swa 58 primary @swa58 Channel on Telegram

swa 58 primary

@swa58


Materials platform for swa 58

swa 58 primary (English)

Unlock a world of educational resources with 'swa 58 primary' Telegram channel! Dedicated to providing a materials platform for swa 58, this channel is a comprehensive hub for teachers, parents, and students alike. Whether you're looking for lesson plans, worksheets, or educational games, swa58 has you covered.

Who is 'swa 58 primary'? swa 58 primary is a Telegram channel designed to support educators, parents, and students associated with swa 58. It offers a wide range of educational materials tailored to the swa 58 curriculum.

What is 'swa 58 primary'? 'swa 58 primary' is a one-stop destination for all your educational needs. From interactive learning tools to engaging activities, this channel is dedicated to enhancing the educational experience of swa 58 students.

Join 'swa 58 primary' today and gain access to a wealth of resources that will help you excel in your academic journey. Let swa58 be your partner in education and watch as your learning experience transforms into one that is both enriching and enjoyable. Don't miss out on this opportunity to elevate your education with 'swa 58 primary'!

swa 58 primary

07 Jan, 07:31


#ጌታችን_ገናና_አምላክ ሆኖ ሳለ በቤቴልሔም በበረት እንደተወለደ ስናስብ "መልካም ነገር አይወጣባትም ተብላ ተስፋ በተቆረጠባት #በናዝሬት_ከተማ እንዳደገም ስንመለከት
እርሱ፦
#የሰዎችን ድካም እንደተጋራ
#ተስፋ ለቆረጡ ኃጢአተኞች ተስፋ ሊሰጥ እንደመጣ
#የተናቁትን ሊያከብር  እንደወደደ
#የወደቁትን ሊያነሣ እንደተገለጠ።
እናስተውላለን።

ስለዚህም በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ሆነን ወደ እርሱ ብንመጣ ከድካማችን ሊያሳርፈን #ኃጢአታችንንም ይቅር ሊለን የታመነ ነው። በሕያው ቃሉ እንዲህ ብሎ ተናግሯልና
“እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።”  ማቴ 11፥28

    #_መልካም_በዓል ይሁንላችሁ 🙏

swa 58 primary

06 Jan, 08:55


5 liters of cooking oil, 10 eggs and birr 500 for each 20 cleaners and guards are given as Christmas gift @SWA 58

swa 58 primary

26 Dec, 15:28


መረጃዎች በቴሌግራም እየተመዘበሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በዛሬው ዕለት በቴሌግራም መረጃዎች እየተመዘበሩ በመሆኑ ተጠቃሚዎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰበ፡፡

አስተዳደሩ እንዳለው ከዛሬ ጀምሮ ብዙ የቴሌግራም አካውንቶች በተጠቀሰው የማስገሪያ (ፊሺንግ ሊንክ) እና ሌሎች ተጨማሪ ማስገሪያዎች አማካኝነት መረጃዎች እየተመዘበሩ ነው ፡፡

በዚህም ከማንኛውም የቴሌግራም ተጠቃሚ (ከሚያውቁትም ሆነ ከማያውቁት) ግለሰብ ሊንክ ቢላክ መክፈት ተገቢ እንዳልሆነ እና ወዲያውኑ ማጥፋት እንደሚገባ አሳስቧል፡፡

swa 58 primary

21 Nov, 12:59


የተለያዩ የሰለጠኑት ሀገራት ታዳጊ ልጆቻቸው ሊኖራቸው የሚገባውን የስክሪን ጊዜ ”Screen Time” በህግ እየገደቡ ይገኛሉ፤
እኛም ታዳጊ ህጻናት ሊኖራቸው የሚገባውን የመጠቀሚያ ሰዓት ወላጆች ገደብ እንዲያበጁለት እንመክራለን፡፡

swa 58 primary

21 Nov, 12:47


አውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ማህበራዊ ሚዲያዎችን እንዳይጠቀሙ አገደች
On Nov 21, 2024 48

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ማህበራዊ ሚዲያዎችን እንዳይጠቀሙ የሚያግደውን ህግ በፓርላማ አፅድቃለች፡፡

በውሳኔው መሰረትም በሀገሪቱ እድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች የቲክቶክ፣ ስናፕ ቻት፣ ፌስቡክ፣ ሬዲት፣ ትዊተር (ኤክስ) እና ኢንስታግራም አካውንት መክፈት አይችሉም፡፡

