ፊደላት ውጪ ስማቸው የሚጀምር ሌሎች ተማሪዎች ምዝገባ ደግሞ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ይከናወናል ብሏል።

አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደዩኒቨርሲቲው ሲሄዱ ሊይዟቸው የሚገቡ፦

• የ8ኛ፣ 10ኛ እና 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት እና የፈተና ውጤት ማስረጃዎች ዋናውና 2 ኮፒ
• 3×4 ፎቶግራፍ (8)
• አንሶላ፣ ብርድልብስ እና ትራስ ጨርቅ
• የስፖርት ትጥቅ
• የኮቪድ-19 መከላከያ ማስኮች

ከተገለፁት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን እንደማያስተናግድ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ለበለጠ መረጃ www.dmu.edu.et መጠቀም ይቻላል ተብሏል።

@tikvahuniversity @TikvahUniversityybot

TlKVAH-UNIVERSITY

03 Jul, 08:20


በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛውን ውጤት ያስመዘገበው ተማሪ የአንድ ዓመት ሙሉ ወጪውን ለመሸፈን ቃል ተገባለት፡፡

የአጣዬ ከተማ ነዋሪው ተማሪ አዲሱ አብተው 651 ነጥብ በማምጣት የሀገሪቱን ከፍተኛ ውጤት አስምዝግቧል፡፡

በሀርቫርድ ዮኒቨርሲቲ በምርምርና ጥናት የሚታወቁት መኮንን ያሬድ (ፕ/ር) ተማሪ አዲሱን ለአንድ ዓመት ለመደገፍ ቃል ገብተዋል፡፡

ሌሎች በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ለ12 ተማሪዎች ድጋፍ ማድረጋቸውን የሰሜን ሽዋ አስተዳደርን በመጥቀስ የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity @TikvahUniversityybot

TlKVAH-UNIVERSITY

03 Jul, 08:20


14ኛው ዓለም ዐቀፍ የሶማሌ ጥናቶች ኮንፍረንስ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ መካሄድ ጀምሯል።

ኮንፍረንሱ በሶማሌ ባህል፣ ቋንቋ፣ በአርብቶ አደሩ ኑሮ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እንዲሁም ቀጣናዊ መስተጋብሮች ላይ ጥናት እና ምርምሮችን ያደርጋል።

በዛሬው መድረክ ከሶማሌላንድ፣ ጅቡቲ፣ ሶማሊያ እና ኬንያ የተጋበዙ እንግዶች ተሳትፈዋል።

ዛሬን ጨምሮ ለ3 ቀናት በሚቆየው መድረክ በሶማሌ ባህል እና ቋንቋ እንዲሁም በአርብቶ አደሩ ኑሮ ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ፅሁፎች ይቀርባሉ ተብሏል።

ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ከ200 በላይ ምሁራን በጉባኤው እየተሳተፉ ይገኛሉ። #SMMA

@tikvahuniversity @TikvahUniversityybot

TlKVAH-UNIVERSITY

03 Jul, 08:20


ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የ2013 ዓ.ም #የክረምት ነባር ተማሪዎች ምዝገባ ሐምሌ 08 እና 09/2013 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

ትምህርት ሐምሌ 12/2013 ዓ.ም ይጀምራል ብሏል።

@tikvahuniversity @TikvahUniversityybot

TlKVAH-UNIVERSITY

03 Jul, 08:20


ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ለ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አዲስ ገቢ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች አቀባበል አድርጓል።

የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች እና የተማሪዎች ኅብረት ተወካዮች ለአዲስ ገቢ ተማሪዎቹ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ አቀባበሉ አርብም ይቀጥላል።

@tikvahuniversity @TikvahUniversityybot

TlKVAH-UNIVERSITY

02 Jul, 08:24


በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ "ልጆቻችን ያሉበት ሁኔታ ይነገረን" የሚል ጥያቄያቸውን ለማቅረብ ወደ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ያመሩት ወላጆች ቀጠሮ ተሰጥቷቸው መመለሳቸው ተሰምቷል፡፡

ቅሬታ አቅራቢዎቹ 5 ተወካዮቻቸውን ወደ ጽ/ቤቱ በመላክ ጉዳያቸውን ለቢሮው ማድረሳቸው ተሰምቷል።

ከቀይመስቀል ማህበር ጋር በመተባበር ልጆቻቸውን ማግኘት የሚችሉበትን ሁኔታ መንግስት እንዲያመቻች
ቅሬታ አቅራቢዎቹ ጠይቀዋል።

የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ጥያቄያቸውን ተቀብሎ ነገ ከ3 እስከ 4 ሰዓት ውሳኔውን እንደሚያሳውቃቸው እንደተገፀላቸው ሰምተናል፡፡

@tikvahuniversity @TikvahUniversityybot

TlKVAH-UNIVERSITY

02 Jul, 08:24


#Update

በትግራይ ክልል ውስጥ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎችን በተመለከተ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ሰጥቷል።

በተማሪዎቹ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከተለያዩ አካላት ፣ የየዩኒቨርስቲዎቹ አመራሮች እና ከዓለም አቀፍ ተራድኦ ተቋማት ጋር በመሆን እየሰራበት እንደሚገኝ ገልጿል።

ሚኒስሩ አደረኩት ባለው ጥረት የዩኒቨርቲዎችን አመራር ለማግኘት የቻለ ሲሆን ተማሪዎች በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ አውቄያለሁ ብሏል።

በተጨማሪም የሁለተኛ መንፈቅ ዓመት ፈተና ለመውሰድ በዝግጅት ላይ ያሉም እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል ሲል ገልጿል።

