ሀዋሳ፦ ህዳር 04/2017 ዓ.ም
የሲብክመ ፍትህ ቢሮ በህጻናት ላይ የሚደርሱ ወንጀሎች በማስመልከት ከተለያዩ መዋቅሮችና ባለድርሻ አካላት ለተውጣጡ የግዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
በስልጠናው ወቅት የመድረኩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሲብክመ ፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የወንጀልና የፍትሐብሔር ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ አቶ መብራቴ መስፍን ስናገሩ፣ በህጻናት ላይ ውስብስብ ጥቃትና ወንጀሎች እንደሚፈጸሙ እና የሚፈጸሙ ጥቃቶችን እና ወንጀሎችን በመቀናጀት ካልተከላከሉ የተሟላ ፍትህ ማረጋገጥ አዳጋች እንደሆነ አስታውቀዋል። የተሟላ ፍትህ ስባል ለተጎጂ ህጻናት የህግ፣ የስነ ልቦና እና የህክምና እርዳታን ጨምሮ የወንጀል ድርጊት የተፈጸመባቸው ህጻናት እንዲያገናኙ ማስቻል እንደሆነ ገልጿል። አቶ መብራቴ አያይዘውም ቢሮው በህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እና ወንጀሎችን ለመከላከል ከተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች እና ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እየተሰራ መሆኑን በመጥቀስ ቅንጅቱን በስልጠና ማጠናከር አስፈላጊ በመሆኑ ይህ ስልጠና እንደተዘጋጀ አስታውቀዋል።
ስልጠናውን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ የሆኑት አቶ በላቸው ባሼ ሲሆኑ፣ በህጻናት ላይ ስለምፈጸሙ ወንጀሎች ዙሪያ በህግ የተደነገጉ ጉዳዮችና፣ የባለድርሻ አካላት ሚናን በማስመልከት ግንዛቤ የፈጠሩ ሲሆን ተሳታፊዎችም በስልጠናው ዙሪያ ሰፊ ውይይት በማድረግ ግንዛቤ እንዳገኙ አንስተዋል።
በመጨረሻም በክልሉ የሚገኙ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ተወካዮች፣ የጣሊታ ራይዝ አፕ መስራች ወይዘሮ አትክልት፣ የአውሳድ ሀዋሳ ማዕከል ተወካይ ወይዜሮ ራሄል በማከላቸው ስለሚሰጡት አገልግሎትና ከፍትህ ቢሮ ጋር በመቀናጀት በህጻናት ዙሪያ ስለሚሰሩት ስራዎች ልምዳቸውን ለሰልጣኞች አካፍለዋል።
ለህግ፣ ለፍትህ ፣ ለርትዕ እንሰራለን!!
አድራሻችን
ፌስቡክ፡https://www.facebook.com/profile.php?id=100067327733988&mibextid=ZbWKwL
ተሌግራም https://t.me/sidamaattorney
ዋትሳፕ https://chat.whatsapp.com/C1Qsj95SkP0DnBUa99MhcJ