ከላይ የተጠቀሱት የማህበራዊ ትስስር ገፆች ታዳጊዎች አካውንት እንዲከፍቱ የሚፈቅዱ ከሆኑ 50 ሚሊየን የአውስትራሊያ ዶላር ቅጣት እንደሚጠብቃቸው መንግስት አስጠንቅቋል።

የአውስትራሊያ መንግስት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ሚሸል ሮውላንድ÷ በሀገሪቱ ሰፊ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ድጋፍ ያገኘው ይህ ውሳኔ የታዳጊዎችን ደህንነት ለመጠበቅ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በአውስትራሊያ እድሜያቸው ከ14 እስከ 17 ዓመት የሆኑ ታዳጊዎች ጎጂ ይዘት ያላቸውን ጉዳዮች በማህበራዊ ትስስር ገፆች ሲመለከቱ እንደነበር አስታውሰው÷ ክልከላው ታዳጊዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚደርስባቸውን ጫና ይቀንሳል ብለዋል፡፡

ከአውስትራሊያ አስቀድማ ስፔን ባለፈው ሰኔ ወር ከ14 እስከ 16 ዓመት ያሉ ታዳጊዎች ማህበራዊ ሚዲያዎችን እንዳይጠቀሙ መከልከሏ ይታወቃል።

በአሜሪካም በተወሰኑ ግዛቶች ላይ ተግባራዊ ሲደረግ ቆይቷል መባሉን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

swa 58 primary

17 Oct, 14:53


#ትኩረት🚨

ከሰሞኑን በርካታ ሰዎች በተለይ ትንንሽ ህጻናት በጉንፋን እና በጉንፋን መሰል የመተንፈሻ አካላት ህመም እየተያዙ ይገኛሉ።

ይህንን ወቅታዊ ሁኔታ አስመክቶ ጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና እንስቲትዩት ያጋራ መግለጫ ልከዋል።

ምን አሉ ?

➡️ የጉንፋን ሕመም በተፈጥሮ የላይኛውን የመተንፈሻ የሰውነት ክፍሎች ማለትም አፍንጫን፣ ጎሮሮን እና የአየር መተላለፊያ ባንቧን የሚያጠቃ ተላላፊ ሕመም ነዉ።

➡️ ሪኖ ቫይረስ ለጉንፉን መከሰት ዋና ምክንያት ሲሆን፣ ኮሮና፣ ኢንፍሉዌንዛ፣ ፓራ ኢንፍሉዌንዛ፣ አር ኤስ ቪ(RSV) ቫይረሶች ደግሞ ለጉንፉን መሰል ህመሞች መከሰት ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸዉ። ከተጠቀሱት ቫይረሶችም ለጉንፋን ሕመም መከሰት 50 በመቶ ድርሻውን የሚይዘው ሪኖ ቫይረስ ነው፡፡ በደረቅ ነፋሳማ ወቅት የአፍንጫ የውስጠኛው ስስ ሽፋን “ ሙከስ መምብሬን ” ስለሚደርቅ የጉንፋን ሕመም እና ተላላፊነቱ ይጨምራል፡፡

➡️ የክረምት ወራት ወይም የዝናብ ወቅት ማብቃቱን ተከትሎ መስከረምን ጨምሮ በጥቅምትና ህዳር ወራት እንደዚህ አይነት ጉንፋን መሰል ህመም የሚጠበቅ ነው፡፡

➡️ ሕመሙ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በቫይረሱ የተጠቃ ሰው በሚያስልበት ወይም በሚያስነጥስበት ጊዜ እንደሆነና በተጨማሪም ሰዎች ቫይረሱ ያረፈበትን የበር እጀታ፣ ጠረጴዛ ወይም በሕመምተኛው የተነካካንን ሰው እጅ ከነኩ በኋላ አፋቸውንና አፍንጫቸውን ሲነካኩ ቫይረሱ ለመተላለፍ በሚፈጠርለት ምቹ ሁኔታ ነው።

➡️ የጉንፋን ሕመም የመጀመሪያ ምልክቱ ከመጀመሩ አንድ ቀን በፊት ተላላፊ ሊሆን ይችላል፤ ሕመሙ ከጀመረ ከ 5 እስከ 10 ባሉት ቀናት ደግሞ ሕመምተኛው ቫይረሱን ያስተላልፋል።