የተማሪ ወላጆች ልጆቻቸው በመልካም ሁኔታ ላይ መሆናቸውን ተረድተው በመንግስት የተጀመሩ ጥረቶችን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርቧል።

በቀጣይ ተማሪዎች ፈተና ወስደው ሲጨርሱ የሚኖሩ ጉዳዮችን አሳውቃለሁ ብሏል።

የተማሪ ወላጆች #በመደበኛ_መገናኛ_ብዙኃን የሚተላለፉ መረጃዎችን ብቻ እንዲጠቀሙ እና ተረጋግተው እንዲጠብቁም አሳስቧል።

@tikvahethiopia

TlKVAH-UNIVERSITY

02 Jul, 08:24


የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ የ2ኛ፣ 3ኛ እና 4ኛ ዓመት #የክረምት ተማሪዎች ምዝገባ ሐምሌ 07 እና 08/2013 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

ትምህርት ሐምሌ 09/2013 ዓ.ም ይጀምራል ብሏል።

@tikvahuniversity @TikvahUniversityybot

TlKVAH-UNIVERSITY

02 Jul, 08:24


ጅማ ዩኒቨርሲቲ ለ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አዲስ ገቢ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች አቀባበል አድርጓል።

የዩኒቨርሲቲዉ የበላይ አመራሮች፣ የተማሪዎች ተወካዮች፣ አባገዳዎች፣ ሀዳ ስንቄዎች እና አባቶች
ለአዲስ ገቢ ተማሪዎቹ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

@tikvahuniversity @TikvahUniversityybot

TlKVAH-UNIVERSITY

02 Jul, 08:24


#ጥቆማ

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዓመታዊ ሀገር ዐቀፍ የምርምር ጉባኤውን ዛሬ ማካሄድ ይጀምራል።

የምርምር ጉባኤው "ሳይንስ፣ ፈጠራ እና ሀገር በቀል ዕውቀትን ማጎልበት ለዘላቂ ልማት" በሚል ጭብጥ ላይ የይመክራል።

ጉባኤው ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት ይካሄዳል።

@tikvahuniversity @TikvahUniversityybot

TlKVAH-UNIVERSITY

02 Jul, 08:24


ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ለ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አዲስ ገቢ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች አቀባበል አድርጓል።

የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች እና የተማሪዎች ኅብረት ተወካዮች ለአዲስ ገቢ ተማሪዎቹ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ አቀባበሉ አርብም ይቀጥላል።

@tikvahuniversity @TikvahUniversityybot

TlKVAH-UNIVERSITY

26 Jun, 12:33


የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ #የክረምት ነባር ተማሪዎች መግቢያ ሐምሌ 09 እና 10/2013 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

@tikvahuniversity1

TlKVAH-UNIVERSITY

26 Jun, 12:33


መቱ ዩኒቨርሲቲ #የክረምት ነባር ተማሪዎች ሐምሌ 05/2013 ዓ.ም ምዝገባቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ አድርጓል።

የመደበኛ ተማሪዎች ትምህርት በቀጣይ ወራት የሚቀጥል በመሆኑ፤ የዶርም አገልግሎት ለክረምት ተማሪዎች አልሰጥም ብሏል ዩኒቨርሲቲው።

በተጨማሪም የዘንድሮ የክረምት ትምህርት በመቱ ከተማ በሚገኙ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚሰጥ መሆኑን አሳውቋል።

@tikvahuniversity1

TlKVAH-UNIVERSITY

26 Jun, 12:33


አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን መደበኛ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች መግቢያ ከሰኔ 26 እስከ 30/2013 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

#የክረምት ነባር ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ደግሞ ሐምሌ 16 እና 17/2013 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል።

በመሆኑም በተገለፁት ቀናት ብቻ በዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ጽ/ቤት በአካል በመገኘት እንድትመዝገቡ ብሏል።

ተማሪዎች አስፈላጊ የትምህርት ማስረጃዎች፣ አንሶላ፣ ብርድልብስ እና ትራስ ልብስ እንዲሁም የኮቪድ-19 መከላከያ ማስኮች መያዝ አለባችሁ ተብሏል።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 057 875 9168 ወይም 057 775 2958 መጠቀም ይቻላል ተብሏል።

@tikvahuniversity1

TlKVAH-UNIVERSITY

26 Jun, 12:33


ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ከ2 ሺህ 400 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ።

ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ በተለያዩ የትምህርት አይነቶች የሰለጠኑ ናቸው ተብሏል።

የዘንድሮ 8ኛ ዙር ተመራቂዎችን ጨምሮ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ እስካሁን ከ13 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ማሰልጠኑ ተገልጿል። #ኦቢኤንአማርኛ

@tikvahuniversity1

TlKVAH-UNIVERSITY

26 Jun, 12:33


አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን መደበኛ መርሃ ግብር የዲግሪ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ሰኔ 28 እና 29/2013 ዓ.ም ሪፖርት አድርጉ ብሏል።

ሰኔ 30 እና ሐምሌ 01/2013 ዓ.ም የምዝገባ ቀናት
ሲሆኑ የገጽ-ለገጽ ትምህርት ሐምሌ 05/2013 ዓ.ም እንደሚጀምር ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደዩኒቨርሲቲው ሲሄዱ ሊይዟቸው የሚገቡ፦

• የ8ኛ፣ 10ኛ እና የመሠናዶ ትምህርት ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው
• ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው
• 3X4 ፎቶግራፍ (8)
• አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ
• የስፖርት ትጥቅ
• የኮቪድ-19 መከላከያ ማስክ

ከተገለፁት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን እንደማያስተናግድ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

@tikvahuniversity1