➡️ ህመሙ አብዛኛዉን ጊዜ እስከ 2 ሳምንት ሊቆይ ይችላል። ምልክቶቹም እንደ ፦
° የአፍንጫ ፈሳሽ መብዛት፣
° ሳል፣
° ትኩሳት፣
° ራስ ምታትና ጉሮሮን መከርከር፣
° ማስነጠስ፣
° አይን ማሳከክ እና መቅላት፣
° ማስታወክ፣
° ከፍ ሲልም የትንፋሽ ማጠር፣
° ከፍተኛ ድካምና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ።

➡️ ከመስከረም ወር ጀምሮ መሰል ህመም ተሰምቷቸው ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ ናሙና ከሰጡት ታካሚዎች ውስጥ አር ኤስ ቪ የተገኘባቸዉ ቁጥር የመጨመር ሁኔታ ያሳያል፡፡ በዚሁ ወቅት የተከሰተው ጉንፋን መሰል ህመም (አር ኤስ ቪ) በተለይ በህጻናት ላይ በብዛት የተከሰተ ሲሆን ለዚህም ወቅቱ ትምህርት ቤት የተከፈተበት በመሆኑ ለበሽታው መስፋፋት አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

➡️ ባለፈዉ 1 ወር ዉስጥ ተመርምረዉ አር ኤስ ቪ ከተገኘባቸዉ ታካሚዎች መካከል 84% ያክሉ እድሜያቸዉ ከ5 አመት በታች ነዉ። እንደዚሁም ባለፈዉ ሳምንት ለአር ኤስ ቪ ከተመረመሩት 81 ናሙናዎች 49 (60.5%) ያህሉ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

➡️ አስፈላጊው ጥንቃቄ ካልተደረገ በሽታው የመዛመት እድሉ ከፍ ሊል እንደሚችል፤ በተለይ ቀዳሚ ተጎጅ ሊሆኑ የሚችሉ እንደ ህጻናትና አረጋውያን ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች አና ተጓዳኝ የጤና ችግር እንደነ አስም፣ የስኳር በሽታ፣ ካንሰር እና ሌሎች ሥር የሰደዱ በሽታዎች ያሉባቸው ሕሙማን ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግላቸው እና ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ አስፈላጊዉን ምርመራና ህክምና ሊያደርጉ ይገባል።

➡️ የጉንፋን ሕመም የጆሮ ኢንፌክሽን እና የሳንባ ምች ሕመምን ጨምሮ ለተለያዩ ሕመሞች ተጋላጭ ሊያደርግ ይችላል፡፡

ጉንፋን መሰል በሽታን የምንከላከልባቸው መንገዶች ምንድናቸው ?
° የእጅ ንጽህናን መጠበቅ፣
° ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ የአፍና አፍንጫ ጭምብል(ማስክ) ማድረግ
° በዕለት ኑሯችን የምንጠቀምባቸውን በከባቢዎቻችን የሚገኙ ቁሳቁሶችን ማጽዳት
° የብዙሃን ማጓጓዣ ትራንስፖርት ላይ መስኮቶችን በመክፈት በቂ የአየር ዝዉዉር እንዲኖር በማድረግ የበሽታዉን የመተላለፍ ዕድል መቀነስ ይቻላል፡፡


#ማሳሰቢያ ፦ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲወስድና ጠንከር ያለ የበሽታው ምልክት የሚታይበት ሰው በፍጥነት በአቅራቢያው ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን የህክምና ምክር አና ዕርዳታ ማግኘት አለበት፡፡

#MoH #EPHI

@tikvahethiopia

swa 58 primary

10 Oct, 17:39


For all grade 7 and 8 students, use this website and sign up to get what's available in this site as you have been briefed this morning.

swa 58 primary

07 Oct, 14:54


ለሳዌአ 58 ወላጆች /ህጋዊ አሳዳጊዎች:-
ነገ ማክሰኞ መስከረም 28 ቀን 2017ዓ.ም. ጠዋት የተጠራው ስብሰባ መደበኛው ትምህርት እየተካሄደ የሚደረግ በመሆኑ የመማር ማስተማሩ ስራ ባለበት እንደሚቀጥል ማስገንዘብ እንወደዋለን።
ሳዌአ 58 አስተዳደር

swa 58 primary

14 Sep, 15:52


ማሳሰቢያ:-
1)የሁሉም ተማሪዎች የክፍል ምድብ በተጨማሪ ት/ቤት ተለጥፏል።
2) ዝርዝሩ ላይ የተማሪው ስም ከሌለ ሰኞ ቢሮ ሪፖርት ያድርጉልን።

swa 58 primary

14 Sep, 15:47


Grade 2-8 Students Class Assignment

swa 58 primary

14 Sep, 12:24


#መውሊድ : 1499ኛው የታላቁ ነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በነገው ዕለት #እሁድ እንደሚከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት አሳውቋል።

@tikvahethiopia

swa 58 primary

14 Sep, 12:22


ውድ ወላጆች/ህጋዊ አሳዳጊዎች:- በዚህ ምክንያት ት/ት ሰኞ መስከረም 6/2017 እንደሚጀመር ማስታወስ እንወደዋለን።

swa 58 primary

11 Sep, 06:16


ለመላው የሳዌአ 58 ቅርንጫፍ ማህበረሰብ 2017ዓ.ም. የሰላም የጤና እና የስኬት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!!
ሳዌአ 58 አስተዳደር

swa 58 primary

27 Jul, 18:07


መንግስት በአጋር አካላት ድጋፍ 5 ሚሊየን የኢትዮጵያ ኮደርስ (5 million Ethiopian Coders) የተሰኘ ስልጠና አመቻችቷል።

መንግስት በአጋር አካላት ድጋፍ “5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ” የተሰኘ አዲስ የስልጠና እድል አመቻችቷል። ይህ ኢኒሼቲቭ ከአይሲቲ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ኮርሶች ጥራቱና በጥልቅ ይዘቶች በሚታወቀው በኦዳሲቲ ፕላትፎርም (Udacity Platform) የፕሮግራሚንግ፣ ዳታ ሳይንስ፣ አርተፊሻል ኢንተለጀንስና ሌሎችም ከአይሲቲ ጋር የተገናኙ ኮርሶችን ከክፍያ ነፃ ማግኘት የሚያስችል ነው።
ተማሪዎች እና መምህራን ያለምንም ወጪ በእነዚህ ኮርሶች በመመዝገብ ይህንን ልዩ የስልጠና እድል መጠቀም የሚችሉ ሲሆን በዚህ ፕሮግራም ውስጥ በመሳተፍና ችሎታቸውን በማጎልበት በአለም አቀፍ ገበያ ከፍተኛ ተወዳዳሪ መሆን ይችላሉ።
በዚህ ስልጠና ተመዝግበውና የትምህርት ይዘቶቹን ተምረው ያጠናቀቁ ተሳታፊዎች በአለም አቀፍ ድርጅቶች እውቅና ያለው እና የስራ እድልን በእጅጉ ሊያሳድግ ከሚችለው Udacity የምስክር ወረቀት ያገኛሉ።

ትምህርት ሚኒስቴር በስልጠናው እንዴት መመዝገብና መሳተፍ እንደሚቻል የሚያሳዩ መመሪያዎችን በጽሁፍና በቪዲዮ አዘጋጅቷል። ስለሆነም ፍላጎት ያላችሁ ተማሪዎችና መምህራን ይሄንን በበዙ ክፍያ ይሰጥ የነበረን ስልጠና መመሪያውን ተከትሎ ብቻ በመመዝገብ በነጻ መሰልጠን ትችላላችሁ።

የመመሪያውን የቪዲዮ ሊንክ https://youtu.be/-zSmhhD5qE4 ላይ በመግባት መመልከት የምትችሉ ሲሆን በምስል የተደገፈውን መመሪያም ከዚህ ፖስት ጋር አጋርተናል።
ይሄንን ጠቃሚና ነጻ የስልጠና እድል ፍላጎቱ ላላቸውና የትምህርት ዝግጅታቸው ከዚህ ስልጠና ጋር ለሚገናኝ ጓደኞቻችሁ፣ ወዳጅ ፣ ቤተሰባችሁ እንዲሁም ተማሪዎችና መምህራን በማጋራት ተጨቃሚ እንዲሆኑ አድርጉ።

swa 58 primary

18 Jul, 12:27


ለዉድ ወላጆች/ህጋዊ አሳዳጊዎች:- ለ2017ዓ.ም የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ሊጠናቀቅ የቀሩት ቀናት ሁለት ብቻ ነው። በጊዜዉ ባልተመዘገቡ ተማሪዎች ቦታ ከሌሎች ትምህርት ቤቶች በመጠባበቅ ላይ ያሉ ተማሪዎችን ለመመዝገብ ስለምንገደድ በወቅቱ ተማሪዎችን በማስመዝገብ ሊፈጠር ከሚችለው ችግር እንድትድኑ አጥብቀን እንመክራለን ።